Sunday, October 5, 2014

በ46 አመቱ የህወሃት አገልጋይ እና የኢምባሲ ጠባቂ በሆነው ሰለሞን ገ/ስላሴ ላይ የአሜሪካን መንግስት ክስ መሰረተበት

Oct 05, 2014
ቢል ሚለር የአሜሪካ ፍትህ አካል ቃላ አቃባይ የሆኑት ባለፈው ሰኞ በሰላማዊ ሰልፈኞች እና በኢትዮጵያ ኢምባሲ ዋሽንግተን ጽ/ቤት መካከል በነበረው ሂደት ላይ የኢምባሲ ጠባቂ በሆነው ሰለሞን ገ/ስላሴ ሽጉጥ ተኩሶ የመግደል ሙከራ ማደርጉ ወንጀል መሆኑን አምነው ይህም የዲፕሎማቲክ ፈቃዱ ከክስ እንደማያድነው ተናገረዋል። በዚህ መሰረት የአሜሪካን መንግስት ፍትህ ጸ/ቤት ክሱን አዘጋጅቶል። ሰውየው ከሀገር ቢባረርም በሌለበት ሂደቱ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ሰለሞን ገ/ስላሴ ከዚህ በሆላ ጥፋተኛ ከተባለ ከ15 እስከ 20 አመት በሚደርስ የእስራት ቅጣት እንደሚጠብቀው የህግ ባለሙያዎች የተነተኑ ሲሆን ይሁን እንጂ ሰለሞን ወይም የኢትዮጵያ ኢምባሲ ይህን ሂደት ስለሚያውቁ ተጠርጣሪው ወደ አሜሪካ የመመለስ አጋጣሚን እንደማያደርግ ይታመናል።
ለህግ ባለሙያው; ከክስ ሂደቱ ማጠናቀቂያ በሆላ ውሳኔዉን ለማስፈጸም የአሜሪካን ሀገር ወንጀለኛውን ለመያዝ የማደኛ ትእዛዝ ሊያስተላልፍ ይችላል ወይ ብለን ላቀርብንላቸው ጥያቄ አሁን የሚወሰን ሳይሆን ወደፊት እንደወንጀሉ ክብደትና ቅለት የሚለካ ነው ሲሉ የህግ ባለሙያው ለአባይ ሚዲያ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በእንደዚህ አይነት የቀለለ ወንጀል ሲገባ የመጀመሪያ ባይሆንም ይህ ለየት የሚያደርገው አምባሳደር ግርማ ብሩም የጉዳዩ ተዋናያን መሆናቸው እንዲሁም በርካታ የአለም ሚዲያዎች የዘገቡት መሆኑ ነው።
አምባሳደር ግርማ ሰሙኑን ከሬዲዮ ፋና ጋርና ከሌሎች የወያኔ ሚዲያዎች ጋር ባደረጉት ንግግራቸው ምንም አይነት ስለ ጠባቂው ሰለሞን የሰጡት ማስተባባያ የለም። በደፈናው የተቃዋሚ ቡድኖች በኤርትራ  ተደግፈው ያደረጉት ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
ዘጋቢያችን በማጠቃለያው የኤርትራ መንግስት አሜሪካ ውስጥ ገብቶ ወያኔን ያስጭንቃል እንዴ? ምን አይነት አምባሳደር ይሁን ሀገሪቱ ይዛ ፕሮፖጋንዳ የምትሰራው ሲል ትዝብቱን በማከል ሪፖርቱን ለ አባይ ሚዲያ ልኮልናል ።
አባይ ሚዲያ

ሚ/ር ሽፈራው በመሥሪያ ቤቶች እና በትምህርት ቤት አካባቢ ክርስቲያኖች ክር እና መስቀል ከማሰር እንደሚከለከሉ አስታወቁ

Oktober 5,2014
የሐራ ተዋሕዶ ትንታኔ
ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!
ከሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ጠንካራ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡
‹‹በሴኩላሪዝም ሰበብ ማዕተብኽን በጥስ ማለት ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፡፡ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› /የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
‹‹ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትና ሕይወት መግለጫ በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡›› /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ/
* * *
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
‹‹ሚኒስትሩ የመንግሥትን ሴኩላርነት ለማረጋገጥ በሚል የሰጧቸው አስረጅዎች የግልጽነትም የአግባብነትም ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሚበዛው ኢትዮጵያዊ አማኝ ከመኾኑ አንፃር ትርጉም እንዳለውና በሕገ መንግሥቱ እምነት ነክ ድንጋጌዎች እንደተንጸባረቀ ከሚታመነው የሴኩላሪዝም ፈርጅ (positive secularism) ይልቅ በርእዮትና አሠራር የተደገፈ ሃይማኖትንና ሃይማኖተኝነትን የማዳከም (negative secularism) አዝማሚያዎች ያይልባቸዋል፡፡ ከእምነት ተቋማት ጀርባ የግንባሩን አባላት ጨምሮ ሰፊው አማኝ ሕዝብ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ ‘በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር’ እንደሚኖር በመንግሥት የኢንዶክትሪኔሽን ጽሑፎች ከተቀመጡት አቅጣጫዎች ጋራም የሚጣጣሙ አይደሉም፡፡ በተለይ ከቤተ ክርስቲያናችን አንፃር ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የሚመስል ‘issue’ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ በዚኽ አኳኋን እንዴት ነው ዜጎች ‘ሚዛናዊ አስተሳሰብ’ እንዲያዳብሩ የሚጠበቀው? ከመንግሥት ጋራ አብሮ መሥራትስ እንዴት ይቻላል?››
‹‹ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ’ የሚል ሴኩላሪዝምን በአዎንታዊነትና በቀላሉ የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያለው ነው፡፡ በሚኒስትሩ የተብራራው የሴኩላሪዝም መርሖ ግን ምእመኑን ለእምነቱ ለዘብተኛ በማድረግ በሒደት ወደ ሃይማኖት አልባነት የመምራት ተንኰል የተሸሸገበት ያስመስላል፡፡››
‹‹ክርስቲያንነታችንን በየራሳችን የምንመሰክርበት መለዮአችን ማዕተብ ለመንግሥት ሴኩላርነት ተፃራሪ እንደኾነና ሊከለከል እንደሚችል መናገር ስለ መንግሥት የሴኩላሪዝም መርሖ የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን አማኝ ፀረ – ሴኩላር የሚያደርግ፣ ሕዝቡንና መንግሥትንም ፊት ለፊት የሚያፋጥጥ እንዳይኾን ያሰጋል፡፡››
/የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች የኾኑ ኦርቶዶክሳውያን የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
የክርስቲያንነት መለዮአችን፣ የርትዕት ሃይማኖት ምስክራችን የኾነውን ማዕተብ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና በትምህርት ተቋማት አስሮ ከመታየት ልንከልከል እንደምንችል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሺፈራው መናገራቸው ተሰማ፡፡
የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖና የፀረ አክራሪነት አጀንዳ ተገን በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ርእዮታዊ እና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን በማስተጋባት የሚታወቁት ሚኒስትር ሺፈራው፣ ይህን መናገራቸው የተጠቆመው፣ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ድረስ በዘለቀውና በኹለት ዙሮች በተካሔደው የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና ላይ ነው፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሔደውና 800 ያህል መካከለኛ አመራሮች በተሳተፉበት የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ግንባታና ፈተናዎቹ›› የሚለውን ሰነድ የሚያብራራና በፓወር ፖይንት የተደገፈ ጽሑፍ ያቀረቡት ሚኒስትሩ የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ መነሻ ያደረገ ነው የተባለ ጥያቄ ከአንዲት ተሳታፊ ቀርቦላቸዋል፡፡
እንደ ስብሰባው ምንጮች፣ የተሳታፊዋ ጥያቄ፣ ‹‹በቢሮ ፊታቸውን ተሸፍነው የሚመጡ ሙስሊሞችን አለባበሳቸው ከቦታው አንፃር ያለውን ተገቢነት በማንሣት እንዲያወልቁ ስንጠይቃቸው ‘እኛ ይኼን የምናወልቅ ከኾነ ኦርቶዶክሱም ክሩን ይበጥስ’ ይሉናል፤ ይኼን እንዴት ነው የምንታገለው?›› የሚል ነበር፡፡
‹‹መንግሥታችን ሴኩላር ነው›› ሲሉ በጠያቂዋ የተጠቀሰውን ዐይነት አለባበስ የተቹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹እርሱም [ማተቡም] ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢኾን መውለቁ አይቀርም፤›› የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተገልጧል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ማጉረምረም በማሰማት በሚኒስትሩን ምላሽ ላይ ተቃውሟቸውን መግለጣቸው ተጠቅሷል፡፡ ሌላው ተሳታፊም፣ ‹‹በመሠረቱ ፊት መሸፈንን ማዕተብ ከማሰር ጋራ ማመሳሰል ልክ አይመስለኝም፤ ማተብም ቢኾንኮ ከሃይማኖታዊነት አልፎ ማንነትና ባህል ኾኗል፤ ማስቀረቱ አደጋ አለው፤›› ሲሉ ከተሳታፊው ከፍተኛ የጭብጨባ ድጋፍ እንደተቸራቸው ተዘግቧል፡፡
ሚኒስትሩ ‹‹ይኼ ግን የዚኽ ሥልጠና አካል አይደለም›› በሚል የተሰብሳቢውን ተቃውሞ ለማለሳለስና እንደዋዛ ለማለፍ ቢሞክሩም ጉዳዩ በዕረፍት ሰዓት በከፍተኛ ስሜት ከማወያየት አልፎ የሚኒስትሩን አጠቃላይ አቀራረብና ስውር ፍላጎት የተመለከቱ ቅሬታዎች ሲሰነዘሩም እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ‹‹የሰውዬው ዓላማ ኹላችንን ፕሮቴስታንት ማድረግ ነው ወይ?›› ያሉ አንድ ተሳታፊ የሥልጠናውን አስተባባሪዎች ‹‹ለምንድን ነው የማትነግሩት?›› በማለት በቁጣ ጠይቀዋል፡፡
የሚኒስትሩ ምላሽ ጥንቃቄ የጎደለው እንደኾነ የጠቀሱ ሌላ አስተያየት ሰጭ፣ መንግሥታዊ ሥራን ከሃይማኖታዊ ውግንና አድልዎ ተጠብቆ በገለልተኝነት ማካሔድ እንደሚገባ ቢያምኑም ይህ በዋናነት የሚገለጸው በሲቪል ሰርቪሱ ሓላፊዎች አመራርና የውሳኔ አሰጣጥ፣ በሠራተኞች አቀራረብና የሥራቸው አፈጻጸም እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ እንደ ጥያቄው አቀራረብና እንደ ሚኒስትሩ ምላሽ፣ ማዕተብ ከአለባበስ ጋራ ተዘምዶ ከተወሰደም የሴኩላር መንግሥትን የገለልተኝነትና የእኩልነት መርሕ የሚጥስበት አልያም የሠራተኛውን ገጽታ በግልጽ ለመለየት የሚያግድበት ከዚኽም ጋራ ተያይዞ የማኅበረሰብ ሰላምና የደኅንነት ጥያቄ የሚያሥነሳበት ኹኔታ በማንም ዘንድ ሊኖር እንደማይችል አብራርተዋል፡፡
‹‹ከአለባበስ አኳያ የሴኩላሪዝም መርሖን ለማረጋገጥ ሃይማኖታዊ ግዴታ ያለባቸውንና የሌለባቸውን አለባበሶች ከግምት ያስገባል፤›› ያሉት አስተያየት ሰጭው፣ ማዕተብ *÷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጥምቀተ ክርስትና አፈጻጸም * * እያንዳንዱ ተጠማቂ የእግዚአብሔር ልጅነትን በጸጋ አግኝቶ የተስፋው ተካፋይ የርስቱ ወራሽ ለመኾን በሰማያዊ ዜግነት የሚታተምበት የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን አካል የመኾኑን የሃይማኖት መግለጫነት መሠረታዊነት በአጽንዖት አስገንዝበዋል፤ ዕቱባን አንትሙ በቅድስት ጥምቀት እንዲል፡፡
ከዚኽም በተጨማሪ ማዕተብ÷ የሲኦል መሠረት የተናወጠበት፣ ሰውንና እግዚአብሔርን ለዘመናት ለያይቷቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ የተናደበት፣ የሞት ኃይሉ ተሽሮ የትንሣኤ መንገድ የተከፈተበት መስቀል ትእምርት በመኾኑ በተሳሳተ የሴኩላሪዝም ግንዛቤ ‹‹ማዕተቡም ሊወልቅ ይችላል›› ማለት፣ ‹‹ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፤ ጉዳዩንም ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን vs. ቦኮ ሐራም
mahbere qdusanየሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ምላሽ ጥንቃቄ የጎደለው ነው የሚለውን አስተያየት የሚጋሩት ሌላው ተወያይ የበኩላቸውን ሲያክሉ፣ ‹‹ከዚኽም በላይ ግን በተለይ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ለተነሡ ጥያቄዎች፣ ‘ማኅበራት’ እያሉ በማስረገጥ ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የኾነ ‘issue’ ያላቸው በሚያስመስል ልዩ አጽንዖት ሲናገሩ ነው የሚታዩት፤›› ብለዋል፡፡
‹‹አብረን ተቻችለን በሰላም ኖረናል እየተባለ ስለ አክራሪነት ተጋኖ የሚነሣበት ኹኔታ አለ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመንግሥት ተጨባጭ ስጋት የኾነ አካል አለ ወይ?›› ተብሎ በጽሑፍ ለቀረበው ጥያቄ ሲመልሱ ትኩረት ያደረጉት÷ ‘በትምክህተኝነት፣ በሥልጣን ጥመኝነት፣ በቀለም ዐብዮት ሰባኪነት’ በከሰሷቸው የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ላይ ነበር፤ ንጽጽራቸውም የፖሊቲካ ፓርቲ ኾኖ መንግሥታዊ ሥልጣን ለመያዝ ከበቃው የግብጹ ሙስሊም ወንድማቾቾች አንሥቶ ከናይጄሪያ መንግሥት ጋራ በትጥቅ የተደገፈ ፍልሚያ ውስጥ እስከገባው የሽብር ቡድን ቦኮ ሐራም ድረስ የጨከነ ነበር፡፡
ውንጀላው ከአነጋገሩ እንደሚታየው በማኅበሩ አባላት ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልኾነ የሚታየው፣ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እዚህ ውስጥ አላችኹ፤ የድርጅትም አባል ናችሁ፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹መታገል ያልቻላችኹት የማኅበሩ አባል ስለኾናችኁ ነው፤ ኹለቱን እያጣቀሳችኹ መሔድ አትችሉም፤›› ለማለት ሲደፍሩ እንደነበር ተወያዩ አስረድተዋል፡፡ ይህም ሚኒስቴሩ በሚያዝያ ወር ፳፻፮ ዓ.ም. ባወጣው ሰነድ፣ ‹‹በማኅበሩ ውስጥ የመሸጉ ግለሰቦችና ቡድኖች መኖራቸውን መጠቆም ማኅበሩን አክራሪ/ጽንፈኛ ብሎ መፈረጅ አይደለም፤ ማኅበረ ቅዱሳንም በዚኽ አልተፈረጀም፤›› በማለት የሰፈረውን ማብራሪያ ተቀባይነት እንደሚያሳጣው ተመልክቷል፡፡
ሚኒስትሩ ከአክራሪነት በአንጻሩ ‹‹አጥባቂነት›› ትክክለኛና ሰብአዊ መብት እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ይኹንና ርቱዕነት፣ ቀናዒነት፣ ጽንዓት፣ ታማኝነት እና ትጉህነት እንጂ ‘አጥባቂ’ የሚባል ሃይማኖታዊ ቅጽል እንደማይስማማቸው፤ ልዝብነት ይኹን አጥባቂነት በቤታቸውም ይኹን በመጽሐፋቸው እንደሌለና እንደማይቀበሉትም ተወያዮቹ በግልጽ ይናገራሉ፡፡ በሚኒስትሩ አነጋገር ከትምክህት ርእዮት ጋራ በመዳበል ይታያሉ ያሏቸው የአክራሪነት አስተሳሰቦችም÷
የራስን እምነት በሌላው ላይ መጋት፤
የትምህርት ሥርዐቱን መረበሽ፤
በሃይማኖት ሽፋን ፖሊቲካዊ አቋም ማራመድ፤
የበላይነትን አጥተናልና ይህንኑ መመለስ ይገባናል፤
ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደሚመች እየጠቀሱ መተርጎም እና
የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እኒኽ አመለካከቶችና ድርጊቶች ግና የራሳቸውን አሳልፈው መስጠት ለማይወዱት፣ የሌላውንም ለማይሹት ኦርቶዶክሳውያን ጠባይ የማይስማሙ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተፈቀደውና ከታወጀው የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማና ተልእኮ እንዲኹም ከእያንዳንዱ አባላቱ አስተሳሰብ አንፃርም ቢኾን ተቀባይነት የሌላቸው ከንቱ ውንጀላዎች ተደርገው ነው የተወሰዱት፡፡
በዚኹ ዐይን፣ በዩኒቨርስቲዎች የሚነሡ ሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ስለምን በወጣው የአምልኮ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያ መሠረት እንደማይስተናገዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በትምህርት በተቋማቱ አካባቢ ከሚገኙ የአምልኮ ተቋማት ጋራ በመነጋገር ችግሩን ማስቀረት ያስፈልጋል፤›› በሚል የሰጡት ምላሽ አፈጻጸምም ማኅበሩ ሃይማኖቱን ያወቀ፣ በምግባሩ የተጠበቀና ሀገሩን የሚረከብ መልካም ዜጋ ለማፍራት ባደራጃቸው ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖረው በትኩረት ሊጤን እንደሚገባው ያስጠንቅቃሉ፤ ግቢ ጉባኤያት፣ በሥነ ምግባር የታነጸ ዜጋና የቤተ ክርስቲያንን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚያግዝ የአበው ተተኪ ትውልድ ማፍሪያ እንጂ ተንኰልና ክፋት በተጠናወተው አእምሮ እንደሚባለው ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት አስቀጣይ ኃይል መመልመያ መድረክ›› አይደሉምና፡፡
‹‹መንግሥት አክራሪዎችን ለምንድን ነው መቆጣጠር ያቃተው? ለምን ርምጃ አልወሰደባቸውም? የሃይማኖት አክራሪነትን የሚያስፋፉ ድረ ገጾችንስ ለምንድን ነው ማገድ ያልቻለው?›› ለሚለው የተሳታፊዎች ጥያቄ÷ ‹‹ወደ እያንዳንዱ ሰው መዝመት አዋጭ አይደለም፤ ዋናው የአመለካከትና የአስተሳሰብ ዝንባሌን ማስተካከል ነው፤ ሐሳብን በሐሳብ የማሸነፍ ስልት ነው የምንከተለው፤›› በማለት የሰጡትን ምላሽ በአዎንታ እንደሚቀበሉት አስተያየት ሰጭዎቹ አልሸሸጉም፡፡
ነገር ግን፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ሳይቀር የእግራቸው መረገጫ እስከ ማድረግና በሃይማኖት ተቋማቱ ላይ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን የበላይነት ለማስፈን እስከ መመኘት የናረ ለከት ያጣ ርእዮታዊ እና ምናልባትም ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን ጭምር በመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና በግንባሩ በካር ካድሬዎች ፊት ለመናገር የቀለላቸው ሚ/ር ሺፈራው፣ በቃል የሚሉትን ያኽል በመረጃና በዕውቀት ላይ ለተመሠረተ ገንቢ የሐሳብ መተጋገል ብቃቱም ፍላጎቱም አላቸው ብለው አያምኑም፡፡
ከዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር አኳያ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሚል ለኢንዶክትሪኔሽን የተዘጋጁት የመንግሥት ጽሑፎች ሊታረሙና በአጽንዖት ሊመረመሩ የሚገባቸውን ጉዳዮች የያዙ ቢኾንም በአጻጻፍ ደረጃ እንኳ፡-
አክራሪነትን ለመዋጋትና ከምንጩ ለማድረቅ፣ ልማታዊ ባህሎችንና ሥነ ምግባሮችን ለማጎልበት ከእምነት ድርጅቶች ጋራ በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር ሊኖረን ይገባል፤ በዴሞክራሲያዊ አኳኋንና የማንንም ወገን ነፃነት በማይነካ መልኩ መመካከር መቻል አለብን፡፡
የሃይማኖት ተቋሞች ከሃይማኖት እኩልነት፣ ከሕዝቦች መፈቃቀድ፣ ከሠርቶ መክበር ጋራ የተያያዙ የሞራል ትምህርት ማስተማር ከቻሉ ከዚያ በላይ እንዲሔዱ ማድረግ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤
ከእምነት ድርጅቶች በስተጀርባ አባሎቻችንን ጨምሮ ሰፊው ሕዝብ እንዳለ መገንዘብ ይገባናል፤
የሚሉ የጥንቃቄ አገላለጾችን በሚያሳዩበት ኹኔታ፣ የሚኒስትር ሺፈራው ጥናት የጎደለውና እርስ በርሱ የሚጋጭ የመድረክ አያያዝ በሰፊው አማኝ ሕዝብ ዘንድ ድርጅቱን እንዳስጠቆረው፣ በራሳቸው በሚኒስትሩም ላይ ከቅርብ የሥራ ባልደረቦቻቸው ጠንካራ ጥያቄ እንዳስነሣባቸውና በበላይ አለቆቻቸው ሳይቀር ክፉኛ እንዳስገመገማቸው መረጃው እንዳላቸው የስብሰባው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
በሴኩላሪዝም ሰበብ…
በታሪክ የአንድ ሃይማኖት መሠረታዊነት (hegemonic religion) በነበራቸው አገሮች የሚመሠረቱ ሴኩላር መንግሥታት ከሃይማኖት ተቋማት ጋራ ስለሚኖራቸው ግንኙነትና ስለሚከተሉት ሴኩላሪዝም “Secularism and State Policies towards Religion: The United States, France, and Turkey” በተሰኘው መጽሐፋቸው የተነተኑት የሳንዴያጎው ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር አኸመት ኩሩ፣ ከቀደሙት አገዛዞች ተጠቅሟል በሚባለው ነባር ሃይማኖት ላይ ጥላቻን ለማስፈን፣ አገራዊ ሚናውን ለመቀነስ ብሎም ከሕዝቡ ሕይወት ጨርሶ ለማጥፋትና በሴኩላሪዝም የበላይነት (the dominance of assertive secularism) ለመተካት መርሖውን በመሣርያነት የሚጠቀሙ ከልኩ ያለፉ ጠርዘኛ ዓለማዊ ኃይሎች (ultra-secularist circles) አይለው እንደሚታዩ የፈረንሳይንና የቱርክን ልምዶች በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡
ከዚኽ በመነሣት ከኢትዮጵያ ታሪክና ወቅታዊ ኹኔታ እንዲኹም ከሃይማኖትና መንግሥት መለያየት ጋራ በተገናኘ፣ በአንዳንድ ሰሞናዊ የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና መድረኮች በጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሰነዘሩ ጽርፈቶች እምብዛም ባያስደንቁም ብዙኃኑን የሥልጠና ተሳታፊዎች ማሳዘናቸው እና በመድረኮቹ ዓላማና ግብ ላይም የብዙኃኑን ኦርቶዶክሳዊ ጥርጣሬ ማስነሣታቸው አልቀረም፡፡
የጽርፈቶቹ መግፍኤ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በመጽሐፋቸው ስለ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ሥሪት በውል እንዳስቀመጡት÷ ስሙ እንጂ ጥቅሙ የሌላ በነበረውና ለሕዝቡም ግልጥ ባልተደረገው ‘ሲሶ መንግሥት አላት’ አነጋገር ቤተ ክርስቲያናችን የንግድ ምልክት ኾና ለዘመናት ስትገፋ የኖረችበት ሥሪት አገሪቱንም ቤተ ክርስቲያኒቱንም የጎዳበትን አሠራር በውል አለመረዳት ብቻ አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በርስተ ጉልት የአድባራት አስተዳደር ካህናቷ ቶፋ በሚል ስመ ጽዕለት የነገሥታቱና የመሳፍንቱ ድርጎኛ ኾነው የአገልግሎታቸውን ዋጋ ያላገኙበት መኾኑን ያለመገንዘብ ብቻም አይደለም፡፡ በስመ ሴኩላሪዝም በአይዲዮሎጂ ላይ የተመረኮዘ ቤተ ክርስቲያናችንን የማጥላላትና ከሕዝቡ ነጥሎ የማዳከም ዝንባሌና የተግባር ውጣኔ እንጂ!
ጊዜ ተገኘ ተብሎ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ከእርሷ በኋላ ለመጡ እምነቶች በሰላም አብሮ መኖር አንዳችም ሚና እንደሌላት ያኽል ‹‹መውጫ መግቢያ እንዳሳጣቻቸው››፤ አእላፍ ቅዱሳኗ በአራቱም የአገሪቱ ማእዝናት በሐዋርያዊ ትጋት አስተምረው ክርስትናን እንዳላስፋፉ ኹሉ ኦርቶዶክሳዊነት ‹‹በመንግሥት ሥልጣን ተደግፎ በሌሎች እምነቶች ላይ የተጫነ›› እንደኾነ፤ ከሐዋርያት ዘመን አንሥቶ የሚቆጠረው ታሪኳ ‹‹ረዥም ነው›› ማለታችንም ዕብለት እና የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌ እንደኾነ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተቻቸውን የሥልጣኔ ስጦታዎች ሳይጨምር ትውልዱ ጀግንነትን፤ አገር ወዳድነትን፤ ለታሪክ፣ ለባህልና ለሃይማኖት ተቆርቋሪነትን ይዞ እንዲያድግ ማስተማሯንና ማበረታታቷን ከትምክህት ርእዮትና በዚኹ ርእዮት ላይ ይመሠረታል ከሚባለው አሸባሪነት ጋራ በማጃመል ከአገዛዞቹ ስሕተት ጋራ ተደርባና ተዳብላ እንደምትታይ፤…አፍ እንዳመጣ መለፈፍ በርግጥም በስመ ሴኩላሪዝም በአይዲዮሎጂ ላይ የተመረኮዘ የማጥላላትና ከሕዝቡ ነጥሎ የማዳከም ዝንባሌና የተግባር ውጣኔ እንጂ ሌላ ሊኾን አይችልም! ጥቂት በማይባሉ ወገኖች አረዳድም ዝንባሌውና የተግባር ውጣኔው መንግሥታዊ ሥልጣንን ተጥቅሞ ፕሮቴስታንታዊነትን በማንገሥ የራስን እምነት የበላይነት የማስፈን አካሔድ እንደኾነ በስፋት ከታመነበት ውሎ ያደረ ጉዳይ ኾኗል!!
maeteb
ሚኒስትር ሺፈራው፣ ‹‹በሃይማኖት ሽፋን የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር›› በሚል በሃይማኖት ተቋማቱ ላይ በምዝገባ መመሪያ በተደገፈ ጥብቅ ቁጥጥር ርእዮተ ዓለማዊ የበላይነትን ማስፈን የሚኒስቴራቸው ቁልፍ ሥራ እንደሚኾን፣ በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የግንባሩ በካር ካድሬዎች ፊት እንደተናገሩ የቀድሞው ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በቅርቡ ባወጡት መጽሐፋቸው ያሰፈሩት ርግጥ ከኾነም መግፍኤው ከዚኽ ተለይቶ የሚታይ አይኾንም፡፡
ደጉ ነገር፣ የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ውሳኔው፣ በእነሚኒስትር ሺፈራው ሥልጠና ከትምክህት ርእዮትና ከአገዛዞች ስሕተት ጋራ ተዳብለን የተፈረጅንበት÷ የታሪካዊነታችንና የቀዳሚነታችን ጥሬ ሐቅ ኹሉም ሰው ሊጽፍበት የሚገባ እንደኾነ፤ ይኽን በመፃረር የሚነገረውና የሚጻፈው ኹሉ ደግሞ ‹‹እውነት ያልኾነና አስመሳይነት እንደኾነ›› በግልጽ ማስቀመጡ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ እውነት ያልኾነው፣ በማስመሰል የሚነገረውና የሚጻፈው ታርሞና ተስተካክሎ እውነተኛውና ትክክለኛው ለሕዝብ፣ ለትውልደ ትውልድ መተላለፍ እንደሚገባው ምልዓተ ጉባኤው ጽኑ አቋም መያዙ ነው፡፡ ይህም እንዲፈጸም የሊቃውንት ጉባኤ፣ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊነትና ታሪካዊነት በጽሑፍ አብራርቶ፣ አስፍቶና አጉልቶ እንዲያቀርብ ቀን ቆርጦ መመሪያ መስጠቱ ነው፡፡ የአፈጻጸሙን ነገር አደራ እንጂ!
የሴኩላሪዝም መርሖ ምርጫ
ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከ97 በመቶ ያላነሰው የአንዱ ወይም የሌላው እምነት ተከታይ በኾነባት አገራችን ከሃይማኖትና ሃይማኖተኝነት ጋራ የሚጫረቱ የሴኩላሪዝም ፈርጆች በጤናማ መርሖው ላይ የሰፊውን አማኝ ግንዛቤ በማዛባት ፍጥጫን እንዳያስከትሉ ጥንቃቄ እንደሚያሻው አስተያየት ሰጭዎቹ ያሳስባሉ፡፡
መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ እንደኾኑ የተደነገገበት ሕገ መንግሥታዊ አንቀጽ÷ አንዳቸው ከሌላቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ተጠብቀው በየራሳቸው የሚጠናከሩበትንና እንዳስፈላጊነቱም የሚተባበሩበትን (the government and religion should not unduly influence each other) እንጂ ሃይማኖትና ሃይማኖተኝነት ከግለሰቡና ከሕዝቡ ሕይወት ጨርሶ የሚጠፋበት የሴኩላር አክራሪነት (secularist fundamentalism) አልያም መርሖውን መሣርያ አድርጎ ጥንታዊውን ሃይማኖትና ተቋማቱን በማዳከም ‹‹ሌላ ገጽታ ያለው የተዛባ የሃይማኖቶች ግንኙነት መፍጠር›› የሚደገፍበት እንዳልኾነ ይታመናል፡፡
በዚኽ ረገድ ከአጠቃላይ ሕዝባቸው የኖሩ ሃይማኖት ተከል – የማንነት ዕሴቶች ጋራ ያልተገናዘበ፣ ግልጽነት የጎደለው ኢ-ፍትሐዊና የማሰነ (unjust and corrupt) የሴኩላሪዝም መርሖ ማራመዳቸው ከስማዊ ልማትና የይስሙላ የሰላም ኹኔታቸው ጋራ ተደማምሮ በእርስ በርስ ግጭትና እምነት ወለድ ሽብር ዋጋ እየከፈሉ ካሉት እንደ ናይጄሪያና ሕንድ ካሉ አገሮች ትምህርት መውሰድ ይገባል፡፡
በፈረንሳይ ነበር-ካቶሊካዊነት እና በቱርክ ነበር-እስላማዊነት ላይ የገነገነው ሴኩላሪዝም (assertive secularist policies) በድጋፍና ተቃውሞ ባስከተለው ፖሊቲካዊና ማኅበራዊ ባላንጣነት ሳቢያ አገሮቹ ከኖሩባቸው ዕሴቶች ጋራ ተራርቆ ሊራመድ ወደሚችለው መርሖ (passive secularism) የመሸጋገር ርምጃዎች እያሳዩ እንደኾነ የሳንዴያጎው ዩኒቨርስቲ ምሁር ይገልጻሉ፡፡ አዎ! በሴኩላሪዝሙ ሃይማኖትና መንግሥት ተነጣጥለዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ሃይማኖትም በመንግሥት አስተዳደር ጉዳይ እጁን አያስገባም፡፡ እዚኽ ላይ ግልጽና የሠመረ ምላሽ የሚሻው ጥያቄ ግን መለያየቱና መነጣጠሉ እንዴትና በምን ደረጃ (the levels of the exclusion) ይኹን ነው፤ ይላሉ ምሁሩ፡፡
ሴኩላር ነው የሚባለው የአገራችን ሕገ መንግሥት ከሃይማኖት ጋራ ለተገናኙ ጉዳዮች የያዛቸው መሠረታዊ መርሖዎች÷ የእምነት ነፃነት እና እኩልነት ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና እንዳገኘ እንዲኹም መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ መኾናቸውን የሚደነግጉ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሲባረኩዜጎች የእምነት ነፃነት ተጎናጽፈዋል ሲባል የሚያምኑበትን ነገር በግልና በቡድን የመግለጽ፣ የማስተማርና የመተግበር መብቶችን ያካትታል፤ የአምልኮአቸውን አስተምህሮና አተገባበር ተቋማዊ መዋቅር በመዘርጋት የማደራጀት፣ የማስተዳደርና የማስፋፋት መብታቸው የተረጋገጠ ነው፤ የሕዝብ ደኅንነትና ሰላም፣ ጤናንና ትምህርት፣ የሞራል ኹኔታ፣ የሌሎችን መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች የማይጋፉና የማይጎዱ እስከኾኑ ድረስ በኃይልና በሌላ መልኩ ሊገደብ አይችልም፡፡
ከዚኽ አኳያ ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ለማጠናከርና አስተምህሮዋን ለትውልድ ለማስተላለፍ የምእመኗን አቅም በማስተባበር ባቋቋመቻቸው የቴዎሎጂ ኮሌጆች ገብተው እንጀራዋን እየበሉ የሌላ እምነትና ባህል ለማስረግ ሲሞክሩ በማስረጃ በተረጋገጠባቸው ላይ ርምጃ እንዳትወስድ ጸጥታዊ ጫና ለመፍጠር፣ ከዚኽም አልፎ መምህራኑን ‹‹መናፍቅ አትበሉ፤ መናፍቃን እያላችኹ አታስተምሩ፤ አክራሪነትና ኋላቀርነት ነው›› ብሎ መመሪያ ለማውረድ የሚሞክሩ ግለሰብ ባለሥልጣናት በሕገ መንግሥታዊ መርሖው መሠረት በሕግ የሚያስጠይቅ የጣልቃ ገብነት ተግባር እየፈጸሙ መኾኑ ሊስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በኮሌጆቻችን ለሐዋርያዊ ተልእኳችን የምንፈልጋቸውን ምሁራን በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሯችን ብቻ የማሠልጠንና የአፈጻጸሙን አግባብነት የመቆጣጠር መብቱ የእኛው ነውና፡፡
ሃይማኖት በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱ እምነቶችን የበላይና የበታች በማድረግ የዴሞክራሲን መሠረት መናድና ደብዛውን ማጥፋት እንደኾነ ከተገለጸ፣ በተመሳሳይ አኳኋን በአንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተማሪው – ምእመን በግሉ በሚፈጽመው ሥርዐተ እምነት ውስጥ ጥቂት ሓላፊዎች በራሳቸው አካሔድ ጣልቃ ሲገቡ የሚወስኑበት ኹኔታ፣ ከተማሪው – ምእመን ሃይማኖታዊ መርሕ ጋራ የሚጋጭና የአንዱ ሃይማኖታዊ ትምህርትና ሥርዐት በሌላው ጫናው ውስጥ እንዲወድቅ የሚፈቅድ በመኾኑ የእምነት ነፃነታችን የሚሸራረፍበት አሠራር አስቸኳይ እርማት ሊደረግበት ይገባል፡፡
በተከታታይ ዘገባዎች እንደታየው፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ አራቱም ካምፓሶች ባለፉት ሦስት ዓመታት በአጽዋማት ወቅት የምግብ ቤት አገልግሎቱ በሙስሊም እና በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች መካከል የመስተንግዶ ልዩነት የሚታይበት መንሥኤ ምንድን ነው? ቤተ ክርስቲያናችን፣ ምእመናን ኹሉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማትን እንዲጾሙ ባዘዘችበት ኹኔታ ‹‹ኹለት አጽዋማትን ብቻ ነው የምናጾማችኹ፤ ሌላውን የማጾም ግዴታ የለብንም፤ የሐዋርያት ጾም የሚባል የምናውቀው የለም፤›› የሚለው የተማሪዎች ዲኑ ውሳኔ በየትኛው አሠራር የተደገፈ ይኾን? ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የተመደበላቸውን በጀት በነፍስ ወከፍ ተጠቅመው ሥርዐተ አጽዋምን በየራሳቸው ማለትም በግላቸው ቢፈጽሙ በመንግሥት ጽሑፎች ከተገለጹልን የሴኩላሪዝም መርሖዎች የትኛውን ይጥሱ ይኾን?
የመንግሥትና የሕዝብ የትምህርት ተቋማት ከሃይማኖታዊ ትምህርትና ሥርዐት ተጽዕኖ ነፃ መኾናቸውን ለማረጋገጥ፣ አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን የማስፋፋት ዕድል ለመገደብ በሚል የተቀመጠው ክልከላ በጥቅሉ የሚለው፣ ‹‹በትምህርት ተቋማት ውስጥ በቡድን መጸለይ፣ በቡድን መስበክ፣ በቡድን መዘመር፣ በቡድን መስገድ፣ በሃይማኖት አለባበስ ሽፋን ማንነትን ለመለየት የማያስችል አለባበስ የተከለከለ ነው፤›› ኾኖ ሳለ የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ዲን ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን ለይተው ከትምህርት ገበታቸው እስከማሳገድ ድረስ የሚበድሉበት ‹የሴኔት ሕግና ፕሪንስፕል› ምን ይኾን? የጅማ ዩኒቨርስቲው አድልዎ ዐደባባይ መውጣቱን ተከትሎ በሌሎቹ ተቋማትም በኦርቶዶክሳውያንና በሥርዐተ እምነታቸው ላይ ያነጣጠሩ የሃይማኖታዊ መልካም አስተዳደር በደሎች እየተፈጸሙ ስለመኾኑ የሚያመላክቱ መረጃዎችና ሪፖርቶች እየወጡ ነው፡፡
የሴኩላሪዝማችን መርሖ÷ ‹‹የአስተሳሰብ ግልጽነትና የአፈጻጸም ወጥነት የጎደለው (vacuous secularism) ነው፤›› በሚል የሚተቸውና በሰበቡም አንዳንድ ባለሥልጣናት በጥንታዊት፣ ብሔራዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ርእዮታዊና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን ለማስፋፋት፣ በፖሊሲዎችና በመዋቅራዊ አሠራሮች ተቋሞቿንና የተከታዮቿን ሃይማኖተኝነት ለማዳከምና ከተከታዮቿ ለመነጠል በመሣርያነት ይጠቀሙበታል፤ የምንለው እንዲኽ ባሉትና በመሰሏቸው ማሳያዎች አስረጅነት እንደኾነ ቢታወቅ መልካም ነው፡፡
ማዕተባችንን እናጠብቃለን፤ ግዴታችንም እንወጣለን
ማዕተብ ከክርስቲያንነት መለዮነቱ (በአእምሮ ወንድማገኘኹ “The Ethiopian Orthodox Church” መጽሐፍ አገላለጽ ‘’badge of Christianity’’) አልፎ ማንነት እና ባህል እንደኾነ የሚኒስትር ሺፈራውን ‹‹ማተቡም ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ መውለቁ አይቀርም›› ማሳሰቢያን ተቃውመው አስተያየት የሰጡ የሥልጠናው ተሳታፊ ገልጸዋል፡፡
ማዕተብ ባህል ኾነ ሲባል በአባባል፣ በአነጋገር፣ በልማድ፣ በሕግ፣ በሥርዐት የእምነትና ክሕደት፣ የፍርድና ውሳኔ መግለጫነቱን ያሳያል፡፡ ማተበ ቢስ ማለት ማተቡን የማያስር ብቻ ሳይኾን ማተብ እያለው ሕገ ወጥ ሥራ የሚሠራ ሰው ማለት ነው፡፡ ማተብ የለሽ በአንገቱ ክር የሌለ፣ በሓላፊነቱ ያልታመነ ሰው ነው፡፡ ማተቡ ተያዘ ማለት የማይገባ ሥራ ስለሠራ ከክርስቲያን ተለየ ማለት ነው፡፡ ማተቡን በጠሰ ማለትም ክርስትናው ካደ ማለት ነው፡፡
በዚኽ ደረጃ ከእምነታችንና ማንነታችን ጋራ የተዋሐደ ይትበሃላችንን በመፃጉዕ አስተሳሰብና ተግባር ለማክሰም ከመጣጣር ይልቅ ሴኩላሪዝማችንን ቢያውደውኮ መርሖውን የፖሊቲካዊና ማኅበራዊ ባላንጣነት መንሥኤ ሳይኾን ሙሉዓ ዕሴት (value-laden) የኾነ የሰላምና የብሩህ ተስፋ ምንጭ ያደርገዋል፤ ሃይማኖት እና አዎንታዊው ሴኩላሪዝም ለሚጋሯቸው የነገረ ሰብእ እና ሞራላዊ ዕሴቶች ማበብም (development of humanistic and moral values) የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ልማታዊነት የምንለው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገትስ ቢኾን በሃይማኖተኝነትና ሞራላዊ ሥሡነት ካልታረቀ መጨረሻው ምን እንደሚኾን ከኹላችን የተሰወረ ነውን?
የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች ‹‹ሞተር ኃይል እና ቁልፍ ሚና ይዘው የሚንቀሳቀሱ›› እንደኾኑ በሥልጠናው መዝጊያ ላይ ከመገለጹ አንፃር፣ በዚኽ ደረጃ በሚገኘው አካል ዘንድ ‹‹ማተቡም ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ መውለቁ አይቀርም›› ዐይነት እምነትንና ማንነትን በቀጥታ የሚፃረር ድፍረት፣ ከአነጋገር ማዳጥ የተፈጠረ ‹‹የግለሰብ የአፈጻጸም ጉድለት›› ተብሎ ይታለፋል ወይስ በሴኩላሪዝሙ መርሖና በፖሊሲው የታዘለ ‹‹ሥርዐታዊ ጥሰት›› ተደርጎ ይወሰዳል!?
ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ’ የሚል ሴኩላሪዝምን በአዎንታዊነትና በቀላሉ የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያለው እንደኾነ የሥልጠናው ተካፋዮች ይገልጻሉ፡፡ የአገራችን የሴኩላሪዝም መርሖም ምእመኑን ለእምነቱ ለዘብተኛ በማድረግ በሒደት ወደ ሃይማኖት አልባነት የመምራት ተንኰል የተሸሸገበት ከሚያሰኝ አቀራረብ ሊጠበቅ እንደሚገባው ይመክራሉ፡፡
ክርስቲያንነታችንን በየራሳችን የምንመሰክርበት መለዮአችን ማዕተብ ለመንግሥት ሴኩላርነት ተፃራሪ እንደኾነና ሊከለከል እንደሚችል መናገር፣ የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ በማማሰንና የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን አማኝ ፀረ – ሴኩላር የሚያደርግ፣ ሕዝቡንና መንግሥትንም ፊት ለፊት የሚያፋጥጥ እንዳይኾንም የሚኒስትር ሺፈራው አነጋገርና ጠቅላላ አካሔድ እርምትና ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ ያስጠነቅቃሉ፡፡

Saturday, October 4, 2014

ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?

Oktober4,2014
አገርና መሪ ላላቸው ኤምባሲ አገር ነው
eagle flag ethiopian

ሰሞኑን ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ”ባንዲራ ቀን” በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ”ባንዲራ ክብር” ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤ የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል።
ባድመ ስትወረር “ደርግ ኢሰፓ” ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ “እናት አገር ጥሪ” ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል ኪዳን ይኸው “አታስፈልግም ጨርቅ ነህ” የተባለው መለያ ነበር። ሲፈልጉ የሚጥሉት፣ ሲጨንቃቸው የሚያነሱት መከረኛ ባንዲራ ዳግም አጀንዳ ሆኖ ሰሞኑንን ቀርቦልናል።
wedi1በአሜሪካ በሚገኘውና ኢህአዴግ “ኤምባሲ” በሚለው ቅጥር ግቢ ውስጥ ወዲ ወይኒ የሚባሉ ታጋይ የፈጸሙት ድርጊት ነው የባንዲራን ጉዳይ ዳግም አጀንዳ ያደረገው። የወዲ ወይኒ ገድለ ዜና አስገራሚ የሆነባቸው፣ ያሳዘናቸው፣ ያናደዳቸው፣ የተደፈርን ስሜት የፈጠረባቸው፣ ክስተቱን በመቃወም ኢህአዴግን በመወከል መግለጫ ያወጡ፣ እስከመቼ ኢህአዴግ “ሆደ ሰፊ ይሆናል” ብለው የጠየቁ፣ አሜሪካንን የወነጀሉ፣ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቁ፣ … በተለይም የሳይበር ሚዲያውን አጣበውት ከርመዋል። በሌላ በኩል ዜናውን እንደዜና ብቻ ወስደው ሚዲያ በዘነጋቸው ኢትዮጵያዊያን ላይ ለሚደርሰው ግፍ ያዘኑ ስፍር ቁጥር የላቸውም።
ዋሽንግተን በሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ውስጥ የመዋቅሩ “መሪ” ተብለው የተቀመጡትን ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንደመጡ የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ወዲ ወይኒ ጥይት ሲተኩሱ ተሰምቷል። ታይቷል። ተረጋግጧል! በኢትዮጵያ ስም የተሰቀለው የህወሃት/ኢህአዴግ ዓርማ ወርዷል! በዚሁ በፊልም ተደግፎ በቀረበው ዜናና የማህበራዊ ገጽ ዓምዶች ላይ ዋሽንግቶን ከተማ ከዋይት ሃውስ 4 ማይል ርቀት ላይ በሚገኘው የኢህአዴግ ግቢ ውስጥ ተሰቅሎ የነበረው “ጨርቅ” ወርዶ ተጥሏል። “የጨርቁ ፍቅር ያቃጠለው” የጽህፈት ቤቱ ሰራተኛ የተጣለውን “ጨርቅ” ሰብስቦ ወደ ቢሮ ሲያስገባም ከካሜራ እይታ አላመለጠም። እንግዲህ ይህንን እውነት ነው ለመካድና “ከዓይናችሁ ጆሯችሁን እምኑ” እየተባልን ያለነው።
በሌላ በኩል የህዝብ ቀልብ ለመሳብ “ባንዲራ ያዋረዱ” በሚል “ኢህአዴግ በፈቃዱ ያሰራውን ጨርቅ” አውርደው የጣሉትን ለመክሰስና ከሃዲ አድርጎ ለመሳል ተሞክሯል፤ ሙከራውም ቀጥሏል። ሁኔታውን የሚከታተሉ እንደሚሉት “ይህ የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው” በማለት የሚጠሩትን ጨርቅ “ይህ የእኔ ባንዲራ አይደለም” በማለት ቀዳደው የሚጥሉ ዜጎች በምን ሂሳብ ተቃውሞ ይሰነዘርባቸዋል የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው።
ህወሃት ትግራይን ነጻ ለማውጣት ትግል ጀምሮ፣ በወቅቱ ደርግ በነበረው የአመራር ጥበብ እጥረትና ሌሎች ተጽዕኖዎች ከአገዛዝ መንበር ተነስቶ ህወሃት/ኢህአዴግ አገር ገዢ ለመሆን ሲታደል የአገሪቱን ባንዲራ “ጨርቅ” ብሎ አዋርዶታል። የቀለብ መቋጠሪያው እራፊ አድርጎ ክብሩን ገፎታል። ባደባባይ አገርና ህዝብ እየተቃወመ በጠብ መንጃ ሃይል አስወግዶታል፤ አቃጥሎታል። ራሱ ባሰፋው ሌላ “ጨርቅ” ተክቶበታል። ይህ የሸፍጥ ታሪክና ተግባር የተረሳ ተደርጎ ዛሬ ህወሃት/ኢህአዴግ ደርሶ ለሠንደቅ ዓላማ ክብር ሰጪ ሆኖ ሙግት መግጠሙ ጥያቄውን የሚያነሱ ክፍሎች ተግባሩ “ያቅለሸልሻል” ባይ ናቸው።
“አገር የነሱ መፈንጫና ሃብት ማግበስበሻ የሆነችላቸው የድጋፍ ቀረርቶ ለማሰማት ቅድሚያ ቢይዙ፣ አገር የላችሁም፣ ባንዲራ አልባ ናችሁ፣ የተባልን የነሱ የሆነውን ጨርቅ አንፈልግም ብንል ምን ይገርማል?” የሚሉት ክፍሎች፣ “በሎንደን የኤርትራ ኤምባሲን ዘልቀው ለሰዓታት የተቆጣጠሩት አምባገነን በሚባሉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ዲፕሎማቶች” ጥይት አልተተኮሰባቸውም። ኢሳያስን አምባገነን በማለት የኤርትራን ህዝብ “ነጻ” አወጣለሁ የሚለው ህወሃት ግን በወዲ ወይኒ አማካይነት ህግ ባለበት አገር የህወሃትን ማንነት ባደባባይ አሳይቷል። “እዛው ህወሃት በሚነዳት አገር ውስጥ ቢሆን ኖሮ ስንቱን ይረሽን ነበር” ሲሉም የሚጠይቁ አሉ። እነዚህ ክፍሎች “አገር ቤት የተረሸኑትንና ታስረው የሚሰቃዩትን ቤት ይቁጠራቸው” ሲሉ ተደፈርን በሚል ስሜታቸውን የሚያንጸባርቁትን ወገኖች “ወዮልኝ ቀን ያጋደለ እለት” በሚል ምጸት ጥርሳቸውን ይነክሱባቸዋል።
ወዲ ወይኒ በጠራራ ጸሃይ፣ በካሜራ ታጅበው፣ እንደ ፊልም አክተር ሽጉጥ ወጥረው ሲያስፈራሩ፣ “ተኩስ፣ ግደለኝ፣ ተኩሰው” እያሉ ሲጠጉዋቸው የነበሩት ወገኖች ግርማ ብሩን እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። “የብሄር ብሄረሰብ መብት በገፍ ተሸክሜ ልገዛ መጣሁ” የሚለው ኢህአዴግ የወከላቸው አቶ ግርማ ሰዎቹን ወጥተው ለምን አያነጋግሩም? ችግራችሁ ምንድነው? ምን እንርዳችሁ? የማይሉበት ምክንያትስ ምንድነው? ይህ የእኛም አቋም meles sibhat embassyነው። ላደላቸው ኤምባሲ አገራቸው ነው። አምባሳደር መሪና ተከራካሪ ጠበቃቸው ነው። ለታደሉ ኤምባሲ በሄዱበት የባዕድ ምድር የሚሰበሰቡበት ቤታቸው ነው፤ ትንሽዋ አገራቸው ነው። መሪውም የቤቱ አስተዳዳሪ ነው። አገር በቤት፣ ህዝቦቿም በቤተሰብ ከተሰየሙ፣ የቤተሰቡ መሪና ረዳቶቹ ልጅና እንግዴ ልጅ ለይተው ላንዱ ወርቅ፣ ለሌላው ጥይት አያቀርቡም። በዚህ እሳቤ “የኢህአዴግ የመዋቅር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት” ብለን በጠራነው ቅጥር ውስጥ ወዲ ወይኒ የፈጸሙት ተግባር ከህወሃት ማንነት የተቀዳ ስለመሆኑ አንጠራጠርም።
በሰለጠነ አለም ውስጥ እንዳሻቸው እየበሉና እየጠጡ የሚኖሩ ሰዎች “ግደለኝ፣ ተኩስብኝ፣ ግደለኝ” በማለት ሞትን ለመጋፈጥ ሲወስኑ ምልክቱ “ብሶት ከልክ ማለፉን የሚያሳይ ነው” የሚሉ ክፍሎች “ይህ ድርጊት ነገ መልኩን ቀይሮ አገር ቤትም ሆነ ሌላ ቦታ ዋሽንግቶንን ጨምሮ ላለመከናወኑ ማረጋገጫ የለም” ይላሉ። ተበልቶና ተጠጥቶ በሚታደርበት አገር ውስጥ ዜጎች ሞትን ከናቁት፣ የኑሮ ጠኔ የሚለበልባቸው የበይ ተመልካቾች ያመረሩ ቀን አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዳሉት “የከፋ ቀውስ” ይከተላል። ህግና ስርዓት ባለበት አገር ጥይት እያንባረቁ አካኪ ዘራፍ ማለት፣ በዚያው ስሜት ተመልሶ “ተደፈርን” ብሎ መጮህ የሚያመለክተው “ከልክ ያለፈ ጥጋብ ተራራ ማከሉን ነው” ሲሉ በድርጊቱ የተበሳጩ ይናገራሉ።
የአገር ቤቱ አልበቃ ብሎ ህግና ስርዓት ባለበት አገር “በጫካ ማንነት አምባገነን ለመሆን መሞከር በጥጋብ መወጠር ያመጣው የትዕቢት ድምር ነው” በማለት አምርረው የሚናገሩት ክፍሎች “በጥጋብ የተወጠሩና ጥጋባቸው ያሳወራቸው ጥቂቶች፣ ርሃብ እንቅልፍ በነሳቸው፣ ግፍ ባንገፈገፋቸው፣ አገር ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያ ተስፋ ባስቆረጣቸው ህዝብ መካከል እንደሚኖሩ መዘንጋታቸው” የወደፊቱን ሲያስቡ ሃዘን እንደሚገባቸው ይጠቁማሉ።
ይህንኑ ከልክ ያለፈ ጥጋብ መተንፈስ እንዳለበት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ ለህወሃት አመራሮች በቅርቡ በላኩት ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፤ “ከእናንተ ጋር ሚቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት ማሰራችሁን አቁሙ! ኃይልን ወይም ጉልበትን በመጠቀም እስከመጨረሻው በሥልጣን አትቆዩም! በዓለም ታሪክ ያልተከሰ ስለሆነ እናንተ ልትከውኑት አትችሉም። እናንተ አለን ከምትሉት ጉልበት በብዙ እጥፍ የሚበልጥ የነበራቸውም ተንኮታኩተዋል። ስለዚህ ከትዕቢታችሁ ተንፍሱ፤ ትህትና አሳዩ፤ ከፍ ብላችሁ የተሰቀላችሁበት ከመሰላችሁ “ፎቅ” ውረዱ! ለለውጥ ያላችሁን ግልጽነት አሳዩ! ለዓመታት ሳታቋርጡ ስታወሩ የነበራችሁትን ውሸት አቁሙ፤ እውነትን መናገር ተለማመዱ። የሃሰትን መንገድ ሳይሆን ትክክለኛውን በመከተል በዜጎች መካከል መተማመን እንዲፈጠር የሚያስችል ሥራ ማከናወን ጀምሩ!”
“ውርደት ቀለቡ” የሚባለው ህወሃትና ሟቹ መሪው ተጠልተዋል። ጥላቻው ልክ አልፏል። መለስ ስድብና ርግማን ጠግበው እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩ። ከህልፈታቸው በፊት ውግዘትና ርግማንን ጠግበው የነበሩት መለስ “ሲሰው” ስብሃት ነጋ ስታርባክስ ቡና ሊጠጡ ገብተው ሃፍረትን በሲኒማ ተከናነቡ፣ “የህወሃት ቁስ” ከሚባሉት አንዱ ሬድዋን ሁሴን የልብስ ሱቅ ውስጥ ልጆችና ቤተሰባቸው አጥንት ስር ዘልቆ የሚገባ የውግዘት መርዝ ተጋቱ፣ አሁን ደግሞ ዋሽንግቶን የተተከለው ቅጥር ግቢያቸው ትዕቢታቸውን አሟሟው። እንደ እነዚህ ክፍሎች ገለጻ በስምምነትም ሆነ በግዴታ ወዲ ወይኒ 24 ሰዓት ሳይሞላ እንዳሻቸው መግደልና ማሰር ወደሚችሉባት የህወሃት ኢትዮጵያ መላካቸው አድሮ የህግ ጥያቄ ያስነሳል። ለዚሁ ይመስላል ህወሃቶች ግድያ ሊፈጽም የነበረው ሰው ትግሬ በመሆኑና የተነካውም ክብር የትግሬ ህወሃቶች በመሆኑ የስምምነት መግለጫ እንዲወጣ ይፈልጋሉ። አሜሪካ ይህንኑ እንድትፈጽም ጥረት ስለመኖሩ አቶ ግርማ ብሩ ፍንጭ መስጠታቸውን ያመለክታሉ።
ለኢህአዴግ ልሳን ቃላቸውን የሰጡት አቶ ግርማ፣ ከስቴት ዲፓርትመንትና ከሌሎች አካላት ጋር በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ተነጋግረናል” ሲሉ መናገራቸውን የሚጠቁሙ እንደሚሉት” ወዲ ወይኒ ወደ ህወሃት የግዛት አገር እንዲሄዱ የተደረገው ለፖሊስ የምርመራ ቃል ከሰጡ በኋላ በሁለትዮሽ ንግግር ነው። “ንግግሩ ምንም ይሁን ምን አሜሪካ ወንጀለኛውን የምትፈልግ ቢሆን “ኤምባሲ” ከሚባለው ቅጥር ግቢ ሲወጡ ፖሊስ ሊያስራቸው ይችል ነበር።
የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ጉዳዩ እንደተፈጸመ “ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዘ ጉዳይ በጥንቃቄ ይታያል” ማለታቸው አይዘነጋም።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

በወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሚወሰደው እርምጃ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

Oktober3,2014
በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ ከተማ አንድ የአገዛዙ ባለሥልጣን የተገደለ ሲሆን አንዱ ደግሞ ክፉኛ ቆስሏል።

የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መዋቅር አካል በመሆን ሕዝብን ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሲያስሩ፣ ሲደበድቡና ሲገድሉ የኖሩትን ሹማምንቶች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ለማስቆም በተጀመረው እንቅስቃሴ፣ በምክር አልመለስ ያሉት ላይ እርምጃ የመውሰድ ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። የዚህ ዘመቻ ዋና አስፈፃሚ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውስጥ አርበኞች /ህቡዕ አባላት/ ሰሞኑን በወያኔ ቅጥረኞች ላይ ያነጣጠረ ተከታታይ ጥቃቶችን በመሰንዘር አስተማሪ እርምጃዎች መወሰዳቸው ይታወሳል።

ይህ በውስጥ አርበኞች የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ በመቀጠል ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ/ም በመተማ ወረዳ ገንዳ-ውሃ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በተወሰደው እርምጃ ሁለት የወያኔ አገዛዝ ባለሥልጣናት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሲሆን፤ በጥቃቱም የወረዳው ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛው ሲገደል፣ ኮንስታብል ሻንበል አበበ በጥይት ተመቶ ክፉኛ ቆስሏል።

በዚህ የማጥቃት እርምጃ መደሰታቸውን የገለጹት የገንዳ-ውሃ ከተማ ነዋሪዎች እነዚህ እርምጃ የተወሰደባቸው ባለሥልጣናት፣ ሥልጣናቸውን ተገን በማድረግ ሕዝቡ ላይ ሲያደርሱ የነበረውን በደልና ግፍ በምሬት የገለጹ ሲሆን ሕዝብን በሚበድሉ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉና በማንኛውም መልኩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።
ሀገርንና ወገንን እያጠፋ ካለ አምባገነን አገዛዝ ጋር ማበር ውጤቱ ሰሞኑን እየተወሰደ ያለው እርምጃ መሆኑን በመረዳት የወያኔ ሆድ አደር ባለሥልጣናት ከእኩይ ተግባራቸው ካልተቆጠቡ የተጀመረው የማጥቃት ዘመቻ ሰለባ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በጥብቅ ያሳስባል።
http://www.arbegnochginbar.org/index.php?option=com_content&view=article&id=806%3A2014-10-03-22-12-14&catid=41%3Anews&Itemid=50

Friday, October 3, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች 28 ቀን ተቀጠረባቸው

Qktober3,2014
በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተያዙ ሌሎች 10 ያህል ዜጎችም ቀርበዋል
በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ዛሬ መስከረም 23/2007 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 አራዳ ችሎት ቀርበው 28 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ እንዲሁም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጅነር ጌታሁን አርባምንጭ ውስጥ ወር ከ15 ቀን ያህል ታስረው የነበር ሲሆን ወደ ማዕከላዊ ከተዛወሩ 24 ቀናት በላይ እንደሆናቸው ታውቋል፡፡ አመራሮቹ ጥቅምት 21 ከሰዓት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ታሳዎቹ በቤተሰብ፣ በኃይማኖት አባትና በጠበቃ እንዳይጎበኙ የተከለከሉ ሲሆን ለመጎብኘት ፈቃድ አግኝተው የነበሩትም እንደገና እንደተገለከሉ ተገልጾአል፡፡ ለአብነትም የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ አባት ከሳምንት በፊት ልጃቸውን እንዲጠይቁ ተፈቅዶላቸው ቢጠይቁም ከሳምንት በኋላ ዳግመኛ ለመጠየቅ በሄዱበት ወቅት ‹‹ከሳምንት በፊት ጠይቀሃል፡፡ ይበቃሃል!›› ተብለው መመለሳቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ተገልጾአል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በዛሬው ችሎት ቤተሰብ፣ የኃይማኖት አባት፣ ጠበቃና ሌሎችም ዜጎች እንዳይገቡ የተከለከሉ ሲሆን የህግ ጉዳይ ኃላፊው ድርጊቱ በታሳሪዎቹ ላይ እየጠፈጸመ ያለውን ህገ ወጥነት ያሳያል ብለዋል፡፡ ኃላፊው ጨምረውም ‹‹ችሎት በዝግ የሚታየው ታሳሪዎቹ ላይ ችግር ይደርሳል ተብሎ ሲታሰብ ነው፡፡ በአሁኑ ሁኔታ በችሎት ሊገባ የሚችለው ህዝብ በታሳሪዎቹ ላይ ችግር እንዳይደርስባቸው መንግስትን የሚጠይቅ እንጅ ችግር ሊያደርስ የሚችል አይደለም፡፡ ያም ሆኖ ግን ታሳሪዎቹ ይህ ነው ተብሎ ባልተነገረ ምክንያት ጉዳያቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ይህ ህገ ወጥነት ነው፡፡›› ሲሉ ሁኔታውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል አዲስ አበባ ውስጥ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተያዙና ለ4ኛ ጊዜ 28 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው
ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ችሎት የቀረቡ 10 ያህል ግለሰቦች መኖራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች
ገልጸዋል፡፡ ይሁንና የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች አለብን ባሉት ስጋት ስለ ታሳዎቹ አያያዝና ሌሎች ጉዳዮች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነገረ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ማቅረብ አልቻለችም፡፡
ባለፈው ሳምንት ወደማዕከላዊ እየታፈኑ የሚወሰዱት ዜጎች ቁጥር መበራከቱንና 12 ያህል ዜጎች ከኦሮሚያ ታፍነው በማዕከላዊ እንደሚገኙ ከእነ ስም ዝርዝራቸው ማቅረባችን ይታወሳል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ “በሸኸዲ ከተማ በፈጸምኩት ጥቃት ፖሊስ አዛዥ እና ወንጀል መከላከል ሃላፊውን ገደልኩ” አለ

Oktober 3,2014
(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ በገንዳ ውሃ /ሸኸዲ/ ከተማ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም ድል መጎናጸፉን ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና አስታወቀ። እንደ ንቅናቄው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሆነ ዛሬ መስከረም 22 /2007 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ የአ.ዴ.ኃ.ን ልዩ ኃይሎች በወሰዱት የተጠና ጥቃት የሸኸዲን ወረዳ ህዝብ ሲያሰቃዩና ሲጨቁኑ የኖሩትን፣ 1ኛ. የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የነበረውን መ/አ ዮሃንስ ገብሬ 2ኛ፣ የወረዳው ፖሊስ ወንጄል መከላከል ሃላፊ የነበረውን አስር አለቃ ሻንበል ተሰማ፣ ላይ በተወሰደው እርምጃ ሁለቱም ተገድለዋል።
ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ መሠረት ከሁለቱ ባለስልጣናት መካከል በቦታው አብሮ የነበረው የሸኸዲ ወረዳ የወያኔ የደህንነት አመራር ሞላልኝ አገኘው አቁስያለው ብሏል። “ኃይሎቻችን ጥቃቱን ፈፅመው ወደ ቦታቸው የተመለሱ ሲሆን ከመካከላቸው አንድ ደጉ ጉቸ የተባለ ጓዳችን ቆስሎ በጠላት ቁጥጥር ስር ውሏል።” ያለው ንቅናቄው ይህንን የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚሁ አጋጣሚ እየገለፀ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎኑ እንዲቆም ጥሪው ያቀርባል።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ፈጽሜዋለሁ ላለው ጥቃትና ገደልኳቸው ስላላቸው ባለስልጣናት ከገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ ምንም መረጃ የለም። ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ከሶስተኛ ወገን እንዲሁም ከራሱ ከኢሕአዴግ መከላከያ ሰራዊት አካባቢ ለማጣራት ያደረገችው ጥረትም አልተሳካም።
(ፎቶ ከፋይል - የአማራ ዲሞክራቲክ ኃይል ጦር ኃይሎች መካከል የተወሰኑት)
                                           (ፎቶ ከፋይል – የአማራ ዲሞክራቲክ ኃይል ጦር ኃይሎች መካከል የተወሰኑት)

የወታደራዊ እና አምባገነን ስርአት መገለጫዎች (በግርማ ሰይፉ)

Oktober 3,2014

የወታደራዊ እና/ወይም አንባገነናዊ መንግሰታት መገላጫ በመኖሪያ አካባባያቸው ይገለፅ እንደሆን በሚል፡፡ ከዚህ ቀጥዬ የማነሳቸውን የወታደር መኖሪያዎች እና የቤተ መንግሰት ሁኔታን ይመለከታል፡፡ ዘወትር እነዚህን ግቢዎች ባየኋቸው ቁጥር የሚመጣብኝ አሳብም ስለሆነ ነው፡፡ ለነገሩ የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ አዲስ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚክስ ትምህርት መጀመሪያ የሆነው አንድ በላተኛ፣ አንድ አቅራቢ፣ አንድ ገበያ የሆነው ከአንድ ሰው ጀምሮ፣ ወደ ቤተሰብ እና ሀገር የሚያድገው ሞዴል ተፅህኖሞ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮችን ከቀላል በመነሳት ወደ ውስብሰብ ደረጃ ለማጥናት ይረዳል የሚል እምነትም አለኝ፡፡
በወታደራዊ አገዛዝ ውስጥ የሆኑ ሀገሮች መጨረሻቸው እንዴት እንደሚሆኑ መረዳት የሚፈልግ ሰው በቦሌ መንገድ ከቦሌ ወሎ ሰፈር አደባባይ ከመድረሳችን በፊት በሚገኘው የመጨረሻ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የፌዴራል ፖሊስ የ ”ቪ.አይ.ፒ ጥበቃ” ማረፊያ መመልከት ነው፡፡ ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የከፍተኛ ባለስልጣን መኖሪያ እንደነበር የሚነገር ሲሆን፣ ዘመናዊ ቪላ እንደነበር ግን ብዙዎቻችን ምስክር ነን፡፡ ይህ ቪላ በአሁኑ ወቅት በአይናቸን እያየነው ፈራርሶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሶዋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ የብሎኬት አጥር እና በፍፁም ለአካባቢው የማይመጥን የቆርቆሮ ግንባታ ተደርጎበታል፡፡ ህገወጥ ግንባታ የሚባለው እነሱን አይመለከትም፡፡ በአጠቃላይ ይህ ጊቢ ከነበረበት ደረጃ አሁን ወዳለበት ደረጃ የወረደው በእኔ እምነት የወታደር መኖሪያ በመደረጉ ነው፡፡ አንዲት ሀገርም በወታደራዊ አስተዳደር ውስጥ ስትወድቅ እንደዚህ እንደምትወርድ ማሳያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ አሁን በግቢው ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ይህ ቤት ቀደም ሲል ምን ይመስል እንደነበር ስለማያውቁ ይህ የምሰጠው አስተያየት ሊገርማቸው ይችላል፡፡ እጅግ የሚያሳፍር ነው፡፡ ኪራይ ቤቶች ይህን ቤት በቅጡ መዝግቦ መያዙንም እጠራጠራለሁ፡፡ በእኔ እምነት ይህ ቤት አሁን ባለው የከተማ የሊዝ ዋጋ ቢሸጥ ለአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ደረጃውን የጠበቀ ፅ/ቤት ሊሰራ የሚችል ገንዘብ ሊያስገኝ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ በከተማው ውስጥ ከግለሰቦች ተወርሰው ለፖሊስ ማረፊያ የተደረጉ ቤቶችን መመልከት ተመሳሳይ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ለምንድነው ግን ከመሻሻል ይልቅ ወደኋላ መሄድ የሚቀናን? የእነዚህ ቤቶች አያያዝ ወታደራዊ መንግሰት ሀገርን እንዴት አድርጎ እንደሚያቆረቁዝ ማሳያ ይመስለኛል፡፡
ከላይ ወታደራዊ መንግሰት መገለጫ ያልኩትን ሞዴል ለማሳየት የሞከርኩ ሲሆን፡፡ የአንባገነን መንግሰታት ደግሞ መገለጫ ሊሆን ይቸላል ብዬ ያልኩትን ላካፍላችሁ፡፡ በአጋጣሚ ሆኖ በቀን አንድ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትራችን ፅ/ቤት በጀርባ መግቢያ በር ማለፌ አይቀርም፡፡ በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ ደግሞ በመኪና ብቻ ሳይሆን በእግር ጉዞ ምክንያትም በሳምንት አንድ ሁለቴ አልፋለሁ፡፡ እነዚህን ጊቢዎች ስትመለከቱ መታዘብ የምትችሉት በጊቢያቸው ያደገውን ሙጃ ሳር ብቻ ሳይሆን የንፅህና ጉድለቱን ጭምር ነው፡፡ እነዚህ መሪዎቻችን የሚኖሩበት ጊቢ በዚህ ደረጃ የቆሸሸ እንዲሆን ሲፈቅዱ የሚመሩትን ሀገር እንዴት አድርገው ገነት ሊያደርጉት እንደሚችሉ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከእነዚህ ጊቢዎች የሚወጣው ፍሳሽ መንገድ አቋርጦ የሚሄድ ሲሆን አስፋልቶቹን እና የእግረኛ መንገዶቹን አበላሽቶ ስንመለከት ማዘናችን የማይቀር ነው፡፡ እርገጠኛ ነኝ መሪዎቹ የሚሄዱባቸው አካባቢዎች ምንጣፍ እንደሚሆኑ እና ሀገሩ ሁሉ እንደዚሁ እንዲመስላቸው እንደሚፈለግ፡፡ በእነዚህ ጊቢዎች አጥር ተጠግቶ መሄድ ግን አይቻልም፡፡ እሳት የሚተፋ ጠብመንጃ ያነገቱ ሰዎች ውክቢያ ይከተሎታል፡፡ ይህች ሀገር እነዚህን ጊቢዎች በንፅህና ለመያዝና ለተመልካች ማራኪ ለማድረግ አቅም የላትም ቅድሚያ የምንሰጠው ሌላ ነገር አለን ሊሉን አይችሉም፡፡ በእኔ እምነት የእነዚህ ትልቅ የሀገር ገፅታ ግንባታ የሚገለፅባቸው ጊቢዎች በሙጃ ተውጠውና ንፅህናቸው ተጓድሎ ከጊቢው አልፎ ሌሎችን ያበላሹበት ምክንያት በውስጡ ያሉት መሪዎች መገለጫ ነው፡፡
ለንፅፅር እንዲሆን ሁልጊዜ በቴሌቪሽን የምንመለከተውን የባራክ ኦባማን ቤተመንግሰት ልብ ይሏል፡፡ ማንም መጠራጠር የሌለበት በተግባርም እንዲሁ ግልፅ እና ንፁህ ማራኪ ነው፡፡ ውጭ ከሚገኘው ክፍት አጥር እስከ ቤቱ ድረስ ያለአንድ ግርዶሽ ፅድት ብሎ ይታያል፡፡ በቅርቡ ሰላም የሚነሱ ጠብመንጃ የታጠቁ ሰዎች አይታዩም፡፡ ይህ ማለት ጥበቃ አይካሄድም አይደለም፡፡ ለዚህም ፅሁፍ መነሻም የሆነኝ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጊቢ በአንድ ሰው መደፈሩን (አጥር ዘሎ መግባት) አስመልክቶ የግቢው የፀጥታ ሃላፊ ከስልጣን መልቀቅ ነው፡፡ ለምን እንደ ኢትዮጵያ ቤተመንግሰት ጠባቂዎች አላስፈራራችሁም በሚል አይደለም፡፡ ወደፊትም ጊቢውን ማጠር እንደመፍተሄ አይወሰድም፡፡ እንደወትሮ ለህዝብ ዕይታ ክፍት ይሆናል ጥበቃው ግን በስርዓት ይጠናከራል፡፡ የህዝብ መብት በማይነካ መልኩ፡፡ በእኛ ሀገር አንድ ሰው አምልጦ ቢገባ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው፡፡ ግንባሩን በጥይት ይባላል፡፡ በዚህም ምክንያት የቤተ መንግሰት የጥበቃ ኃለፊ የሚወስደው አንድም ኃላፊነት  አይኖርም፡፡ ከኃላፊነት ይለቃልም ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ይህ ነገር  በእኛ ሀገር ስልጣን እንጂ ተጠያቂነት የሚባል ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው፡፡ ተረኛ ጠበቂው ግን ዘሩ ተጣርቶ ከአንዱ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ መከራውን ይበላል፡፡ ኦሮሞ ከሆነ ኦነግ፣ አማራ ከሆነ ግንቦት 7፣ ወዘተ. ….
ልጅ ሆኜ በቢቢሲ የሰማሁት ነገር ታወሰኝ፡፡ ጋዜጠኛው ዲሞክራሲ የሌለባቸው መንግሰታት ሰር ያሉ ሀገራትን በምን እነለያለን? የሚል ጥያቄ  ያቀረበለት አንድ የፖለቲካ ተንተኛ እነዚህ ሀገራት በአብዛኛው “ዲሞክራቲክ” የሚል ቅጥል አላቸው ሲል ሰምቻለሁ፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ …….፡፡ ለምሳሌ የእኛን ጉድ ብንመለከት “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ” እንደሚለው ማለት ነው፡፡ በተግባር ዲሞክራሲም ፌዴራሊዝምም እንዳልሆነው ማለት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ዛሬ የምለው ሀገራት ዲሞክራት መሆናችው እና አለመሆናቸው የሚለየው በቤተመንግሰት ጊቢ አያያዝና ጥበቃ ሰርዓታቸው ነው ቢባልም ሊያስኬድ ይችላል ነው፡፡ ይህን ሞዴል ወደሌላ አፍሪካ ሀገር ሰፋ አድርጎ የሚያየው ቢገኝ በንፅህና የሚጠበቅ ቤተ መንግሰት እና ለህዝብ ግልፅ የሆነ ቤተ መንግሰት ያላቸው ሀገሮች የተሸለ ዲሞክራቲክ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ፡፡  አስተሳሰብ በአካባቢ ከሚኖር ሁኔታ ሊመነጭ ይችላል፡፡ አካባቢውንም እንዲህ እንዲሆን የሚፈቅዱት ውስጡ የሚገቡት ሰዎች ናቸው፡፡ ለነገሩ ቤተ መንግሰትን ለማስተዳደር ኃለፊነት የሚሰጣቸው ሰዎች የሚመረጡበት መስፈርት እኮ …….
ሁለት ሺ ሰባት የቤተመንግሰት ጊቢውንም ሆነ ከዚያ ውጭ ያለውን አስተዳደር የምንሻሽልበት እንዲሆን እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!!

Thursday, October 2, 2014

በጋምቤላ ክልል የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋቱ የተረፉ አማሮች ወደ መኢአድ ቢሮ መጡ!

Oktober2,2014
በፋሽሽቱ ወያኔ ከጋምቤላ ክልል በግፍ የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋት ወንጀል የተረፉት አማሮች ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መጥተዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ ጎሽኔ ቀበሌ አቶ በለጠ ጌታቸው ጎጃም ቢቸና አካባቢ የመጡ የግራ እጃቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 

በዚሁ ቀበሌ ከወሎ መካነሰላም ቦረና አካባቢ የመጡ አቶ ገበየሁ ኮስትር በጀርባቸው በኩል በከፍተኛ ሁኔታ በጥይት ከተመቱ በኋላ ጥይቱ በሰውነታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ በአካባቢው በተደረገላቸው ህክምና ጥይቱን ማውጣት ስላልተቻለ በከፋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸው ይሙቱ ይዳኑ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው በጭንቀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ጀምበሬ ኮስትር፣ወ/ሮ ሳዓዳ ተፈራ፣ ወ/ሮ ኮከቤ ኮስትር ከእነ ህፃን ልጆቻቸው በባሰ ችግር ውስጥ ሆነው ወደ መኢአድ ጽ/ቤት በመምጣት በሰቀቀን ችግራቸውን ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃዮችና ከዘር ማጥፋት የተረፉት፤ እኛስ ከእነ ችግሩም ቢሆን የተወሰነ ድጋፍ አግኝተናል፡፡ ከዚያው የቀሩት ወንድሞቻችን ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል ካሉ በኋላ ለእኛም ሆነ ለወንድሞቻችን የኢትዮጵያ ህዝብ በአሰቸኳይ እንዲደርስልን ሲሉ ተማጽነዋል፡፡
ተስፋሁን አለምነህ
LikeLike ·  · 

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊሲ ትመርምር

Oktober 2,2014

መስከረም 15 ቀን 2007 ዓም፣ የዩ. ኤስ. አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦቦማና ባልደረቦቻቸው በአንድ በኩል ኃይለማርያም ደሣለኝና አለቆቹ በሌላ በኩል ሆነው የሁለትዮሽ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማ ያደረጉት ንግግር የዲፕሎማሲ ጨዋነት ከሚጠይቀው ርቀት በላይ ተጉዘው ሸሪኮቻቸው ባልሠሯቸው ጀብዶች ማሞገሳቸው አሳዝኖናል። ፕሬዚዳንት ኦባማ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ያደረጉት ንግግር ላይ በርካታ ስህተቶች፣ ህፀፆችና ግድፈቶች የያዘ ከመሆኑም በላይ አንዳንዱ አስተያየት የኢትዮጵያዊያንን ክብር የሚነካ ሆኖ አግኝተነዋል።
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን የጀመሩት “ኢትዮጵያ በዓለም ከሁሉም በላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለች አገር ነች“ በሚል ዓረፍተ ነገር ነበር። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት የፈጠራ ቀመሮች በዓለም ባንክ በኩል ዞረው በሚስ ሱዛን ራይስ ተቀነባብረው በባራክ ኦባማ አንደበት መስማት የሚያሳፍር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ኦባማ የተናገሩትን ዓረፍተ ነገር ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥና ራድዮ ደጋግሞ ሰምቶ ሰልችቶታል። ኦባማ፣ ይህ የተሰለቸ ዓረፍተ ነገር በእሳቸው አንደበት ሲነገር ስለሚሰጠው ትርጉም ጥቂት ቢያስቡ ኖሮ ለእሳቸውም ለአሜሪካም የተሻለ ነበር ብለን እናምናለን። “በአንድ ወቅት ራሷን መመገብ ያቅታት የነበረችው አገር ዛሬ ከፍተኛ እድገት የሚታይባት ሆናለች፤ አሁን የግብርና ብቻ ሳይሆን [የኤሌክትሪክ] ኃይልንም በመሸጥ በቀጠናው ቀዳሚነት ይዛለች” ሲሉ ያሞካሿት ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊያን የማያውቋት መሆኑን፤ እሳቸው የሚያወድሷት ኢትዮጵያ በህወሓት ፕሮፖጋንዳ እንጂ በመሬት ላይ የሌለች መሆኑን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማወቅ ነበረባቸው። በአንፃሩ የእውነተኛዋ ኢትዮጵያ 70% ሕዝብ በድህነት ወለል በታች በሆነ ኑሮ ሕይወቱን እየገፋ እንደሆነ፤ የሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያን የእለት ጉርስ ምንጭ የአሜሪካና የአውሮፓ አገሮች እርዳታ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ አያውቁም ማለት ይከብዳል። ፕሬዚዳንት ኦባማ የተናገሩለት የመብራት ኃይልም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተስፋ ተረት መሆኑን፤ ዛሬም የኢትዮጵያዊው የምሽት ኑሮ የሚገፋው በባትሪ፣ በሻማና በኩራዝ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ አያውቁም ማለት ያስቸግራል።
ፕሬዚዳንት ኦባማ ከተናገሩት ውስጥ ትርጉም የሚሰጥ ነገር ቢኖር ስለ “ሰላም ማስከበር” የተናገሩት ነው። የህወሓት አገዛዝ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ገንዘብ ባለበት እና አሜሪካ ወደ ፈለገችው ቦታ ሁሉ የሚልክ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የጦሩ የሰላም ማስከበር ሥራ ማሞካሸታቸው የሚጠበቅ ነው። እንዲያውም የፕሬዚዳንቱ ሙሉ ንግግር የተቃኘው ከዚህ አቅጣጫ ይመስላል። እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የራሳቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያወጣውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፖርትን ውድቅ የሚያደርግ ነገር ባልተናገሩም ነበር። አንዳችም ነፃ ተቋማት በሌሉበት አገር ውስጥ ፍትሃዊ ምርጫ የሚባል ነገር ሊኖር እንደማይችል አውቀው ቀዳሚው ጥያቄዓቸው የሰብዓዊ መብቶች መከበር እና የነፃ ተቋማት ግንባታ ጉዳይ ባደረጉት ነበር። ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለኢትዮጵያ ተጨንቀው ቢሆን ኖሮ የራሳቸው ስቴት ዲፓርትመን የዘንድሮውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፓርት ያስታውሱ ነበር። ሪፓርቱን በማስታወሳቸው ብቻ በግፍ እየታሰሩ ስላሉት ዜጎች፣ በኦጋዴን፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር እና በአማራ እየተጨፈጨፉ ስላሉ ዜጎች፣ ስለ መሬትና የሀብት ዘረፋ፣ ስለፍትህ እጦት፣ ስለ ተቋማዊ ዘረኝነት እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች እንዳነሱ ይቆጠር ነበር፤ ምክንያቱም ያ ሪፓርት የያዘው ይህንን ሁሉ ነው። ፕሬዚዳንት ኦባማ ግን የንግግራቸው ግብ ዘማች ወታደር ማግኘት በመሆኑ የራሳቸውን የስቴት ዲፓርትመንት ሪፓርት ትተው የወያኔን ሪፓርት ይዘው የቀረቡ አስመስሎባቸዋል። ይህ አካሄድ አሜሪካ ወደማትፈልገው የጦር አረንቋ የሚላኩ የሠራዊት አባላት ሊያስገኝ ቢችልም የሚያስከትላቸው ጉዳቶችም መታየት ነበረባቸው። የንግግራቸው ፈጣን አሉታዊ ውጤት ለማየት ቀናትም አልፈጀም፤ እነሆ በኦባማ አይዞህ ባይነት የተነቃቁት የህወሓት ገዳዮች ከኢትዮጵያ አልፈው በአሜሪካ ምድርም በኢትዮጵያዊያን ላይ መተኮስ ጀምረዋል።
የኦባማ ንግግር ትኩረት የፀጥታ ጉዳዮች ሆኖ ኢኮኖሚ የግኑኝነት ማሳለጫ ሆኖ ቀርቧል፤ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ደግሞ ፈጽመው ተገፍተው ወጥተዋል። ይህ ንግግር አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፓሊሲ አመላካች ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በፀጥታ ጉዳይም ቢሆን አሜሪካ የያዘችው አቋም በረዥም ጊዜ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአሜሪካን ጥቅም የሚጎዳ ነው ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ከወታደር ምንጭነት በላይ የምታገለግል አገር ናት። ኢትዮጵያ ውስጥ ከራሱ ሕዝብ ጋር የታረቀ መንግሥት መኖር ለቀጠናው ሰላም እና ብልጽግና ወሳኝ ከመሆኑም በላይ የቀጠናው ሰላምና ብልጽግና የአሜሪካም ስትራቴጂያዊ ጥቅም ነው ብለን እናምናለን። የአጫጭር ጊዜ ጊዜዓዊ ጥቅሞችን ብቻ በመመልከት አምባገነኖችን መደገፍ አሜሪካን ምን ያህል ውድ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ በዓይኖቻችን እያየነው ያለ ሀቅ ነው። አሜሪካ አምባገነኖችን መደገፏን ከቀጠለች ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የምታገኘው እስካሁን ስታገኝ የነበረውን ውግዘትና የጽንፈኞች መጠናከር ነው። አሜሪካ የተሳሳተ ፓሊሲ በያዘችባቸው አገሮች ሁሉ ግንባር ቀደም ተጎጂዎች ለዘብተኞችና ዲሞክራቶች ሲሆኑ እየተጠናከሩ የሚመጡት ደግሞ ጽንፈኖች ናቸው። አሁንም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊሲ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ኃይሎችን የሚያዳክም እና ጽንፈኛ ኃይሎችን የሚያበረታታ እንደሆነ ከወዲሁ ሊጠን ይገባዋል።
ዩ. ኤስ አሜሪካ የምትመራባቸው የነፃነት፣ የእኩልነትና የፍትህ እሴቶች የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እሴቶችም ናቸው። ኢትዮጵያዊያን እንደ አሜሪካ ዜጎች ሁሉ ፍትህን፣ ነፃነትን፣ እኩልነትንና ዲሞክራሲን ይሻሉ፤ እነዚህ መሻት ደግሞ መብታቸው ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል፤ ለዚህም ይታገላል። አሜሪካ ይህን ትግል ማገዝ ይገባታል። በተግባር የምናየው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። አሜሪካ ለአጫጭር ጊዜ ጥቅም ስትል ከአምባገነን ኃይሎች ጋር ማበሯ የዓላማ ተጋሪዎቿን እያዳከመ መሆኑ የወቅቱ የዓለም ሁኔታ የሚመሰክረው ሀቅ ነው። በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለችው ያለው ፓሊሲው ተመሳሳይ የረዥም ጊዜ መዘዝ እንዳያመጣ ያሰጋል። ይህ እንዳይሆን እርምት የሚገባው አሁን ነው።
ስለሆነም፣ ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ዩ. ኤስ. አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊስ እንደገና እንድትመረምር እና ዘረኛና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝን መርዳት እንድታቆም አበክሮ ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!


የየሸዋስ፣ ኃብታሙ፣ ዳንኤልና አብርሃ ችሎት ያለ ጠበቃ ተካሄደ

Oktober 2,2014
• ትክክለኛውን የቀጠሮ ቀን ለማወቅ አልተቻለም
(ኮማንደር ተክላይ ጥቅምት 20 ነው ሲሉ፤ ፖሊስ ጥቅምት 22 ነው ብሏል)

ዘሬ መስከረም 22/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ኃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ የአረና ም/ የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ችሎት ያለ ጠበቃ ተካሄደ፡፡ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ መቼ እንደተቀጠረ ያልታወቀ ሲሆን ችሎቱ ግቢ ሆኖ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ የችሎቱን ውሳኔ ከመዝገብ ቤት ጠይቆ እንዳይረዳ በፖሊስ ተከልክሏል፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ቀጠሮውን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ፖሊስ ቀጠሮው ጥቅምት 22 ነው ሲል ኮማንደር ተክላይ ቀጠሮው ለጥቅምት 20 እንደሆነ ገልጸውለታል፡፡

ችሎቱ 8 ሰዓት ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበር ቢሆንም የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀብታሙ አያሌውና የአንድነት ም/ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዳንኤል ሺበሽ 10 ሰዓት እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ሸዋስ አሰፋና የአረና ም/የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ 10፡30 አካባቢ ላይ ወደ ችሎት ገብተዋል፡፡

የዛሬው ችሎት ከእስከ ዛሬው በተለየ በርካታ ትዕይንቶች የታዩበት እንደሆነም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ከእነዚህም መካከል እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች የበለጠ ህዝብ የተገኘበት ሲሆን ህዝቡም ለመጀመሪያ ጊዜ እየተፈተሸ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች በተለየ ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግ ታይቷል፡፡ በችሎቱ የሰማያዊና የአንድነት ሊቀመናብርት፣ ዶክተር ያቆብ ኃይለማሪያምን የመሳሰሉ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተለያዩ አገራትና ተቋማት ተወካዮች፣ የተለያዩ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ዜጎች በችሎቱ ግቢ በመገኘት ለታሳሪዎቹ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ጋዜጠኞች ገብተው ችሎቱን መከታተል እንደሚችሉ ተገልጾ የነበር ቢሆንም በኋላ ግን እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአራቱ የፖለቲካ አመራሮች ጠበቆች የተለያየ ምክንያት እየተፈጠረ ደንበኞቻቸውን እንዳያገኙ መደረጋቸው፣ ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው በመሆኑና ህጉ የማይከበር በመሆኑ በጊዜ ቀጠሮ ለደንበቻቸው መቆም ስለማይችሉ ለጊዜው ለአመራሮቹ የሚያደርጉትን ጥብቅና በማቆማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡

ችሎቱ 11፡30 አካባቢ ያበቃ ሲሆን አጋርነቱን ለማሳየት ወደ አራዳ ምድብ ችሎት ያቀናው ህዝብ ታሳሪዎቹ ከችሎቱ ግቢ ከወጡ በኋላ እስኪርቁ በር ተቆልፎበት ችሎቱ ግቢ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ
Photo: የየሸዋስ፣ ኃብታሙ፣ ዳንኤልና አብርሃ ችሎት ያለ ጠበቃ ተካሄደ

• ትክክለኛውን የቀጠሮ ቀን ለማወቅ አልተቻለም

(ኮማንደር ተክላይ ጥቅምት 20  ነው ሲሉ፤  ፖሊስ ጥቅምት 22  ነው ብሏል)

ዘሬ መስከረም 22/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ኃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ የአረና ም/ የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ  ችሎት ያለ ጠበቃ ተካሄደ፡፡ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ መቼ እንደተቀጠረ ያልታወቀ ሲሆን ችሎቱ ግቢ ሆኖ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ የችሎቱን ውሳኔ ከመዝገብ ቤት ጠይቆ እንዳይረዳ በፖሊስ ተከልክሏል፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ቀጠሮውን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ፖሊስ ቀጠሮው ጥቅምት 22 ነው ሲል ኮማንደር ተክላይ ቀጠሮው ለጥቅምት 20 እንደሆነ ገልጸውለታል፡፡

ችሎቱ 8 ሰዓት ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበር ቢሆንም የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀብታሙ አያሌውና የአንድነት ም/ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዳንኤል ሺበሽ 10 ሰዓት እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ሸዋስ አሰፋና የአረና ም/የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ  10፡30 አካባቢ  ላይ ወደ ችሎት ገብተዋል፡፡

የዛሬው ችሎት ከእስከ ዛሬው በተለየ በርካታ ትዕይንቶች የታዩበት እንደሆነም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ከእነዚህም መካከል እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች የበለጠ ህዝብ የተገኘበት ሲሆን ህዝቡም ለመጀመሪያ ጊዜ እየተፈተሸ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች በተለየ ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግ ታይቷል፡፡ በችሎቱ የሰማያዊና የአንድነት ሊቀመናብርት፣ ዶክተር ያቆብ ኃይለማሪያምን የመሳሰሉ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተለያዩ አገራትና ተቋማት ተወካዮች፣ የተለያዩ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ዜጎች በችሎቱ ግቢ በመገኘት ለታሳሪዎቹ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ጋዜጠኞች ገብተው ችሎቱን መከታተል እንደሚችሉ ተገልጾ የነበር ቢሆንም በኋላ ግን እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ 

በተመሳሳይ የአራቱ የፖለቲካ አመራሮች ጠበቆች የተለያየ ምክንያት እየተፈጠረ ደንበኞቻቸውን እንዳያገኙ መደረጋቸው፣ ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው በመሆኑና ህጉ የማይከበር በመሆኑ በጊዜ ቀጠሮ ለደንበቻቸው መቆም ስለማይችሉ ለጊዜው ለአመራሮቹ የሚያደርጉትን ጥብቅና በማቆማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡  

ችሎቱ 11፡30 አካባቢ ያበቃ ሲሆን አጋርነቱን ለማሳየት ወደ አራዳ ምድብ ችሎት ያቀናው ህዝብ ታሳሪዎቹ ከችሎቱ ግቢ ከወጡ በኋላ እስኪርቁ በር ተቆልፎበት ችሎቱ ግቢ ውስጥ እንዲቆይ  ተደርጓል፡፡

የዋሽግተኑ ጉዳይ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር ሲታይ

Oktober 2,2014
ከጌታቸው በቀለ
”ዓለም አቀፍ ሕግ፣ዓለም አቀፍ ሕግ” የምትል ቃል በእየቦታው ትሰማ ጀመር።እሰይ! እንዴት ደስ ይላል።ይህንን ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ-ገፅ ላይ የሚጠቅሱት ደግሞ የስርዓቱ አድናቂዎች ናቸው።ጉዳዩን የሚያነሱትደግሞ በዋሽግተን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተደረገው ተቃውሞ ሳብያ ነው።እስኪ ለህሊናችን መጀመርያ በሀገር ውስጥ እራሱ ላወጣው ሕግ መገዛት ቢያቅተው ለዓለም አቀፍ ሕግ እንዲገዛ ስርዓቱን እንምከረው።እንዲህም እንጠይቅ-
ለመሆኑ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደ ዓለም ዋንጫ ቅሪላ በእግሩ የሚያጦዛት ማን ነው?
embassy shooter
ማን ነው የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውን የጋምቤላ አስተዳዳሪ ከደቡብ ሱዳን ጠልፎ ወስዶ ያሰረው? ዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ቁጥር ስንት እንበለው?
ማን ነው የእንግሊዝ ፓስፖርት የያዙትን አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን ጠልፎ ያሰረው? ዓለም አቀፍ ሕግ ቁጥር ስንት እንበለው?
ዓለም አቀፍ ሕግ የአፍ ማሟሻ አደለም! በተግባር ለእራስ ሲሉ የሚያከብሩት ነው።ዛሬ የዋሽግተን ኤምባሲ ሲደናገጥ ”ሕግ ምናምን” አትበሉ።የዋሽግተኑን ጉዳይ በዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር ካየነው የኤምባሲው የሕግ ከለላ ከባዕዳን ነው እንጂ ከሀገሩ ተወላጆች አይደለም! አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ውስጥ ገብቶ የመቃወምም ሆነ ዋሽግተን ላይ ባለው በሀገሩ ኢምባሲ ውስጥ ገብቶ የመቃወም መብቱን ዓለም ዓቀፍ ሕግ አይገድበውም።የሰንደቅ አላማው ጉዳይም ሰንደቅ አላማው በሌላ ሰንደቅ አላማ ተተክቶ ቢሆን ነበር የሚያሳዝነው።ይህ ቢሆን ኖሮ በሕግም አከራካሪ ይሆን ነበር።የሉዓላዊነት ጥያቄም አብሮ ሊነሳ ይችል ነበር።የሆነው ግን ለሕግ ወቀሳም አይበቃም። ተቃዋሚዎቹ የተኩት ቀድሞ የኢህአዲግ አርማ ያለበትን በእራሷ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነው።
አንድ ሀገር የውጭ ቆንስላ ወይንም ኤምባሲን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።ይህ የሚያደርገው ግን ከእዛ ሀገር ዜጎች የበለጠ ኃላፊ ሆኖ አይደለም።የኤምባሲው ሀገር ተወላጅን ወደ ኤምባሲው ‘ግባ አትግባ’ ማለት ሌላ ሳይሆን አንድን ኢትዮጵያዊ ወደ እራሱ ሀገር ‘ግባ አትግባ’ ንትርክ ውስጥ መግባት ማለት ነው።የዋሽግተኑ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ጉዳይ ይሄው ነው።ኢትዮጵያውያን በኤምባሲያቸው ቅጥር ግቢ ሆነው የሚያደርጉት ሁሉ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዳደርጉ ነው የሚቆጠረው።የኢምባሲ ግቢ ማለት የታፈረ የተከበረ ኢምባሲው የተጠራበት ሀገር ምድር ማለት ነው።ለእዚህ ነው አንድ ስደተኛ ወደ አንዱ ሀገር ኤምባሲ ገብቶ ጥገኘነት ቢጠይቅ ኤምባሲው ሀገር እንደገባ የሚቆጠረው እና ኤምባሲው ያለበት ሀገር ፖሊስ ዘሎ ሊገባ የማይችለው።ኢህአዲግ አዲስ አበባ ሲገባ ጣልያን ኤምባሲ እጃቸውን የሰጡ ባለስልጣን የፌድራል ፖሊስ መያዝ ያልቻለው ለእዚህ ነው።ግቢው ሃገሩ ነው።ተቃዋሚዎችም ዋሽግተን ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግቢ ሀገራቸው ነው።የመቃውም መብታቸው ላይ አሜሪካን አይመለከታትም።ጉዳዩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ነው።አሜሪካ የሚመለከታት በምድሯ ላይ የማይፈቀደው የመግደል ሙከራ፣ማስፈራራት እና ድምፁ በግቢው ውስጥ መወሰን ያልቻለው አካብቢውን ያሸበረው የተኩስ ድምፅ ነው።
ባጭሩ አሜሪካ ኃላፊነት ያለባት የጦር መሳርያ ይዘው ወይንም የሚያሸብር ነገር ይዘው ወደ ኢምባሲ የመጡትን የመጠበቅ እንጂ በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ለመቃወም ሰንደቅ ዓላማ እና የታሰሩ እስረኞች ፎቶ ይዘው ለመጡ አይደለም። እንዲያውም አሜሪካ በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ከገባች አሁንምበኢትዮጵያ የሀገር የውስጥ ጉዳይ እንደገባች ነው የሚቆጠረው።በነገራችን ላይ ከእዚህ በፊት ለአመታት ኢትዮጵያውያን በዋሽግተንም ሆነ ሌሎች ኢምባሲዎች ፊት ሰልፍ ካደረጉ በኃላ የሰልፋቸውን ጥያቄ የያዘ ደብዳቤ ለአምባሳደሩ ለመስጠት ሲጠይቁ የኢህአዲግ የኤምባሲ ሰራተኞች ከፎቅ ላይ ሆነው ቪድዮ ማንሳት እንጂ ደብዳቤ አይቀበሉም።እናም ዜጎች እንዴት ሃሳባቸውን ይግለፁ? ተቃዋሚዎቹ ሌላ አማራጭ ነበራቸው ወይ? የሚለውን የአሜሪካ መንግስትም የሚመለከተው ነው። በሰልፍ ሲወጡ ፖሊስ እንዲጠራ ይደረጋል።በፅሁፍ ሲያቀርቡ ኤምባሲው ለፎርማልቲም ቢሆን አይቀበልም።ልክ ‘ምናምን’ እንደነካው እንጨት ይጠየፋል።
ይህ ትልቅ የኢምባሲዎቹ የትዕቢት መገለጫ ነው።አንድ ዜጋ የፈለገው ጉዳይ ላይ የመቃወም ሃሳቡን በቃልም ሆነ በፅሁፍ የማቅረብ መብት አለው።ኢምባሲው እዝያ በተሰለፈው ሕዝብ እና በቤተሰቡ ገንዘብ ደሞዙን እንደሚያገኝ ዘንግቶ የተቃውሞ ደብዳቤ አለመቀበሉን በምን እንግለፀው? አዲስ አበባ ላይ ሆኖ ”እሰይ ደግ አደረካቸው” እያሉ መፎከር አይደለም።አሰራርን መፈተሽ፣ትዕቢትን መቀነስ ነው የሚያስፈልገው። መጨረሻ ምን ሆነ ዜጎች ”ስሙን!!! ኡ ኡ ኡ !!” እያሉ ወደ ኤምባስያቸው ገቡ።አሳፋሪው ድርጊት ግን የሀገራቸው ኤምባሲ ተኮሰባቸው።ይህ ነው አሳፋሪ ተግባር የሚባለው።ዓለም የገረመው ይህ ነው።ኢትዮጵያውያን ምን አይነት አሳፋሪ አገዛዝ ስር እንደወደቁ የተረዳው እዚህ ላይ ነው።በሀገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ የተናደዱ፣ያዘኑ ዜጎች ዋሽግተን ላይ ሃሳባቸውን መግለፅ ካልቻሉ በሃገራቸውማ ቢሆን በታንክ ነው የሚሏቸው ብሎ የደመደመው ለእዚህ ነው።የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቶሎ መግለጫ አላወጣም።ጉዳዩን የሚመለከተው ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች አንፃር እንደሚሆን ይታወቃል።የውጭ መገነኛ ብዙሃን በተቃዋሚዎች ላይ የመተኮሱን ጉዳዩን ከገለፁበት ቃላት ውስጥ ”በካሜራ የተያዘ ድራማዊ እንቅስቃሴ” ብሎ የዘገበው የእንግሊዝን ”ዴይሊ ሜይል” ይጠቀሳል።
ከሰሞኑ ዋሽግተን ላይ ከተከሰተው ክስተት አንፃር ኢትዮጵያውያንም ለሁሉም ወገን ማስረዳት ያለባቸው ከላይ ከተጠቀሱት የአፈና ደረጃዎች አንፃር መሆን ይገባዋል።ፀሐፊዎች፣ጋዜጠኞች፣በውጭ ሀገር በልዩ ልዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሁሉ ለዓለም (ለአሜርካኖችም ጭምር) ማስረዳት በእንግሊዝኛም መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።የኢህአዲግ አድናቂዎችም ከህሊናችሁ ጋር ኑሩ! እውነታውን መርምሩ።መንግስታችሁ እንዴት ወዴት እየሄደ እንዳለ እና በውስጡ የተሰገሰጉት የትዕቢት አባቶች አደብ እስካልገዙ ድረስ ከትርፍ ይልቅ ኪሳራው እየበዛ መሄዱ አይቀርም።ዓለም አቀፍ ሕግን ግን ለቀቅ አድርጉት።
ጉዳያችን
መስከረም 21/2007 ዓም (ኦክቶበር 1/2014)

Wednesday, October 1, 2014

የፓርቲዎቹ አባላት ጠበቃ ደረሰብኝ ባሉት ጫና ለጊዜው ሥራቸውን ማቆማቸውን አስታወቁ

Oktober 1,2014
በ  አሸናፊ ደምሴ
በሕገመንግስቱ መሠረት ለደንበኞቼ አገልግሎት መስጠት አልቻልኩም፤ ከፍርድ ቤትና ከፖሊስም ማስፈራሪያ ደርሶብኛል ያሉት የአንድነት፣ የሰማያዊና የዓረና ፓርቲ አባላት ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ። ደንበኞቼ የምርመራ ቃላቸውን ለፖሊስ ከመስጠታቸው በፊት ላገኛቸው ሲገባ ይህ አልተደረገም ያሉት ጠበቃው፤ የጊዜ ቀጠሮው ችሎት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለቀጣዩ አንድ ወር ደንበኞቻቸውን እንደማያገኙና ሕግን ባልጠበቀ መንገድ ለሚከናወን ተግባር የፕሮፓጋንዳ ሽፋን መሆን እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል።
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለአንድነት ፓርቲ አባላቱ ለሀብታሙ አያሌውና ለዳንኤል ሺበሺ፤ ለአረናው አብርሃ ደስታ እና ለሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ ጠበቃ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኙ የነበሩ ሲሆን፤ ደረሰብኝ ባሉት ጫና እና ኢ-ሕገመንግስታዊ አሰራር ምክንያት ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለጊዜውም ቢሆን ማቋረጣቸውን ለፓርቲዎቹ አመራሮች መግለፃቸውን አስረድተዋል። ይህም በመሆኑ ሦስቱ ፓርቲዎች (ማለትም አንድነት፣ ዓረና እና ሰማያዊ) በእስረኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት በተመለከተ ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም በአንድነት ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እንደማንኛውም ጠበቃ ደንበኞቼን ማግኘት ቢኖርብኝም፤ ላገኛቸው አልቻልኩም፤ በፍርድ ቤት የምናቀርባቸው አቤቱታዎች እና ስሞታዎች በሙሉ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ ይደረጉብናል፣ ይባስ ብሎም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር በመኖሩ ለስርዓቱ ሕጋዊ ከለላ መሆን አልፈልግም የሚሉት አቶ ተማም አባቡልጉ፤ በዚህም ምክንያት የታሰሩት የፖለቲከኛ እስረኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ ከለላ ማግኘት አልቻሉም ሲሉ ነገ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደሚያነሱ ምንጮች ጠቁመዋል።
በጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ በጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡት ያለጠበቃ ቢሆንም፤ ምናልባትም ከወር በኋላ ዐቃቤ ሕግ ክስ የሚመሰርት ከሆነ፤ በችሎት ተገኝቼ ደንበኞቼን አገለግላለሁ የሚሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ፤ ደንበኞቼ ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት እኔን ማግኘት ሲገባቸው ሳያገኙኝና ቃላቸውን ሰጥተው ከፈረሙ በኋላ ባገኛቸው ምን አደርግላቸዋለሁ? ሲሉ ጥያቄ አዘል ኀሳባቸውን ይሰነዝራሉ። ከዚህም ባሻገር ደንበኞቼ ከተጠረጠሩበት ጉዳይ ውጪ በሆነ መልኩ የሚደረግባቸው ምርመራ በፓርቲ ጉዳይ ላይ ሆኗል ሲሉ ቅሬታቸውን የሚያቀርቡት ጠበቃው፤ ለዚህም ጠንካራ አባል ማነው? የገንዘብ ምንጫችሁ ከየት ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው እንደነበር ደንበኞቼ ለፍርድ ቤት ቀርበውም አመልክተዋል ሲሉ ያስረዳሉ።
      ይህም በመሆኑ የተላላኪነት ስራ ከመስራት ውጪ የምፈይደው ነገር የለም በሚል ለጊዜው ከደንበኞቼ ጋር መገናኘቱን አቁሜያለሁ ያሉት ጠበቃ ተማም፤ በዚህ አጋጣሚ ደንበኞችዎ ምን ሊያጋጥማቸው ይችላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “የሚደርስባቸው ሁሉ ደርሶባቸዋል፤ እኔም ኖሬ ምንም አይነት የሕግ ከለላ አላገኙም” ሲሉ መልሰዋል።
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

የወያኔ አምባሳደር ግርማ ብሩ ኮከብ የለሽ ባንዲራን የሰቀሉትን ጋጣ ወጦች አላቸው

Oktober 1,2014

ኢትዮጵያዉያኖች በኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረጉት የተቃዉሞ ሰልፍ፣ ኮከብ ያለበትን የአገዛዙ ባንዲራ አንስተው፣ የጠራዉን የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ መትከላቸው ይታወቃል። መሳሪያ ያልታጠቁ፣ ወረቀትና ባንዲራ ብቻ በእጃችቸው የያዙ ሰላማዊ ዜጎች “ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንፈልጋለን፣ ወንጀለኞች አይደለንም” በሚሉበት ጊዜ፣ አንዱ የኤምባሲ ጠባቂ፣ ጥይት መደቀኑና ሶስት ጊዜ መተኮሱ፣ በኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ሜዲያዎች ሁሉ በስፋት እየተዘገበ ነው።
መሳሪያ ባልያዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይት መደቀኑ ብዙዎችን እያስቆጣ ባለበት ወቅት፣ የአገዛዙ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ፣ ለኢትዮጵያ ፈርስት በሰጡት አስተያየት፣ ሠልፈኞቹን “ጋጣወጦች” ሲሏቸው፣ ጥየት የተኮሰዉን ግለሰብ ደግሞ “ስራውን በትክክል የሰራ” ሲሉ አሞግሰዉታል።
በሰልፉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንን ላይ ክስ እንዲመሰረትና እርምጃ እንዲወሰድ ጠበቃዎች እንደሚቀጥሩ የገለጹት አቶ ግርማ ብሩ፣ “ተቃዋሚዎቹ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ የተናደዱ ናቸው” ሲሉም ከሰዋቸዋል። ከአሜሪካኖች ጋር በቅርበት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ እየተነጋገሩበት እንደሆነም የተናገሩት አቶ ግርማ፣ ሰልፈኞቹ ተቃዉሞ እንዲያሰሙ ስለገፋፋቸው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚደረገው ዜጎችን የማሽበር፣ የማሰር መረን የለቀቀ የሰባአዊ መብት ረገጣ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡
አምባሳደሩ ሰልፈኞችን ጋጣወጦች ቢሏቸውም፣ ህዝቡ በሰልፉ ለነበሩ ወገኖች ያለዉን አድናቆትና ክብሩን እየገለጸ ሲሆን፣ ብዙዎች በኤምባሲ የተሰቀለዉን ባንዲራ የሚያሳየዉንን ፎቶ የፌስቡክ ፕሮፋይላቸዉ እያደረጉ ነው። በርካታ በዉጭ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች፣ አክቲቪስቶችም በ ኤምባሲ የታየው በተጠናከረ መልኩ መቀጥል እንዳለበት ይናገራሉ።
በጉዳዩ ላይ ያነጋግርናቸው የፖለቲካ ተንትታኝ “ በዲስም ሆነ እንደ ለንደን ብራሰልስ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ለአገራቸው፣ ለሕዝባቸውና ለባንዲራቸው ክብር የቆሙትን የሚያኮሩ ኢትዮጵያዉያንን “ጋጠወጦች” ብሎ ለጠራው የወያኔ ቅጥረኛ ግርማ ብሩ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል” ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፣ በኤምባሲ የታየው ህዝቡን ኤነርጃይዝድ በማድረጉ አንጻር ፣ ትግል ብዙ እርምጃ ወደፊት እንደወሰደው ይናገራሉ።

በማዕከላዊ የሚታፈኑት ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ ነው

Oktober 1,2014
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየታፈኑ ወደ ማዕከላዊ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እያሸቀበ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ዘገቡ፡፡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ታፍነው ወደ ማዕከላዊ የሚመጡት ዜጎች ስለ አሉበት ሁኔታ ቤተሰብ እንዳያውቅ እንደሚደረግም ምንጩቹ ጠቅሰዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ታፋኞች ከኦሮሚያ ክልል የመጡ እንደሆነ የጠቀሰው ምንጩ ከደቡብ ጎንደር አካባቢም ታፍነው የመጡም እንደሚገኙበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ለጊዜው ከኦሮሚያ አካባቢ ታፍነው እንደመጡ የሥም ዝርዝራቸው የደረሰን የሚከተሉት ሲሆኑ ነገረ ኢትዮጵያ የሌሎቹንም እየተከታተለች ለማሳወቅ ትጥራለች፡፡
የታፋኞቹ ስም ዝርዝር
1. ንሞና ጫሊ ኦሮሚያ
2. አበበ ሁርጌሳ ኦሮሚያ
3. ብሊሱማ ዳማና ኦሮሚያ¬ (አዳማ)
4. ልንዲሣ አለማየሁ ኦሮሚያ (ጅማ)
5. ተሻለ በቀለ ኦሮሚያ (ጅማ)
6. መገርሳ ወርቁ ኦሮሚያ (ጅማ)
7. ብሉሲማ ጎንፋ ኦሮሚያ
8. ጫልቱ (ወልገሁ) ኦሮሚያ
9. ኦፋርካ ከበደ አልታወቀም
10. አዱኛ አስቴር ኦሮሚያ
11. ጉተላ ጃለታ ኦሮሚያ (ጅማ)
12 ገመቹ በቀለ ኦሮሚያ (ጅማ)
በማዕከላዊ የሚታፈኑት ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ ነው</p>
<p>ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየታፈኑ ወደ ማዕከላዊ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እያሸቀበ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ዘገቡ፡፡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ታፍነው ወደ ማዕከላዊ የሚመጡት ዜጎች ስለ አሉበት ሁኔታ ቤተሰብ እንዳያውቅ እንደሚደረግም ምንጩቹ ጠቅሰዋል፡፡ </p>
<p>አብዛኛዎቹ ታፋኞች ከኦሮሚያ ክልል የመጡ እንደሆነ የጠቀሰው ምንጩ ከደቡብ ጎንደር አካባቢም ታፍነው የመጡም እንደሚገኙበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ለጊዜው ከኦሮሚያ አካባቢ ታፍነው እንደመጡ የሥም ዝርዝራቸው የደረሰን የሚከተሉት ሲሆኑ ነገረ ኢትዮጵያ የሌሎቹንም እየተከታተለች ለማሳወቅ ትጥራለች፡፡</p>
<p>የታፋኞቹ ስም ዝርዝር</p>
<p>1. ንሞና ጫሊ            ኦሮሚያ<br />
2. አበበ ሁርጌሳ            ኦሮሚያ<br />
3. ብሊሱማ ዳማና          ኦሮሚያ¬   (አዳማ)<br />
4. ልንዲሣ አለማየሁ         ኦሮሚያ  (ጅማ)<br />
5. ተሻለ በቀለ              ኦሮሚያ  (ጅማ)<br />
6. መገርሳ ወርቁ            ኦሮሚያ  (ጅማ)<br />
7. ብሉሲማ ጎንፋ           ኦሮሚያ<br />
8. ጫልቱ  (ወልገሁ)         ኦሮሚያ<br />
9. ኦፋርካ ከበደ             አልታወቀም<br />
10. አዱኛ አስቴር            ኦሮሚያ<br />
11. ጉተላ ጃለታ             ኦሮሚያ (ጅማ)<br />
12 ገመቹ በቀለ            ኦሮሚያ  (ጅማ)