Friday, March 1, 2013

በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ሲሆን ፣ የወያኔ ካድሬዎችም ድርጊቱን ለማስቆም የተጠናከረ አሰሳ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።


በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ሲሆን ፣ የወያኔ ካድሬዎችም ድርጊቱን ለማስቆም የተጠናከረ አሰሳ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በመላ ሀገሪቱ እየታየ ያለው የሕዝብ መነሳሳት ስሜትና ተጋድሎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከለውጥ ፈላጊው ሕዝብ ጎን የቆመ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያቶች በጠላት ላይ በሚያደርሰው ጥቃት የሀገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረ ሲሆን፣ ከወታደራዊ ትግሉ ጎን ለጎን የአካባቢውን ህብረተሰብ የማስተማር፣ የመቀስቀስ፣ የማደራጀትና የማስታጠቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገለፀ።
በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ደጋፊዎች አማካኝነት የድርጅቱ ወቅታዊ የሀገር አድን ጥሪ በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ በመገኘቱ ስጋት የገባው አሸባሪው የወያኔ ገዥ ቡድን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ወከባና እንግልት እያደረሰ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን የመረጃ ምንጭ ያስረዳል።
በመላ ሀገሪቱ እየታየ ያለው የሕዝብ መነሳሳት ስሜት በተደራጀ መልኩ እንዲቀጥልና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀጣጠለ የመጣው ሕዝባዊ ተቃውሞ ለፍሬ ይበቃ ዘንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተነስ! ታጠቅ! ዝመት! የሚለውን ወቅታዊ የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀት በሃገሪቱ በተለያዩ ከተሞች በብዛት እንዲሰራጩ በድርጅቱ ደጋፊ አባሎች አማካኝነት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረግን ሲሆን ይህ የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀትም በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነትን ከማግኘቱም በተጨማሪ ለስርዓት ለውጥ በሚደረገው የትጥቅ ትግል መላውን ህብረተሰብም መነሳሳትን እንደፈጠ...ረለትና የተጀመረውም ሕዝባዊ አመፅ ግፊቱ እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።
በመተማና አካባቢው እየተሰራጨ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀት ዋና አላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ ላይ ያለው ጥላቻ ግልፅ ማድረግ ቢሆንም ሕዝብ እንደ ሕዝብ እጅ ለእጅ በመያያዝና በመደጋገፍ በአምባገነኑና አሸባሪው ገዥ ቡድን አፋኝና ቀፍዳጅ ስርዓት ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር መነሳት፣ መታጠቅና መዝመት የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ህብረተሰቡ የጀመረውን ሕዝባዊ ተቃውሞ አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የታለመ ሲሆን በዚህ የተደናገጠው ወያኔና ተላላኪዎቹ በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ህብረተሰቡን በማስፈራራትና በማዋከብ ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሰን የመረጃ ምንጭ ያስረዳል።
አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ የወቅቱን የፖለቲካ ትኩሳትና ተጨባጭ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ህብረተሰቡን ለበለጠ የፀረ- ወያኔ የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በሰፊው በማሰራጨት ትግሉ የደረሰበትን የእድገት አቅጣጫ እንዲሁም አናሳው የወያኔ ቡድን በሕዝብና በሃገር ላይ እየፈፀመ ያለውን ስውር ደባ በማጋለጥ ክፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልፀው፣ የጀመሩትን ፀረ- ወያኔ አመፅና ተቃዎሞ አጠናክረው እንደሚገፉበትና የድርጅቱን ወቅታዊና የሀገር አድን የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀት በተለያዩ ቦታዎች በሰፊው የሚሰራጭበትን ስልት ቀይሰው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
 
    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

No comments:

Post a Comment