Oktober 7/2013
በቅርቡ አንድ የመዲናችን የግል ኮሌጅ በሥራ አመራር የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ፤ ግብረ ሰዶማዊነት በአገራችን እያስከተለ ስላለው አደጋ የሚያስቃኝ በጥናት የተደገፈ ጽሑፍ ቀርቦ ነበር፡፡ ፅሁፍ አቅራቢው፤ የግብረሰዶም አራማጆች ለኢትዮጵያ መንግስት “የመደራጀት መብታችን ይከበር” በሚል ያቀረቡትን ጥያቄና የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የሰጡት ምላሽ በሚል ያቀረቡት ቀልድ ለአንባቢያን የሚያስተላልፈው ቁም ነገር አያጣምና ልጥቀሰው። ጠ/ሚኒስትሩ የመብት ጠያቂዎቹን ተወካዮች አስጠርተው እንዲህ አሏቸው፡:
“እንድትደራጁ ከመፍቀዳችን በፊት ጥያቄያችሁ ከሕግ፣ ከሞራል፣ ከባህል፣ ከሥነ ምግባር…አንፃር ተቀባይነት ይኖረው አይኖረው እንደሆነ ማጣራት አለብን፡፡ ይሄን ለማጣራት ደግሞ የእናንተም ትብብር ያስፈልገናል፡፡ የመጀመርያው ተግባራችሁ የሚሆነው የድጋፍ መጠየቂያ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ነው፡፡ የሰልፉ መነሻ መሐል መርካቶ ይሆናል፡፡ ድምፃችሁን እያሰማችሁ፣ መፈክሮቻችሁን በጽሑፍ ይዛችሁ በመጀመሪያ የምታልፉት በራጉኤል ቤተክርስቲያን በኩል ይሆናል፡፡ በመቀጠል አንዋር መስጊድን ታቋርጣላችሁ፡፡ ከዚያ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ትዘልቃላችሁ፡፡ በአፍንጮ በር በኩል በ6 ኪሎ ዩኒቨርስቲና የሰማዕታት ሐውልትን ካለፋችሁ በኋላ፣ በ4 ኪሎ ዩኒቨርስቲ በኩል የነፃነት ሐውልትን አቋርጣችሁ፣ በሁለቱ ቤተመንግስቶች መሐል በመጓዝ መስቀል አደባባይ መድረስ ከቻላችሁ፣ የመደራጀት ጥያቄያችሁ ምላሽ ያገኝ ይሆናል”

No comments:
Post a Comment