October 18/2013
የወያኔዉ ጠ/ሚኒስቴርኃ/ማርያም ደሳለኝ ከጌቶቹ በተሰጠዉ መመሪያ መሰረት የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙትን የወያኔ መሪዎች ከተጠያቂነት ለማዳን ቀንና ማታ እየሰራ መሆኑን ጉዳዪን በቅርብ የሚከታተሉ ዘጋቢዎቻችን ዲፕሎማቲክ ምንጮችን በመጠቀስ በላኩልን ዜና ገለጹ። በኬንያ አነሳሽነት የአፍሪካ ኅብረት በቅርቡ በአዲስ አበባ ዉስጥ በጠራዉ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የወቅቱ የኅብረቱ ሊቀ መንበር የሆነዉ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ‹‹የአፍሪካ መሪዎችን አዳኝ ተቋም›› ብሎ ሲጠራዉ የተደመጠ ሲሆን ኃ/ማሪያም ከዚህ በተጨማሪ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ ላይ በሚወስዳቸው ዕርምጃዎች የአፍሪካ ኅብረት በተደጋጋሚ ቅሬታውን ያሰማ ቢሆንም፣ አንድም ጊዜ አልተደመጠም የሚል ተልካሻ አስተያየት ሰጥቷል፡፡ የአፍሪካ ህብረት በእንደዚህ አይነቱ ጉዳይ ላይ በመሪዎች ደረጃ ሲሰበሰብ የመጀመሪያ ቢሆንም የኢትዮጵያ መሪዎች አለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሲያወግዙ ግን ኃ./ማሪያም ደሳለኝ የመጀመሪያ አይደለም። የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ባለበት ቦታ እጁ ተይዞ ለአለም አቀፉ ፍርድ ቤት እንዳይሰጥ ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ።
የአይጥ ምስክር ድንብጥ እንዲሉ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆነዉ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ‹‹የፀጥታው ምክር ቤትና ፍርድ ቤቱ በተከተሉት ‘ደብል ስታንዳርድ’ ምክንያት ኅብረቱ ያቀረባቸውን ቅሬታዎች ‘ጆሮ ዳባ ልበስ’ ብለውታል ሲል ተደምጧል፡፡ ቀጥሎም የራሱ ፓርቲ አባል የነበዉና የትግል ጓደኛዉ መለስ ዜናዊ አይኑ ፊት የአኝዋክን ህዝብ ሲጨፈጭፍ ዝም ብሎ የተመለከተዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም “ዜጐቻቸውን የሚጨፈጭፉ የአፍሪካ መሪዎችን ተቀምጠን አናይም” ብሏል፡፡ “ድምፃችን ከፍ ብሎ መሰማት መጀመር አለበት” በሚል ኃይለቃል ንግግሩን ያጠቃለለዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የአፍሪካ ኅብረት አባል አገር መሪ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ መጠየቅ ፍፁም ንቀት መሆኑን ተናግሯል፡፡
ኃይለማሪያምና ቴዎድሮስ አድሀኖም “እንዳሰኘን መግደል ይፈቀድልን” የሚል አስቀያሚ ዘመቻ መጀበሩበት በአሁኑ ወቅት አፍሪካን ከአለም አቀፉ የወንጀለኞቸ ፍርድ ቤት ለመነጠል የሚደረገዉን ጥረት አምርረዉ የሚቃወሙ አገሮች፤ምሁራንና ተደማጭነት ያላቸዉ ታላላቅ ሰዎች በየቦታዉ ብቅ ማለት ጀምረዋል።ከእነዚህም መካከል የቀድሞዉ የተመድ ዋና ጸሐፊ ጋናዊዉ ኮፊ አናንና የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚ የሆኑት ደቡብ አፍሪካዊዉ ዴዝሞንድ ቱቱ ይገኙበታል፡፡ ጋናዊዉ ኮፊ አናን የአፍሪካ መሪዎች እራሳቸዉን ከአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለማግለል የሚያደርጉትን ጥረት “የኃፍረት ባጅ” ማንጠልጠል ነዉ ብለውታል፡፡ የኖቤል የዓለም የሰላም ተሸላሚው ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ደግሞ “ፍርድ ቤቱን ዋጋ ቢስ” ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ አነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝን የመሳሰሉ መሪዎች ሕዝባቸውን ለመግደል፣ ለማሰቃየትና ለመጨቆን ፈቃድ እየጠየቁ እንደሆነ ነው የምቆጠረው ብለዋል፡፡

No comments:
Post a Comment