ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ደህንነቶች እንደሚመረመሩና እንደሚታሰሩ ተገለጠ
ዩናይትድ
ስቴት አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ጋምቤላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ተጉዘው የነበሩት ዶ/ር ማኝ አንግ ለኢሳት እንደገለጡት
በጋምቤላ በክልሉ ፕሬዚዳንት ተጠርተው ደህንነቶች እንደሚፈልጎቸው ከተነገራቸው በሆላ ለ 2 ሰአት ያህል እንደመረመሮቸው
አስታውቀዋል::
ማንኛውም
የጋምቤላ ተወላጅ ወደተወለደበት ሀገር ሲሄድ ያሬድ፡ ኤፍሬምና ዳዊት በሚባሉ የመንግስት ደህንነቶች ይመረመራል፤ በጋምቤላ ከሚገኙ
የተቃዋሚ መሪዎች፤ ከግምቦት ሰባትና በጋምቤላ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ስላለው ግንኙነት ይጠየቃል ያሉት ዶ/ር ማኝ አንግ
በሳቸው ላይም ተመሳሳይ ምርመራ ከተደረገ በሆላ በነጻ መለቀቃቸውን ተናግረዋል::
ይሁንና
በርካታዎቹ በደንነት ከተመረመሩ በሆላ እንደሚታሰሩ የገለጡት ዶ/ር ማኝ አንግ በቅርቡ በቦሌ አየር ማረፊያ የታሰሩና በአሜሪካ
ኤምባሲ ጥረት ተፈተው ከቦሌ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ስለተመለሱት ሁለት የአኝዋክ ተወላጆች ተናግረዋል:፡
በተወለዱበትና
ባደጉበት ሀገር ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ የሄደ ሰው በመንግስት ደህንነቶች መታደኑ፡ መመርመሩና መታሰሩ በጋምቤላ የተለመደ ነው ያሉት
ዶ/ር ማኝ አንግ 20 አመት አሜሪካ ቆይተው በሀገራቸው ስለደረሰባቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ተግባር ኮንኖል
No comments:
Post a Comment