የወያኔ አገዛዝ የቀድሞ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮንኖችን ከተጠቀመባቸዉ በኋላ እንደሚያስራቸዉ ታወቀ
February 12, 2013
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ያሰለጠነቻቸዉንና ከፍተኛ ወታደራዊ ሳይንስ ችሎታ ያላቸዉን የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር አባላት ሲያሰኘዉ እየተጠቀመባቸዉ ሳያሰኘዉ ደግሞ ተቃዋሚዎችን ትረዳላችሁ እያለ እስር ቤት እንደሚወረዉሯቸዉ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ምንጮች ከሰሞኑ በላኩልን ዜና ገለጹ። ባለፉት ሃያ አንድ አመታት ወያኔ የማይበገር ሰራዊት ገነባሁ ብሎ የሚፎክርበትን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት በተደረገዉ ጥረት ዉስጥ ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን የቀድሞ ጦር ከፍተኛ መኮንኖች በአንድ በኩል ተቃዋሚ ድርጅቶችን ትረዳላችሁ የሚል በሌላ በኩል ደግሞ የቅንጅትን ወታደራዊ ክንፍ እያጠናከራችሁ ነዉ የሚ...ል ሰንካል ምክንያት በመፍጠር ከ10 እስከ 15 አመት የሚደርስ እስር ፈርዶባቸዉ እያሰቃያቸዉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
የ1997ቱ ምርጫ ካለቀ በኋላ በተደረገዉ ግምገማ ተቃዋሚዎችን ትረዳላችሁ፤ ህገመንግታዊ ስርአቱን በሀይል ለመናድ ሞክራችኋል በሚልና የጦር መሳሪያ ለቅንጅት ወታደራዊ ክንፍ አቀብላችኋል በሚል የሀሰት ክስ ተከስሰዉ ታጠቅ ጦር ሰፈር ተወስደዉ ከታሰሩት ከፍተኛ መኮንኖች ዉስጥ አምስቱ ኮሎኔሎች ሲሆኑ አንዱ ሻምበል ናቸዉ። የወያኔዉ አቃቤ ህግ ወታደራዊ መኮንኖቹ ላይ ምንም አይነት መረጃ ማቅርብ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን የቅንጅት ወታደራዊ ክንፍ የሚባል ኃይል በሌለበት ቦታ ንጹህ ዜጎችን የቅንጅት ወታደራዊ ክንፍ አባላት ናችሁ ብሎ ማሰር በፍትህ ስርአት መቀለድ ነዉ ሲሉ የመኮንኖቸቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል። የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክረሲ ፓርቲ ተዳክሞ ከጠፋና የታሰሩት የፓርቲዉ አባላት ከተፈቱ በኋላ ወታዳራዊ መኮንኖቹም ይፈታሉ የሚል ከፍተኛ ግምት የነበረ ቢሆንም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ማንሰራራት በተለይ እንደ ግንቦት ሰባት አይነት ድርጅቶች መፈጠር ያስደነገጠዉ ወያኔ ተቃዋሚዎችን ትቀላቀለላችሁ በሚል ወታደራዊ መኮንኖቹ እንደታሰሩ እንዲቆዩ አዟል።
ወያኔ በግፍ ካሰራቸዉ የቀድሞ ጦር መኮንኖች ዉስጥ ኮሎኔል ተስፋ ኃይሉ የሚባሉት መኮንን እስር ቤት አንዳሉ በህመም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን ስማቸዉ ከዚህ በታች የተዘረዘረዉ መኮንኖች ግን አሁንም እንደታሰሩ ነዉ።
ኮሎኔል አበበ አስረስ
ኮሎኔል ተስፋዬ ለማ
ኮሎኔል ጌትነት አድማሱ
ኮሎኔል ጎሳዬ ቦጋለ
ሻምበል ካሳሁን
የግንቦት ሰባት ድምፅ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች አክለዉ በላኩልን ዜና መሠረት ወያኔ በግፍ ያሰራቸዉ ወተደራዊ መኮንኖች በሙሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸዉ።