Wednesday, July 10, 2013

ኢሕአዴጎች እንደራደር እያሉ ነዉ – በደሴ ፣ ጎንደር ቅስቀሳው ቀጥሏል

ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም

የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት፣ በጎንደርና በደሴ የሚያደርጉትን ቅስቀሳ ቀጥለዉበታል። በደሴ ወረቀቶች እየተበተኑ፣ ፔትሽኖችም እየተሞሉ ሲሆን፣ በመኪና ላይ በመሆንና በየሰፈሩ በመዘዋወር በላውድ ስፒከር የትግል ጥሪ እየተላለፈ ነዉ።

እንደዚያም ሆኖ ግን ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ ባህሪዉ ነዉና፣ አፍራሽ እርምጃዎችን ከመዉሰድ አልተቆጠበም። ላለፉት ሃያ አመታት እንዳደረገዉ፣ የሕዝብን መሰረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችንና ሕገ መንግስታዊ መብቶች ለማፈን ደፋ ቀና እያለ ነዉ። አቶ ነብዩ ፣ የፍኖት ጋዜጣ ዋና ኤዲተር እንደገለጹት « መንግስታዊ ሽፍታነቱን ገፍቶበታል» ። ዛሬ ጠዋት ሐምሌ 3 ቀን በደሴ ከተማ የቅስቀሳ ተልእኳቸዉን ለመወጣት፣ ከአዲስ አበባ የተጓዙትን የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖት ነጻነት ጋዜጠኛ የሆነዉን አቶ ወንደወሰን ክንፈን በማገት «እንደራደር» በማለት ላይ ይገኛል።

dessie«አግተዉ እንደራደር የሚሉት ሽፍቶች ናቸው። መንግስት አግቶ እንደራደር ሲል ሽፍታነቱ በአደባባይ መረጋገጡ ነዉ» ያሉት አቶ ነብዩ «አንድነት የፓርቲዉ ጽ/ቤት እስኪዘጋና አባላቱ እሥር ቤቶችን እስኪሞሉ ሕዝባዊ ንቅናቄዉ ይቀጥላል» የሚል የጸና አቋም አባላቱና ደጋፊዎቹ እንዳላቸው አስረድተዋል። ፓርቲው ያነሳዉ ሕዝባዊ ጥያቄ በመሆኑ «የአንድነት አመራሮችና አባላት መስዋእት ቢሆኑም ሕዝቡ ትግሉን ከዳር እንደሚያደርሰው አንጠራጠርም» ሲሉም ትግሉ ወሳኝ ምእራፍ ላይ እንዳለ ሳይጠቁሙ አላለፉም።

የሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ በአዲስ አበባ በጠራው ፣ መኢአድና አንድነትም በደገፉት የሰላማዊ ሰልፍ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ በአገዛዙ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ማሰማቱ ይታወቃል። በወቅቱ ሰልፈኞቹ ባለፉባቸው መንገዶች ዙሪያ አንድ የተዘጋ ሱቅ እንዳለነበረ፣ አንድ ጠጠር እንዳልተወረወረና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሰልፉ እንደተጠናቀቀ የሚታወቅ ነዉ። የአንድነት ፓርቲ፣ በአንድ ጊዜ በደሴና በጎንደር ከተሞች የጠራቸው ሰላማዊ ሰልፎች ሕዝባዊ እንቅስቃሴዉ፣ አዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፣ አገር አቀፍ መሆኑንም በግልጽ ያሳየ ነዉ።

ለሚደረጉት እንቅስቃሴዎች የሚያስፈልጉ ከፍተኛ ወጭዎችን አገር ቤት ያለው ድሃዉ ሕዝብ፣ በራሱ ተነሳሽነት በስፋት እየሸፈነዉ እንዳለ እየገለጹ ያሉት የአንድነት አመራር አባላት፣ ዳያስፖራዉ በአገሩ ጉዳይ ላይ እንግዳ ሆኖ፣ ተነጥሎ መቆም እንደሌለበት፣ ሁኔታዎችን በቅርበት እንዲከታታልና የድርሻዉንም ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል።

Many detained, harassed in Southern Ethiopia after protest

ESAT News  July 9, 2013

Over 300 protesters, who called for the release of their leaders in Selam Ber town, Gamogofa Zone of Southern Ethiopia, have been detained and harassed by police on Sunday July 7, 2013.  Police have beaten and detained teenagers as young as 13 years old. Berhanu, a resident of the town said, the acts of the police was not even committed by the “ruthless Derg” during the previous regime.

Mesbo Madalcho, an elderly who was one of those that represented the protesters in Awasa city, said the police assailed the protesters when they gathered to voice their concerns peacefully.  A prison guard said to ESAT that although over 300 prisoners had appeared before Court, the prisoners said they had no confidence in the court and refused to be tried.  Severely beaten youth have been refused medical care.

Daniel Shibeshi, native of the area and representative of the Unity for Democracy and Justice (UDJ) Southern Ethiopia, said the main cause of the protest was the government’s refusal to respond to the “identity, good governance and development questions of the people”.  Daniel said, currently the only people seen roaming in the town are members of the Defense Force and police. Yesegat Sentan, Administrator of the Woreda, said he was in a meeting when approached by ESAT.

በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ450 በላይ መድረሱ ታወቀ

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል።

ወደ  አርባምንጭ እስር ቤት ከተላኩት መካከል አቶ አማኑኤል ጎቶሮ ፣ ደፋሩ ዶሬ ፣  እዮብ ጦና፣  ሻምበል ሻዋ፣ አልመሳ አርባ፣ አቶ ባንቲርጉ ሄባና፣ ወ/ሮ ጊፍታነህ ፈርአ፣ ባሻ ፋንታሁን ታደሰ፣ አቶ አበራ ገ/መስቀል፣ መ/ር ዶለቦ ቦንጃ ፣ መምህር መሸሻ ማላ፣ አቶ ጴጥሮስ ሀላላ እና አቶ ቲንኮ አሻንጎ ይገኙበታል።

የወረዳው ፖሊስ በዛሬው እለት 15 የሚሆኑ ወጣቶችን ከእስር ለመልቀቅ መፈለጉን ቢያስታውቅም፣ “እስረኞቹ ግን መጀመሪያውኑ ለምን አሰራችሁን አሁንስ በምን ምክንያት ትለቁናላችሁ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው እስካሁን እንዳልተለቀቁ ታውቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው በከተማዋ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንደተናገሩት ፖሊስ ምግብ ከሚያቀብሉ ሴቶች እና ልጆች  በስተቀር ሌሎች ነዋሪዎች ወደ አካባቢው እንዳይጠጉ በመከልከሉ የእስረኞችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ከ470 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ኢሳት ከ86  በላይ የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል።  ከእስረኞች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው በሙያቸው ረዥም ዓመታትን ያገለገሉ  ከ22 የማያንሱት ደግሞ የኢህአዴግ አመራር አባላት የነበሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ሥራ አጦች፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ሌክቼሬሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፤ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው፡፡

አካባቢው ዛሬም በመከላከያ እና በልዩ ፖሊስ አባላት እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል
እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ማሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Tuesday, July 9, 2013

አንዱአለምና ጋዜጠኛ እስክንድር የኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ

የአንድነት ፓርቲ የህዝባዊ ንቅናቄ ግብረሀይል፣ የሶሻል ሚዲያ ኮሚቴ አባላት የነፃነት ታጋዮቹን አንዱአለም አራጌንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጎበኙ፡፡ የሶሻል ሚዲያ አባላቱ ትላንት በቃሊቲ እስር ቤት ባደረጉት ቆይታ የአንዱአለም እና የእስክንድር መንፈሳዊ ጥንካሬ እንዳስደሰታቸው ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የነፃነት ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አበረታች መሆኑን አስምረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በንቅናቄው መሳተፍ እንዳለበት መክረዋል፡፡ ታጋዮቹ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለጎንደርና ለደሴ መልዕክት እተላልፈዋል፡፡


ወጣቱ የነፃነት ታጋይ አንዱአለም አራጌ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነፃነቱ በሰላማዊ መንገድ መታገል አለበት ካለ በኋላ “በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ በተጠሩት ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የጎንደርና የደሴ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ማሰማት አለበት፡፡ ሰላማዊ መሆናችንን ለሁሉም ወገን ማስመስከር ዘለብን” ብሏል፡፡


ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ ኢትዮጵያ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ብሔራዊ ውርደታችንን የሚያሳይ መሆኑን አስረድቶ “የጎንደርና የደሴ ነዋሪዎች በህዝባዊ ንቅናቄው ተሳተፉ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ በንቃት ተሳተፉ ድምፃችሁን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሰሙ፡፡ ሳር እንኳን እንዳይበጠስ ጠጠር እንኳን እንይወረወር” ብሏል፡፡


 ምንጭ ፍኖተ ነፃነት

ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ (ወያኔ) ኢምባሲ

July 9, 2013

(ECADF) – ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና በተለይም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ የሚታወቀው የአውራምባ ታይምስ ኢዲተር ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ (የወያኔ ኢምባሲ) ሲገባ መታየቱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?ሰኞ፣ ጁላይ 8፣ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በሗላ 4 ሰዓት ላይ ነው ዳዊት ከበደ ወደ ግርማ ብሩ ቢሮ ከሌሎች ካድሬዎች ጋር ሲገባ የታየው።

የዋሽንግተን ምንጮቻችን ጉዳዩን እንዳብራሩት ከሆነ የኢምባሲው ሰራተኞች አመሻሹ ላይ ወደየቤታቸው ሲሄዱ ያስተዋሉ ሲሆን ዳዊት ከበደ ግን ከገባበት ቢሮ ለሰዓታት ሲወጣ አልታየም።

ዳዊት ከበደ በባለቤትነት ያስተዳድረው የነበረው “የአውራምባ ተይምስ ጋዜጣ” ባልደረቦች በወያኔ ቁንጮዎች የሀሰት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ቤት በመሰቃየት ላይ እያሉ ነው ወደ አሜሪካን ሀገር ቪዛ ተመቶለት የወጣው። ሁኔታው በአንዳዶች ላይ ጥርጣሬን አጭሮ የነበረ ሲሆን፣ ይባስ ብሎ ዳዊት ከበደ አወጣጡን በተመለከተ የሚናገረው የተጣረሰ ታሪክ ይበልጥ

 እንዲጠራጠሩት አድርጓቸዋል።

በቅርቡ እየወጡ ባሉት መረጃዎች መሰረት ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የመቀጠር ፍላጎት አሳይቶ የነበረ ሲሆን.. በተለያዩ ምክንያቶች ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

ይህ በዚህ እንዳለ “አለማቀፉ የበቃ ንቅናቄ በኢትዮጵያ” (BEKA – Global Civic Movement for Change in Ethiopia) ዳዊት ከበደ በውይይት መድረኩ እንዳይሳተፍ መታገዱን ለአባላቱ ባሰራጨው ደብዳቤ አሳውቋል።

የበቃ ንቅናቄ ባሰራጨው ደብዳቤ ጨምሮ እንደገለጸው ከሆነ፣ ከወራት በፊት ዳዊት ከበደ በአንድ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ መኖሪያ ተጋብዞ በተገኘበት ወቅት በግብዣው ላይ የተገኙትን እንግዶች ተደብቆ ቪዲዮ ሲቀርጽ ተይዟል።

Monday, July 8, 2013

በጋሞጎፋ ዞን በተነሳው ተቃውሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታሰሩ ብዙዎችም ተደበደቡ

ሐምሌ ፩( አንድ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን 300 የሚሆኑትን   ደግሞ ማሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።

አንዳንድ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጹት ፖሊሶች እድሜያቸው ከ13 አመት በላይ የሆኑ ልጃገረዶችንና ወንዶችን ሳይቀር ከቤታቸው እያወጡ በመደብደብ አስረዋቸዋል።  አቶ ብርሀኑ የተባሉ ነዋሪ ፖሊሶች የፈጸሙት ድርጊት ጨካኝ በሚባለው የደረግ ስርአት ጊዜ እንኳን ያልታየ ነው ብለዋል ። የችግሩን አሳሳቢነት ለክልል ባለስልጣናት ለማስረዳት  አዋሳ ከሚገኙት የአገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሰቦ ማዳልጮ  እንደተናገሩት ፖሊሶቹ እርምጃውን የወሰዱት ጥያቄያቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማቅረብ በመሰባሰብ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነው ።

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የእስረኞች ጠባቂ ፖሊስ እንደተናገረው  300 የሚሆኑ እስረኞች በአንድ ክፍል ውስጥ  ታጉረው የሚገኙ ሲሆን፣ ፖሊስ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቢያቀርባቸውም፣ እስረኞቹ ግን በወረዳው ፍርድ ቤት ላይ እምነት የለንም በሚል ጥለው መውጣታቸውን ገልጿል።  በድብደባው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች ህክምና እንደተከለከሉም ተናግሯል።
የአካባቢው ተወላጅ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ የሆነው አቶ ዳንኤል ሽበሺ እንደገለጸው ችግሩ የተፈጠረው መንግስት የቀረበለትን የማንነት፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ባለመቻሉ ነው።

በሰላም በር ከተማ ዛሬ ሀምሌ 1፣  ከመከላከያ ሰራዊት  ፣ ከልዩ ሀይሎችና ከአካባቢው ፖሊሶች በስተቀር  በከተማ የሚንቀሳቀስ ሰው አለመመልከታቸውን አቶ ዳንኤል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳው አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ የስጋት ስንታን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ሳይሰካልን ቀርቷል።

ሰበር ዜና, ኢህአዴግ ደንግጧል!! በአዲስ አበባ የአንድነት አባላትን ማሰር ተጀምሯል

በአዲስ አበባ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት የበተነ የአንድነት አባል በአደራ ታሰረ፡፡

 አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መንግስት የማደናቀፍ ተግባሩን በአዲስ አበባም ጀምሯል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ሙሉጌታ ተፈሪ የተባለውን የአንድነት ፓርቲ የወረዳ 15 አባል ካዛንችስ አካባቢ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስሯል፡፡... ሙሉጌታ ካዛንችስ አካባቢ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጭ መታሰሩን ፖሊስ ተናግሯል፡፡

 የአባሉን መታሰር የሰሙት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ ግርማ ሰይፉና አቶ በላይ ፍቃዱ ካዛንችስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው ሙሉጌታ በህገወጥ መንገድ መታሰሩን በማስረዳት ተከራክረዋል፡፡ የጣቢያው ፖሊሶች ግን “ሙሉጌታን ያሰረው ፖሊስ ስለሌለ እሱ ሳይመጣ አይፈታም” በማለት “የአደራ እስር” ከጎንደር በተጨማሪ በአዲስ አበባም መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ አመራሮቹም “እኛም ወረቀቱን እየበተንን በመሆኑ እሰሩን” በማለት ተሟግተዋል፡፡


 ዘግይቶ በደረሰን ዜና የአንድነት አመራሮች የታሳሪውን ጉዳይ መከታተላቸውን ተከትሎ ሙሉጌታ ተፈሪ ክቤ በተባለች ፖሊስ “ተመርምሮ” ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሊወሰድ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

 የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን አባላት ዛሬ ጠዋት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ህዝባዊ ንቅናቄውን በአዲስ አበባ ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮ ተቀብለው ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ100ሺ በላይ የሆነ በራሪ ወረቀትም በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡
 
ምንጭ ፍ ኖተ ነፃነት

የሰሜን ጎንደር የአንድነት ሰብሳቢ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው

የሰሜን ጎንደር የአንደነት አመራሮችን ማሰር ቀጥሏል ዛሬ ዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አለላቸው አታለለ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በሚፈፅመው ህገወጥ እስርና እንግልት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንደማያስሰርዘው ገልጧል፡፡

አንድነት በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የክልሉ መንግስት የሰሜን ጎንደር አንድነት የፓርቲውን አመራሮች የማሰር ዘመቻ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ አቶ አለላቸው አታለለ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን በመንግስት ህገወጥ እርምጃ እንደማይቀለበስ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከፍተኛ አመራሮቹም በንቅናቄው ላይ ግምባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የሚመጣውን መስዋዕትነት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

Saturday, July 6, 2013

በግብፅ ያየነው ህዝባዊ ትዕይንት በኢትዮጵያም እንደምናየው ጥርጥር የለንም!

July 6, 2013
ስምንቶቹ

በአለማችን እጅግ አስከፊ አምባገነናዊ ስርዓቶች ታይተው አልፈዋል:: በቅርቡ ካየናቸው አምባገነኖች መካከል የግብፁ ሙባረክ፣ የቱኒዚያው ቤን አሊ፣ የሊቢያው ጋዳፊ፣ እንዲሁም የኛው መለስ ዜናዊ ይጠቀሳሉ። ለአምባገነናዊ ሥርዓት መፈጠር በዋናነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ ከጥቂት ግለሰቦች ከልክ ያለፈ የበላይነትን የማፍቀር አስቀያሚ ባህሪ የመነጨ በመሆኑ፤ እንደነዚህ ያሉ ሰይጣን ግለሰቦች አሁንም ድረስ በሰው ልጅ መሃል መብቀላቸው አይቀሬ ነው። በተለይ በአፍሪካ የሚገኙ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት ውስጥ አምባገነን ሲገረሰስ ሌላ አምባገነን ሊወጣ እንደሚችል አስቀድሞ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። አምባገነኖች የግለኝነት ባህሪያቸውን በሚገርም መልኩ መቆጣጠር ባለመቻላቸው ምክንያት በሚችሉት አቅምና በሚያገኙት ቀዳዳ ሁሉ የግል ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግ መሞከራቸው አይቀሬ ነው። ለዚህም በቅርቡ በግብፅ አምባገነኑ ሙባረክን ለማስወገድ በአንድነት የወጣው ህዝብ የእግር ኮቴ ሳይደርቅ ዳግም አምባገነን ለመሆን ሲሞክሩ የተወገዱት ፕሬዚዳንት ሙርሲን እንደ አብነት ማስታወሱ በቂ ይመስለናል:: የኚህ ሰው ታሪክ በራሱ አምባገነንን ለመጣል በሚደረግ ትግል ውስጥ ሌላ አምባገነናዊ ሥርዓት ዳግም እንዳይመጣ ለማረጋረጥ ሊወሰዱ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች ስለመኖራቸው ጠቋሚ ነው። በዚህ ዙሪያም በቅርቡ ሃሳባችንን በስፋት ለማካፈልና ለመወያየት እንሞክራለን።

የሁሉም አምባገነናዊ ሥርዓቶችና በጭቆናቸው ቀንበር ስር ወድቀው የሚሰቃዩ ህዝቦች ብሶቶች ተመሳሳይነት በፅሁፋችን ርዕስ ባነሳነው ሃሳብ ዙሪያ መወያየቱ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራሉ። በተጨማሪም አበው “ነገር በምሳሌ …” እንዳሉት፤ በቅርቡ “የአረብ ስፕሪንግ” ተብሎ የሚጠራው በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ የተካሄደውን የህዝብ አመፅ እንደ አብነት ማንሳቱ ጠቃሚ ይመስለናል::

ቱኒዚያ የአረብ ስፕሪንግ ጀማሪዋ ሃገር መሆኗ ይታወቃል:: የህዝብ አመፁ በቱኒዚያ በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቀና ቤንአሊም ከተባረረ በኋላ ይህ የህዝብ አመፅ ወደ ግብፅ ሊሄድ ይችል ይሆን? በሚለው ጥያቄአዊ ሃሳብ ላይ የፖለቲካ ጠበብቶች ብዙ ብለው ነበር:: በተለይ ቱኒዚያ ግብፅ አይደለችም ስለዚህ የህዝብ አመፁ እንደ ቱኒዚያ ሁሉ በግብፅ ሊከሰት አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ ደግፈው ምክንያታቸውን ሲደረድሩ የነበሩ ብዙ ናቸው::

ይህንን ቱኒዚያ ግብፅ አይደለችም የሚል ሃሳባቸውን ለማስረዳት ሲጠቅሷቸው ከነበሩት ምክንያቶች መካከል በቱኒዚያ ህዝብ መካከል ያለው የሙስሊሙና የክርስትናው ሃይማኖቶች ውጥረት ግብፅ ካለው እጅግ በጣም ያነሰ ስለሆነ በግብፅ ህዝብ አንድ ሆኖ ሊታገል አይችልም፣ ቤንአሊ እንደ ሙባራክ ጨካኝ አይደለም፣ ሙባራክ ጠንካራ የጦር ሰራዊት አለው ስለዚህ በቀላሉ ከህዝብ መካከል ጥቂቶችን ገድሎ ሊቀጨው ይችላል፣ ቱኒዚያዎች ከግብፆች የበለጠ የተማሩ ናቸው፣ የፌስቡክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎችንም ቱኒዚያዎች በስፋት ተጠቃሚዎች ስለሆኑ ግብፅ ውስጥ እንደ ቱኒዚያ ያለ አመፅ ሊከሰት አይችልም፣ ሌላም ሌላም… እያሉ ትንታኔዎችን ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወቃል:: ይታዩአቸው የነበሩት ምክንያቶች ግብፆች በሙባረክ አምባገነናዊ አገዛዝ ለአመታት ብዙ ተረግጠዋል፣ ተጎድተዋል፣ ተበዝብዘዋል፣ እነርሱ በድህነት እየማቅቁ ሳሉ ጥቂት ግለሰቦች በሃብት ሲትረፈረፉ ምንም አላደረጉም የሚሉት ብቻ ነበሩ:: ነገር ግን ፍፃሜው ላይ የታየው እውነታ፤ ግብፆች እጅግ ማራኪ የሆነ የህዝብ ትብብርና ሰላማዊ ተጋድሎን በአደባባይ ለአለም ህዝብ በሚገባ ማሳየታቸውና፤ አስፈሪና ጨካኝ እየተባለ ሲነገርለት የነበረውን የሙባረክ ስርዓት ከትከሻቸው ላይ አሽቀንጥረው መጣል መቻላቸው ነው:: በዚህ ዙሪያ ምሁሮቹና ፖለቲከኞቹ ያለማስተዋል ችላ ብለውት የነበረው ዋናው ቁምነገር የህዝብ እምቅ ሃይል በአምባገነኖች አስፈሪነት ሊሟሽሽ ፈፅሞ እንደማይችል ነበር::

የወያኔ/ኢህአዴግ ቡድን ስልጣን ከተቆናጠጠበት ሰአት ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጅግ ስር የሰደዱ ችግሮችንና በደሎችን ሲፈፅም ኖሯል:: የኢትዮጵያ ህዝብ የተጫነበት ህመም ከግብፅና ከቱኒዚያ እጅግ የከፋ ነው:: በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ 11ኛው ሰአት ላይ እንደሚገኝ ለሁላችንም ግልፅ ነው:: ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደ ግብፆቹ ሁሉ፤ የወያኔ/ኢህአዴግ ጦር ሰራዊት መብዛት፣ ፍቅር እያለው በዘር በሃይማኖት ሳይወድ መከፋፈሉ፣ ጥቂቶች ሲበለፅጉ እርሱ ግን በድህነት መማቀቁ፣ በተቃውሞ ሰልፍ ብሶቱን ለማሰማት በወጣ ቁጥር በአጋዚው የወያኔ ሃይል በተደጋጋሚ በግፍ መጨፍጨፉ፣ መታሰሩና፣ ስቃይን መቀበሉ የህዝብን እምቅ ሃይል በበለጠ ያጎለብትለት እንጂ ሊያዳክመው ፈፅሞ አይቻለውም::
ነገር ግን በግብፅ የተደረገው የተሳካ አመፅ ዝም ብሎ በመላ የመጣ አይደለም:: የአመፁ አስተባባሪዎችና አንቀሳቃሾች እጅግ በጣም በሳል ስራዎችን ስለሰሩ፣ የህዝብን የልብ ትርታ እጅግ አድርገው በመረዳታቸው፣ ቁስሉ ስለተሰማቸው፣ የሙባረክ ስርዓት ሃገርንና ህዝብን እንደሚያጠፋ በመረዳት እውነታውን ለህዝብ ስላመላከቱት፣ ብሎም ህዝብ ወዶና በቃኝ ብሎ ትግሉን እንዲቀላቀል ስላስቻሉት ነው:: የኛም ፖለቲከኞችና የድርጅት መሪዎች ፍፁም የሆነ የአመለካከትና የአካሄድ መሰረታዊ ለውጥ በማድረግ፤ የህዝብ ቁስል ሊያማቸው፣ እውነታውንም ሊነግሩትና፣ ወደ ህዝብ ገብተው ከዚህ ስቃይና መከራ ሊታደጉት ይገባል:: ስለሆነም እጅግ ብዙ ስራዎች እንደሚጠብቃቸው መረዳት ያለባቸው ይመስለናል:: ከግብፆቹ ተምረው እራሳቸውን ካስተካከሉ የምንመኛትን፣ ለሁሉም እኩል የሆነችና፣ የህዝብ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን በቅርቡ እንደምናያት ጥርጥር የለንም::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

http://ecadforum.com/



Amnesty International in Canada launched petition campaign to the release of Eskinder Nega

Eskinder Nega: Journalist unjustly jailed in Ethiopia

Please add your name to Amnesty International’s petition to the Ethiopian authorities to release Eskinder Nega immediately.

Eskinder’s story

Amnesty International for the release of Eskinder NegaEskinder Nega is an Ethiopian journalist and human rights activist.

Eskinder has been subjected to outrageous injustices. He was sentenced to 18 years in jail for writing articles calling for freedom of expression and an end to torture in Ethiopia.

Sadly, this is not the first time that Eskinder has been jailed for his activism. Eskinder and his wife, Serkalem, a newspaper publisher, were previously jailed for speaking out against the government in 2005 and released in 2007 after continued campaigning by Amnesty International.

His previous arrest came after the Ethiopian government ordered a violent crackdown on post-election protests in 2005. Security forces reportedly killed nearly two hundred people. Eskinder and Serkalem wrote and published articles criticizing the government’s actions. For this, they were both arrested and put in prison.Their son, Nafkot, was born in that prison.
For Eskinder, this was one more brutal act of oppression in a life spent being hounded by his government for defending human rights. Few families have sacrificed more for their people.

In recent years, the Ethiopian government has clamped down alarmingly on its citizens for speaking out. According to Serkalem, “freedom of expression and press freedoms are at their lowest point.” Now the regime has enacted a “terrorism” law that they use to silence anybody critical of them.

They used these laws to threaten Eskinder. To ban him from writing. To force Serkalem to stop publishing. To terrorize their family and threaten Eskinder with the death penalty.

And now – to arrest Eskinder alongside many other prominent journalists.

Amnesty International believes Eskinder Nega is a prisoner of conscience detailed solely for his peaceful and legitimate activities as a journalist. Join our call for his immediate release.

Human Rights in Ethiopia

In Ethiopia, the authorities routinely use criminal charges and accusations of terrorism to silence dissenters. Repression of freedom of expression has increased alarmingly in recent years. The Ethiopian government has systematically taken steps to crush dissent in the country by jailing opposition members and journalists, firing on unarmed protesters, and using state resources to undermine political opposition. More than a hundred other Ethiopians, including nine journalists, were charged under the antiterrorism law. About 150 Ethiopian journalists live in exile — more than from any other country in the world.

Use this form to add your name to Amnesty’s call for the Ethiopian government to immediately and unconditionally release Eskinder Nega from prison.

ከእስራኤል አገር በደህንነት ሙያ ሰልጥነው ስራ ከጀመሩት መካከል የተወሰኑ ሰራተኞች መታሰራቸው ታወቀ

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከእሰራኤል አገር በደህህነት ሙያ ሰልጥነው በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት  እና በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ከተመደቡት መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የደህንነት አባሎች ታሰሩ።

አባሎቹ የታሰሩት መረጃውን ለኢሳት አቀብላችሁዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። እስካሁን ምን ያክል የደህንነት ሰራተኞች ተይዘው እንደታሰሩ አልታወቀም። ኢሳት ከአስተማማኝ የደህንነት ምንጮች ባገኘው መረጃ ስልጠናውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ከተመለሱት 987 ሰዎች መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት የአንድ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ተመድበዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲን ለማነጋገር ሙከራ አድርገን ሳይሳካ ቀርቷል።

Friday, July 5, 2013

አንድነት ጎንደር ላይ የጠራው ሰልፍ ለሓምሌ 7 ማስተላለፉን አስታወቀ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ለሓምሌ 7ቀን 2005 ዓ.ም ማስተላለፉን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጨ አስታወቀ፡፡ ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ የታሰሩ አባላቱ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የስራ አስፈፃሚና የብሔራዊ ም/ቤት አባላት በሰለላማዊ ሰልፉ ላይ በመሳተፍ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውም ተገልጧል፡፡

አንድነት ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በጎንደር የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ለሓምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ያስተላለፈው መንግስት ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ዕለት የሀይል እጥተት አለብኝ የሚል ጥያቄ በማቅረቡ መሆኑን ገልጧል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግዛቱ አቢዩ ጌታው አንድነት ሰላማዊ ሰልፉ እንዳያደረግ ከመወሰናቸው በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ከአማራ ክልላዊ መስተዳደር ከመደበኛ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች በተጨማሪ ልዩ ግብረኃይል መቋቋሙን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልፀዋል፡፡ የከተማው ምክትል ከንቲባ በበኩላቸው ፓርቲው ሰኔ 30 ሊደረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲዛወር የጠየቁ ሲሆን የዞኑ የአንድነት ፓርቲ በበኩሉ ሰላማዊ ሰልፉ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. እንዲቀየር መወሰኑን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

የክልሉ መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን በማሰር ላይ ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁንም 10 አመራሮችና አባላት በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጮ ወረዳ ነዋሪ እና የአንድነት ፓርቲ የወረዳው አመራር አቶ ተገኝ ሲሳይ ከወረዳው ሳንጃ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው እስካሁን ያሉበት አይታወቅም፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በአብርሀጅራ ከተማ የታሰሩት 4 የአንድነት አባላትና አመራሮች ሰኔ 24 ቀን 2005ዓ.ም. በወረዳው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ለምርመራ የ14 ቀን ጠይቆ ተቀባጥነት አጥቶ ጠነበረ ቢሆንም በአስገራሚ ሁኔታ ዛሬ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ ይህንንም ተከትሎም ታሳሪዎቹ ከአርብ ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የርሃብ አድማ በማድረግላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በብሔራዊ ምክርቤቱ ባስወሰነው መሰረት በመላ ሀገሪቱ በሚደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና የብሄራዊ ም/ቤት አባላት ከፊት በመሆን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል፡፡

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/

Thursday, July 4, 2013

በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛ የመድረክ/አንድነት ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የብሮድካስት ባለሥልጣን በጀቱ እንዲቀነስና እንዲፈርስ ላቀረቡት ሞሽን (የውሳኔ ኃሳብ) ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በቂ ምላሽ ሳይሰጡ ቀሩ፡፡

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :- አቶ ግርማ ለፓርላማው ሁለት ሞሽን ያቀረቡ ሲሆን አንደኛው ሞሽን መንግስት በ2006 በጀት ዓመት የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ከመንግስት ባንኮች ሊበደር ያሰበውን 16 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በግማሽ ያህል (8 ቢሊየን ብር) በመቀነስ በተለይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች የብድር ድጋፍ እንዲውል የሚጠይቅ ነው፡፡

ሁለተኛው የብሮድካስት ባለስልጣን ብሮድካስትን ከማስፋፋትና ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ለማቀጨጭ ተግቶ እንደሚሰራ፣ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳይኖር ያደረገ ደካማ መ/ቤት መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ በጀት ከሠራተኞች የደመወዝ በጀት በስተቀር እንዳይፈቀድለት፣ወደፊትም እንዲዘጋና ፍቃድ የመስጠት ስራ በሌሎች መ/ቤቶች ተደርቦ እንዲሰራ የሚጠይቅ ነበር፡፡

አቶ ኃ/ማርያም ይህንን ሞሽን በመቃወም በሰጡት ምላሽ ባለስልጣኑ ከ20 የማያንሱ የማህበረሰብ ራዲዮ፣ 5 የግል ራዲዮ ጣቢያዎችን ፣በየክልሉ የመንግስት ቴሌቪዝን ጣቢያዎች እንዲስፋፉ መስራቱን፣ ማስታወቂያ ሚ/ር ሲፈርስ የፕሬስ ቁጥጥር ወደእሱ መምጣቱን፣ የማስታወቂያ አዋጅ ስልጣን የሚሰጠው ለሱ መሆኑን በመዘርዘር በተዘዋዋሪ ሥራ የሚበዛበት ተቋም በመሆኑ መፍረስና በጀቱም መቀነስ እንደሌለበት አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም የብሮድካስን ስርጭትን ወደ ዲጂታል ለማዛወር እየተሰራ መሆኑን፣ ባለሃብቱንም ያን ጊዜ ማሳተፍ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ጠ/ሚኒስትሩ በአቶ ግርማ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ወገኖች በተደጋጋሚ የብሮድካስት አዋጁ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለግል ባለሃብቶች ለመፍቀድ የሚያስችል ሆኖ እያለ በተግባር ለምን ተከለከለ በሚል ለሚነሱ ቅሬታዎች ምንም ዓይነት ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡

የብሮድካስት አዋጅ ከወጣ ከ12 ዓመታት በላይ የተቆጠረ ቢሆንም ባልታወቀ ሁኔታ ባላስልጣኑ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ፈቃድ ለባለሃብቶች ለመስጠት አልቻለም፡፡ በአንድ ወቅት አቶ በረከት ስምኦን ስለጉዳዩ በፓርላማ አባላት ተጠይቀው የሕዝቡ ንቃተ ሕሊና ባልዳበረበት ሁኔታ የግል ቴሌቪዥን መፍቀድ እንደማይቻል በመጥቀስ አስፈጻሚው አካል ከሕግ አውጪው በላይ መሆኑን በተግባር ማረጋገጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

በተያዘም ፓርላማው ያልተጠበቁ ተሿሚዎችን ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴርን ከወ/ሮ ገነት ዘውዴ ቀጥሎ ገድለውታል በሚል ክፉኛ የሚተቹትን አቶ ደመቀ መኮንን ከተደራቢ የትምህርት ሚኒስትር ሃላፊነታቸው በማንሳት በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ሥራቸው እንዲቀጥሉ፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልል ፕሬዚዳንትነት በማንሳት የትምህርት ሚኒስትር አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡

የጠ/ሚኒስትሩ የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ አማካሪ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሬድዋን ሁሴን በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር፣ አቶ መኮንን ማንያዘዋልን ወደፕላን ኮምሽን በማዛወር በእሳቸው ምትክ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር በመሆን አቶ አህመድ አብተው፣ የአዲስአበባ ከንቲባ እንደሚሆኑ እየተነገረላቸው ባሉት አቶ ድሪባ ኩማ ምትክ የትራንስፖርት ሚኒስትር የፖሊስ ኮምሽነር የነበሩት ወርቅነህ ገበየሁ ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ወደክልል በተዛወሩት ወ/ሮ አስቴር ማሞ ምትክ ወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር፣ በድክመት በቅርቡ በተነሱት አቶ ብርሃን ኃይሉ ምትክ አቶ ጌታቸው አምባዬ የፍትህ ሚኒስትር፣ በሙስና በተከሰሱት አቶ መላኩ ፈንታ ምትክ አቶ በከር ሻሌ በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ በአካባቢ ሳይንቲስቱ በዶ/ር ተወልደ ገ/እግዚአብሔር ምትክ አቶ በለጠ ታፈረ የአካባቢና ደን ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ለፓርላማ ሳያቀርቡ በትላናትናው ዕለት በሥራ አፈጻጸማቸው ደካማ የሆኑትን እና የሕዝብም ድጋፍ የራቃቸውን አቶ በረከት ስምኦንን እና አቶ ኩማ ደመቅሳን በሚኒስትር ማዕረግ የጠ/ሚኒስትሩ የጥናትና ምርምር አማካሪ አድርገው መሾማቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ አቶ ኃ/ማርያም ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ የህዝብ ግንኙነት ሥራ ድክመት መኖሩንና ስራውን ለማጠናከር መታሰቡን የገለጹ ሲሆን የአቶ በረከት መነሳት  ከዚሁ ትችት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ሪፖርተርና ፎርቹን ጋዜጦች አቶ በረከት በአለቃ ጸጋየ በርሄ የተያዘውን የጸጥታ አማካሪነቱን ቦታ ይይዛሉ በማለት መዘገባቸው ይታወቃል። አንዳንድ ወገኖች አዲሱ ሹመት የአቶ በረከት የስልጣን ፍጻሜ መጨረሻ መጀመሪያ ነው በማለት ከአቶ አርከበ እቁባይ ታሪክ ጋር በማዛመድ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ይሰማሉ።

ጠ/ሚኒስትሩ በዛሬው ሹመት ይካተታሉ ተብለው የተጠበቁትን የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነር፣ የመረጃና ደህንነት ሚኒስትር ሹመቶችን ሳያቀርቡ ቀርተዋል፡፡

ወያኔ እያለ ሙሰኝነትን ማጥፋትም መዋጋትም አይቻልም!

         
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ባለፉት ሃያ አንድ አመታት ማንነቱን ከገለጸበትና የዚህ ዘረኛ ስብስብ ተክለ ሰዉነት ቀዳሚ መገለጫ ከሆኑ ሁለት ትልልቅ ባህሪያት ዉስጥ አንዱ ሙሰኝነት ሲሆን ሌላዉ ዘረኝነት ነዉ። የወያኔ ስርአት የተገነባዉ በሙሰኝነት ላይ የቆመዉም ለሙሰኝነት ነዉ። ወያኔንና ዘረኝነትን ነጣጥሎ ማየት እንደማይቻል ሁሉ ወያኔንና ሙሰኝነትንም ነጣጥሎ መመልከት በፍጹም አይቻልም። ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔና ስርአቱ በስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ሙሰኝነትም ይኖራል።

ወያኔ ባለፉት ሦስት ወራት ይህንን የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የአለም ህዝብ ጭምር በግልጽ የሚያዉቀዉን አስቀያሚ ገጽታዉን ለመሸፈን “ሙሰኝነትን አጠፋለሁ” በሚል ሽፋን አንዳንድ የሽንገላ እርምጃዎችን መዉሰድ ጀምሯል: አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ:: በዚህም እርምጃው የሙሰኝነትን ምንጭና ባላባቶች ሳይሆን ስርአቱ በሙሉ ድምጽ የይሁንታ ምልክት ሳይሰጣቸዉ ሙሰኘነት ዉስጥ የተዘፈቁ ትናንሽ ሙሰኞችን በማሰርና ፍርድ ቤት በማቅረብ አንዳንድ ለአገራቸዉ በጎና ቀና አስተሳሰብ ያላቻዉን ዜጎች ለማታለል ይሞክራሉ።

የወየኔን ዘረኛ አምባገነን ስርዐት ከቀደሙት ስርአቶች ለየት የሚያደርገዉ ነገር ቢኖር ስርዐቱ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ፤ የትምህርት እድል እንዲሁም የስራና በኢኮኖሚ የመበልጸግ እድል የሚሰጠዉ “ወርቃማዉ ዘር” እያለ ለሚጠራዉ የራሱ ወገን መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ያለ የለለ ጥሪት ያለገደብ እንዲቦጠቡጡ የሙሰኝነቱን በር ወለል አድርጎ የከፈተዉም ለዚሁ “ወርቃማዉ ዘር” እያለ ለሚጠራዉ ወገን መሆኑም ጭምር ነዉ። ይህም ኢትዮጵያ ዉስጥ ሙሰኝነት የተፈቀደላቸዉና ያልተፈቀደላቸዉ ዜጎችና ተቋሞች እንዳሉ በግልጽ ያሳያል። በቅርቡ በዜና ማሰራጫዎች ሙሰኝነታቸዉ ተጋልጦ ታሰሩ እየተባለ የተነገረላቸዉ ግለሰቦች ወያኔ ከፈቀደላቸዉ በላይ በሙሰኝነት የከበሩ ወይም ከከፍተኛዎቹ የወያኔ ሹሞች ጋር የስልጣን ሽሚያ ዉስጥ የገቡ ግለሰቦች ዳውላዎች ናቸዉ።

ባለፈዉ ሳምንት ማብቃያ ላይ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች የሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በግልጽ እንደሚያሳየዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሙሰኝነት ላይ እንዲሰማራ ብቻ ሳይሆን የሙሰኝነቱን ዘርፍ እንዲመራ በህግ ያልተጻፈ ሀላፊነት ከተሰጠዉ ተቋም አንዱ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ነዉ። ባለፈዉ ሚያዚያ ወር የፌዴራሉ ዋና ኢዲተር መስሪያ ቤት ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኗል ብሎ በሪፖርቱ ካሰፈረዉ አምስት ቢሊዮን ብር ዉስጥ ሦስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮኑ የመከላከያ ሚኒስትር መሆኑ የሚታወስ ነዉ። እዚህ ላይ አንድ የሚገርመን ነገር ቢኖር በቅርቡ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ አንደተናገሩት ከሆነ የኢትዮጵያ ፓርላማ “ሚስጥር ለመጠበቅ” በሚል ሽፋን በሙሰኝነት እንዳይጠየቅ ህግዊ ሽፋን የሚሰጥ አዋጅ በማርቀቅ ላይ የሚገኘዉ ይህንኑ በሙሰኝነት የተዘፈቀዉን የመከላከያ ሚኒስትርን ሆድ ለመደበቅ ነዉ።

ለመሆኑ ሀላፊነቱና የስራ ድርሻዉ አገርን ከዉጭ ጠላት መጠበቅ የሆነዉ የወያኔ መከላከያ ተቋም በንግድ፤ በእርሻ፤ በኮንስትራክሺንና በከባድ እንዱስትሪ ግንባታ የስራ መስኮች ዉስጥ ያለቦታዉ ተዘፍቆ እየታየ ለምን ይሆን የዚህ ተቋም የሂሳብ መዝገብ በኦዲትሮች እንዳይታይ የሚደነግግ አዋጅ እንዲወጣ ያስፈለገዉ? ለምንድነዉ ጠ/ሚኒስትር ተብዬዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት በኦዲተር አይመረመሩም ያሉት?

መልሱ ቀላልና ግልጽ ነዉ። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማዘናጋት ሙስናን አጠፋለሁ ብሎ የጀመረዉ የዉሸት ዘመቻ ያነጣጠረዉ የአገሪቱን የመከላከያ ተቋም ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠሩት የወያኔ ጄኔራሎች ላይ በመሆኑ ነዉ። ወያኔ የሾማቸዉ የራሱ ኦዲተሮች አመታዊ የሂሳብ ቁጥጥር ሪፖርት በግልጽ እንደሚያመለክተዉ ከፍተኛ የሂሳብ ጉድለትና የመዝገብ አያያዝ ዝርክርከነት የታየባቸዉ ወያኔያዊ ተቋሞች የመከላከያ ሚኒስቴር፤ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የአገር ዉስጥ ደሀንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ ናቸዉ።

 ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከህወሃት አለቆቹ በተሰጠዉ ቀጭን ትዕዛዝ መሠረት ወንጀላቸዉን ለመደበቅ ህጋዊ ድጋፋ እንዲያገኙ የሚጣጣረዉም ለእነዚሁ ሦስት ተቋሞች ነዉ። እነዚህ ህዝብን ሰላም የነሱ፤ የአገሪቱን ሀብት ሙልጭ አድርገዉ የዘረፉና ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማያዉቁ ስግብግበች የሞሉበትን ተቋም ጭራሽ ህግ ሽፋን ከተጠያቂነት ዉጭ ማድረግ የበለጠ እንዲዘርፉና በህዝብ ደም እንዲነግዱ ህገ መሰነግስታዊ እዉቅና መስጥት ነዉ።

ወያኔ ያሻዉን ያክል አስቀያሚ ገጽታዉን ሸፍኖ ለህዝብና ለአገር የሚያስብ መስሎ ለመታየት ቢሞክርም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንኳን ሙሰኝነትን የመሰለ በአይን የሚታይ ጉልህ የወያኔ መታወቂያ ቀርቶ ወያኔ ለወደፊት ለማድረግ በዕቅድ የያዘዉን ሁሉ ከወዲሁ የሚያዉቅ ህዝብ ስለሆነ ሙሰኝነትንና በስልጣን መባለግን ለማጥፋት የመጀመሪያዉ ትግል ከወያኔ ዘረኞች ጋር መሆኑን ተረድቶ ትግሉን ቀጥሏል። ይህ የተጀመረ ህዝባዊ ትግል ወያኔንና ሁለቱን መንታ ልጆቹን ማለትም ሙሰኝነትና ዘረኝነት ከአገራችን ምድር እስኪነቀሉ ድረስ ይቀጥላል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Wednesday, July 3, 2013

በገንዳሆ ከተማ በመከላከያ ሰራዊትና ጸረ-ሽምቅ በሚባሉት ልዩ ሀይሎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውጥጥ በርካታ ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ ሰኔ 25፣ 2005 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰአት ከ30 ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና ጸረ-ሽምቅ እየተባሉ በሚጠሩ ሀይሎች መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ4 እስከ 7 የሚደርሱ  ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 2 የወረዳው ባለስልጣናት ደግሞ ቆስለዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ጸረ-  ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ከ 150-200 የሚደርሱ የመንግስት ታጣቂዎች ለወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና በሚል በቀድሞ ስሟ ሽንዲ በአዲሱ ስሟ ገንዳሆ ከተማ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተሰባሰቡ ሲሆን፣ ትናንት ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው ሰፍሮ ከሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ሌሊቱን ሙሉ ጎራ ለይተው ሲታኮሱ አድረዋል።

ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከመከላከያ 2 ከጸረ- ሽምቅ ሀይሎች ደግሞ 3 ሰዎች ሲገደሉ፣ አበበ የሚባል የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊና ሌላ ባለስልጣን ቆስለዋል። ከሟቾች መካከል ወረቀት የሚባለው ሰው አስከሬኑ ወደ ሳንጃ  ተልኳል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የሟቾችን ቁጥር ከተጠቀሰውም አሀዝ ይልቃል።

የወረዳው የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር አስማማው ስብሰባ ላይ በመሆናቸው መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል። ምሽት ላይ በድጋሜ ስንደውልላቸው ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በቅርቡ በመተማ ወረዳ ከመሬት ጋር በተያያዘ ከ50 እስከ 60 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ጫካ መግባታቸው  ይታወቃል። የአካባቢው ነዋሪዎች ብሎክ የሚል ስያሜ የሰጡትን መሬት የማከፋፈል ስርአት፣  የመንግስት ታጣቂዎች ሳይቀሩ ሲቃወሙት ቆይተዋል።


አባሎቻችንን በማሰር ሕዝዝባዊ ንቅናቄያችንን ማደናፍ አይቻልም!! አንድነትፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት የህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልቱ  የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለሰሜን ጎንደር ዞን ማወቅ ለሚገባቸው የመንግስት አካልና ለከተማ መስተዳድሩ አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ ከገባ ጥቂት ቀናት አልፈዋል፡፡

ምንም እንኳን ህግ አክብረን ሰላማዊ ትግላችንን ብንቀጥልም በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብርሃ ጅራ ከተማ የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ አንድነት ፓርቲ የሰጣቸውን ተልኮ ተቀብላችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን በተናችሁ ተብለው ከቅዳሜ ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ አቶ ማህሙድ ሸሪፍ፣ አቶ ጀማል ሰይድና አቶ አለሙ አባይነህ ፓርቲው የጀመረውን የሚሊዮኖች ድምፅ የሚያሰባስብ ፔቲሽን ለምን ታስፈርማላችሁ ተብለው ታስረዋል፡፡

ይህ ተግባር ህጉን ጠብቆ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፓርቲያችን ላይ አሁንም በገዥው ፓርቲ ህግ ጥሶ ሰላማዊ ሰልፉን የማደናቀፍ ተግባር እየተፈፀመ ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነው፡፡ ይህና ሌሎች የገዢው ፓርቲ እኩይ ድርጊቶች አንድነትን በፍፁም ወደኋላ ሊመልሱት እንደማይችሉ ማሳወቅ እንወዳለን ፡፡ ይህን በድፍረት እንድንናገር ያስቻለን ከዓላማ ቁርጠኝነታችን በተጨማሪ ህግ አክባሪነታችን ነው፡፡ ስለዚህ በቅስቀሳ ቡድኑ ላይ ከሚካሄደው ዛቻና ማስፈራሪያ ውጭ በተለያዩ ወረዳዎች የፓርቲያቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በፍፁም ሰላማዊነት እየሰሩ ያሉ አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ትግላችንን ሊቀለብሰው እንደማይችል ተገንዝቦ መንግስት ከህገ ወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

እነዚህ አባሎቻችንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን ምንም አይነት ህገ ወጥ እርምጃ መብታችንን ከመጠየቅ እንደማይገድበን በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና የፀጥታ ሀይሎች በአንድነት አባላት ላይ እየወሰዱ የሚገኙትን እስርና ማስፈራሪያ ፊትለ ፊት በመቃወም ቁርጠኝነቱንና አጋርነቱን በማሳየቱ አንድነት ፓርቲ ለጎንደር ህዝብ የአክብሮት ምስጋናውን ያስተላልፋል፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

UDJ
 

የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አዋጅ ጸደቀ

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡

የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ እና የደህንነት አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም በአገር ውስጥ የጸረ ሸብርተኝነት እና የበረራ ደህንነትን የማስጠበቅ ሥራዎችን በኃላፊነት
ይሰራል።

መ/ቤቱም ካለበት ህገመንግስታዊና አገራዊ ሃላፊነት እንዲሁም ካለው ስልጣንና ተግባር በመነሳት በሚኒስቴር መ/ቤት ፕሮቶኮል ደረጃ እንደሚሰራ በአገሪቱም የተለያዩ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን ከፍቶ እንደሚንቀሳቀስ አዋጁ ያስረዳል፡፡

ማንኛውም ሰው በመ/ቤቱ መረጃ ሲጠየቅ የመተባበር፣ የሠጠውንም መረጃ በሚስጢር የመያዝ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ይህንን የተላለፈም በወንጀል እንደሚጠየቅ ደንግጓል፡፡

አገሪቱ በተለይም በኤደን ባህረሰላጤ አካባቢ የሚስተዋለውን ተለዋዋጭ የስጋት ምንጭ ለመከላከልና ለመቋቋም የሚቻለው ብቃት ያለው የመረጃና ደህንነት ተቋም ሲገነባ ነው በማለት አዋጁ የወጣበትን ምክንያት አስቀምጧል።

የአዋጁን መጽደቅ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ተቃውመውታል። አዋጁ አዎንታዊ ጎኖች እንዳሉት የገለጹት አቶ ግርማ ለትርጉም አሻሚ የሆኑ አሻሚ ድንጋጌዎች መካተታቸው ለተቃውሞአቸው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ እንዲሁም ኢህአዴግ የተለያዩ ደህንነት መስመሮች  እንዳሉዋቸው አስታወሱት አቶ ግርማ ምናልባትም አዲሱ ጠ/ሚ የደህንነት መስመሩ አንድ ወጥ በሆነ እና እርሳቸው በሚያዉቁት መንግድ ብቻ እንዲህ   በመፈለጋቸው የተደነገገ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ተናግረዋል

በአዲሱ አዋጅ አንድ የደህንነት ሰራተኛ አስቸጋሪ ሁኔታ ካልገጠመው በስተቀር በዜጎች ላይ አንድ ጥፋት ቢፈጽም ሊጠየቅ እንደሚችል በአዋጁ መደንገጉን የገለጹት አቶ ግርማ ፣ ይሁን እንጅ “አስቸጋሪ ሁኔታ” የሚለው ሀረግ ለትረጉም አሻሚ ነው በማለት ገልጸዋል ። መረጃን በመቀበልና ይፋ በማድረግ በኩልም አዋጁ ችግሮች እንዳሉበት አቶ ግርማ ተናግረዋል
“ብሄራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት ተቃዋሚዎችን እንዳይሰልል፣ ወይም በተቃዋሚዎች ላይ እንግልት እንዳይፈጽም የሚያስገድድ ድንጋጌ አለ ወይ?”  በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ አዋጁ” ምንም ” እንደማይል  ገልጸዋል።

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነቶች ሀይሎችን በተለያዩ የሀይማኖት እና የመንግስት ተቋማት ማሰማራቱን፣ ሌሎች አዳዲስ የደህንነት ሰራተኞችም በስልጠና ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

Tuesday, July 2, 2013

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችን አሰማራ

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችን አሰማራ

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና  ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው  987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡
ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ  አቀላጥፈው የሚናገሩ ፣ ቁራንን በስርዓት የተማሩ እና እስልምናን ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡
ቀሪዎቹ ሰልጣኞች በቴሌ ኮሚኒኬሸን መስሪያ ቤት የተመደቡ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ጠለፋ  ስራ ላይ ይሰማራሉ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 631 ዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በትምህርት ደረጃም የ2002 ምሩቃን በብዛት ይገኙበታል።
በቴሌ የተቀጠሩት አዲሶቹ የደህንነት ሰራተኞች መንግስት ከፈቀደላቸው ውጭ ሌላ የስልክ ግንኙነት የተጠቀሙትን ሚኒስትሮች በድምጽ እንዲለዩ በተሰጣቸው ፈተና መሰረት የተወሰኑ ሚኒስትሮችን ስም ዘርዝረው አቅርበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር፣ የንግድ ሚኒስትርነት አቶ ከበደ ጫኔ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ዘርፍ (ክላስተር) አስተባባሪ  አቶ ሙክታር ከድር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣እንዲሁም  የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት ከፈቀደላቸው የስልክ ግንኙነት ውጭ በራሳቸው መንገድ ስልክ ሲያወሩ ተገኝተዋል ።
ባለስልጣኖቹ በእነዚህ ስልኮች ተጠቅመው የተናገሩት በ ዶ/ር ደብረ ጽዩን አማካኝነት ወደ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ መተላለፉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ኢሳት መንግስት በእስራኤል አገር ልኮ ያሰለጠናቸውን የደህንነት ሰራተኞች እውነተኛ ስም እና ዝርዝር ታሪክ አስፈላጊ ነው ብሎ በሚያምንበት ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለማስታወቅ ይወዳል፡፡
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው 987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡

... ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ አቀላጥፈው የሚናገሩ ፣ ቁራንን በስርዓት የተማሩ እና እስልምናን ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡

 ቀሪዎቹ ሰልጣኞች በቴሌ ኮሚኒኬሸን መስሪያ ቤት የተመደቡ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ጠለፋ ስራ ላይ ይሰማራሉ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 631 ዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በትምህርት ደረጃም የ2002 ምሩቃን በብዛት ይገኙበታል።
በቴሌ የተቀጠሩት አዲሶቹ የደህንነት ሰራተኞች መንግስት ከፈቀደላቸው ውጭ ሌላ የስልክ ግንኙነት የተጠቀሙትን ሚኒስትሮች በድምጽ እንዲለዩ በተሰጣቸው ፈተና መሰረት የተወሰኑ ሚኒስትሮችን ስም ዘርዝረው አቅርበዋል።


 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር፣ የንግድ ሚኒስትርነት አቶ ከበደ ጫኔ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ዘርፍ (ክላስተር) አስተባባሪ አቶ ሙክታር ከድር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣እንዲሁም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት ከፈቀደላቸው የስልክ ግንኙነት ውጭ በራሳቸው መንገድ ስልክ ሲያወሩ ተገኝተዋል ።

 ባለስልጣኖቹ በእነዚህ ስልኮች ተጠቅመው የተናገሩት በ ዶ/ር ደብረ ጽዩን አማካኝነት ወደ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ መተላለፉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

 ኢሳት መንግስት በእስራኤል አገር ልኮ ያሰለጠናቸውን የደህንነት ሰራተኞች እውነተኛ ስም እና ዝርዝር ታሪክ አስፈላጊ ነው ብሎ በሚያምንበት ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለማስታወቅ ይወዳል፡፡

በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የቦንድ ምንተፋ በተቃዋሚዎች የድምጽ ማእበል እየታመሰ ነበር

አትላንታ ጆርጂያ፥
ሳዲቅ አህመድ

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን የሚያዉለበልቡ ብቻ ሳይሆን የለበሱም ነበሩ።የኢትዮጽያ መንግስት አባይን ለመገደብ በሚል ስም ቦንድን ለመመንተፍ የሚያደርገዉን ሴራ እንቃወማለን አባይ ከመገደቡ በፊት ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ ለመላዉ ኢትዮጵያን ያሻል በማለት በዘር በሃይማኖት ሳይለያዩ እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ድምጻቸዉን ያሰማሉ።

Protest in Atlanta, Georgia

ቁጥራቸዉ የተመናመነ ግለሰቦች ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ወደ አዳራሹ ቢያመሩም ከመካከላቸዉ አንዳንዶቹ አንዳንዶቹ  በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የሟቹን መለስ ዜናዊ ቲሸርት በመልበስ ቢንጎማለሉም በፍርሃት እየነፈሩ መሆናቸዉ ግን ያስታዉቅ ነበር። “ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም” በማለት ኅብረ-ዜማን የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን “ተመልከቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዝግጅት ቢያዘጋጁም የኢትዮጵያን ባንዲራን ለማዉለብለብ ግን ፍላጎቱ የላቸዉም! እኛ ግን በአባይ ስም አትነግዱ ስንላችዉ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያዉለበለብን ነዉ” ይላሉ።

Ethiopians Protest in Atlanta, Georgia

“እኛ  ኢትዮጵያዉያን ነን ወደ አዳራሹ ለመግባት የዘር መለዮ ሳይሆን  ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ የሚያሻን” ብሉዉ ለመደራደር ቢሞክሩም አዘጋጆቹ የአባይ ጉዳይ በዘር የተደለደለ እንዲመስል አድርገዉታል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከሰላሳ የሚያንሱ የቦንድ ተመንታፊዎች በሰአት 400 ዶላር በሚከፈልበት አዳራሽ ዉስጥ ሲገቡ ተስተዉሏል። በአዳራሹ ዉስጥም መዝጋቢ ሰዉ እንደሌለ ፣እንኳን ደህና መጣቹ ባይ እንዳልነበረ አንድ በተክለ ሰዉነቱ የስብሰባዉን አዘጋጆች የዘር መስፍርት የሚያሟላ ልቦናዉ ግን ለኢትዮጵያዊነቱ የጸና ግለሰብ ዉስጥ ገብቶ የታዘበዉን ገልጿል።

Rally in Atlanta, Georgia

በተገቢዉ መልኩ ጥናት ያልተደረገበት አባይን የመገደቡ ሙከራ የዲፕሎማሲና የደህንነንት አደጋ አለዉ፤ ስልጣንን ለማራዘምና አቅጣጫን ለማስቀየር በሚደረግ ደፋ ቀና ነዉ አባይን መገደብ በሚል ስም የኢትዮጵያ መንግስት የሚንቀሳቀሰዉ የሚሉ ተቺዎች ብዙ ናቸዉ። ባንጻሩ አባይ አሁን አይገደብ የሚሉት ፖለቲካውዊ ክፋት የተጠናወታችዉ ናቸዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ለማጣጣል ይሞክራል። አንድ የጋራ እዉነታ ግን አለ  በአባይ የመገደብ ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን የተለያየ ሃሳብ የላችዉም! ህዝባዊ ዉክልና የሌዉ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃግድቡን   አያርገዉ  ባዮች ቢኖሩ እንጂ…
ጁን 30 በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የአትላንታ ጆርጂያ የቦንድ ምንተፋ ሂደት ክዉ ድንግጥም ያለ ነበር።