Wednesday, March 13, 2013

መንግስት ታላቁን የአፋር ኡለማ ሊያስር ነው!

አፋሮች ትግሉን መቀላቀላቸው ተከትሎ ታላቁ የሀይማኖት መሪ ሸህ መሀመድ አወል ሃይታንን ለማሰር ፌዴራል ፖሊስ እየተጠራ እንደሆነ ታወቀ::በአፋር ህዝብ ዘንድ እንደ አባት የሚታዩትን ታላቁን ዐሊም ሸህ መ…ሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ታወቀ፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ሊወስድ ያሰበው ለወትሮውም ቢሆን ለዲኑ ቀናኢ መሆኑ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በአሁን ሰዐት በዲኑ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን መቃወም በመጀመሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአፋር ነዋሪዎች እንደሚሉት የአፋር ህዝብ ስለ ዲኑና ስለ ማንነቱ ጠንቅቆ ያወቀበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የትኛውንም አይነት ጭቆና ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለም፤ ለዚህም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል፡፡ የአፋር ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንቃቱ ያሰጋው መንግስት በበኩሉ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ክብር ያላቸውን ሸህ ለማሰር እንደወሰነ፣ ይህ ደግሞ ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እየተነገረ ነው፡፡
ሸህ መሀመድ አወል ሀይታን በሎጊያና በሰመራ በአፋርኛ የቁርዐን ተፍሲርና ሃዲስ ህዝቡን ከማስተማራቸውም በላይ ህዝቡ እርስ በእርሱ እንዲቀራረብ ፣ እንዲከባበር፣ እንዲዋደድና ከሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋርም እንዴት ተቻችሎ መኖር እንደላለበት የሰበኩ ታላቅ የሃይማኖት አባት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የህዝቦች መቀራረብና ሰላም መሆን ምቾት ለማይሰጣቸው የመንግስት አካላት ግን ጉዳዩ ፍርሃት ስለለቀቀባቸው ሸሁን ማሰር አማራጭ አድርገው እንደያዙት ታውቋል፡፡ ሸህ መሀመድ እንዲታሰሩ ለመንግስት ያማከሩ ግለሰቦችና ምክሩንም ተቀብለው ተግባራዊ ያደረጉ ባለስልጣናት የመንግስትን ውድቀት የሚሹ እንደሆኑ የጠቆሙት ምንጮቻችን ቁርዐንና ሃዲስ ለምን አወራህ፣ ህዝብ እንዲከባበርና አንድ እንዲሆን ለምን መከርክ በሚል ሰበብ ሸሁ እዲታሰሩ ሲወስኑ የአፋር ህዝብን በሙሉ ሰብስቦ እስር ቤት እንደማስገባት አድርገው ሊቆጥሩ እንደሚገባና ይህም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ህዝብ ሀይማኖቱን የሚጨቁኑበትንና የሀይማኖት አባቶቹን ወደ እስር ቤት የሚልኩበትን አካላት በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም ከምንግዜውም በላይ እንደተዘጋጀ ታውቋል፡፡ መንግስት ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ እንደታወቀ የአካባቢው ሰዎች እንደገለፁት ‹‹መንግስት ህዝብን ማዳመጥ አለበት፣ ህዝብ ያልፈለገውን ነገር በግድ ለመጫን መሞከር ከብለዋል፡፡መንግስት አይጠበቅም፡፡ መንግስት ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ያስባል በሚል አመት ሙሉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ ጥሪ ላይ ቢገኝም አንዳንድ የመንግስት ፅንፈኛ ባለስልጣናት ከታሪክ መማር ባለቻላቸው ለሀገሪቷ የማይጠቅም ውሳኔ ውስጥ እየገቡ ነው ›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹የህዝብ ሙስሊሙ ጥያዌ ምላሽ ያገኛል በሚል ተስፋ ላይ እያለን ጭራሽ በክልላችን እንደ አባት የምናያቸውን ታላቁን ዐሊማችንን ለማሰር መወሰኑ የአፋርን ህዝብ ከምንግዜውም በላይ ድምፁን እንዲያሰማ ያደርገዋል እንጂ ወደ ኋላ አይጎትተውም››
  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
 

No comments: