May24/2014
By Gezahegn Abebe (Norway Lena )
የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ህልውና የሚወሰነው ወጣቶች ባላቸው ሚና ላይ ሲሆን በብዙ ሀገራት እንዳየነው እና እንደተመለከትነው ወጣቶች ስለ ነፃነታቸው ፊት ለፊት መንግስታትን በመጋፈጥ ለመብታቸው ታግለዋል መስዋህትነትምበመክፈል የፈለጉትን አለማና ግብ አሳክተዋል::ለዚህም የሰሜን አፍሪካ አገሮችንና የመካከለኛው ምሥራቅን የለውጥ አብዮት ያቀጣጠሉትን ወጣቶች ዞር ብሎ መመልከት ያሻል:: የአንባ ገነኖች የስልጣን አገዛዝ አልዋጥላቸው ያላቸው እነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገሮች እንደነ ግብጽ ፣ ቱኒዚያ እና ሊቢያ ያሉ ሀገሮች የሚኖሩ ወጣቶች በጊዜው ለናፈቁት እናለተመኙለት ነጻነት ብዙ መስዋትነትን በመክፈል ዓላማቸውን አሳክተዋል:: በወቅቱ የነበረው የዓረብ የፖለቲካ ትኩሳትመነቃቃት ለብዙ ሀገራት ወጣቶች ትምህርት ሰጥቶ ያለፈ ታሪክ ነው::
ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመለስ የኢትዮጵያን የፖለቲካ አካሄድ ወደ ኋላ ዞር ብለን በምናይበት ጊዜ በኢትዮጵያ ሲደረግ በነበረው የፓለቲካ እንቅስቃሴ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ትልቁን ሚና ይጫወት እንደነበር ከታሪክ መረዳት እንችላለን::እነሆ በኢትዮጵያ ረዥም ታሪክ ውስጥ እያንዳንዱ ትውልድ በተለያየ ጊዜና ወቅት የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል፡:
በተለይ በንጉሡ ጊዜ የመሬት ላራሹንና ሌሎችንም የፖለቲካዊ ጥያቄዎች አንግቦ ሲንቀሳቀስ የነበረው የተማሪ ንቅናቄ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በዚያን ጊዜው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የነበሩትና ግንባር ቀደሞቹ ዋለልኝ መኮንንና ጥላሁን ግዛው በድንገት በወታደራዊው ኃይል ቁጥጥር ሥር ለወደቀው የተማሪው አብዮት ተጠቃሾች ሲሆኑ፣ በዘመኑ ለነበረው ሃይለኛ እና ወኔን የታጠቀ ትውልድም መታወቂያ ሆነው ማለፋቸውን የታሪክና የፖለቲካ ተንታኞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚያወሱት የታሪክ ትውስታ ነው፡፡
ከቅርብ አመታት በፊትም ማለትም በ97 ምርጫ ሁሉም ሰው እንደሚያስታውሰው ይህ ወቅት ወያኔ ወጣቶችን ሙሉ በሙሉ የገፋበት ወቅት ጊዜ እንደነበር እና መንግስት ስራ አጥተው የሚንከራተቱ ወጣቶችን “አደገኛ ቦዘኔ” የሚል ታፔላ በመስጠት የተለያዩ እስሮችና የማንገላታት እርምጃዎችን የወሰደበት እና የፈፀመበት ወቅት እንደነበር በብዙዎች ዘንድ ይታመናል፡፡ ይህ አይነቱ የመንግስት ግብታዊ እርምጃ ወጣቱን ወደ ተቃውሞ ጐራ እንዲያዘነብል አድርጐታል፡፡ ለዚህም ይመስላል በወቅቱ በምርጫ 97 ዋዜማ ወያኔ ትግሬ ያቀረባቸውን የተለያዩ ማባበያዎች “አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ” የሚል ዜማ በማቀንቀን ለተቃዋሚዎች ድጋፍ የሰጠው፡፡ ወያኔ በምርጫ 97 የደረሰበትን አስደንጋጭ ሽንፈት ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ቀዳሚ ተጠቂ የሆነውም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደነበር እናስታውሳለን፡:ለዚህም ነው ምርጫ 97 ተከትሎ በጊዜው የወያኔው መለስ መንግስት ከሃያ ሺ በላይ ወጣቶች በእስር ቤቶችና በወታደራዊ ካምፖች ታሰረው የተሰቃዩት እና ከ200 በላይ የሆኑ ባብዛኛው ወጣት የሆኑ ንፁሀን ዜጐች በግፍ በአደባባይ የተገደሉት::ይህንን ለነጻነት ትግል የተደረገን የወጣቶች የህይወት መስዋትነት ሁል ጊዜ ስናስታውሰው የምንኖረው ነው::
እንደሚታወቀው በአሁን ወቅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚኖረው ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር ይዞ የሚገኘው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል መሆኑ ይታወቃል:: ይህንንም ተከትሎ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከወጣቶች ብዙ የምትጠብቀው ነገር መኖሩ የማያጠያይቅ እውነታ ነው;; ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሀገራችን የወደፊት ሁለንተናዊ ህልውናዋ ያለው እና የሚወሰነውም በእነዚሁ በዛሬዎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስለሆነ :: ከላይ እንደገለጽኩት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚኖረው ሕዝብ አብዛኛውን ቁጥር የያዘው ወጣቱ እንደመሆኑ ይሄ ወጣት የህብረተሰብ ክፍል በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፍላጐቱ ሊሞላለት አልቻለም:: ከዚያም ባለፈ ወጣቶች የነጻነትም ሆነ የመብት ጥያቄያቸውን ወይም ፍላጐታቸውን መግለጥ እና መናገር የሚችሉበት አግባብ የተዳፈነ በመሆኑ፣ በአለም ላይ ኢትዮጵያን የተገፉ ወጣቶች የበረከቱባት ሀገር እና ሀገራቸውን እየጣሉ ከሚሰደዱ ወጣቶች መካከል ቅድሚያውን እንድትይዝ አድርጓታል፡፡
የወያኔ መንግስት በስልጣን በቆየባቸው ባለፉት 23 አመታቶች እየበደለ እና እያሰቃየ ያለው በመላ ሀገሪቱ ላይ የሚኖረውን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ቢሆንም ይበልጥኑ በወያኔ ራዳር ውስጥ በመግባት በአገዛዙ ጭቆናና ግፍእየደረሰበት ያለው በሀገራችን የሚኖረው ወጣቱ ዜጋ መሆኑ የታወቀ ነው:: ዛሬ የአማራው፣ የጋምቤላው፣ የኦሮሞው ፣የደቡቡ፣ የአፋሩ መላው የኢትዮጵያ ወጣት ዜጋ ለነጻነቱ በሚያደርገው ትግል በወያኔ ጨካኝ መንግስት እያተደበደበ፣እየታሰረና እየተገደለ ለነጻነቱ መስዕዋትነትን በመክፈል ላይ ይገኛል :: ለዚህ ማሳያ የሚሆነን በሀገራቸው ፖለቲካበመሳተፍ የተቃዋሚዎችን ጐራ የተቀላቀሉ እንደነ አንዱ አለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን እና ኦልባና ሌሊሳ የመሳሰሉወጣት ፖለቲከኞች እንዲሁም እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዮት አለሙን የመሳሰሉ የወደፊቷ ኢትዮጵያተስፈኞች ብዙ የምትጠብቅባቸው ወጣት ጋዜጠኞች እንዲሁም በቅርቡ ህገ መንግስቱ ይከበር በማለት ሀሳባቸውን በብህራቸው የገለጡ የዞን9 ጦማሪዎች የወያኔ መንግስት እያራመደ ካለው የዘረኝነት ፖለቲካ የተለየ አቋም በመያዛቸው እና በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው ወደ እስር ቤት በግፍ መወርወራቸው የኢትዮጵያ ወጣቶች በገዥው ስርዓት ምን ያህል መብታቸው እየተረገጠ እና ነጻነታቸው እየታፈነ በወያኔ የግፍ አለንጋ እየተገረፉ እንደሚኖሩ አመላካች ነው፡፡
የወያኔ መንግስት በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እየወሰዳቸው ያnለው እነዚህ በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ወጣቶች እጃቸውን አጣጥፈው እንዲቀመጡ አላደረገም፡፡ ይባሱኑ ወጣቱ ሀይሉን እያጠናከረ እና ወደ ተቃዋሚ ጎራ በመግባት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለወያኔ መንግስት የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል::ከተለያዩ አካባቢዎች በአሁን ሰአት እንደማገኛው መረጃዎ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶች የወያኔን መንግስት ለመጣል በሚደረጉ ማንኛውም አይነት ትግል መስዋህት ለመሆን ከመቼውም ጊዜ ቆርጠው መነሳታቸውን በብዙ መንገድ እያስመሰከሩ ይገኛሉ ::በመሆኑም ይህ በወያኔዎች የግፍ አለንጋ እየተገረፈ ለነፃነቱ መስዕዋት እየከፈለ ያለ ወጣት የወያኔን ዘረኛ መንግስት ወደ መቃብር እንደሚያስገባው ምንም ጥርጥር የለኝም::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

No comments:
Post a Comment