የሙስሊሙ ጥያቄ ከመንግስት እጅ እየወጣ ስለመሆኑ የሚያመላክት ሁኔታ መታየቱን ኢሳት የካቲት 22 ቀን 2005 ዓ ም ዘገበ። ኢሳት እንዳለው የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች በነደፉት መርሐግብር መሰረት በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ተቃውሞዎች ተደርገዋል።
በመቀሌ፣ በመቱ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር፣ በጅማ፣ ወልቂጤ፣ ጎንደር፣ በአዲስ አ...በባ እና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ማህበረሰብ “መሪዎቻችን ይፈቱ ድምጻችን ይሰማ በቤታችን ሰላም ስጡን” የሚሉ መፈክሮችን ማሰማታቸውን ያስታወቀው ኢሳት አሁን ባለው ሁኔታ የሙስሊሙ ጥያቄ ከመንግስት እጅ እየወጣ ለመሆኑ አመላካች እንደሆነ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ለመከፋፈል መንግስት በእየለቱ የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ሙስሊሙን በቁጭት እንዲነሳ እያደረገው መሆኑን ታዛቢዎች እንደሚናገሩ ያመለከተው ኢሳት፤ “በመላው አገሪቱ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሙት ተቃውሞ ብዙዎችን እንዳስደመመ ቀጥሎአል” በማለት ዘገባውን ቋጭቷል።
No comments:
Post a Comment