Monday, March 4, 2013

"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተሳተፉበት የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ስብሰባ"

አስገራሚ መረጃ

የኢህአዴግ ጉዳ ይ ዘመኑ የፈጠራቸውን አባላት አይመለከትም::
"ድርጅታችንን ከመበታተን እና ከውድቀት ማዳን " እንዴት??
ከቀናት በፊት ለሊቱን የኢሕኣዴግ ነባር ታጋይ ባለስልጣናት እና ጄኔራሎቻቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የታሰሩ የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞችን የሚፈቱበትን ብልሃት እና ድርጅታቸው የገባበትን አጣብቂኝ እንዲሁ ከመበታተን እና ከመፍረስ ለመዳን በሚል ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሩ እንቅልፍ አስተኝተው እስከንጋት መዳረሻ ሃይለማርያምን ያላሳተፈ ዉይይት አድርገዋል::

እነዚህ በሙስና የተዘፈቁ እና የነገ ህይወታቸው ያሳሰባቸው የወያኔ ቀደምት ታጋዮች የመጀመሪያ አጀንዳ ብለው የያዙት ድርጅታቸውን ከመፈራረስ እንደት ሊያድኑት እንደሚችሉ ነው :: በአሁን ሰኣት እየተጠቀሙበት ያለ አይነት የፖለቲካ አካሄድ ከደርግ እንደማይለይ እና የደርግንም ውድቀት ያፋጠነ እንደዚህ አይነቱ አፈጻጸም የጎደለው የፖለቲካ ስልት ነው በሚለው ሃሳብ ዙሪያ መነሾነት ከቀበሌ ጀምሮ የተደራጁት የፖለቲካ ህዋሶች መረጃ እየሸጡ ነው ለግል ጥቅም ባገኙበት ሁሉ ይገባሉ አዳዲስ አባላትንም ብንመለምል ለስለላ እንጂ ሊያገለግሉ አልቻሉም ስለዚህ መፍትሄ ያስፈልጋል ብለዋል :: ለዚህ የሚያስፈልጉ ድርጅታዊ ጉዳዮች ሳይሰሩ ስብሰባውን ለመጋቢት ያስተላለፍነውም ለዚህ ነው እና ስብሰባው ከመድረሱ በፊት የተሰሩ ስራዎች እንደሌሉ እና ፉርሽ እንደሆኑ እየታየ ነው በሚለው ተስማምተዋል::

ኦህዲድን እና ደሕኣዴግን ያላሳተፈው ይህ የህወሓት እና የብኣዴን ታጋዮች ስብሰባ በነባር የትግራይ ተወላጅ ታጋዮች መካከል የተነሳውን የመከፋፈል አደጋ አንስቶ ለቀሪዎችም አባል ድርጅቶች መጥፎ ገደል እየሆነ መሆኑ ተጠቁሟል::ስለዚህ ከኣሁ ሰአት ጀምሮ ሁለቱ አንጃዎች መስማማት አለባቸው በማለት አቶ ስብሃት ነጋ ቢያንገራግሩም በሕወሃት መካከል በመርህ ደረጃ ስምምነት ተደርሷል:: ወይዘሮ አዜብ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ባይሰጡም ሆኖም የኢህኣዴግ ለዚህ ችግር መብቃት ተጠያቂ ያደረጉት ሳይመዘኑ ዘለው ማእከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የገቡት አዳዲስ አባላት ናቸው ብለዋል::

በስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበሩት ስብሃት ነጋ ኣርከበ ዕቁባይ ፀጋይ በርሀ በረከት ስምዖን ኣዜብ መስፍን ትርፉ ኪዳነማርያም ተክለወይኒ ኣሰፋ ሳሞራ ዮኑስ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ኣዲሱ ለገሰ ዓለም ገብረዋህድ አዲስአለም ባሌማ ሕላዊ ዮሴፍ ስዩም መስፍን ጌታቸው አሰፋ ኣባይ ፀሃዬ እንዲሁም ለጊዜው ስማቸው ያልተጠቀሰ 5 ጄኔራሎች ነበሩ::እነዚህ ተሰብሳቢዎች በተደጋጋሚ ያነሱት ድርጅታችንን እንዴት እናድን ነው::
በዚህም መሰረት ድርጅታቸውን ማዳን የሚችሉበት አዳዲስ ታማኝ ትውልዶችን ሰብስቦ ስልጣን በመስጠት በማስተማር አላማቸውን እንዲያስፈጽሙ ማድረግ ድርጅታቸውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ማዳን እንደሚችሉ ...የደርግ እጣ እንዳይገጥማቸው ሰራዊቱ ውስጥ ያሉትን አስቸጋሪ የተባሉ ከፍተኛ መኮንኖችን ጠቀም ያለ እና አፋቸውን የሚያዘጋ ገንዘብ እና ንብረት እየሰጡ ማሰናበት ...ከትግራይ ክልል እና አከባቢው ታማኝ አባሎችን አምጥቶ አዲስ አበባ ውስጥ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ላይኛው እርከን መሾም:...እስረኞችን መፍታት :አስፈላጊ የሚባሉ የቀድሞ አባላትን ወደ ድርጅቱ ጋብዞ ስለተሃድሶ መነጋገር እና ለውጦችን ማድረግ ማስፈጸም:: እንዲሁም ታማኝ የሰራዊት አባላትን እና የፖሊስ ሃይሎችንእና የደህንነትአባላት በማስታጠቅ አስፈላጊውን ጥቅማጥቅም በመስጠት በመንግስት (በግለኝነታቸው መባሉ ነው) ላይ የሚከሰተውን ማንኛውንም ችግር ፈጥነው እንዲያመክኑት ሲሉ በቅርቡ ሰልጥኖ የተመረቀው የኮማንዶ ሃይል በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዲሰፍር በማለት ተነጋግረዋል:: በተጨማሪም በሃገሪቱ የተማረ የሰውሃይል በሚበዛባቸው ከተሞች ደህንነቶች እንዲሰማሩ ብለዋል::

የሃገሪቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ምንም ያልተነጋገረው የሀው የታጋዮች ስብሰባ እስረኞችን በተመለከተ አለማቀፍ ጫና እየበረታ መምጣቱን እና በእነዚህ እስረኞች የመጣ ዲያስፖራው ወዳጆቻችን እንኳን ፊታቸውን እያዞሩ ነው የሚለውን ሃሳብ አንስተው ተወያይተዋል::
በዚህም መሰረት እስረኞቹን መፍታት እንደሽንፈት የሚያዩት አቶ በረከት ስምኦን እንዳሉት እስረኞቹን ለመፍታት እንዲያመች ሽማግሌዎች ብንልክም ማንም የሚቀበላቸው የለም :: በሌላ በኩል እየሞከርን ብንገኝም እንዲሞክሩልን የጠየቅናቸው ከየክልሉ የሰበሰብናቸው ሽማግሌዎች በቀጥታ ፍቷቸው እኛ ከ ህዝብ ጋር መጣላት አንፈልግም ብለዋል :: አኩርፈውም ሄደዋል:: እንዲሁም ከአፋር የመጡት ሽማግሌዎች የይቅርታ ቅድመ ሁኔታዎች ብናቀርብ ሊቀበሉን አልቻሉም ትተውን ሄደዋል:: ዲያስፖራው እና አጋሮቻችንንም ቢሆን በየምናገኛቸው ወቅት የሚያነሱልን የእስረኞችን አጀንዳ ነው ብለዋል:: ማድረግ ያለብን ምንድነው ታዲያ? ....ሲሉ ተደምጠዋል::

ሁነታዎችን እያዩ እና ሰበብ እየፈለጉ መፍታት አሁን ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተጀመረው ዉይይት ጥሩ ነው ችግሩ ሰዎቹ የይቅርታ ፎርም ፈርሙ ሲባሉ አሻፈረኝ ማለት ጀምረዋል::(ለማስታወስ ከዚህ ወራት በፊት እንዳስታወቅነው ፎርም የሚሞሉ እንደሚፈቱ ተነግሮ ነበር) ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ የተጀመረው ስራ በእንጥልጥል መተው የለበትም ለእኛም ያሰጋናል:;አስቸኳይ መፍትሄ ይፈለግ ብለዋል::በየጊዜው እየተወያየን አዲስ የተለየ ሃሳብ ላይ ወስነን የተወሰኑ እስረኞች መፈታት አለባቸው ዋናው ዲያስፖራው የሚያራግብባቸው ስማቸው በብዛት የሚነሳ ሰዎች መለቀቅ አለባቸው:: ይህ በንዲህ እንዳለ አንዳንድ ነባር አባላት መረጃዎች እየሸጡ ስለሆነ የት እንደሚውሉ ከማን ጋር እንደሚገናኙ ከነቤተሰቦቻቸው መሰለል አለባቸው ሲሉ ወስነዋል::

በዚህ ስብሰባ ላይ የአቶ መለስ ዜናዊ ራእይ የሚባል ነገር አልተነሳም:: እንዲሁም የኢህአዴግ ጉዳ ይ ዘመኑ የፈጠራቸውን አባላት አይመለከትም:: ያሉት አና የተስማሙት ነባር አባላቱ አቶ ሃይለማርያም ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ አልተነሳም:: ኦሆዲዶች የታሉ ያለም አልነበረም:;አብዮት ማለት እንዲህ ነው::አስገራሚ መረጃ

በዚህ ስብሰባ ላይ የአቶ መለስ ዜናዊ ራእይ የሚባል ነገር አልተነሳም:: እንዲሁም የኢህአዴግ ጉዳ ይ ዘመኑ የፈጠራቸውን አባላት አይመለከትም:: ያሉት አና የተስማሙት ነባር አባላቱ አቶ ሃይለማርያም ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ አልተነሳም:: ኦሆዲዶች የታሉ ያለም አልነበረም:;አብዮት ማለት እንዲህ ነው::

No comments:

Post a Comment