ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ከላሊበላ ሰቆጣ ይሰራል ተብሎ የነበረው መንገድ ባለመሰራቱ የተበሳጩት የከተማዋ ነዋሪዎች በራሳቸው አነሳሽነት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ወጣቶቹ አጋጣሚውን በመጠቀም ” ነጻነት እንፈልጋለን፣ እኛ ወታቶች ብዙ ችገሮች አሉብን፣ ሰቆጣ መብት የለም፣ ብልጭጭልታ የእድገት ምልክት አይደለም፣ እድገት የለም፣ መንገድ ላሳ ህዝብ መንገድ ሊከለከል አይገባውም፣ ልማት በተግባር እንጅ በውሬ አይደለም፣ ዋግ ለጦርነት ብቻ ሳይሆን ለልማትም ዝግጁ ናት፣ ዋግ ውስጥ ለውጥ የለም፣ መንገዳችን ልንነጠቅ አይገባም፣ የህዝብ ድምጽ አይጣስም የሚሉትን እና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል ፡፡
የከተማው ምክትል ከንቲባ ወጣቶቹ የሚያሰሙዋቸውን መፈክሮች እንዲያቆሙና ጥያቄአቸውን እንዲያቀርቡ በጠየቁት መሰረት አንድ የህዝቡ ተወካይ የህዝቡን ጥያቄ በንባብ አሰምቷል ፡፡
ከህዝብ ለተነሳው ጥያቄ ምክትል አስተዳዳሪው መንግስት የገንዘብ ጥረት ስላጋጠመው ፕሮጅቱን ለመሰረዝ መገደዱን ሲናገሩ ህዝቡ ተቃሟቸዋል ፡፡
ምክትል ከንቲባው ጥያቄያቸውን ለበላይ አካል እንደሚያቀርቡ ቢገልጹም ህዝቡ ግን ሳይቀበለው ቀርቷል።
በጉዳዩ የተበሳጩ የሚመስሉት የኢህአዴግ ደጋፊዎች የህዝቡ ጥያቄ ነው በማለት ሌላ ጥያቄ ይዘው ቀርበው ነበር። የኢህአዴግ ደጋፊዎች ” በመለስ ራእይ በርካታ የልማት ስራዎች መሰረታቸውን እና እነዚህ ልማቶች በጸረ ሰላም ሀይሎች እንዳይደናቀፉብን” የሚል ንግግር ሲጀምሩ ህዝቡ በድጋሜ ተቃውሞውን አሰምቷል ፡፡ በመጨረሻ ግን የኢህአዴግ ደጋፊዎችም የህዝቡን ጥያቄ ደግፈው በመቆመቻው ድጋፍ አግኝተዋል የኢህአዴግ ደጋፊው ንግግራቸውን ካቀረቡ በሁዋላ ህዝቡ በሰላም ወደ መጣበት እንዲመለስ ሲታዘዝ አንዳንድ ወጣቶች ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል ።
በሰልፉ እለት ገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ሰልፈኞቹ የአቶ መለስን ፎቶ ግራፍ እንዲይዙ እና ኢህአዴግን የሚደግፉ መፈክሮችን እንዲያሰሙ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር በስፍራው ነበሩ ወጣቶች ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ አብዛኞቹ ወጣቶቹ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሚነግሩዋቸውን መፈክሮች በመተው የራሳቸውን መፈክሮች ሲያቀርቡ፣ ካድሬዎቹም ምንም አይነት ግጭት ሳይፈጥሩ ወጣቶቹ ስሜታቸውን እንዲገልጹ ፈቅደውላቸዋል።
ለእረፍት የመጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሮናል ለውጥ እንፈልጋለን የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር በስፍራው ነበረ አንድ ታዛቢ ገልጿል።
“ህዝቡ መሮታል፣ ይ
ህ መንገድ ቶሎ ካልተሰራ ” ችግር የሚፈጠር ይመስለኛል ሲል ታዛቢው አክሎ ገልጿል።
በቅርቡ የጎንደር ከተማ ቀበሌና 6 እና 7 ነዋሪዎች ተመሳሳይ የልማት ጥያቄዎችን በማንሳት በራሳቸው አነሳሽነት ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።

No comments:
Post a Comment