Wednesday, February 27, 2013

ሶስተኛው ዙር የአፈና እና የስለላ መምሪያ ንድፍ/እቅድ

 





በፈረንጆቹ አዲስ አመት ተከትሎ ወያኔ ያቋቋመው የአፈና እና የስለላ መዋቅር በደረረሰን መረጃ መሰረት ባለሃብት ናቸው የሚባሉ ሙስሊሞችን ለመጉዳት...የቤት ለቤት አሰሳ እና ፍተሻ እንደሚያካሂድ እንዲሁም ወደ ኢንተርኔት ካፌዎች ሊዘምት እቅድ እንደነደፈ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ይኅን ጉዳይ ብሎግ ያደረግንበት ድህረገጻችን እትዮጵያ ዉስጥ ለ2ኛ ጊዜ ታግዶ ይገኛል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምኒሊክ ሳልሳዊ ባደረሱት መረጃ መሰረት የስለላ እና የአፈና መምሪያው ከብሄራዊ መረጀ እና ደህንነት መምሪያ ጋር በመሆን አዲስ ሚስጥራዊ ያሉትን የአፈና ስልት ነድፈው በይፋ ለመጀመር ቅድመዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተደርሶበታል::
በዚሁ መሰረት 3ኛው ዙር የአፈና እና የስለላ እቅድ የሞባይል ጠለፋ እና ሰበብ በመፍተር ሙስሊም ወጣቶችን ከመንገድ ላይ አፍኖ የመውሰድ ሴራ ነድፈዋል:: ያሉት የምኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ይህንን እቅድ ተከትሎ በሙስሊም ስሞች ተመዝግበው የሚገኙ ሲም ካርዶችን የባለቤቶቹን ስም እና አድራሻ በዝርዝር እንዲሰጠው በአቶ ደብረጺሆን በኩል ለቴሌ ምስጢራዊ ያሉት እነሱ ትእዛዝ የተላለፈ ሲሆን እያንዳንዱ የስልክ ግንኙነት እንዲመረመር ሲነገራቸው እንዲሁም የተቃዋሚ ሃይሎች እና ለቤተክርስቲያን ቅርብ ናቸው ተብለው በተቃዋሚነት የተፈረጁ ግለሰቦች የዚህ አፈና ኢላማ ናቸው::

ሌላኛው በንኡስ አንቀጽ የተቀመጠው በትምህርት በስለዋል የሚባሉ ሙስሊም ወጣቶችን እና የማህበረቅዱሳን `አማፂ` የተባሉ እንዲሁን የራእይ ወጣቶች ማህበር አባላትን ኢላማ አድርጎ ከመንገድ በሰባብ አስባቡ አፍኖ መውሰድ ሲሆን ይህም በብዛት የሚአተኩረው ፈረንሳይ ለጋሲዎንን መነሻ አድርጎ እስከ ጉለሌ እና ላፍቶ ድረስ ሊሰራ የታሰበ ሲሆን በመሃል ከተማ አከባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ ተፈጻሚ ይሆናል::ሲሉ የምኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::
ስለዚህ በሰፊው ማብራሪያው ደርሶን መርጃውን እስከምንሰጣቹህ ድረስ ይህንን መሰረታዊ መረጃ ተመርኩዛችሁ ቤያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ ላይ ከ ፈጣሪ ጋር ተጠንቅቃችሁ እንድትታገሉ ምክር እየሰጠን ለሁላችንም ፈጣሪ ይረዳን ዘንድ በፆም እና በጸሎት እንድንተጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን::

No comments: