Monday, February 16, 2015

የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ እና የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ

ፌብርዋሪ 14, 2015 በኖርዌይ የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎና በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የድርጅቱ አባላቶች የተገኙ ሲሆን የአባላት ስብሰባው አስቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በኖርዌጂያን የሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 13፡30 ተጀምሮዋል።

ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ በ 24 ዓመት የወያኔ አረመኒያዊ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉት እና በየእስር ቤቱ በግፍ ለሚስቃዮ ንጹሀን ዜጐች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጹሎት በማድረግ ስብሰባውን ያስጀመሩት ሲሆን በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመበር አቶ ዮሐንስ አለሙ አባላቱን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግር አቅርበው የዛሬው የአባላት ስብሰባ ከሌሎቹ ጊዜያት በሁለት ምክንያቶች የተለየ መሆኑን ለተሰብሳቢው ገልፀዋል ይሄውም፦
1 የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60 ኛ ዓመት የልደት በአል የሚከበርበት ቀን በመሆኑና
2 የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዩጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የተመሰረተበትን 10ኛ አመቱ ላይ መገኘቱ እንደሆነ በማስረዳት ድርጅቱ በእነኚህ አስር ዓመታት ውስጥ ብዙ አመርቂ ስራዎችን እንደሰራና ቅንጅት ይዞለት የተነሳው አላማ እስከ አሁን ድረስ ይዞ በመጓዝ ላይ ያለ ድርጅት በመሆኑ ስለዚህም በድርጅታቸው ኩራት የሚሰማቸው መሆኑን በመግለፅ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ወጣቶች እና ሴቶች እየሰሩ ያለውን ስራ አድንቀው ወጣቶች ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው በመሆኑ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ትግላቸውን አጠንክረው መቀጠል እንዳለባቸው በማሳሰብ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌንና በወያኔ መንግስት በግፍ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችን በትግላችን እናስፈታለን በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
unnamed (1)

በመቀጠልም የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች የስድስት ወር የስራ ክንውን ረፖርት ለአባላቱ ያቀረቡ ሲሆን ከበርገን፣ ከስታቫንገር፣ እና ከትሮንዳይም የመጡ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የስራ ኃላፊዎች በስድስት ወር ውስጥ ስለሰሩት ስራዎች እና ወደፊትም ሊሰሩ ያቀዱትን ስራዎች ለአባላቱ በዝርዝር አስረድተዋል።

በወቅቱ ከአባላቱ የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ለጥያቄዎቹም በድርጀቱ ሊቀንበር በአቶ ዮሀንስ አማካኝነት ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል:: በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሚረዳቸው ድርጅቶችን በማስመልከት በድርጅቱ በተወከሉት ሠዎች አማካኝነት ስለድርጅቶቹ አላማ እና ድርጅቶች እየሰሩ ስላሉት ስራዎች ሰፋ ያለ ግምገማ አቅርበዋል።'

ግንቦት ሰባትን በመወከል ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቅርቡ ግንቦት 7 ከአርበኞች ጋር ውህደት እንደፈጠሩ በመግለፅ ውህደት ያስፈለገበትንና የውህደቱን ጠቀሜታ በመግለፅ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚለው ስምም አርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሚል መተካቱን በመናገር ድርጅቱን እየመሩ ያሉትን አመራሮች እነማን እንደሆኑ ለአባላቱ አስተዋውቀዋል ።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ እየደገፈ ያለውን የሰማያዊ ፓርቲ አላማ እና እየሰራ ያለውን ስራ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ያቀረቡት ደግሞ አቶ ተዘራ ሲሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ ከአረመኔያዊው የወያኔ መንግስት የተለየ ወከባ እንደሚደርስበትና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ አባላቶች በወያኔ እየደረሰባቸው ያለውን ጫና በመቋቋም ትግላቸውን  አጠናክረው በመቀጠል ላይ እንደሆኑ በማስረዳት ወደፊትም ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባላቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስለ አንድነት ፓርቲ አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ አቶ ዮሐንስ  ሲሆኑ እሳቸው በወያኔ መሰሪ ሴራ አንድነት ፓርቲ በመፍረሱ እንዳዘነኑና ነገር ግን ዘጠና ከመቶ የሚሆኑት የአንድነት አባላትም ሆነ አመራሮች ሠማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ጠቅሰው ይሄም እንዳስደሰታቸውና ለጊዜው አንድነትን መደገፋቸውን በማቆም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አላማ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ድርጅቶች ሠማያዊ ፓርቲ እና አርበኞች ግንቦት 7 ድርጅቶችን በመደገፍ እንደሚቀጥሉ አባላቱ በአንድነት ድምፅ ወስነዋል። ከዚህ በፊት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አንድነት ፓርቲን፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና ግንቦት ሰባትን ሲደግፉ መቆየታቸው ይታወቃል።

በመጨረሻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ የመዝጊያ ንግግር አድርገው የአባላት ስብሰባው 16፡30 ተጠናቋል።


ከአባላት ስብሰባው በመቀጠልም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን 60ኛ አመት የልደት በአል አከባበር ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን ዝግጅቱንም  በንግግር ያስጀመሩት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዮሀንስ አለሙ ሲሆኑ  ስለ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አጭር ንግግር በማድረግ ነበር ፕሮግራሙን ያስጀመሩት ።  በፕሮግራሙ ላይ የአንዳርጋቸውን ታሪክ የሚዳስስ አጭር ፊልም በወጣቶች ክፍል የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም አቶ  አንዳርጋቸው ፅጌ ማን ነው? በሚል በአንዳርጋቸው ህይወትታሪኩ ዙሪያ እና ለሀገሩ ያደረጋቸውን የትግል ተሞክሮዎች በቅርበት ከሚያውቋቸው ሰው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል። እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸውን የሚያወድሱና ስለጀግንነቱ የሚያወሩ የተለያዩ ግጥሞችም ቀርበዋል።

በመጨረሻም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ምስል የያዙ ኬኮች ከድርጅቱ ዋና ፅፈትቤት እና ትሮንድላንድ ቅርንጫፍ ፅፈትቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን በድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሁም በወጣቶችና ሴቶች ክፍል ተወካዮች የመልካም ልደት ኬኩ ተቆርሶ ስነስርአቱ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተደረሰው ላንቺ ነው ሀገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው በሚለው ዝማሬ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 22፡00 ተጠናቋል።

በመጨረሻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ወጣቶች ፕሮግራሙን በመዘጋጀትና

በመምራት ላደረጉት  አስተዋጾ በድጅቱ ና በስራ አስፈጻሚኮሚቴ ስም ምስጋና እናቀባለን!1

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ



Sunday, February 15, 2015

Gagging the media in Ethiopia – MWC News

February 15,2015
ethiopia-mediaNobody trusts politicians, but some governments are more despicable than others. The brutal gang ruling Ethiopia is especially nasty. They claim to govern in a democratic pluralistic manner, they say they observe human rights and the rule of law, that the judiciary is independent, the media open and free and public assembly permitted as laid out in the constitution. But the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) systematically violates fundamental human rights, silence all dissenting voices and rules the country in a suppressive violent fashion, that is causing untold suffering to millions of people throughout the country.
There is no freedom of the press, journalists are persecuted, intimidated and arrested on false charges, so too their families. All significant media outlets and print companies are state owned or controlled, as is the sole telecommunications company – allowing for unfettered Government monitoring and control of the Internet. Radio is almost exclusively state owned and, with adult literacy at around 48%, remains the major source of information. Where private media has survived they are forced to self-censor their coverage of political issues, if they deviate from “approved content”, they face harassment and closure.
In many cases journalists are forced to leave the country, some are illegally tried in absentia and given long prison sentences or the death penalty. Human Rights Watch (HRW) states in its detailed report ‘Journalism is Not a Crime,’which Ethiopia has more journalists in exile than “any country in the world other than Iran,” and estimates, “60 journalists have fled their country since 2010 while at least another 19 languish in prison.” More than 30 left in 2014, twice the number escaping in 2013 and 2012 combined, and numerous publications were closed down, revealing that the media situation and freedom of expression more widely is becoming more and more restrictive. “If they cannot indoctrinate you into their thinking, they fire you,” said a dismissed journalist from state-run Oromia Radio, summing up the approach of the ruling party to press freedom and indeed democracy as a whole.
With upcoming elections in May the media should be allowed to perform its democratic responsibility – revealing policies and the incumbent regime’s abuses, providing a platform for opposition groups and encouraging debate. However, the guilt ridden EPRDF government, desperate to keep a lid on the human rights violations it is committing, sees the independent media as the enemy, and denies it the freedom, guaranteed under the constitution, to operate freely.
Tools of control
Soon after the 9/11 attacks on the World Trade Centre in New York, President George W. Bush made his now notorious speech in which he reaffirmed Ronald Reagan’s 1981 declaration to initiate a worldwide ‘war on terror’, against terrorism and nations that “provide aid or safe haven to terrorism.” Bush’s understandable if hypocritical political statement of intent allowed regimes perpetrating terror like the EPRDF to impose ever more repressive laws under the guise of ‘fighting terrorism’ and ‘containing extremism’.
A year before the 2010 Ethiopian general election the government introduced a raft of unconstitutional legislation to control the media, stifle opposition parties and inhibits civil society: The Charities and Societies Proclamation introduced in 2009 decimated independent civil society, and created, Amnesty International (AI) says, “a serious obstacle to the promotion and protection of human rights in Ethiopia.” It sits alongside the equally unjust Anti­–Terrorism Proclamation (ATP) of the same year, which is the sledgehammer commonly used to suppress dissent and silence critical media voices both inside the country, abroad and on the Internet.
Overly broad and awash with ambiguity, the ATP allows for long-term imprisonment and the death penalty for so-called crimes that meet the government’s vague definition of terrorism, and allows evidence gained through torture to be admissible in court, which contravenes the United Nations Convention Against Torture, ratified by Ethiopia in 1994. In 2012 the government added the Telecom Fraud Offences Proclamation to its arsenal of repression, criminalizing “the use of popular voice over IP (VoIP) communications software such as Skype for commercial purposes or to bypass the monopoly of state-owned Ethio-Telecom.” Eight years imprisonment and large fines are imposed if anyone is convicted of “using the telecommunications network to disseminate a “terrorizing message” – whatever that may be.
The anti-terror legislation violates international law and has been repeatedlycondemned by Amnesty International and Human Rights Watch. As well a group of United Nations (UN) human rights experts, who in September 2014urged the ruling party “to stop misusing anti-terrorism legislation to curb freedoms of expression and association in the country.” The eminent group went on call upon the Government “to free all persons detained arbitrarily under the pretext of countering terrorism,” saying: “let journalists, human rights defenders, political opponents and religious leaders carry out their legitimate work without fear of intimidation and incarceration.” Their visit followed one made by members of the European Parliament’s Sub-committee on Human Right who visited Ethiopia in July 2013 when they pressurized the government to release journalists and opposition activists imprisoned under the ATP.
Wrapped in arrogance and paranoia the EPRDF disregarded these righteous demands as well as requests to allow a visit by the “Special Rapporteurs on freedom of peaceful assembly and association, on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment” to visit the country and report “on the situation of human rights defenders.” No doubt the people of Ethiopia would welcome such a visit; one questions the protocol that allows regimes like the EPRDF the right to deny such a request.
Keep quiet
The ATP has been widely used to punish troublesome journalists who criticize the government or publish articles featuring opposition members and regional groups calling for self-determination. Anyone who challenges the EPRDF’s policies or draws attention to the human rights violations taking place throughout the country are branded with the T word, intimidated and silenced.
The two most prominent journalists to be imprisoned are award-winningEskinder Nega and Reeyot Alemu Gobebo. Arrested at least seven times Nega is currently serving an 18 year sentence for doing nothing more than calling on the government to respect freedom of expression laws enshrined in the constitution (that the EPRDF themselves penned), and end torture in the country’s prisons. Reeyot Gobebo, winner of the 2013 UNESCO-Guilermo Cano World Press Freedom Prize, is currently serving a five-year jail term (commuted from 14 years after two of the charges were dropped on appeal), after being charged with a variety of unfounded, unsubstantiated terrorist related charges.
These two courageous professionals, HRW relates, have “come to symbolize the plight of dozens more media professionals, both known and unidentified, in Addis Ababa and in rural regions, who have suffered threats, intimidation, sometimes physical abuse, and politically motivated prosecutions under criminal or terrorism charges.” When an article critical of the government is published, writers or editors receive threatening phone calls and text messages (e-mails in my case) from government stooges. If publications and broadcasters persist in publishing such pieces they suffer persecution, arrest and closure.
The ERPDF’s paranoid desire to control everything and everybody inside Ethiopia is not restricted to the national media alone. Voice of America (VoA) and Deutsche Welle (DW), who both have a presence in Addis Ababa, are routinely targeted by the government, as is ESAT TV, a shining light of independent broadcasting in Amharic from America and Europe. Their satellite transmissions are regularly jammed, their staff and family members threatened and harassed; on 11th January 2015 the wife of Wondimagegne Gashu, a British Citizen, long time human rights activist and ESAT worker, was violently detained with her three young children for two days inside Addis Ababa airport. Before being deported security personnel threatened to kill her husband if he continues his associations.
The government also restricts access to numerous websites including independent news, opposition parties and groups defined by the government as terrorist organisations and political blogs. The required technology and expertise to carry out such criminal acts is supplied by unscrupulous companies from China and Europe; companies that should “assess [the] human rights risks raised by potential business activity, including risk posed to the rights of freedom of expression, access to information, association, and privacy.” In other words: behave in a responsible ethical manner.
State Terrorism
Freedom of the media and freedom of expression, sit alongside other democratic principles, like an independent judiciary, consensual governance, participation and freedom of assembly. Where these basic tenets are absent so too is democracyIf the state systematically crushes independent media and commits widespread human rights violations, as in Ethiopia, we see not a democratic government but a brutal dictatorship committing acts of state terrorism.
In HRW’s damning report on media freedoms within the country a series of commonsense recommendations are made that should be immediately enforced. Chief among these are that all journalists currently imprisoned be released; that the government immediately cease jamming radio and television stations and unblock all websites of political parties, media, and bloggers; that all harassment of individuals exercising their right to freedom of expression stops and that the regime repeal or amend all laws that infringe upon privacy rights.
By essentially banning independent media and making freedom of expression a criminal offense, the Ethiopian government is in gross violation of its own legally binding constitution as well as a raft of international covenants. All of which is of no concern to the ruling party who treat international law with the same indifference they apply to their own people. Pressure then needs to be applied by those nations with longstanding relationships with Ethiopia:
America and Britain come to mind as the two nations who have the biggest investment in the country and whose gross negligence borders on complicity. As major donor nations they have a moral responsibility to act on behalf of the people, to insist on the observation of human rights and the rule of law and to hold the EPRDF regime accountable for its repressive criminal actions.
– See more at: http://mwcnews.net/focus/analysis/49707-media-in-ethiopia.html#sthash.9ysGxWvn.dpuf

Saturday, February 14, 2015

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

February 14,2015

pg7-headerአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።
ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።
ያም ሆኖ ግን በምርጫ ላይ ያላቸው ተስፋ ፈጽሞ ያልተሟጠጠ ፓርቲዎችን በማክበርና ሥራቸውንም አስቸጋሪ ላለማድረግ ሲባል ከምርጫ 97 ወዲህ የነበሩ ብሄራዊም ሆነ ክልላዊ ምርጫዎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ዉጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አድርጎ አያውቅም ነበር። አሁን ግን የአገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ሁኔታዎች ይህንን የቆየ አቋም በሚያስቀይር መንገድ፤ የአገራችንን የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያካባቢውን ሰላም በሚጎዳ መልኩ ተቀይሯል። የሰሞኑ የወያኔ እርምጃዎች ትንሽ ተስፋ ያደርግ የነበረውን የዴሞክራሲ ወገንተኛ ተስፋም እምሽክ አድርጎ በልቶታል:: እየተቃረበ ያለው ዓይነት የፌዝ ምርጫ ወያኔ እንደ እንጄራ የራበውን የተቀባይነት እጦት ለአጭር ጊዜ ያስታግስለት ይሆናል እንጂ የሀገሪቱን እያደር እየተወሳሰበ የመጣ ችግር ለጊዜውም እንኳን የሚያስታግስ አይሆንም፤ ይልቁንም ጊዜው በገፋ ቁጥር ችግሩ መቋጠሪያ የጠፋው እየሆነ ይሄዳል::
የሁኔታውን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር የወቅቱን የአገራችን የፓለቲካ ሁኔታ በጥንቃቄ መርምሮ የሚከተሉት ግንዛቤዎች ላይ ደርሷል።
1. ህወሓት ብዙዎች እትዮጵያዊያን የተሰውላቸውን አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በመበተን የድርጅቶቹን ስምና ንብረት ለአገልጋዮቹ መስጠቱ፤ ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው የመራጭን ድምጽ መስረቅ ሳይበቃው የምርጫ ተወዳዳሪንም መዝረፍ መጀመሩን አመላካች ነው። ይህ ተግባር ህወሓት የምርጫ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪዎችንም እሱ ራሱ ለመምረጥ መወሰኑን ያሳያል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴራ ምርጫውን ከጅምሩ ጀምሮ አስቀድሞ እስከተወሰነለት መዳረሻው ድረስ ለምንም ዓይነት ያልተጠበቀ አጋጣሚ (በምርጫው ወቅት የሚደረጉትን ክርክር ተብዬዎች ጨምሮ) እድል ላለመስጠት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፤
2. ይህ እኩይ ውሳኔ በምርጫ ቦርድ ፊርማና አንደበት ቢነገርም ምንጩ የህወሓት ፓሊት ቢሮ መሆኑን የሚከተሉት ተግባራት ይጠቁማሉ፤
2.1. በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲገለጽ የተወሰነው እርምጃ ለማስመሰል ያክልም ቢሆን የህጋዊነት ሽፋን እንዲኖረው አለመደረጉ ውሳኔው ፍጹም እብሪተኛ በሆነ አካል መወሰኑን ያመለክታል። እንዲህ ዓይነቱ እብሪተኛ አካል ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ነው። ውሳኔውን ለማስፈፀም የነበረው ጥድፊያም ይህንኑ ያጠናክራል።
2.2. ለማስመሰያ ያክል እንኳን ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ፓሊስ የአንድነትና የመኢአድ ቢሮዎችን መውረሩ፤ ህወሓት አንድነትንና መኢአድን አጥፍቶ የድርጅቶቹን ስሞችና ንብረቶች ለሚፈልጋቸው ሰዎች ሰጥቶ በአስቸኳይ ለምርጫ ድራማው በፊት መስመር ሊያሰልፋቸው መወሰኑን አመላካች ነው። እንዲህ ዓይነት ከባድ ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ብቻ ነው።
2.3. ወደ ፈቃድ መንጠቅ ከመደረሱ በፊትም በሰማያዊ ፓርቲ፣ በአንድነትና በመኢአድ አባላት የደረሰው አረመኔያዊ ድብደባ፤ ንቁ የፓለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ዜጎች ላይ የሚደርሰው እስር፣ መሰወርና እና ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መገኘት መብዛት እነዚህን አገራዊ ፓርቲዎች የመበተን የፓለቲካ ውሳኔ መሰጠቱን አመላካቾች ናቸው።
3. ለጊዜው የፈቃድ ነጠቃና የንብረት ዘረፋ የተፈፀመው በአንድነትና በመኢአድ ላይ ቢሆንም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በየእለቱ እየጠነከረ የመጣው የአፈና እርምጃም በተመሳሳይ ፓርቲውን ወደማገድ አለዚያም ፈጽሞ መንቀሳቀስ ወደማይችልበት ደረጃ ሊያደርሰው ይችላል የሚል እምነት አሳድሯል። ሌሎች ፓርቲዎችም ከዚህ ህወሓት ካሰመረው የውሸት ጫወታ መስመር የመውጣት ዝንባሌ ቢያሳዩ ተመሳሳይ እርምጃ አይቀርላቸውም።
4. የህወሓት የወቅቱ የጥፋት ዒላማ ያነጣጠረው አንፃራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ መዋቅርና ማኅበራዊ መሠረት ባላቸው እና በአገራዊ አጀንዳዎቻቸው በሚታወቁ ፓርቲዎች ላይ መሆኑ፤ የወቅቱ የጥፋት ዘመቻ የኢትዮጵያ አንድነትን የማዳከምና ከፋፍሎ የመግዛት የህወሓት ትልቁ አጀንዳ አካል መሆኑን ያሳያል።
5. እራሱን በዘር ያደራጀዉና ኢትዮጰያ ዉስጥ ያለዉ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አደረጃጀት ከዚሁ እሱ ከተደራጀበት የዘር አደረጃጀት ዉጭ እንዲሆን በፍጹም የማይፈቅደዉ የወያኔ አገዛዝ፤ መጣፊያው ሲያጥረውና ወደ ማይቀረው ውድቀቱ ሲያመራ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አገራችን ኢትዮጵያን በቀላሉ ወደማትወጣዉ የዘዉግ ግጭት ዉስጥ አስገብቶ ዘመናት ያስቆጠረዉ አንድነቷ እንዲፈረስ በትጋት እየሠራ መሆኑን ያሳያል።
6. ከመለስ ዜናዊ ሞት ወዲህ ህወሓት ከሁሉን ጠቅላይ (totalitarian) አገዛዝ ወደ ፋሽስታዊ ቡድንነት ያሽቆለቆለ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ህወሓት ዘረኛ፣ ጠቅላይና ፈላጭ ቆራጭ ጨቌኝ በመሆኑ ፋሽስት ብለነዋል። ሆኖም በታሪክ የሚታወቁ ፋሺስታዊ አገዛዞች ከፍተኛ ብሄራዊ ስሜት የነበራቸው ሲሆን የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ግን ብሔራው ስሜት አልባ መሆኑ ልዩ እና የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን የህወሓት መሪዎችንና ጥቂት ሌሎች አጫፋሪዎቻቸውን የያዘ ለጊዜው አስተባባሪ መሪ የሌለው ሆኖም ግን የጦር ሠራዊትን፣ የስለላ መዋቅሩንና ፓሊስን ተቆጣጥሮ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ይህ አስኳል የለሽ ፋሽስታዊ ቡድን መሆኑ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን ተደላድሎ መሪ እንዲፈጥር ከተፈቀደለት አገራችንን የከፋ መከራ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል።
ከላይ በአጭሩ ከተራ ቁጥ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን በማገናዘብ በግንቦት 2007 ሊደረግ የታቀደውን አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሴራ ምርጫን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውሳኔዎችን አስተላልፎ ከዚህ የሚከተሉት ጥሪዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርቧል።
1. በምርጫ 2007 መሳተፍ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ ፋሽስታዊውን ቡድን የሚያጠናክርና የኢትዮጵያን ሕዝብ የወደፊት ዕድል የሚገድል በመሆኑ፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት፤ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት ግድ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ከአሁኑ ከዚህ የይስሙላ ምርጫ ዉጭ ዓይኖቻቸውንና ሙሉ ጉልበታቸዉን በሌሎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት በሚያፋጥኑ አማራጮች ላይ እንዲያሳርፉ ጥሪ ያደርጋል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ዓይን ያወጣ የሴራ ምርጫ ይልቅ መብቱን፤ ነፃነቱንና እኩልነቱን በሚያፋጥኑለት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመፅ የትግል አመራጮች ላይ እንዲሳትፍ ለመላው ያገሪቱ ሕዝብ ጥሪ ያስተላልፋል። ህወሓት ማኅበረሰባችንን ለመከፋፈልና ለማባላት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ በጋራ እንድናከሽፈው ወገናዊ ጥሪ ያስተላልፋል፤ “አንከፋፈልም፤ ተከፋፍለንም አንጠቃም“ እንበል ይላል::
2. ህወሓትን ማስወገድ የሚቻለው በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ በመሆኑ፤ ከሁለቱ አንዱንም አለመያዝ ሌላ ሰው ታግሎ ነፃነቴን ያቀዳጀኝ እንደማለት የሚቆጠር በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአፋጣኝ ከእነዚህ ሁለት የትግል ዘርፎች ዉስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ አበረክታለሁ በሚለው የትግል ዘርፍ ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል።
3. አርበኞች ግንቦት 7፣ በሁለቱም የትግል ዘርፎች ድርጅታዊ መዋቅሩን እያሰፋና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በስፋት እንዲቀላቀሉት፤ በኅብረት እንድንቆም እና የህወሓትን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንድናፋጥን ጥሪ ያደርጋል::
4. ያለንን አቅም በሙሉ ህወሓትን በማስወገድ ላይ ካዋልነው አንድ ጠንክር ያለ ሕዝባዊ አመጽ አገዛዙን ሊያፍረክርክው የሚችል በመሆኑ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ሊውል ታስቦ የነበረው የሰው ኃይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብና እውቀት ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀሻነት እንዲውል ጥሪ ያደርጋል።
5. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም በ2007 ምርጫ ላይ ጊዜና ንብረት ከማባከን ይልቅ በአንድ ልብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ያደርጋል። ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የተውጣጣ አካል የዚህን ጥሪ ተፈፃሚነት እንዲከታተል ቢደረግ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል ብሎ ያምናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ወያኔ ከትግራይ ተወላጆች ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡

February 14,2015
Supporters of the ruling EPRDF party and PM Zenawi chant slogans after he addressed them at the Meskel Square in Addis Ababa
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ምንጮቻችን አስረድተዋል፣ ጥር 24 /2007 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ… ካድሬዎች ተላላኪ የሆነው ይርጋ የተባለ የትግራይ ተወላጅ የትግራይ ተወላጆችን ብቻ በመስብሰብ ለምን ተቃዋሚ ድርጅቶችን ትደግፋላችሁ፥
ተቃዋሚ ድርጅቶች ከፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው በቅርቡ እንኳን የሰማያዊና የአንድነት ድርጅቶች አምስት ፖሊሶችን ደብድበውብናል ስለዚህ አትደግፏቸው እያለ መናገር በጀመረበት ጊዜ ህዝቡ በበኩሉ ፖሊሶቻችን ተደብድበውብን ከማለት ይልቅ ለምን በፖሊስ የተደበደቡትን ወገኖቻችን የማትናገሩላቸው አይደለም አንተ ሃላፊህ እንኳን አይፈታውም ሊፈታው አይችልም ይሄ ደግሞ ያንተ አቅም ስላልሆነ ከአቅምህ በላይ አትናገር እንዳሉት ታውቋል፣ 
ተሰብሳቢዎች ጨምረውም ቅንና ቢኖርህ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ስለሚታከሙት ከ11 በላይ ንፁሃን ሲቪል ዜጎች እና አፍናችሁ ስለወስድዋቸው በተናገርህ ነበር ያለአቅምህ መልዕክት ይዘህ ልታታልለን አትሞክር የሚል ሃይለኛ ተቃውሞ እንዳጋጠመው ለማወቅ ተችሏል::

Friday, February 13, 2015

ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም (ቢኒያም ግዛው ከኖርዌይ ኦስሎ)












አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል።
                        ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። ቀደምት ተብላ እንደመጠራቷም ሀገሪቷ ከ100 አመታት በፊት በቱርክ ግዛት ስር ሆና ደማስቆን እና የቤሩትን የወደብ ከተሞች የሚያካልል ሀዲድ ተዘርግቶ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠቃሚም ሆናለች። ከዚያም በመነሳት ነጻነቷን አውጃ ራስዋን ማስተዳደር ስትጀምር የዛሬ 60 አመት በፊት 1956 እ.ኤ.አ ሞደርን ሲኤፍኤስ ፓሴንጀር ትሬን በማለት አዲስ መዋቅር አበጅታ እስከ 2012 ተገልግላበታለች።አሁን ያ ያላት መልካም ገጽታ እና ታሪኳ እንዲሁም ከሁሉ በፊት ባብር ነጂ መሆናዋ ከመሰባበር አላዳናትም።

                   የሶርያ ፕሬዘዳንት ባሻር አል አሳድ በአንባገነንነት ምድሪቷን መግዛት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ከ2011 ዓ.ም ወዲህ አሁን ድረስ መልኩን ቀያይሮ እና የተለያየ ስም ይዞ ታልቅ እልቂት ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ220,000 ንጹሀን ዜጎች በላይ ለህልፈተ ሞት ያበቃ ሲሆን 11 ሺህ 420 ህጻናት መገደላቸው እና ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የሆነ ዜጋ ሀገሩን ጥሎ በየጎረቤቱ ጥገኛ እና ስደተኛ ሲሆን የፍትህ የዲሞክራሲ ረሀብ እና ናፍቆት እንጂ መንገድ፣ ፎቅ፣ ባቡርና ሀዲድማ ነበራቸው። ዴሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ እና ስርዓት ምድሪቷን እስካልተቆጣጠራት ድረስ ሁሉም ነገር ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው።

ስለ ኢትዮጵያ ደግሞ እናንሳ ። በ1895 ዓ.ም አንድ በደረት ላይ የሚንጠለጠል የምድር ባቡር ማሳሰቢያ ባጅ ነበር። በአንዱ ገጽ የአጼ ምኒልክ ምስል በሌላው ደግም 1895 የምድር ባብር ማሳሰቢያ የሚል ተቀርጻበታል። የዛሬ 112 ዓመት በፊት መሆኑ ነው።በአጼ ምኒልክ ውሳኔ የመሰረት ድንጋዩ ተቀምጦ የስዊዝ ተውላጅ በሆኑት ኢንጅነር አልፍሬድ ኢልግ http://en.wikipedia.org/wiki/Alfred_Ilg እገዛ መሰረት የሀዲድ መሰመር ግንባታው እኤአ በ1893ተጀምረ። ከ24 ዓመት በኃላ ስራው ተጠናቅቆ በ1917ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ባብር ተነዳ። ይህም የዛሬ 98 ዓመት መሆኑ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያ ምን ያህል ቀደምት የስልጣኔ ከፍታ እንዳላት ያስረዳል።በአፍሪካ ካሉት ቀደምት የባቡር ተጠቃሚዎች መሀል 1ኛ)ግብጽ በ1856 ዓ.ም 2ኛ) ደቡብ አፍሪካ በ1897 ዓ.ም 3ኛ) ሱዳን በ1898ዓ.ም 4ኛ)ኬንያ በ1901ዓ.ም 5ኛ)ታንጋኒካ በ1905 ዓ.ም 6ኛ) ሴራሊዮን 1909ዓ.ም 7ኛ) ናይጄርያ 1912 ዓ.ም 8ኛ) ኢትዮጵያ በ1917 ዓ.ም በሀገራቸው ላይ ባቡርን ለህዝብ ጥቅም ካዋሉት የመጀመራዎቹ ተርታ ትሰለፋለች።

                       የዛሬው ዘመን ላይ ደርሰን ባቡር እና ሀዲዱ ብርቅ ሆኖ ባብር! ባብር !ባቡር እየተባለ ጡርንበኞች ሲጮሁ መስማት ምን ያህል ከፍትህ እና ከሰላም ይልቅ ግኡዝ ነገር አእምሮአቸውን እንደጨመደደው ልብ ይሏል። በምድሪቷ ላይ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት የተከሰከሰው የአባቶች አጥንት ለባቡር ለፎቅ እና ለመንገድ አልነበረም። ይልቁንም ለፍትህ ለሉዐላዊነት ለነጻነት እና ለአንድነት ነበር። አሁንም ያ አጥንት ትውልዱን ይወቅሳል። ባቡርማ ብርቅ አይደለም! ኢትዮጵያም ነበራት። ሶርያም ኢራቅም ነድታለች ዳሩ የህዝብ ረሀብ ነጻነት ሆነ እንጂ። ሶርያ ያላት ህንጻ፣መንገዷ፣ባብሯ እና ሀዲዷ ከመበታተን ከመሰባበር አላዳናትም።የሀገር ሀብት ዲሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ የሆነ እንደሆን ብቻ ሀገር ይለማል። ሀብት እና ንብረታችን ነጻነት እና አንድነታችን ነው። የድል ክንዳችን መያያዛችን እና መቀባበላችን ብቻ ነው።

                    በወያኔ አለንጋ ደንዛዛ እንዲሆን የተመተተብት ትውልድ አፍዝ አደንግዙን ረግጦ ስለኢትዮጵያው ሊነቃ የሚገባበት ዘመን አሁን ነው። ባቡሩና ሀዲዱ መጥፎ ነው ለማለት አይደለም ስላስፈለገም ነው ከ98 ዓመት በፊት የተገነባው። ድሮስ ወያኔ የራሱን ሆድ ሲያጭቅ ድሆች ከፍርፋሪው ባቡር እና ሀዲድ እንደቡችላ ቢወረውርላቸው ምን ይከፋል። ይህ እኮ የወያኔ ካዝና ውድቅዳቂ እና ፍርፋሪ ነው።ፍርፋሪ ደግሞ ሆድ አይሞላም እንዲያውም ቢያስርብ እንጂ።ይህ ማታለያ  ወያኔ ሀፍረቱ እንዳይታይበት የለበሰው ብጣቂና ቅዱስ የመሰለበት ማስመሰያው  ነው። ተኩላ በበግ ለምድ እንዲከለል ሰይጣንም አውሬነቱን ለመደበቅ ራሱን እንዲከልል ወያኔም ነፍሰ ገዳይነቱን ለመደበቅ አዛኝ መስሎ የማይበስል ቅቤ ያነጉታል። ለኢትዮጵያ እድገት እና ልማት ለሀገሪቷ ፍቅር ያለው መሪ ህዝብን ነጻ ከማድረግ እና የእኩልነት መንፈስ በምድሪቷ ላይ እንዲሰፍን ከመትጋት ይጀምራል ። ነጻነት የሌለው ህዝብ ፎቅ ላይ ቢወጣ በባቡር ቢሳፈር ዳሩ እስረኞቹ ተሳፍረው እየሔዱ ነው ቢባል እንጂ ሌላ የማታለያ  መጠርያ ቢሰጠው በመጫኛ መጣል ይሆናል። እንዶሮዋ።

                      ዳሩ በግኡዛን ቁሳቁስ ብናምር ብንቆጠቆጥ ማን እርሱን ይጠላል። ግን እርሱ ሐብት አይደለም። አንድ ቀን ይከዳል። ምድሪቷ ድንገት ቢያስነጥሳት አሊያም ብትንጠራራ ከበላይዋ በብድር ገንዘብ ያንጋጠጠው ፎቅም በሉት ባቡር አሊያም ሌላ ግኡዝ የፍርስራሽ ቁልል ሁኖ ለመዛቅ ዕዳ ይሆናል። ስለዚህ ስለብልጽግና ስናወራ ስለ ገንዝብ ካወራን ስተናል ማለት ነው። ገንዘብ ኖሮህ ነጻነት ከሌለህ ፎቅ ገንብተህ በየደቂቃው የወያኔ አባት በጣረ ሞት መንፈስ እየመጣ ካስጨነቀህ ከዚህ በላይ ምስኪንነት የለም። ኢትዮጵያ በለጸገች አሊያም ብሩህ ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሎ ወያኔ ራሱን በራሱ ቢያንቆለጳጵስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የማባበያ እና የማታለያ ባዶ ዲስኩር ፊቱን ሊመልስ እና ሊነቃ ግድ ነው።

                       የሀገር ሀብት ፍትህ፣አንድነት፣እኩልነት፣ እና ለአንዲት ሀገር በአንድ ክንድ ለሀገር ሉአላዊነት የቆመ አንድ ህዝብ እንጂ ብሩም ወርቁም ነጻ ባልወጣ ሀገር አያምርም! አያደምቅም! የውሸት ነው። በአዲስ አባባ ላይ ብቻ የታየው ብልጭልጭታ ህጻኑ እንዳያለቅስ የተሰጠው ማታለያ ይመስላል። ኢትዮጵያ አዲስ አባባ ብቻ አይደለችም ።

ከቤት እንሰሳት ጋር የውሀ ጥሙን ለመቁረጥ ወደወንዝ የሚርደው ህዝብ፣ ዛፍ ስር በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ወጉ እንዳይቀር ሀ ሁ ሂ . . . እያለ ፊደል የሚቆጥረው፣ ለቀዶ ጥገና የ2 አመት ቀጠሮ የሚጠብቁ ታማሚዎች፣በየክፍለሀገራቱ ከልጅነት እስከእውቀት በበጋም በክረምትም መጠለያ ሳይኖራቸው በየጥጋጥጉ ቆሼ ተራ እየተመገቡ ያደጉት ሌላም ቢተረክ ጌዜ የማየበቃው ቁርቁዝና ከሁም በላይ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ እውነቱን እንዳይናገር የታፈነ እና የተለጎመ የታሰረ አንደበት የተጠራቀመባት ምድር ናት ኢትዮጵያ የሚትባለው። ይህች ናት በወያኔ የተቀረጸችው ኢትዮጵያ። ስለዚህም ነው አሁን የመንቃት ጊዜ እንደሆነ የምንናገረው። ኢትዮጵያውያንን እንደ ህጻን በብልጭልጭ ነገር የማታለል የወያኔ ዘመን ያክትም። ሀብታችን ባቡርና ፎቅ ሳይሆን አንድነት እና እኩልነታችን ነው። በመጀመሪያ ነጻነት!!!

እናቸንፋለን !!!
Biniam Gizaw (Norway) 

“ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”

February 13,2015

የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም የካቲት 3/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉን የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሰልፉ ወቅትም ነዋሪዎቹ መንግስት ለአካበቢው ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ 10 ከተሞች ላይ መብራት በራሳቸው ገንዘብ ማስገባታቸውን፣ ትምህርት ቤቶችን ራሳቸው እንደሰሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን የተዘረጋው በህዝቡ ወጭ መሆኑን፣ መንግስት ሰራሁት ያለው ውሃ ከሶስት ሳምንት በኋላ መበላሸቱ ሙስና እንደተበላበትና እንዳልተሰራ እንደሚያምኑ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሰልፈኞቹ “ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል፣ ስራ አጥተው የሚሰደዱትን ልጆቻችን መንግስት ህገ ወጥ ስደተኛ ሊላቸው አይገባም፣ ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር፣ መንግስት ከምባታን የሚያውቀው በስም ብቻ ነው፣ ተንቀናል፣ መብታችን ለማስከበር እንታገላለን፣ ….” እና የመሳሰሉትን መፈክሮች እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ የተገኙ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዳይገኙ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የመንግስት ሰራተኞችም ሰልፉን መቀላቀላቸውንና በአጠቃላይ ከ20 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሰልፉ መሳተፋቸውንም አቶ ኤርጫፎ ገልጸዋል፡፡
ሰልፉ የተደረገው በከምባታ ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመምጣቱና የደኢህዴን ባለስልጣናት ችግሩን ለመቅረፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የሚፈጸመውን በደል ለማሰማት ሲሆን የተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ ራሱን በማስተባበር የጠራው መሆኑም ተገልጾአል፡፡ 

Wednesday, February 11, 2015

አበበ ገላው በአባዱላ ገመዳ 2 የውሸት ዲግሪዎች ግዢ ዙሪያ ማስረጃዎችን ለቀቀ

February11,2015
aba dula

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሃሰት ዲግሪዎችን ከአሜሪካና አውሮፓ እንዲሁም ከቻይና እየገዙ እንደሚጠቀሙ በተደጋጋሚ እየተጋለጠ መሆኑ የሚታወስ ነው;; አበበ ገላው የዛሬ አንድ ወር ገደማ የዶ/ር ኮንተንጢኖስ በርሀን የሃሰት ዲግሪዎችን ያጋለጠ ሲሆን አሁን ተረኛው አባዱላ ገመዳ ናቸው ብሏል::

“ክቡር አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ አሜሪካ ሴንቸሪ ከሚባል የዲግሪ ወፍጮ ቤት የሃሰት ዲግሪዎች ገዝተው ጥቅም ላይ ማዋላቸው ተረጋገጠ” ሲል በፌስቡክ ገጹ ያስታወቀው አበበ ገላው ማስረጃዎቹን ዛሬ ለቋል::

አባ ዱላ ገመዳ የባችለር ዲግሪያቸውን እና የማስተር ኦፍ አርት ዲግሪያቸው ከአሜሪካው ሴንቸሪ ኮሌጅ በ2001 እና በ204 የገዙ ሲሆን ከ እንግሊዙ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲም ማስተር ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ታውቋል::

አባዱላ በውሸት ዲግሪዎች የ80 ሚሊዮኑን የውሸት ፓርላማ ቁጭ ብለው ይመራሉ:: የኦሮሚያን መሬቶች ቸብችበዋል እየተባሉ የሚወገዙት እኚሁ ባለስልጣን በሃብት ደረጃም የሚወዳደራቸው ባለስልጣናት የሕወሓት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ይነገራል::

(አዲስ ቮይስ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የሆኑት አባዱላ ገመዳ በኢንተርኔት ያለምንም ትምህርት ዲግሪ በመሸጥ ከሚታወቅ አንድ የዲፕሎማ ወፍጮ ቤት (diploma mill) የሃሰት ዲግሪዎችን ገዝተው መጠቀማቸውን አዲስ ቮይስ አረጋገጠ።

አፈጉባኤው የባችለርስ ዲግሪ እ.ኤ.ኤ በ2001 እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪ በ2004 አሜሪካን አገር በሚኖረውና አሊ ሚርዛኢ በሚባል ኢራናዊ ከሚንቀሳቀሰው “አሜሪካን ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ” (ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ) ያለምንም ትምህርት መግዛታቸው በመረጃ ተረጋግጧል። አባዱላ ሁለቱንም ዲግሪዎች የህዝብ አስተዳደር ትምህርት ተምረው አንዳገኟቸው ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን ይህንንም በፓርላማ ድረገጽ፣በፌስቡክ፣ ዊኪፔድያ፣ በመንግስትና በግል የመገናኛ ተቋማት በይፋ ታትሞ እንዲሰራጭ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቻይና መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በወታደራዊ አመራር የባችለርስ ዲግሪ እንዳገኙ በህይወት ታሪካቸው ላይ በይፋ ያሰፈሩት አባዱላ እንዲህ አይነት ዲግሪም ይሁን ትምህርት ከቻይና የትምህርት ተቋም አለማግኘታቸው ታውቋል።

ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ከማንም እውቅና ያልተሰጠው ሲሆን አሊ ሚርዛኢ በዋነኛነት ከቤቱ የዲግሪ ሽያጭ እንደሚያከናውን አዲስ ቮይስ በምርመራው ከማረጋገጡም በላይ ምርመራውን ደንበኛ መስሎ ላካሄደው ጋዜጠኛ አበበ ገላው የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪዎችን በ4000 ዶላር ሊሸጥለት ሞክሯል። ይህንንም ህገወጥ የዲግሪ ሽያጭ የሚያረጋግጡ በርካታ የኢሜይልና የሰነድ መረጃዎች ጋዜጠኛው እጅ ገብተዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት የህወሃቶች ቁንጮ ምሁራን ተደርገው ይቆጠሩ ከነበሩት አንዱ ቆንስጣንጢኖስ በርሄ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ከሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ገዝተው እራሳቸው በዶክተርነትና በፕሮፌሰርነት መሾማቸው መጋለጡ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ የሃሰት ዲግሪና ሰርተፍኬት ተጠቅሞ ለራስም ሆነ ለሌሎች ጥቅም ማግኘትና ማስገኘት በማጭበርበር ወንጀል የሚያስከስ ስና እስከ አንድ አመት እስር የሚያሰቀጣ ድርጊት ነው።
የሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ከዚህ በፊት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም ተደርሶበት በባለቤትነት ሲመራው የነበረው የሃዋይ ቢዝነስ ኮሌጅን እኤአ 2007 እንዲዘጋ ተደርጓል።

በኢፌዲሪ ህገ መንግስት መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛው የስልጣን አካል ሲሆን አፈጉባኤው ዋነኛው ህግ አውጭ ተደርጎ ይቆጠራል። የዛሬ አራት አመት አፈጉባኤ ሆነው የተሾሙት አባዱላ ገመዳ (ሚናሴ ወደጊዮርጊስ) ትምርታቸው ከ8ኛ ክፍል አቋርጠው የደርግ ወታደር ሆነው የነበር ሲሆን በኤርትራ በሻቢያ ተማርከው የነበረ ሲሆን በህወሃትና በሻቢያ መካከል በተደረገ ስምምነት መሰረት ከእነ አቶ ኩማ ደመቅሳ (ታዬ ተክለሃይማኖት) ጋር ለህወሃቶች ተላልፈው ከተሰጡ በሁዋላ የኦህዴድ መሪና መስራች እንዲሆኑ ተደርጓል።

የእነ አባዱላን ዲርጊት አሳፋሪ ሲሉ የገለጹት እውቁ ጋናዊው ምሁር ፕሮፌሰር ጆርጅ አይቴ እንዲህ አይነት እርካሽ የማጭበርበርና የማስመሰል ድርጊት የስርአቱን ንቅዘት ፍንትው አድርጎ አንደሚያሳይ ገልጸዋል። ፕሮፈሰሩ ተጠያቂነት የሌለው ህገውጥነት የአንባገነኖች ባህሪ መሆኑን አስገንዝበው አጭበርባሪ የስልጣን ጥመኞች ለውጥ ፈላጊ በሆነው አዲስ ትውልድ መተካት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። አይቴ አገር ለመምራት የምያስፈልገው እውቀት እንጂ ዲግሪ አይደለም ብለዋል። “ዲግሪ መግዛት ይቻላል፣ እውቀት ግን ፈጽሞ አይገዛም” በማለት የእነ አባዱላን ድካም ከንቱነት ጠቁመዋል።

የቀድሞው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር ዴታ የነበረው ኤርምያስ ለገሰ በበኩሉ አባዱላ በራስ መተማመን የሌለው የሃሰት ስብእና በህወሃቾች የተፈጠረለት ግለሰብ በመሆኑ ያንን በዲግሪ ጋጋታ ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት አካል ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ሰንዝሯል።

በርካታ ዜጎች ያለምንም ወንጀልና ጥፋት ለበርካታ አመታት ያለፍርድ በእስር በሚሰቃዩባት ኢትዮጵያ እነ አባዱላ በሃሰት ዲግሪ አገር ሲመሩ ማየት ህዝቡን የበለጠ ለለውጥ ሊያነሳስው ይገባል ሲል አስተያተቱ ሰጥቷል።
—-
ተያያዥ መረጃዎች:
Abadula Gemeda’s official biography on Ethiopia’s parliament website (screenshot)
http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/02/Abadula-Gemeda-par.pdf
House of People Representative: Abadula biography
http://www.hopr.gov.et/web/guest/higherofficial
Ethiopia: Abadula Gemeda, Speaker of the Parliament (Addis Fortune)
http://allafrica.com/stories/201309161711.html
Facebook official page: Honorable Abbaaduula Gammadaa
http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/02/Abadula-facebook-official.pdf
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38893#sthash.B3HTRC52.dpuf

Tuesday, February 10, 2015

የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍል ጥለው መውጣታቸው ተገለጸ

February 11.2015
• ‹‹የተማሪዎች ጥያቄ የእኛም ጥያቄ ነው›› መምህራን
ዳይሬክተራችን ያለ አግባብ ተነስቶብናል ያሉ ዓለም ባንክ አካባቢ የሚገኘው የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍል ጥለው ከግቢ መውጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዳይሬክተራቸው ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ባለመመቸቱ ከቦታው እንደተነሳ የገለጹት ተማሪዎቹ ዛሬ የካቲት 2/2007 ዓ.ም ጠዋት ላይ ‹‹በዳይሬክተሩ ጉዳይ እንድታነጋግሩን እንፈልጋለን፡፡ እኛ የምናውቀው ምንም ስህተት እንደሌለበት ነው፡፡›› ብለው ሲጠይቁ የትምህርት ቤቱ ስራ አስኪያጅ ‹‹ስለዚህ ጉዳይ እናንተ አያገባችሁም፡፡ ከፈለጋችሁ ተማሩ፡፡ ካልፈለጋችሁ ለቃችሁ መውጣት ትችላላችሁ፡፡›› እንዳሏቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ መምህር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተለይ የ7ኛ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥያቄያቸው ካልተመለሰላቸው መማር እንደማይፈልጉ በመግለጻቸው በሩ ተከፍቶ ከግቢ እንዲወጡ ተደርገዋል ተብሏል፡፡ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ግቢ ወጥተው ውጭ መቆማቸው ተከትሎም ግጭት ይፈጠራል የሚል ስጋት እንደተፈጠረ መምህራኑ ገልጸዋል፡፡
‹‹ርዕሰ መምህሩ ከተማሪዎችና ከመምህራን ጋር ተግባብቶ በመስራቱ ለትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎች ስላልተመቸ እንጅ ያጠፋው ጥፋት የለም፡፡ የተማሪዎች ጥያቄ የእኛም ጥያቄ ነው፡፡ ሆኖም የርዕሰ መምህሩ ጉዳይ ብቸኛ ችግራችን አይደለም፡፡ ትምህርት ቤቱ በበርካታ ችግሮች የተተበተበ፣ ለመምህራንና ተማሪዎች የማይመች ትምህርት ቤት ሆኗል፡፡›› ሲሉም መምህራኑ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡

Monday, February 9, 2015

Ethiopia refuses to allow access to imprisoned British citizen

February 9,2015































Ethiopia has refused to allow a delegation of parliamentarians to visit a British dissident facing the death penalty in the African country.

Andy Tsege, who is the secretary-general of a banned Ethiopian opposition movement, was sentenced to death at a trial held in his absence in 2009.  He was travelling from Dubai to Eritrea last June when he disappeared during a stopover in Yemen, in what campaigners regard as a politically motivated kidnapping. Weeks later, he emerged in detention in Ethiopia.

A delegation led by Jeremy Corbyn, Mr Tsege’s constituency MP, was to visit Ethiopia in a bid to secure his release. But the trip was abandoned after a meeting with Ethiopian ambassador Berhanu Kebede in London last week.

Mr Corbyn told The Independent: “We had made plans to go and see him next weekend and they said we would be refused admission to the detention facility.”

Lord Dholakia, the vice-chairman of the all-party parliamentary group on Ethiopia, who was due to travel out with Mr Corbyn, said it was made clear that they would not be welcome. Mr Corbyn is demanding that the Ethiopian government allows Mr Tsege’s lawyer, Clive Stafford-Smith, the director of Reprieve, to visit him and will raise the issue in the Commons this week. The Ethiopian embassy in London has accused Mr Tsege – who came to Britain as a political refugee in 1979 – of being a member of a “terrorist organisation” which wants to “overthrow the legitimate government of Ethiopia”.

A spokesman for the Ethiopian embassy said: “The ambassador advised the parliamentarians that there was no need for them to go to Ethiopia as the case is being properly handled by the courts.”
Last night, Yemi Hailemariam, Mr Tsege’s partner and mother of their three children, accused the ambassador of being “a mouthpiece for his bosses who have no regard for basic human rights”. Mr Tsege’s family will go to Downing Street today – which is his 60th birthday – to hand in a petition calling on David Cameron to demand his return. It can also be revealed that the Foreign Office minister Tobias Ellwood broke a promise to Mr Tsege’s family that his case would be raised during the African Union summit in Ethiopia last month.

Mr Ellwood had pledged that senior officials would raise the case. But in an email sent to Ms Hailemariam last week, a government official admitted: “Access to Ethiopian ministers is extremely limited during the summit and so it wasn’t possible to have a bilateral meeting with senior officials who might have influence over the case.”

A spokesman for the Foreign Office said: “We remain deeply concerned about Ethiopia’s refusal to allow regular consular visits to Mr Tsege and his lack of access to a lawyer, and are concerned that others seeking to visit him have also been refused access.”
source the independent

ወያኔ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት ለጠየቁ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላትን ፈቃድ ከለከለ::

February9,2015

- የወያኔ ባለስልጣናት የእንግሊዝ የፓርላማ ቡድን ልኡካን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እንዳይጎበኙ ፈቃድ መከልከላቸውን ከሎንዶን ተሰማ::አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ከየመን ሰንአ አየር መንገድ ታፍነው በአዲስ አበባ የተለያዩ የማሰቃያ ቦታዎች ከፍተኛ ቶርች ሲፈጸምባቸው ቆይቶ በዚህ ሳምንት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንደተዘዋወሩ ተጠቁሞ ነበር::
በጀርሚ ኮርቢን የሚመራው የእንግሊዝ የፓርላማ ቡድን ልኡካን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ አቶ አንዳርጋቸው የሚለቀቅበትን ጉዳይ ለመነጋገር እቅድ አድርገው የነበረ ቢሆንም በእንግሊዝ የወያኔ ኤምባሲ አምባሳደር ብርሃኑ ከበደ ከሎንዶን ከልኡኩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ጉዞው እንደተሰረዘ ታውቋል::
ወደ አዲስ አበባ ሄደን አንዲን ለመጎብኘት በሚቀጥለው ሳምንት ያሰብነው ጉዞ በባለስልጣናት እውቅናና ፍቃድ ባለማግኘቱ ልንሰርዘው ተገደናል ሲሉ የልኡኩ መሪ ተናግረዋል::ሎርድ ዶላኪያ በእንግሊዝ ፓርላማ የፓርቲዎች ሕብረት የኢትዮጵያ ጉዳይ ምክትል ሊቀመንበር ከሚስተር ኮርቢን ጋር ሊያደርጉት ያሰቡት ጉዞን አስመልክቶ አለመፈቀዱን ተቃውመውት ግልጽ የሆነ ሂደት እንዲኖር የጠየቁ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ጠበቃ ክሊቭ ስታፎርድ ስሚዝ አንዳርጋቸውን እንዲጎበኙ እንዲፈቀድ አጥብቀው የጠየኡ ሲሆን በዚህ ሳምንት ጉዳዩን በፓርላማ እንደሚያነሱት ገልጸዋል::
የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወይዘሮ የምስራች ሃይለማርያም በእንግሊዝ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ እና አምባሳደር በሰብአዊ መብት ገፈፋ የሚያደርጉ አለቆቻቸው የገደል ማሚቱ ሆነው ያገለግላሉ ሲሉ ተችተዋል::በለንደን ዳውን ስትሬት የሚከበረው የአቶ አንዳርጋቸው የ60ኛ አመት የልደት በአል ለማክበር እና አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የተሰበሰበውን ፊርማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ካሜሮን ይሰጠሉ::ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቶብሊስ ኢልውድ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ ንዝህላል መሆናቸውና በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ አለማንሳታቸው ቃላቸውን በማጠፋቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ሲሆን ባለፈው ወር በእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ዲፕሎማቶች መካከል ከፍተኛ አተካሮ ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል::የእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ እንዳሉት የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች የፓርላማ አባላቱን የጠበቃውን እና የአማካሪእን ጉብኝት መከልከላቸው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል::
ሚኒሊክ ሳልሳዊ

Sunday, February 8, 2015

ለወያኔ ዉንብድና መልሱ ህዝባዊ እምቢተኝነትና ህዝባዊ አመጽ ነዉ!

February 8,2015
pg7-logoዘረኞቹ የወያኔ መሪዎ የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ጨብጠዉ በኖሩባቸዉ ባለፉት ሃያ አራት አመታት የአገራችን የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ በጣም ከዘቀጠና ከረከሰ የወያኔ ድራማ ዉጭ ሌላ ምንም ነገር የማይታይበት አለባሌ መድረክ አድረገዉት ቆይተዋል አሁንም እያደረጉት ነዉ። አንድ ቋንቋ የሚናገሩትና ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸዉ የወያኔ መሪዎች ኢህአዴግ የሚባል አጋሰስ የሽፋን ድርጅት ፈጥረዉ በኢትዮጵያ ህዝብ ሰብዓዊ መብትና ነጻነትና ላይ ተነግሮም ተጽፎም የማያልቅ ግዙፍ ግፍና በደል ፈጽመዋል። ህጻን፤አዛዉንት፤ ወንድና ሴት ሳይለዩ መብቴን አትንኩ ያለቸዉን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለምንም ርህራሄ በጥይት ጨፍጭፈዋል። ሴቶች እሀቶቻችንን እጅና እግራቸዉን አስረዉ ጡታቸዉን በመቆንጠጫ እየቆነጠጡ በሴትነታቸዉ ላይ የዉርደት ተግባር ፈጽመዋል። ወንዶች ወንድሞቻችንን ደግሞ ዉስጥ እግራቸዉን ገልብጠዉ እየገረፉ ጥፍራቸዉን አይናቸዉ እያየ በጉጠት እየሳቡ ነቅለዋል። ባጠቃላይ የወያኔ ዘረኞች በዛሬዉ ዘመን አንኳን ወገን በወገኑ ላይ የዉጭ ጠላትም በህዝብ ላይ የማይፈጽመዉ በደል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፍጽመዋል።
ወያኔ ስልጣን እንደያዘ “አባይ ትግራይ” ወይም “ታላቋ ትግራይ” የሚለዉን ህልሙን ለማሳካት ወልቃይት ጠገዴን ከጎንደር ቆርሶ ከትግራይ ጋር ቀላቅሏል። ስልጣን ይዞ ከተደላደለ ከአመታት በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያን ገበሬ ከመሬቱ አፈናቅሎ ለምለም መሬቱን በርካሽ ዋጋ ለባዕዳን ሽጧል፤ ከዚህ አልፎ ተርፎም የአባቶቻችን አጽም ያረፈበትን የአገራችን ዳር ድንበር ቆርሶ ለጎረቤት አገር ገጸ በረከት አቅርቧል። ይህ አገራቸዉንና የሚመሩትን ህዝብ በሚጠሉ ጠባቦች የተሞላ ድርጀት ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቹንና በአንቀልባ ታዝለዉ አስከዛሬ ያቆዩትን ምዕራባዉያን ጭምር ግራ ያጋባ ፀረ አገርና ፀረ ህዝብ እርምጃ ወስዷል። ድርጅት እያፈረሰና በፓርቲ ላይ የራሱን ተለጣፊ ፓርቲ እያቋቋመ ዛሬ ላይ የደረሰዉ ወያኔ ምርጫ የሚባል ድራማ በደረሰ ቁጥር የሚይዘዉ በሽታ ዘንድሮም ይዞት አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲንና መላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን አፍርሶ በምትካቸዉ የራሱን መኢአድና የራሱን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፈጥሯል። ይህ ወያኔ ከሰሞኑ የወሰደዉ የፖለቲካ እርምጃ በየትኛዉም አለም በተለይ የመድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዐትን እንከተላለን በሚሉ አገሮች ዉስጥ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ እጅግ በጣም ትልቅ የፖለቲካ ሸፍጥ ነዉ።
የወያኔን ታሪክ ተወልዶ ካደገበት ከደደቢት በረሃ እስከ ሚኒልክ ቤ/መንግስት ድረስ ያደረገዉን ጉዞ ስንመለከት ወለል ብሎ የሚታየን አንድ ሐቅ አለ፤ እሱም ወያኔ ሁሉንም ነገር በዘር መነጽር ብቻ የሚመለከትና ህዝብን በወዳጅና በጠላት ጎራ ለይቶ ወዳጅ አይደለም ያለዉን ሁሉ እንደ ሩሲያዊዉ ዮሴፍ ስታሊን እየገደለ የመጣ ድርጅት ነዉ። በእርግጥም ወያኔ ጫካ ዉስጥ እያለም ሆነ ዛሬ ከተማ ገብቶ የሚቃወመዉንና በሀሳብ የማይግባባዉን ድርጅትም ሆነ ግለሰብ እያፈረሰና እገደለ ባፈረሳቸዉ ድርጅቶች ምትክ ደግሞ የራሱን ተለጣፊ ድርጅት እየፈጠረ የመጣና ከዲሞክራሲያዊ አሠራርና ከስልጣኔ ጋር የማይተዋቅ ድርጅት ነዉ።
በመርፌ የተጠቃቀመ ቁምጣና ጥብቆ ለብሶ አስራ ሰባት አመት ጫካ ለጫካ የተጓዘዉ ወያኔ ጎንደር፤ ጎጃምና አምቦ እያለ ወደ አዲስ አበባ ሲጠጋ ከተገነዘባቸዉ ነገሮች አንዱ የለበሰዉ የተጠቃቀመ ቁምጣ የትም እንደማያደርሰዉና ለከተማ ኑሮ የሚስማማ አዲስ ልብስ እንደሚያሰፈልገዉ ማዉቁ ነዉ። በጥላቻ ተረግዞ በክፋት ላደገዉ ወያኔ ቢበቃዉም ባይበቃዉም ወይም ቢያምርበትም ባያምርበትም ይህንን ለከተማ ዉስጥ ኑሮ የሚያስፈልገዉን አዲስ ልብስ ለማዘጋጀት ብዙ ግዜ እልወሰደበትም። የሚሰርቅና የሚስቅ ምን ግዜም ተባባሪ አያጣም እንዲሉ ወያኔ የአዲስ አበባን መሬት የረገጠዉ ጦር ሜዳ ላይ የማረካቸዉን ወታደሮችና አገር ዉስጥ ያገኛቸዉን ደካማ ሰዎች ሰብስቦ በፈጠረዉ ኢህአዴግ በሚባል ፈረስ ጀርባ ላይ ተፈናጥጦ ነበር። ትግራይን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ትግል የጀመረዉ ወያኔ ኢህአዴግን የፈጠረዉ ወያኔነቱን ለመተዉ ሳይሆን እራሱን በዚህ በኢትዮጵያ ስም በፈጠረዉ ድርጅት ዉስጥ ሸሽጎ እዉነተኛ ባህሪዩን ለመደበቅ ነበር።
ከግንቦት 1983 ዓም አስከ ግንቦት 1987 ዓም ድረስ የዘለቀዉንና በወያኔ የበላይነት ተጀምሮ ወያኔን በማንገስ የተጠናቀቀዉን የሽግግር መንግስት ወደ ኋላ መለስ ብሎ የቃኘ ማንም ሰዉ የወያኔን ሁለት ዋና ዋና መሠሪ ስራዎች በቀላሉ መመልከት ይችላል።
አንደኛ- ኦነግንና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄን ጨምሮ አያሌ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን አቅፎ ስራዉን የጀመረዉ የሽግግሩ መንግስት የስራ ዘመን የተገባደደዉ የኢትዮጵያን አንድነት ጥያቄ ያነሱ ግለሰቦችን በማሰርና ከወያኔ ቁጥጥር ዉጭ እራሳቸዉን ችለዉ ለመንቀሳቀስ የሞከሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከሽግግሩ መንግስት በማባረር ነበር።
ሁለተኛ- ወያኔ የኋላ ኋላ እያደር ለመስራት ላቀዳቸዉ አገር የመበተንና ህዝብን የመለያየት ስራዎች እንዲያመቸዉ ከእያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት ጀርባ የኢትዮጵያ ህዝብ ተለጣፊ እያለ የሚጠራቸዉን ድርጅቶች በራሱ አምሳል እየፈጠረ ማሰማራቱ ነዉ።
ባጠቃላይ ወያኔ የፈጠረዉ የሽግግር መንግስት ኢትዮጵያዊ አጀንዳና አገራዊ ራዕይ ይዘዉ የተንቀሳቀሱ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን አጥፍቶ ወያኔን ዘለአለማዊ ንጉስ ለማደረግ ከመሞከሩ ዉጭ ሌላ ምንም ኢትዮጵያን የሚጠቅም ስራ አልሰራም።
ከሽግግሩ መንግስት በኋላ ወያኔ ተወዳዳሪዉም አሸናፊዉም እሱ ብቻ የሆነባቸዉን ሁለት ትርጉም የለሽ ምርጫዎችን አካሂዷል።እነዚህን ተወዳዳሪ የለለባቸዉን ሁለት ምርጫዎች በቀላሉ በማሸነፉ ህዝብ የወደደዉ መስሎት ልቡ ያበጠዉ ወያኔ ሦስተኛዉን አገራዊ ምርጫ ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ምርጫዎች በተለየ መልኩ ለቀቅ አድርጎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ፤ መራጩን ህዝብ መቅረብ እንዲችሉና ወያኔን እራሱን ምርጫዉን አስመልክቶ ክርክር እንዲገጥሙት በሩን ከፈተላቸዉ። ነገሩ “የማይነጋ መስሏት” እንዲሉ ሆነና ሜዳዉም ፈረሱም ይሄዉና ብሎ የፊልሚያዉን ሜዳ የከፈተዉ ወያኔ የምርጫዉ ቀን ደርሶ በዝረራ መሸነፉን ሲሰማ በራሱ ሜዳና በራሱ ዳኞች ፍት ያሸነፉትን የህዝብ ተመራጮች ከየመኖሪያ ቤታቸዉ እያደነ አስሮ በአገር ክህደት ወንጀል ከሰሳቸዉ ። የሚገርመዉ ወያኔ በምርጫዉ ተወዳድረዉ በምስክር ፊት በአደባባይ ያሸነፉትን የህዝብ ተመራጮች በማሰር ብቻ አልተወሰነም። በወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን ይመለከተዉ የነበረዉን ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲን አፍርሶ እንደለመደዉ የራሱን ቅንጅት ፓርቲ ፈጥሮ ይበጃል ብሎ ላሰባቸዉ ደካማና ሆዳም ግለሰቦች አስረክቧል።
ይህ ቆየት ያለ በሽታዉ ዘንድሮም አገርሽቶበት አንድነትንና መኢአድን ለክፏቸዋል። ይህ ወያኔ ከሰሞኑ መኢአድና አንድነት ላይ የወሰደዉ እርምጃ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች በመጪዉ ምርጫ ላይ ያሸንፉኛል ከሚል ፍራቻ አይደለም። ወያኔ ምርጫዉ የሚካሄድበት ሂደት ብቻ ሳይሆን ህዝብ የሰጠዉ ድምጽ የሚቆጠርበትና የምርጫዉ ዉጤት ለህዝብ የሚገለጽበት መንገድ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር እንደሆነና ይህንን ምርጫ ብቻ ሳይሆን የሚቀጥለዉንም ምርጫ ከሱ ዉጭ ሌላ ማንም እንደማያሸንፍ በሚገባ ያዉቃል። ወያኔ መኢአድንና አንድነትን የጥቃቱ ሰለባ ያደረጋቸዉ ህዝባዊ አላማቸዉንና አገራዊ ራዕያቸዉን በተለይ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ፤ አንድነትና እኩልነት ጥያቄ ላይ ያላቸዉን የጠራና የማያወላዉል አቋም እጅግ በጣም ስሚጠላ ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ እንዲህ በአጭር ግዜ ዉስጥ መኢአድንና አንድነትን የጨፈለቃቸዉ እነዚህ ሁለት አንጋፋ ፓርቲዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ የዘረጉት መዋቅርና ከህዘብ ጋር የፈጠሩት የቅርብ ግኑኝነት እንቅልፍ ስለነሳዉ ነዉ። ሌላዉ በፍጹም መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ይዋል ይደር እንጂ ወያኔ እኛ ቀድመን ካላጠፋነዉ በቀር “ኢትዮጵያዊነት” ፤ “አንድነት” ወይም ፍትህና ነጻነት ብሎ የተነሳን ማንንም ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይም ድርጅት ማጥፋቱ አይቀርም። በእርግጥም ከትናንት ወዲያ ቅንጀትን፤ ዛሬ ደግሞ መኢአድንና አንድነትን አፍርሶ የራሱን ተለጣፊ አሻንጉሊቶች የፈጠረዉ ወያኔ ነገ እነዚህ ፓርቲዎች የቆሙለትን አላማ የተሸከምነዉን ኢትዮጵያዉያን አንድና ሁለት እያለ ለቃቅሞ እንደሚያጠፋን ምንም ጥርጥር የለዉም።
ወያኔ አምስት አመት አየቆየ በሚመጣዉ የምርጫ ድርማ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ ላይ እንደማይወርድ በ1997 ዓም ሰኔ ወርና በ 1998 ዓም ህዳር ወር በአዲስ አበባ አደባባዮች ላይ በወሰደዉ ፋሺስታዊ እርምጃ በግልጽ አሳይቶናል።ከላይ ከፍ ሲል ለመግለጽ አንደተሞከረዉ ወያኔ ፊታችን ላይ ባለዉ በ2007ቱ ምርጫ ወይም በተከታታይ በሚመጡት ምርጫዎች ተሸንፌ ከስልጣን እወርዳለሁ የሚል ምንም አይት ስጋት የለበትም፤ ምክንያቱም በምርጫዉ ጨዋታ ዉስጥ ተጫዋቹም ፤ ሜዳዉም ዳኛዉም ወያኔ ብቻ ነዉ። ዛሬ የወያኔን መሪዎች ያንቀጠቀጣቸዉና እንዳበደ ዉሻ ያገኙትን ሁሉ እንዲነክሱ ያደረጋቸዉ አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ በተግባራዊ ስራዎች ላይ መናበብ በመጀመሩና በህዝባዊ እምቢተኝነቱና በህዝባዊ አመጹ ዘርፍ የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ህዝባዊ ሙቀት አግኝቶ እየተጋጋለ በመምጣቱ ነዉ። ወያኔዎች እነሱንና የገነቡትን ዘረኛ ስርዐት ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርጎ የሚያጠፋዉ የህዝባዊ አመጹና የህዝባዊ እምቢተኝነቱ ጎርፍ መሆኑን ካወቁ ቆይተዋል። ይህ ከሰሞኑ በማሰር፤ በመደብደብና ድርጅት በማፍረስ የወሰዷቸዉ እርምጃዎች የሚያሳዩን ወያኔዎች ህዝባዊ ጎርፉን ቢቻል ለማጥፋት አለዚያም ጉዳት በማያደርስ መልኩ ለመገደብ ያሚያደርጉትን ከንቱ ሙከራ ነዉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፤ የኢትዮጵያ ወጣት፤ ገበሬና ሰራተኛ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ትናንት ቅንጅትን አፍርሶ የራሱን መናኛ ቅንጅት የፈጠረዉ ወያኔ ዛሬም እንደገና አሉ የሚባሉትንና አገራዊ ራዕይ ይዘዉ የሚንቀሳቀሱትን አንድነትንና መኢአድን አፍርሶ በምትካቸዉ እንደጌኛ ፈረስ የሚጋልብባቸዉን የራሱን ሁለት መናኛ ፓርቲዎች ፈጥሮ መኢአድና አንድነት ብሎ ሰይሟቸዋል። ይህ በዋና ዋናዎቹ ዘረኛ የወያኔ ባለስልጣኖች ተጠንቶ በጥንቃቄ የተወሰደዉ እርምጃ ፓርቲዎቹ ህግ ስላላከበሩ ነዉ የሚል ሽፋን ይሰጠዉ እንጂ የምርጫ ቦርዱ ሊ/መንበር ሳያስቡት ከአፋቸዉ አፈትልኮ የወጣዉ እዉነት በግልጽ እንዳስቀመጠዉ ከምርጫዉ ጨዋታ ወጥተዉ እንዲፈርሱ በተደረጉት አንድነትና መኢአድ ፓርቲና ወያኔ በተለጣፊነት ባስጠጋቸዉ ሁለቱ ተለጣፊ ፓርቲዎች መካከል ያለዉ ልዩነት አንዱ ቆሜለታለሁ ለሚለዉ ህዝብ የሚታዘዝ ህዝባዊ ሌላዉ ደግሞ ሆዱን ለሚሞላለት ወያኔ የሚታዘዝ ሆዳም መሆናቸዉ ብቻ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወያኔ መብቴን ብለህ ስትጮህ በጥይት እየጨፈጨፈህ ነጻነት ስትለዉ በዱላ እየደበደበህና ሰላማዊ ሰልፍ ስትወጣ ደግሞ አፍሶ እያሰረህና ዉስጥ እግርህን ገልብጦ እየገረፈህ በሰላማዊ መንገድ የምታደርገዉን ትግል ምርጫ አሳጥቶሃል። ሆኖም ግልጽ በሆነ መንገድ እንነጋገር ከተባለ ወያኔ የትግል አማራጭ አያሳጣህም፤ ሊያሳጣህም አይችልም። ወያኔ እሱ እራሱ ህግ በሆነበት አገር ህጋዊ ወይም ሠላማዊ ትግል ብሎ ነገር ዋጋ ቢስ አንደሆነ ሁላችንም የተረዳን ይመስላል። ትግላችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ነዉና ከዛሬ በኋላ ወያኔን ጥያቄ አንጠይቀዉም፤ አድርጉ የሚለንን አናደርግም፤ ሁኑ የሚለንንም አንሆንም። ትግላችን ህዝባዊ አመጽ ነዉና ከዛሬ በኋላ ወያኔ ሲገድለን እኛም እየገደልነዉ እንሞታለን እንጂ አንገታችንን ደፍተን የእሳት እራት አንሆንም። አዎ! ት ግላችን እምቢ ማለት ወይም ህዝባዊ እምቢተኝነት ነዉ፤ ትግላችን በወያኔ ላይ ማመጽ ወይም ህዝባዊ አመጽ ነዉ።

Saturday, February 7, 2015

ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!

February 7,2015
“አሜሪካ በህወሃት/ኢህአዴግ ላይ ፖሊሲዋን ልትቀይር ይገባታል”
obang metho1


* ኢንቨስተሮች “የደም ከፈን” ላለመግዛት ወሰኑ

በኦሞ ሸለቆ ድሆችን ከመሬታቸው በማባረር የሚያመርተውን ጥጥ ወደ ውጭ ለመላክ ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኢህአዴግ ባለፈው ሰሞን ያልጠበቀው ምላሽ ደርሶታል፡፡ ምላሹን ተከትሎ የጥጥ ግብይቱ የጨነገፈው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መሆኑን በገሃድ አመነ፡፡ በኢህአዴግ ስትራቴጂክ በሆኑ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድሞ የመልስ ምት በመምታት ፈተናው ውስጥ የከተታቸው አኢጋን እና መሪው ኦባንግ ሜቶ መዋቅራቸው ሊገኝ አለመቻሉ ኢህዴግን እንዳስጨነቀው ተሰማ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በሰማሁት ተዝናንቻለሁ ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አሜሪካ መከተል የሚገባትን አካሄድ በመዘርዘር ለፕሬዚዳንት ኦባማ ፖሊሲ ሊያስቀይር የሚችል ደብዳቤ ልከዋል፡፡
ኢህአዴግ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ በቦታቸው ላይ ጥጥ እያበቀለና ጨርቅ እየሰፋ ለምዕራባዊ ኩባንያዎች ለመቸርቸር የገባውን ውለታ ያጠፉበት ሁለቱ ኩባንያዎች ዓለምአቀፋዊው የስዊድን ጨርቃ ጨርቅ ሻጭ ኤች ኤንድ ኤምና የጀርመኑ ቼቦ ናቸው፡፡ ባለሃብቶቹ ከኦሞ ሸለቆ ሰብዓዊ መብታቸው እየተገፈፈ መሬታቸው በተነጠቀባቸው ዜጎች መኖሪያ ላይ ጥጥ ተመርቶ የሚፈበረከው ጨርቃጨርቅ “የደም ከፈን” አድርገው በመቁጠር ስምምነታቸውን መሰረዛቸውንና ውሉ መጨናገፉን ያመኑት የኢህአዴግ ጨርቃ ጨርቅ ተቋም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ባንተ ይሁን ገሠሠ ለሪፖርተር ባለፈው ሰሞን በተናገሩበት ወቅት ነው፡፡
“የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ ነን ባዮች” በማለት የንግድ ስምምነቱ ውል ቀለሙ ሳይደርቅ፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ሃሳብ ሳይሰጥ፣ በተቋም ደረጃም ይሁን በፖለቲካ ፓርቲ መግለጫ ሳይሰጥበት፣ በአገር ውስጥም ይሁን በተለይ በውጭ የሚገኙ “አክቲቪስቶች” ድምጻቸውን ሳያሰሙበት ጉዳዩን የራሱ አድርጎ በቀጥታ ለኤች ኤንድ ኤምና ለዋና ሥራ አስፈጻሚው “የደም ከፈን” በማለት ኩባንያው ራሱን ከዚህ ዓይነት እርም የተላበሰ ስምምነት እንዲያጸዳ ማስጠንቀቂያ የላከው አቶ ኦባንግ የሚመሩት አኢጋን ነበር፡፡
ይኸው በዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ጥቁሩ ሰው” ተፈርሞ የተበተነው የማስጠንቀቂ ደብዳቤ ቅድሚያ የተዘገበውም በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ነበር፡፡ ይህ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ኤች ኤንድ ኤም ሲደርሰው በወቅቱ “በመልካም የንግድ ተግባር” ዓለምአቀፋዊ ሽልማት በዋሽንግተን ዲሲ የሚቀበልበት ወቅት ላይ ነበር፡፡ በወቅቱ የጋራ ንቅናቄው ለኤች ኤንድ ኤም ከጻፈው ደብዳቤ በተጨማሪ ከጀርመኑ ቼቦ ጋር ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች በመነጋገርና ተጽዕኖ በማድረግ የፈረመውን ውል በአንክሮ እንዲከታተል ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው አድርጎ እንደነበር የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል አስታውቋል፡፡
የኢህአዴጉ ሹመኛ ለሪፖርተር ቃላቸውን ሲሰጡ ስም አይጥሩ እንጂ “ነን ባዮች” ሲሉ የገለጹት በቅድሚያ አቶ ኦባንግ የሚመሩትን አኢጋን ስለመሆኑ ጥርጥር እንደሌለ ከአዲስ አበባ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አመልክቷል፡፡ ከዚሁ አዲስ አበባ የተገኘው መረጃ እንደሚመለክተው አቶ ኦባንግ በኢህአዴግ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድመው መረጃ በማውጣትና በማጋለጥ “ደንቃራ” እንደሆኑባቸው ታውቋል፡፡
ለኢህአዴግ ከሚያገለግሉ ቁልፍ ሰዎች መካከል የተገኘ መረጃ እንደሆነ በመጥቀስ እንደተጠቆመው ኢህአዴግ የአቶ ኦባንግን እና አኢጋንን አሠራር እንዲሁም ያለውን የግንኙነት ደረጃ በተጨባጭ ለመሰለል እንዳቃተው ታውቋል፡፡
በተለይ በዳያስፖራው የፖለቲካ ስልጠት (ሲስተም) ያለው የህወሃት/ኢህአዴግ አደረጃጀት ኦባንግ እና ድርጅታቸውን አስመልክቶ የሚሰበስበው መረጃ አቶ ኦባንግ በፌስቡክ ከሚለቁት ብዙም ያልተለየ በመሆኑ ብዥታን ፈጥሮባቸዋል፡፡ በታላላቅ ቦታዎች፣ በከፍተኛ ስብሰባዎች፣ “አንቱ” በሚጠሩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይሎች፤ ግዙፍ በሚባሉ የዓለም ተቋማት፣ በታላላቅ መንግሥታት ወዘተ ኢትዮጵያን በብቸኝነት እየወከሉ ፖሊሲ እስከማስቀየር የደረሱት አቶ ኦባንግ “ለኢህአዴግ ራስ ምታት ሆነዋል” በማለት የአገዛዙ ባለሥልጣን መናገራቸውን ከመረጃ ሰዎቻችን ለማወቅተችሏል፡፡
ይህንን አስመልክቶ አቶ ኦባንግ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ “እንዲህ ያለው የኢህአዴግ ስጋት ለእኔ እንደመዝናኛ እቆጥረዋለሁ” ነው ያሉት፡፡ በማያያዝም ድርጅታቸው አኢጋንም ሆነ እርሳቸው ምስጢር የሚባል ነገር እንደሌለው አገር ወዳዶች የሚመሩት፣ የስልኩም ሆነ ማንኛውም የመገናኛ መንገዱ በገሃድ የሚታወቅ፣ በግልጽ ቋንቋ ዘረኝነትን የሚጸየፍ፣ ለሰብዓዊነት የሚቆረቀቆር፣ አጀንዳውም ግልጽ የሆነ፣ በየትኛውም ቦታ የሚገኝ ድርጅት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶቹ አኢጋንን አወቃቀሩንና አሠራሩን ለማወቅ ስባሪ ሰከንድ ማባከን የለባቸውም፤ አስፈላጊ ነው ብለው የሚገምቱትን ነገር በሙሉ ቢጠይቁን እንነግራቸዋለን፤ ከሕዝብ ደብቀን የምንሠራው ሥራ የለንም፤ ዘረኝነትን ለመቃወም እና ለማፍረስ፤ ሰብዓዊነትን ከዘረኝነት በፊት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ለማስፈን ለምን ምስጢራዊ ሥራ ያስፈልገዋል? እኛ ለስለላና ለምስጢራዊ ሥራ የምናባክነው ጊዜና ገንዘብ የለንም፤ ይልቁንም የህወሃት/ኢህአዴግ ሰዎች እውነትን ለመጋፈጥ ካልፈሩ በቀጥታ በማንኛውም ጊዜ ሊያገኙን ይችላሉ” በማለት “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያውያን የጥሪ ድምጽ በተሰማመበት ቦታ ሁሉ ቀድመው በመድረስ የሚታወቁት ኦባንግ በስደት እስር ቤት ሲማቅቁ ተረስተው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ከሜክሲኮና ከጃፓን ነጻ በማስወጣት፤ በአውሮጳ አገራት የስደተኛ ጉዳያቸው በህወሃት/ኢህአዴግ ሰላዮችና በሥርዓቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ መከራ ውስጥ እንዲገባ የተደረገባቸውን ወገኖች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር የስደተኛ ፖሊሲዎችን በማስቀየር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ካሩቱሪና መሰል ድርጅቶች በኢንቨስትመንት ስም አለአግባብ የነዋሪዎችን መሬት በመንጠቅ የሚያደርሱትን ግፍ በተጠናቀረ ዘገባ መልክ በማውጣት የዓለም ሕዝብ እንዲያውቀው ከማድረግ አልፎ የህወሃት/ኢህአዴግን ፖሊሲ በማጋለጥ ሕንድ ድረስ በመሄድ ባደረጉት ውትወታ የካሩቱሪን አካሄድ በማስቀየር፤ የዓለም ባንክ ለኢህአዴግ የሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ ኢህአዴግ ለወታደሮቹ ደመወዝ መክፈያ በማድረግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መከራ እያደረሰ መሆኑን ይህም የባንኩን አሠራር በግልጽ የሚጻረር መሆኑን በማጋለጥና የፖሊሲ አቅጣጫ በማስቀየር፤ ወዘተ በዳያስፖራ ከሚገኙት ድርጅቶች በተለየ መልኩ የሚንቀሳቀሱት አቶ ኦባንግ ሜቶና ድርጅታቸው ሲሰራ ብዙ ባይዘፈንለትም ውጤት በማስመዝገብ ግን “ወደር እንደማይገኝለት” ኢትዮጵያ ድረስ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች ይመሰክሩለታል፡፡
የደም ከፈን” አልገዛም ያለውና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የልብስ መደብሮች ያሉት የስዊድኑ ኤች ኤንድ ኤም ድርጅት ስመጥር ኩባንያ እንደሆነ መረጃዎች ይናገራሉ፡፡ የጀርመኑ ቼቦም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚጠቀስ ይታወቃል፡፡ ጎልጉል ባለው መረጃ መሠረት የንግድ ስምምነቱ የጨነገፈው ከጥጥ ማምረት ጋር በተያያዘ ሳይሆን በአካባቢው ያለው የሰላም መደፍረስ፣ የሕዝብ እምቢተኝነት ማየል፣ የግፍ መባባስ ዝርፊና ቅሚያው ከልክ እያለፈ መሄድ ከአካባቢው ሙቀት ጋር ተዳምሮ “ለባለሃብቶቹ” ሰላም የሚሰጥ ኢንቨስትመንት ባለመሆኑ ነው፡፡ የተለያዩ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከዚህ በፊትም ጎልጉል በተለያዩ ጊዜያት አስቀድሞ እንደዘገበው በኦሞ ሸለቆና በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ያሉ ታላላቅ ኢንቨስትመንቶች እያደር መጨናገፋቸው የማይቀር እንደሆነ በስፋት ይታመናል፡፡ የተፈጥሮን ደን በማውደም ጣውላ ሲቸበችቡ የነበሩት “ኢንቨስተሮች” እንኳንስ ሊያለሙ የተበደሩትን መክፈል አቅቷቸው እያቃተቱ መሆናቸውን በቅርቡ ኢህአዴግ እያመነ መሆኑን በራሱ በኢህአዴግ አፍ ተመስክሯል፡፡
አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “በጥምባሆ መግዣ ዋጋ መሬት እየቸበቸበ፣ ምስኪን ንጹሃንን እያፈናቀለ፤ ምነው ያሉትን እያሰረና እየገደለ፣ “አገር አደገች፤ ተመነደገች፤ ልማት ነው፤ ሥራ ላይ ነን” የሚለው ኢህአዴግ፤ ሸራተን በውስኪ አጅቦ ያወጀው ኢንቨስትመንት መጨረሻው ይኸው ነው፡፡ በአበባ እርሻ ላስቲክና ካርቶን የባንክ ዋስትና (ኮላተራል) አድርገው የአገሪቱን ባንክ አልበው የሄዱትን አጭበርባሪ ድርጅቶችና አጋሮቻቸውን ልማት ባንክና ህወሃት ያውቋቸዋል፡፡ ይህ ቀን ጠብቆ ሕዝብና ትውልድ ፍርድ የሚሰጡበት ነው” ብለዋል፡፡ በምዕራብ ኢትዮጵያ በተለይ በጋምቤላ አካባቢ በትንሹ ከ70 በመቶ በላይ “ባለሃብት” ተብለው መሬት የወሰዱት የትግራይ ነዋሪዎች ከኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት የተገኘው ይፋዊ መረጃ ያረጋግጣል፡፡
በሌላ በኩል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ አሜሪካ ህወሃት/ኢህአዴግን ይዛ የትም መድረስ እንደማትችልና ይልቁንም የሕግ የበላይነት እንዲከበር ፖሊሲዋን ልትመረምር እንደሚገባ በማሳሰብ ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በተለይ መጪውን ምርጫ ተያይዞ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለውን የአፈና ፖሊሲ የምርጫውን ውጤት አስቀድሞ የሚተነብይ መሆኑን አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ማስረጃዎችን በመጥቀስ ዘርዝረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ላይ ምርጫ ቦርድ የወሰደው ዕርምጃ ተጠቃሽ መሆኑን “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ አስታውሰዋል፡፡
ስለሆነም ምህዳሩ እንዲሰፋ፣ አፈናው እንዲቆም፣ ምርጫ ቦርድ ያለአድልዎ መስራት እንዲችል፣ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ያረቀቁት “ኦምኒበስ ረቂቅ 2015” ተግባራዊ እንዲሆን፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም ቁልፍ በሆኑ የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች ላይ ወደ አሜሪካ የመግባት ዕቀባ (የበረራ ማዕቀብ) እንዲጣልባቸውና በውጭ አገር ያከማቹትን ገንዘብና ሃብት እንዳይንቀሳቀስ እንዲደረግ፣ ወዘተ አሜሪካ የፖሊሲ ለውጥ እንድታደርግ ለፕሬዚዳንቱ አሳውቀዋል፡፡ ኦባንግ ይህንን ያቀረቡት በልመና መልክ ወይም “ያለ አሜሪካ እርዳታ አይሆንልንም” በማለት መንፈስ ሳይሆን የኢህአዴግን የበጀት ኮሮጆ በመሙላትና “አሸባሪዎችን ለመዋጋት” በሚል ድጋፍ በመስጠት ቀዳሚዋ አሜሪካ በመሆኗ ከግብር ከፋይዎቿ እየሰበሰበች በምትሰጠው ገንዘብ ሕዝብ እንዳይበደል፣ እንዳይሰቃይ፣ እንዳይገደል፣ መብቱ እንዲከበር፣ ነጻነት እንዲያገኝ፣ ወዘተ የማድረግ የሞራል ግዴታ ስላለባት ነው፡፡ የአቶ ኦባንግ ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይነበባል፡-

An Open Letter to President Barack Obama,

The alarming political conditions in Ethiopia that may threaten the future security and stability of this strategic country in the Horn of Africa
February 5, 2015
Honorable Barack Obama
The President of the United States of America
The White House
1600 Pennsylvania Avenue
Washington, DC 20501
Dear President Obama,
I am writing this to you on behalf of the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) to alert you to the alarming political conditions in Ethiopia that may threaten the future security and stability of this strategic country in the Horn of Africa. Current United States policies that strongly support the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) are being abused by this regime to undermine the democratic aspirations of the Ethiopian people. As the EPRDF intensifies the crack down on the political and human rights of the people there is fear that some event may ignite the simmering tensions, causing them to explode into violence, killing and chaos.
My name is Obang Metho. I am the Executive Director of the SMNE, a non-violent, non-political grassroots social justice movement representing the diverse people of Ethiopia.
I come to you first and foremost as a human being who believes that the future well being of our global society rests in the hands of those among us who can put humanity before ethnicity or any other distinctions that divide and dehumanize other human beings from ourselves; inspiring us to care about these others; not only because of the intrinsic God-given value of each life, but also because none of us will be free until all are free. These are the underlying principles of the SMNE. The SMNE is committed to bringing truth, justice, freedom, equality, reconciliation, accountability, respect for human and civil rights and economic prosperity to the people of Ethiopia and beyond.
Urgency of concern:
The escalation of frustrations regarding the upcoming Ethiopian national elections scheduled for May 24, 2015, may become the trigger to violence as Ethiopians face the dismal reality that all avenues to democratic political change are solidly blocked. If violence breaks out, it may spin out of control. Now is the time to take steps to avoid it; however, the TPLF/EPRDF fears the people to the degree that they may find it impossible to alter their direction, even if it is what pushes people over the edge towards a violent backlash. The SMNE seeks to help all parties avoid such an outcome.
Unfortunately, the TPLF/EPRDF will never voluntarily give up power by holding a free and fair election. They know opening up political space would lead to a reversal of power. As a result, there is little hope that the situation will improve without leverage.
We know that, the United States is the chief financial, political and security backer of the TPLF/EPRDF. If the appropriate actions are taken, it may give the US an opportunity to improve the long-term interests of the US in Ethiopia and the Horn as well as to contribute to a better future for Ethiopians and their neighbors.
Clearly, Ethiopia is the most stable country among its neighbors like Eritrea, Somalia, Sudan and South Sudan, but if it were to descend into instability, it would be devastating for the Horn of Africa and beyond. There needs to be an alternative that would offer a peaceful way out for all parties, including the TPLF/EPRDF. The TPLF/EPRDF will not and cannot do it alone. The people of Ethiopia must do the major work, but if they are facing a strongly-US, UK or EU-supported TPLF/EPRDF; the job will be all the more difficult.
The TPLF/EPRDF has become an increasingly totalitarian government over the last 24 years they have been in power; however, the real power behind them is the ethnic-based Tigrayan Peoples Liberation Front (TPLF) that dominates every branch of the government. Their stated goal is to gain perpetual rule and hegemony of Ethiopia. As documented by both the US Embassy in Addis Ababa and the US State Department’s human rights division, the Ethiopian government is becoming increasingly brutal in its crack down on basic freedom, democratic processes, and the rule of law. This is not new.
Since coming to power, this regime has never held a free and fair election. The closest it came to allowing a degree of political space was in 2005 when the opposition nearly won. Instead, the TPLF/EPRDF claimed a victory, killed 193 election protestors in the streets, imprisoned opposition members, and closed down all political space in the 2010 election. At that time they even misused humanitarian aid to control voting at every level; finally claiming an absurd 99.6% electoral victory. The Ethiopian Parliament has only one opposition member out of 547.
Some are willing to overlook the lack of democratic progress, believing that claims of economic progress make up for it. However, although there may be some advances made, TPLF/EPRDF statistics claiming double-digit economic growth are being challenged as Ethiopians remain at the bottom of most every poverty index. There is little to no private sector, but instead, economic opportunities are limited to regime cronies, another source of contention among Ethiopians.
A robust civil sector that could act as watchdogs of society has been eliminated due to the implementation of the Charities and Societies Proclamation. This is a law that has made it a crime for civic organizations who receive more than 10% of the funding from foreign sources to advance human and democratic rights, to promote equality among ethnicities, genders and religions, to promote rights for the disabled and children, to promote conflict resolution or reconciliation, or to promote the efficiency of justice and law enforcement services. Some 2,600 or more civic organizations closed in response. In their place, the TPLF/EPRDF has set-up pseudo-organizations they control.
Similarly, they have passed an Anti-Terrorism Law that is used to silence democratic voices, journalists, bloggers, editors, opposition leaders and religious leaders under false pretenses. Ethiopia has become one of the highest jailers of political prisoners in Africa. In present day Ethiopia, every important public and private institution is under the control of the TPLF/EPRDF, whether it is the judiciary, the police and security forces, government offices and ministries all the way to the local level, the military, the media, the telecom system, the Internet, the educational system, the economy, and most importantly right now, the National Election Board of Ethiopia (NEBE).
In the last month, they have increased their efforts to eliminate any competition. This includes beating up opposition leaders and any who speak out against them, even pregnant women and the elderly. Many are jailed in an effort to intimidate any who call for a legitimate democratic process. Obstacles are erected to block every effort of opposition parties to satisfy the impossible requirements of the NEBE.
Two prominent opposition political parties, the Unity for Justice and Democracy (UDJ) and the All Ethiopian Unity Party (AEUP), have both made valiant attempts to comply with unreasonable demands; however, they now have been denied participation in the election. Instead, the TPLF/EPRDF has hijacked the ownership of these parties, even taking on their names, UDJ and AEUP. They have appointed their own people to run as candidates against others in the TPLF/EPRDF, essentially competing with themselves in a ruse to confuse the people.
Recommendations for meaningful US action regarding Ethiopia:
US silence or only symbolic gestures regarding the evolving crisis in Ethiopia may work for the short-term, but no one knows for how long. In fact, continued US support or meaningless action may inadvertently exacerbate the crisis and undermine stability. Instead, the US should use their leverage to bring democratic change and sustainable stability to the country; both of which would enhance long-term US interests in Ethiopia and the Horn.
Meaningful actions include:
  • Calling for an independent election commission
  • Implementing the Omnibus Bill 2015 concerning Ethiopia
  • Releasing imprisoned political prisoners
  • Freezing security cooperation with the regime
  • Implementing travel bans on key regime officials and freezing their assets
It is not in the interests of anybody to wait for an explosion. Ethiopia is in crisis. Our goal is to bring peace even as some are beating the drums of violence. We strongly encourage you to put pressure on this regime. Condemn these actions. The US should not be silent when such a stance could contribute to the future wellbeing and stability of this strategic country of over 90 million people.
Respectfully yours,
Obang Metho,
Executive Director of the SMNE
910- 17th St. NW, Suite 419
Washington, DC 20006
Email:Obang@solidaritymovement.org.
Website: www.solidaritymovement.org
This letter has been Cc to
Vice President Joseph Biden
Secretary of State John Kerry
National Security Advisor Susan Rice
Senior Director for African Affairs on the National Security Council Gayle Smith
Senior Director for Democracy on the National Security Council Linda Thomas-Greenfield
Assistant Secretary of State for the Bureau of African Affairs Earl Gast