ኢሳት ዜና:- ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ለኢሳት በላከው ዘገባ በኦሞ ሸለቆ ላይ የሚገነባው ግልገል ጊቤ 3 እና ለስኳር እርሻ በሚል የሚካሄደው የመሬት ወረራ በአካባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ቢያስከትልም፣ መንግስትን በገንዘብ የሚደጉሙት ለጋሽ አገራት ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት አልሰጡትም። በቦዲ. ክዌጎ እና ሙርሲ ህዝቦች ኩራዝ እየተባለ ለሚጠራው የስኳር ፕሮጀክት መሬቱ ይፈለጋል በሚል ከቦታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። ነዋሪዎቹ አብዛኛውን ከብቶቻቸውን በመሸጥ የተወሰኑ ከብቶችን ብቻ እንዲይዙ መመሪያ የተላለፈላቸው መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል።
... ከዚሁ የስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ200 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ሊታረም በማይችል አደጋ ውስጥ መውደቃቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።
አሜሪካ እና እንግሊዝ ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ እርዳታ የሚሰጡ አገሮች ቢሆኑም፣ በዚህ በኩል ምንም እርምጃ አለመውሰዳቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።
No comments:
Post a Comment