Friday, December 25, 2015

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ይመለከታል!

December 25, 2015
def-thumbየንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት የትግል ጥሪ በ11ኛው ሰዓት ላይ እንደምንገኝ ገልጸዋል ። የ 11ኛው ሰዓት መልዕክት፣ አንደኛ፣ ወደ 12ኛው ሰዓት ወይም ወደ ፍጻሜው እየተቃረብን መሆኑን የሚነገረን ነው። የ11ኛው ሰዓት የትግል ጥሪ የአንድን የትግል ምዕራፍ ለመዝጋት እና አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሪው ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት ከአሁኑ ማሰብ መጀመር እንዳለብን የሚያነቃን ደወል ነው። 11ኛው ሰዓት ላይ ቆመን ከ12ኛው ሰዓት በሁዋላ ስለሚፈጠረው ነገር መጨነቅ ካልቻልንና በጊዜ ቤታችንን ካላሰናዳን ፣ ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ሊገጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶች በጊዜና ብቃት ባለው መልኩ ለመፍታት መቸገራችን አይቀርም ። አንድ በእድሜ የገፋ ሰው 11ኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ከህይወቱ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚኖረው ህይወት ማሰላሰሉ ተፈጥሯዊ ነው። የ11ኛው ሰዓት ጥሪም የአንድን አገዛዝ እርጅናና ፍጻሜ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ በቦታው የሚወለደውን አዲስ ስርዓት ምንነትም የሚያሳይ ነው።
የ11ኛው ሰዓት ጥሪ ተደራሾች እነማን ናቸው? የጥሪው ተደራሾች በኢህአዴግ ዙሪያ የተሰባሰቡት እና እነዚህን ስብስቦች በማፍረስ አዲስ ስርዓት ለመገንባት የሚታገሉት የነጻነት ሃይሎች ሁሉ ናቸው። የ11ኛው ስዓት ጥሪ ለወያኔ ገዢዎች መገርጀፋቸውን የሚያረዳ የሞት ጥሪ ደወል ነው፤ ወደማትመለሱበት መቃብር ከመወርወራችሁ በፊት በቀራችሁ የአንድ ሰአት እድሜ አሟሟታችሁን አሳምሩ ብሎ የሚመክር ነው። በተለይ በጣት የሚቆጠሩ የሻገቱ ገዢዎችን ደግፋችሁ የቆማችሁ የመከላከያ፣የፖሊስና የደህነት አባላት አሰላለፋችሁን በጊዜ አስተካክሉ የሚል አርቆ ከማሰብ የመነጨ ምክር ነው ። የ11ኛው ሰዓት ጥሪ የሚመክር ብቻ ሳይሆን የሚያስጠነቅቅም ነው። ይህን የገረጀፈ አገዛዝ ደግፈው የቆሙ ሁሉ በጊዜ ከህዝብ ጋር እንዲታረቁ ይህ ካልሆነ ግን በመጨረሻው ሰዓት ከፍርድ እንደማያመልጡ የሚያስጠነቅቅ ነው። ካለፈው የሚመጣው ይበልጣል፤ ወያኔን ደግፋችሁ የቆማችሁ ሁሉ ያለፈ ጥፋታችሁን ለወደፊት በምትስሩት ስራ እንድትክሱ መልእክት ተላልፎላችሁዋል።
የ1ኛው ሰዓት ጥሪ የነጻነት ሃይሎች በአንድነት እንዲሰባሰቡና ትግሉን እንዲያቀጣጥሉም ያሳስባል። አገዛዙ 11ኛው ሰዓት ላይ ነው ማለት በራሱ ጊዜ ይወድቃል ማለት አይደለም። አገዛዙ ከደሃው በዘረፈው ገንዘብ ኪኒኖችን እየዋጠና ምርኩዞችን እየገዛ እድሜውን ሊያራዝም ይችላል። ከገፋነው በቀላሉ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ ዝም ካልነው ግን ድዱ ረግፎም በህይወት መቆየቱና ስቃያችን ማራዘሙ አይቀርም። እኛ በዘር፣ በጾታ፣ በትምህርት ወይም በሌሎች ጥቃቅን ነገሮች ሳንለያይ አንድ ሆነን ይህን የሻገተ አገዛዝ እንድናስወግድ ግልጽ ጥሪ ተላልፏል።
የ11ኛው ሰዓት ጥሪ ያረጀውን ስርዓት ወደ መቃብሩ ከከተትነው በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት እንድናስብ የሚመክርም ነው። ዛሬ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንድንነጋገርና የነገውን ትልም እንድንተልም የሚጠይቅ ነው። አስቀድሞ በጋራ መተለሙ ነገ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ከመቀነሱም በላይ፣ የሻገተውን አገዛዝ በህብበረት ለመጣል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል። በጭሩ የ11ኛው ሰዓት ጥሪ ወያኔን ተባብሮ ለመቅበር ብቻ ሳይሆን፣ በመቃብሩ ላይ ስለሚተከለው አዲስ ችግኝ ለመነጋገር ጥሪ የሚያቀርብ ነው።
ሁላችንም የ11ኛውን ሰዓት ጥሪ ተቀብለን ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። ድሉ የሁላችንም ነው!
አርበኞች ግንቦት7!

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የመሰጠቱን ጉዳይ ዳግም አረጋገጡ።

December25,2015
ንግግራቸው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አስመስሏቸዋል።

''በታሪካችን ያላየነው ረሃብ ላይ ነን'' አቶ ኃይለ ማርያም

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ታህሳስ 15/2008 ዓም በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ በተለይ በኦሮምያ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የድንበር ጉዳይ ላይ  የተለመደ አወዛጋቢ እና የበለጠ አወሳሳቢ ንግግሮችን ተናግረዋል።

በኦሮምያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ችግሩን፣መነሻውን እና መፍትሄውን የጠቆሙበት አገላለፅ የእራሳቸውን እና የመንግስታቸውን መፍትሄ ቢስነት በአደባባይ በድጋሚ ያጋለጠ ነው።ችግሩ ገበሬው መረጃ አለማግኘቱ ነው ማለታቸው እና በውጭ ኃይሎች ቅስቀሳ ነው የሚለው እርስ በርሱ የተቃረነ አነጋገር በእራሱ ለእራሳቸውም በአግባቡ የገባቸው አይመስልም።ችግሩን መንግስት ስለ ፕላኑ አለመንገሩ ነው ያሉት እና አሁን መንግስታቸው እያናገረ ያለው በጥይት መሆኑን ለሚያስተውለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግራቸው በሕዝቡ ላይ ከመዘባበት ያለፈ አንዳች የሚሰጠው ፋይዳ የለም።በመፍትሄነት ያስቀመጡትም ምንም አዲስ ነገር የሌለው እና አሁንም መልሰን እንነግረዋለን የሚለው አባባል ንግግሩ በጥይት እንደሆነ አመላካች ነው።ሕዝብ የሚባለው እና የሚደረገው ስላልገባው ነው የሚለው አባባል በእራሱ ለሕዝብ ያለን የንቀት ደረጃ አመላካች ነው።በሰላማዊ ሰልፍ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ እየሰቀሉ ድምፃቸውን ያሰሙ ታዳጊዎችን በጥይት አረር ከመቱ (እንደ አቶ ኃይለማርያም አነጋገር 'ካናገሩ') በኃላ አሁንም እናናግራለን እያሉ መዘባበት በእራሱ ህዝብን የአላዋቂነት ጥግ ነው።

በሌላ በኩል የሱዳን እና የኢትዮጵያን የድንበር ማካለል ጉዳይ ላይ የጀመሩበት አረፍተ ነገር እና በመካከል እና በመጨረሻ ላይ የደመደሙበት ንግግር ኢትዮጵያ በእዚህ አይነት ደረጃ የባዕዳንን ጉዳይ የሚያስፈፅም መንግስት ኖሯት እንደማያውቅ በግልፅ የሚያሳይ ነው።

''በመሬት ጉዳይ ላይ የተደረገ ድርድር የለም። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መሃል ያለው ድንበር በደንብ ስላልተስተካከለ በእርሱ ላይ ነው እየሰራን ያለነው'' ካሉ በኃላ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር የሚናገሩ እስኪመስል ድረስ የኢትዮጵያን ክብር በሚነካ መልኩ ሱዳንን እየረበሽን ያለነው የእኛ ገበሬዎች ናቸው።አሁን የሚያርሱት መሬት የሱዳን መሬት ነው ብለው ለመከራከር ሞክረዋል።ይህ ማለት ባጭሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲያርሱት የነበረው መሬት በእራሳቸው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር መሬቱ የሱዳን ነው እየተባሉ ነው ማለት ነው።በተለይ የሱዳን ወታደሮች ለስራ በወሰዷቸው ኢትዮጵያውያን ላይ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስለመገደላቸው አንዳች ያልተነፈሱት አቶ ኃይለማርያም ይልቁንም የኢትዮጵያን ገበሬዎች በሱዳን ተገብተው ሲወቅሱ እንዲህ ብለዋል-
''ከእኛ አካባቢ እየሄዱ ሱዳናውያንን እየገደሉ የሚመለሱ'' እንደሳቸው አገላለጥ ''ሽፍቶች''ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።በመቀጠል አቶ ኃይለማርያም እንዲህ አሉ: ''በርካታ ኪሎ ሜትሮች ሱዳን ውስጥ ገብተው የሚያርሱ እኛ የምናውቃቸው ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች እና ባለሀብቶች አሉ''  በማለት እነኝህ መሬቶች ለጊዜው ለሱዳን አይሰጡ እንጂ የሱዳን መሆናቸውን ባረጋገጡበት ንግግራቸው በቀጣዩ የድንበር ማካለልም መንግስታቸው የሱዳን መሆናቸውን እንደሚያውቅ አሁንም እንደ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሳይሆን እንደ ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ባጠቃላይ ድንበሩን በተመለከተ ከተናገሩት መረዳት የሚቻለው ሁለት ጉዳይ ነው።አንዱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ማካለል ሂደት ላይ ናቸው የሚለው ዜና ትክክል መሆኑን።በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሁንም እንደ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን በሱዳን ወገን ተገብተው የኢትዮጵያን ገበሬዎች እና ባለ ሀብቶች የሱዳንን መሬት አረሱ እያሉ ይህ መሬት ለሱዳን እንደሚገባ በአንደበታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል።በሌላ አነጋገር ለብዙ ትውልዶች መሬቱን ሲያርሱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከመሬታችን አንነቀልም ካሉ ከሱዳን ወታደሮች ጋር ተባብረው ገበሬዎቹን እና ባለ ሀብቶቹን የማባረር ሥራ እንደሚሰራ እየገለጡ ነው ማለት ነው።ምክንያቱም በአደባባይ መሬቱ የኢትዮጵያን አይደለም።ለጊዜው ነው ሱዳኖች የፈቀዱልን ካሉ በኃላ ይህንንም የሱዳን ውለታ መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስረዳት ሲውተረተሩ ተሰምተዋል።

በመጨረሻም አቶ ኃይለማርያም ''በምግብ እራሳችንን ችለናል'' ብለው በተናገሩ በወራት ውስጥ በዛሬው እለት ደግሞ ካለ አንዳች እረፍት ''የገጠመን ድርቅ በታሪካችን ምናልባትም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ አይተነው የማናውቅ በእኔ አመለካከት እጅግ የከፋ ድርቅ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል።ለድርቁ የሰጡት መፍትሄ ግን የበለጠ አስቂኝ ነው።መፍትሄዎቹ የሚመጡ እርዳታዎችን መቀበል እና የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ነው ይላሉ አቶ ኃይለማርያም።ጥያቄው ግን  ከእሩብ ክ/ዘመን አምባገነናዊ እና የከፋፍለህ ግዛ የኢህአዴግ/ህወሓት አገዛዝ በኃላ ኢትዮጵያ በታሪክ ያላየችው ርሃብ ላይ ነች ማለት እና የውሃ እጥረት ችግር ለሆንባት አገር የውሃ ጉድጓድ መቆፈር መፍትሄ ነው ማለት ምን አይነት የአስተሳሰብ ድህነት ነው? የሚል ነው።ባጭሩ አቶ ኃይለማርያም ህወሃቶች ስልጣን እንዲለቁ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ሿሚዎቻቸውን ቢመክሩ እና የመሸበት ቢያድሩ የተሻለ ነው።

ጉዳያችን GUDAYACHN

Friday, December 18, 2015

የህወሓት የደንነት ቢሮ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን አስጠነቀቀ፡ መፈንቅለ መንግስት ሊደረግ እንደሚችል የቅርብ አዋቂዎች ተንብየዋል

December 18,2015
tigrai

የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር ወስኖአል። የውሳኔውን ቅጅ ከ አንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ጋር በአቶ ካሳ ተክለብርሀን በኩል ለጠቅላይ ሚንስትሩ ልዃል።

የአቶ ሀይለማርያም አስተዳደር አመፁን ለመቆጣጠር መመሪያ ከአሜሪካ መንግስት መቀበሉን በአስቸዃይ አቁሞ የተነሳውን መጠነ ሰፊ አመፅ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የሚያስችል የኦፕሪሽን መርሀ ግብር አውጥቶ ለፊደራል ፓሊስና መከላከያ ማስረከብና ለተግባራዊነቱም ካልተንቀሳቀሰ ሙሉ ሰላም የማስከበሩን ስራ መከላከያ ይረከባል ይላል። በአጭሩ መፈንቅለ መንግስት ይደረጋል ማለት እንደሆነ ምንጮቸ አረጋግጠዋለል።

Thursday, December 17, 2015

ትግላችንን ተጠናክሮ በአንድነት ይቀጥል!

December 17, 2015
def-thumbየኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ በያቅጣጫው መነሳቱ የሚያኮራ ነው። ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን የመብት ትግል ጨምሮ በደቡብ፣ አማራ፣ አፋር፣ ጋምቤላና በሌሎችም አካባቢዎች በርካታ የነጻነት ትግሎች ተካሂደዋል። አሁን በኦሮምያ እና በአማራ በተለይም በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት የነጻነት ትግሎች የአጠቃላዩ የነጻነት ትግል አካሎች ናቸው። በእነዚህ የነጻነት ትግሎች ገዢው ፓርቲ ከህዝብ ጋር ለምንጊዜውም መለያየቱን ለማየት ችለናል። ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲልም፣ አቅሙ ቢፈቅድለትና ማግኘት ቢችል በምድር ላይ ያሉትን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ሁሉ በገዛ ህዝቡ ላይ ለመጠቀም ወደ ሁዋላ የማይል የአረመኔዎች ስብስብ መሆኑን አረጋግጠናል። በጭካኔውና በፍርሃቱ ብዛት የተነሳ በርካታ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ መብታቸውን በሰላም ለመጠየቅ ወደ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ተገድለዋል፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች በእስር ተንገላተዋል፤ በእስር ቤትም ማንነታቸውን ከማዋረድ ጀምሮ የተለያዩ አካላዊ ጥቃቶች ተፈጽሞባቸዋል።
የኦሮሞ ህዝብ መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መነሳቱን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ከያቅጣጫው ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው። ይህ ለነጻነት ሃይሎች ብስራት ሲሆን ዘርን ከዘር በማጋጨት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ለሚፈልገው የሽፍታ አገዛዝ ደግሞ ትልቅ መርዶ ነው። ባለፉት 25 ዓመታት ወያኔ አንዱን ዘር ከሌላው ዘር እያጋጨ፣ በወንድማማቾችና እህትማማቾች መካከል መተማመን እንዳይፈጥር መርዙን ሲረጭ ቆይቷል፤ ያሰበው አልሰምርለት ሲል ደግሞ በአገሪቱ አንጡራ ሃብት በሸመተው ጠመንጃ ለመብቱ የተነሳውን ህዝብ ደረት ደረቱን እየመታ ፈጅቶታል። በተለይም የአማራው ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአንድነት ተሰልፎ በህወሃት አገዛዝ ላይ የነጻነት ክንዱን ለማሳረፍ እንዳይችል ሌት ተቀን የጥላቻ መርዙን በመርጨት ከሌላው ህዝብ ጋር እንዲጋጭ ለማድረግ በእጅጉ ደክሟል። ወያኔ የረጨውን የጥላቻ መርዝ የኦሮሞ እና የአማራ ልጆች በጋራ እያረከሱት መገኘታቸው፣ የሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦች ህዝቦችም እንዲሁ ” አንለያይም” በማለት በጋራ ለመሰለፍና ትግሉን ለማቀጣጠል ዝግጁነታቸውን መግለጻቸውና በተግባር እያሳዩ መምጣታቸው የ25 አመታት የወያኔ የአፈናና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ እያከተመ መምጣቱን የሚያመላክት ነው። ወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው በመላው ኢትዮጵያውያን ትብብር እንደረከሰበት ሲያውቅ ደግሞ የግድያ አዋጅ አውጥቶ በ-ኢትዮጵያውያኑ ላይ ጥይት አርከፍክፎ ጸጥ ሊያሰኛው መዘጋጀቱን በአዋጅ አስነግሯል። ከታሪክ መማር የማይችለው ጠባቡ ወያኔ፣ ህዝባቸውን አዋጅ አስነግረው የገደሉ ጨቋኝ መንግስታት መጨረሻቸው ምን እንደነበረ እንኳን ቆም ብሎ ማሰብ አልቻለም። ዛሬ የእሳት ላንቃ በሚተፋ ጠመንጃቸው ሊጨፈልቀው የሚያስበው ህዝብ ነገ መልሶ ራሱን እንደሚጨፈልቀው ለአፍታም ቢሆን ለማሰላሰል አልቻለም። የዘረፈው ሃብትና የታጠቀው መሳሪያ አእምሮውን ደፍኖት፣ እየመጣ ያለውን ህዝባዊ ሱናሚ ለማየት ተስኖታል። በጦር መሳሪያ ጋጋታና ድንፋታ ቢሆን ኖሮ ወራሪዋ ጣሊያን እስከዛሬ ድረስ ከአገራችን ለቃ ባልወጣች ነበር፣ በጦር መሳሪያ ጋጋታ ቢሆን ኖሮ እነ ጋዳፊን ዛሬ ቤተመንግስት እንጅ መቃብር ውስጥ አናገኛቸውም ነበር።
የአገራችን ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለነጻነቱ የሚያደርገውን ትግል በጥንቃቄ የሚመራበት ጊዜ ላይ ነን ። የገጠመን ጠላት በታሪካችን አይተነው የማናውቅ፣ የገዛ ህዝቡን በጠላትነት ፈርጆ ሊያጠፋው የተነሳ በመሆኑ፣ አገዛዙ እስከዛሬ ካደረሰው ጥፋት ሌላ ተጨማሪ ጥፋት ሳያጠፋ፣ ከአገራችን መሬት ለመንቀል እንድንችል እርምጃችን ሁሉ ጥንቃቄ የተሞላበት ሊሆን ይገባል። ጠላታችን ህዝብን ከህዝብ ለማፋጀት ያለ የሌለ ሃይሉን የሚጠቀም መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ አቅሙ በፈቀደለት መጠን ሁሉ ህዝቡን በጅምላ ለመፍጀት ወደ ሁዋላ የማይል ነው። ህዝቡ የጠላቱን አውሬነት ተገንዝቦ እሱ በሚከፍተው ቀዳዳ ዘው ብሎ ላለመግባት መጠንቀቅ አለበት። ሊገድሉን ሲመጡ ዘወር ብሎ በማሳለፍ፣ እንደገና ደግሞ ወደ አደባባይ በመውጣት፣ እንዲሁም የተቃውሞውን አድማስ በማስፋትና የሃይል መከፋፈል እንዲፈጠር በማድረግ ወያኔን አዳክሞና ተስፋ አስቆርጦ ካለሙት ግብ መድረስ ይቻላል። አሁን እየታየ ያለው አንድነት ይበልጥ እየተጠናከረ፣ ከኦሮሞው ጎን አማራው፣ ከአማራው ጎን ጉራጌው፣ ከጉራጌው ጎን ትግሬው፣ ከትግሬው ጎን አፋሩ፣ ከአፋሩ ጎን ጋምቤላው፣ ከጋምቤላው ጎን ሀረሪው፣ ከሃረሪው ጎን ጉሙዙ፣ ከጉሙዙ ጎን አዲስ አበቤው፣ ከአዲስ አበቤው ጎን ጋሞው በአጠቃላይ መላው ህዝብ እጅ ለእጅ እየተያያዘ የነጻነት ባበሩ ወደፊት እንዲሮጥ ማድረግ አለበት። ወጣቱ ራሱን ባለበት ቦታ እያደራጀና አመራር እየሰጠ በያቅጣጫው የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ ይቀጥል።
አርበኞች ግንቦት7 ትግሉን በተለያዩ አቅጣጫዎች አጠናክሮ ቀጥሎአል፤ የአርበኛው ሰራዊት የወያኔን ጀሌዎች በቀኝና በግራ መውጫና መግቢያ እያሳጣቸው ነው። የንቅናቄው አባላት በዳር አገር በአፈሙዝ፣ በመሃል አገር ደግሞ ወጣቱን እያደራጁ ለትግል እንዲሰልፍ እያደረጉት ነው። የንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ “ከነጻነት ትግሎች ጎን አለን” እንዳሉት የአርበኛው ልጆች ፊት ለፊት ተሰልፈው አመራር በመስጠት የነጻነት ትግሉን ለማቀጣጠል እና መከፈል ያለበትን የህይወት መስዋትነት ለመክፈል ተዘጋጅተው በያቅጣጫው እየተንቀሳቀሱ ነው።
ተደጋግሞ እንደተነገረው የአርበኞች ግንቦት7 አላማ በአገራችን የዲሞክራሲያዊ የሽግግር ስርዓት ማስጀመር ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ አላማ ዙሪያ ተሰልፎ ትግሉን ይቀጥል። ይህን አላማ የሚደግፉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ዛሬውኑ ከጎናችን ተሰልፈው ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው የሞት ሽረት ትግል ይሰለፉ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
አገራችን በልጆቿ ነጻ ትወጣለች!
አርበኞች ግንቦት7

“ፕሮፌሰር፣ ጄኔራል” ሳሞራ

December 17,2015
የቻይና ደም-መላሽ!
samoray
ረቡዕ በተሰማው ዜና መሠረት የቻይናው ቲያንጂን የቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለሳሞራ የኑስ የክብር ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
ሚያዚያ 1999 የዖጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግምባር በክልሉ በሚገኝ የነዳጅ ፍለጋ ቦታ ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ70 በላይ ንጹሃንን በገደለበት ወቅት ዘጠኝ ቻይናውያን ከሞቱት መካከል ነበሩ፡፡
በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር አዛዥነት በየጊዜው በዖጋዴን ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ሲቃወም የነበረው ኦብነግ ለወሰደው ድንገተኛ እርምጃ በሟቹ መለስ የሚመራው ህወሃት በክልሉ አምስት ቦታዎች ማለትም በፊቅ፣ ቆራሄ፣ ጎዴ፣ ዋርድሄር እና ደጋሃቡር ዘግናኝ የሆነ የመልሶ ማጥቃት ጭፍጨፋ በነዋሪው ሕዝብ ላይ አድርሷል፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት (ሂውማን ራይትስ ዎች) ባወጣው ዘገባ መሠረት ኦብነግ ላደረሰው የአጸፋ መልስ እና ታጣቂዎችን ለመደምሰስ በሚል ህወሃት ያዘመተው ጦር በተደጋጋሚ በሰላማዊው ሕዝብ ላይ ፍጹም ጨካኝና ዘግናኝ ዕልቂት ፈጽሟል፡፡
samorayየመልሶ ማጥቃቱን ዘመቻ ለማካሄድ ጂጂጋ ላይ የክልሉ የደኅንነት ኃላፊዎች ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት የመለስ የጸጥታ አማካሪ አባይ ጸሃዬ እና ሳሞራ የኑስ በጥቃቱ ዕቅድ አወጣጥ ላይ ተገኝተው እንደነበር ታማኝ ምንጮቹን ጠቅሶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ያስረዳል፡፡
ከዚያም በ1999 ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ አቶ መለስ መጠነ ሰፊ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ እንዲካሄድ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ የዖጋዴን ሕዝብ ፍዳውን በላ፤ እንደ ቅጠል ረገፈ፤ ዕድሜያቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጃገረዶች፣ ሴቶች አዛውንቶችንም ጨምሮ ተደፈሩ፡፡ ህጻናት ወንዶችም ሳይቀሩ የዚህ ሰለባ ሆነዋል፡፡
የቀድሞው የቻይና መሪ ማዖ ሴቱንግ ሽምቅ ተዋጊዎችን ስለማጥፋት የተናገሩት ቃል በመለስ ፊት አውራሪነት ተፈጸመ፡፡ “ዓሣ በባህር እንደሚዋኝ ሽምቅ ተዋጊም በሕዝቡ መካከል መንቀሳቀስ አለበት፤ (ሽምቅ ተዋጊን ለማጥፋት ካስፈለገ ዓሣው ያለበትን ባህር ማድረቅ ነው)” ያሉት የማዖ ቃል በመለስ ትዕዛዝ በሳሞራ የኑስና ሌሎች የህወሃት አጋፋሪዎች ተፈጸመ፡፡
ውለታ የማይረሱት ቻይናውያን የትምህርት ደረጃው በውል የማይታወቀውን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አሉ ከሚባሉት የጦር አካዳሚዎች ሥልጠና ስለመውሰዱ ምንም ማስረጃ ላልተገኘለት “ቻይናዊ ጄኔራል ደምመላሽ” ባቋራጭ “የላቀ ምሁርነት” አጎናጸፉት፡፡
ውለታን መመለስ ከሆነ አይቀር እንዲህ ነው፡፡
ማዖ ነኝ ከቲያንጂን

“እኛ አማራ ነን እንጂ ትግሬ አይደለንም” የወልቃይት ሕዝብ

December 17,2015

Annexation_Tigray

* “(ችግራችን) ትግሪኛ መናገር፤ ትግሪኛ መጻፍ፤ በትግሪኛ መዝፈን፤ አለብህ የሚል ነው፤ እኛ መሽከርከር አንችልም” የወልቃይት ሕዝብ
“እኛ አሁን የምናቀርበው ምንድነው ማንነት ነው፤ አማራነት በማመልከቻ ለማምጣት አይደለም የተነሳነው፤ አማራ ነን፤ ትላንት አማራ ነን፤ ነገ አማራ ነን፤ ለዘላለም አማራ ነን፤ ይኼ አያሳፍረንም፤ እኛ ስንዘፍን፣ ስናለቅስ፣ ስንፎክር፣ ስንሸልል፣ ለቅሶ ስንደርስ፤ ስናመሰግን ለማንኛውም የምንገልጸው በአማርኛ ነው፡፡ ይህ አማርኛችን ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የገኘነው ነው፤ አያሳፍረንም፡፡
“የወልቃይት ሕዝብ አንዲት ጎጆ ተከዜ ተሻግሮ አልቀለሰም፤ ስለዚህ ይህ ምን ማለት ነው፤ የምን ስሜት ነው፤ ሠርጋችንን፤ ሃዘናችንን፤ ደስታችንን የምናወሳውም እንዲሁ ነው፡፡ ለቅሷችንን የሚያውቅ፤ ደስታችንን የሚያውቅ፤ እንጂ በእኛ ላይ አናታችን ላይ መጥቶ አይደለህም፤ አባትህ ሌላ ነው ሊለን አይችልም፤ ማንነት እንደዚሁ ነው የሚገለጸው፤ ማንነት ለቅሶ የምገልጽበት ቋንቋ ነው፤ ማንነት ሳዝን የምገልጽበት ቋንቋ ነው፤ በተለያዩ መልኮ የሚገለጽ ነው፤ እኛ በተለያዩ ሁኔታዎች ከአማራ የሚለየን ምንነት የለም፡፡ ዛሬ ታሪክን የመቶ ዓመት ያደረጉ ሰዎች ሌላ ቋንቋ ሊያወሩ ይችላሉ፤ ታሪክን በትክክለኛ ሁኔታ የገለጹ ምሁራን ግን አማራነታችንን በትክክል ይገልጻሉ፡፡
“24 ዓመት ሙሉ ሕዝባችን እያለቀሰ፤ እንዳይናገር አጎንብሶ እየሄደ ቀና ብሎ እንዳይናገር ያሳፈረው አንድ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ይህም ትግሪኛ መናገር፤ ትግሪኛ መጻፍ፤ በትግሪኛ መዝፈን አለብህ የሚል ነው፤ እኛ መሽከርከር አንችልም፤ … አማርኛችን ጥርት ያለ አማርኛ ነው፤ እንደማንኛውም ተናግረን፤ ጽፈን የምንገልጸው ነው፤ … ስለዚህ ዛሬ አማራ መሆናችንን በማመልከቻ ዕርዱን እያልን አይደለም፤ በደማችንና በሥጋችን፣ በማንነታችን፣ በዘራችን የመጣ አማርኛ ነው፤ (ትግሬ አይደለንም) … ይህ የወልቃይት ሕዝብ ድምጽ ነው፡፡”
ሙሉውን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

Saturday, December 12, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 የመጀመሪያ ምክር ቤት ስብሰባ መግለጫ

December 12,2015
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከህዳር 26 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓም ድረስ ሰራዊቱ በሚገኝበት የትግል ቦታ የመጀመሪያውን የምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ በስኬት አጠናቋል::
ይህ ስብሰባ የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከተሰኘ ወዲህ የተደረገ የመጀመሪያው የምክር ቤት ስብሰባ ነው::
ይህ ስብሰባ፦
1. ውህደት ከተደረገበት ከጥር 2 2007 ዓ.ም ወዲህ የስራ አስፈፃሚውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጧል፤
2. ከውህደት ወዲህ ንቅናቄው የፈጸማቸውን ተግባራት በጥልቀት መርምሯል፤
3. የንቅናቄውን ህገ-ደንብና አሰራሮችን መርምሮ ማሻሻያዎችን አድርጓል፤
4. የምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል
5. ተተኪና ወጣት የአመራር አባላት ምክር ቤቱ ውስጥ እንዲካተቱ አደርጓል፤
6. የሃገራችንን የወቅቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች በጥልቀት መርምሯል፤
7. በወቅቱ ሁኔታዎች ጥናት ላይ ተመርኩዞ የወደፊት የትግል አቅጣጫውን ቀይሷል፣ ግልጽ የሆነ የትግል ስትራቴጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፤
8. ከስብሰባው በኋላ መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት ቅደም ተከተል አውጥቶ ለስራ አስፈጻሚው መመሪያዎችን አስተላልፏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የህወሓትን አምባገነን አገዛዝ አስወግዶ በምትኩ ፍትህ የነገሰባት፣ የዜጎች እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ዴሞክራሲያዊት አገር ለመገንባት የሚያደርገውን ትግል በግንባር ቀደምትነት ለማስተባበርና ለመምራት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መነሳቱን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይገልጻል::
አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ወደ አዲስ ደረጃ ተሸጋግሯል ብሎ ያምናል:: ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችና ድርጅቶች በሙሉ በሚያመቻቸው መንገዶች እየተደራጁ ከንቅናቄያችን ጋር ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ትግል አምባገነኑን ወያኔ ከስልጣን እንድናስወግድና በምትኩ ፍትህ፣እኩልነትና የሃገርን አንድነት የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ስርዓት እንድናቋቁም ጥሪ ያደርጋል::
ድል ለ ኢትዮጵያ ህዝብ!

ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በህወሓት አገዛዝ የጦር ኃይል ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ!!

December 12.2015
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ተደጋጋሚ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የህወሓትን መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡
ባለፈው ሳምንት ህዳር 21/2008 ዓ.ም ጀግናው ሰራዊታችን በዋልድባ በጠላት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዋልድባ ወደ አዲ-አርቃይ በመወርወር ማክሰኞ ህዳር 28/2008 ዓ.ም አዲ-አርቃይ ላይ ከወያኔ መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል ጋር ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ በማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የጠላት ጦር በመግደልና በማቁሰል ድልን ተጎናፅፏል፡፡
ሰራዊታችን በጦር ሜዳ ውሎው፣ ከጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት በተቀዳ ወኔ፣ እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የህወሓትን መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በጦር ሜዳው ላይ በጥይት ቆልቶና አሳሮ አስቀርቶታል፡፡
ፍልሚየው በማግስቱ ረቡዕ ህዳር 29/2008 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት ማለትም እስከ ረፋዱ አራት ሰአት በዚያው አዲ-አርቃይ ላይ የቀጠለ ሲሆን ፣ ወያኔ ከሌላ ቦታ አጓጉዞ ለጦርነት ያሰለፈውን ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ጀግኞቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ፋኖዎች የጠላትን ጦር ድባቅ መትተውታል፡፡
ለነፃነት የሚደረገው ጦርነት አሁንም ቀጥሏል፡፡የወያኔ ባለስልጣናት የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው በተለይ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የሚገኘውን ድንበር የበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሰራዊት ለመዝጋት ቢሯሯጡም ድንበር ላይ የተመደበው ወታደር ከወያኔ እየከዳ የነፃነት ትግሉን ከነትጥቁ እየተቀላቀለ ይገኛል፡፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት በተቀዳጀው ድል የአካባቢው ህዝብ ጮቤ እየረገጠ እደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ጀግናው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት ህዝቡን ከጎኑ በማሰለፍ፣ በህዝብ ድጋፍ ታጅቦ ወደ መሃል አገር እየገሰገሰ ነው፡፡

Wednesday, December 9, 2015

በረሃብ የተጎዳው ወገን ቁጥር በእርዳታ ድርጅቶች ዳታ 13 ሚሊዮን ደረሰ:: ቀየውን ጥሎ የሚሰደደው በርክቷል::

December 12,2015
ተለያዩ የሰሜን እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት የተሰማሩ ከተለያዩ የአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የተገኙ ዳታዎች እንደሚያመለክቱት በድርቅ የተጎዳው እና በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ ያለው ሕዝብ ቁጥር 13 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት መሰረት በጥር 2016 አስረ አምስት (15 )ሚሊዮን እንደሚገባ ተረጋግጧል::የእርዳታ ድርጅቶቹ ሰራተኞች እንደጠቆሙት በምስራቅ ኢትዮጵያ ሃረርጌ ውስጥ ብቻ ካለፈው ወር ከነበረው የረሃብ ተጎጂ ወገን ቀር በዚህ ዲሴምበር 2015 65% ከፍ ብሌል::የተረጂዎች ቁጥር እና የምግብ አቅርቦቱ እንዳይጨምር የመንግስት ባለስልጣናት ጫና ይፈጥራሉ ያሉት ሰራተኞቹ ሕዝቡ ቀየውን ትቶ ወደ ከተሞች እየዘለቀ መሆኑን ይናገራሉ::
በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና በአገው ልዩ ዞን እንዲሁም በአዲስ ዘመን አከባቢ ያለው ሁኔታ ከሌሎች የባሰ ሲሆን ከምስራቅ በለሳ እና ከአገው ምድር ሰቆጣ ቀያቸውን ጥልው በረሃብ ምክንያት የተሰደዱ በጎንደር አዲስ ዘመን ተሰፈሩ መሆኑ ሲታወቅ በትግራይ እንዲሁ እስካሁን እርዳታ ያላገኙ አከባቢዎች እንዳሉ ተጠቁሟል:: በአዲስ ዘመን ያሉ የብኣዴን ባለስልጣናት ከሰቆጣ እና በለሳ ተሰደው የሄዱትን ወገኖች መንግስት በያላችሁበት በጀት እየመደበ ስለሆነ በሚል ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በማስገደድ ላይ መሆናቸው ታውቋል::ባለፈው ሳምንት በትግራይ በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው ኣንድ እስካንያ መከኒ ከነተጎታቹ የእርዳታ እህል በወረዳው ባለስልጣናትና ነገዴዎች በመመሳጠር የተራገፈ ኣስመስለው በሌላ መኪና ገልብጠው ጭነው ሲወስዱ የኲሓ ህዝብ እጀ ከፈንጅ ይዞ ለፖሊስ ማስረከባቸው ይታወሳል::

Friday, December 4, 2015

ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!

December 4,2015

“ጥላቻ የሚሰብኩ ፈቃድ የሌላቸው መስጊዶች ይዘጋሉ” ኢማም ሃሰን
mosque Paris France
በመጪው ጥቂት ወራቶች ፈረንሳይ እስከ 160 የሚጠጉ መስጊዶችን ለመዝጋት መወሰኗ ተሰማ፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ ኢማም እንዳሉት በሥራ ላይ በዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ የእምነት ቦታዎች መዘጋትአለባቸው፡፡
በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ በፓሪስ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ጽንፈኛ አቋም አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት መስጊዶች መዘጋታቸውን የአገር አቀፍና የአካባቢ ኢማሞች ለመምረጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢማም ሃሰን ኤል-አላዊ ለአልጃዚራ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በቀጣይ ወራቶች በርካታ መስጊዶች እንደሚዘጉ አስረድተዋል፡፡
“ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋር በምናደርገው ውይይት እና ይፋ በሆኑት መረጃዎች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ታክፊሪ ንግግር የሚደረግባቸው ከ100 እስከ 160 መስጊዶች ይዘጋሉ” በማለት ኢማም ሃሰን ተናግረዋል፡፡ ታክፊሪ ንግግር ማለት በእምነቱ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ሙስሊሞችን በከሃዲነት የሚነቅፍ ንግግር ነው፡፡ “እንዲህ ዓይነቱ ንግግር ዓለማዊ በሆነችው ፈረንሣይ ብቻ ሳይሆን በእስላማዊ አገራትም ቢሆን መፈቀድ የለበትም” በማለት የመጀመሪያው የእስርቤት ኢማም (ቻፕሊን) ለመሆን የበቁት ሃሰን ኤል አላዊ ተናግረዋል፡፡
franceይህ በፈረንሳይ አገር በቤተ እምነት ላይ የተወሰደ የመጀመሪያው የተባለለት እርምጃ የተወሰደው “አንዳንድ ሕገወጥ ነገሮች በመገኘታቸው” መሆኑን የጠቀሱት ኢማም ድርጊቱ ባለሥልጣናት ማድረግ የሚገባቸው ሕጋዊ እርምጃ ነው ማለታቸውን አልጃዚራ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ለ130 ሰዎች መሞት ምክንያት የሆኑትን “አሸባሪዎች” በማለት የጠቀሷቸው ኢማም ሃሰን “እነዚህ የሃይማኖት ልብስ የተጎናጸፉ ሌቦችና አደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎች ናቸው፤ ነገሩ የአሸባሪዎች ጉዳይ ነው እንጂ ከሙስሊሞች ጋር ምንም ግንኑነት የለውም፤ የሁሉንም ሰው ደኅንነት ማስፈን የመለከተ ነው” በማለት ኢማም ሃሰን በጥቃት አድራሾቹ ላይ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ሌላው ለአልጃዚራ አስተያየታቸውን የሰጡት የአል-ካዋኪቢ ድርጅት ተባባሪ መሥራች የሆኑት የፋርሱ ሙስሊም ፊሊክስ ማርቃርት የመስጊዶቹ መዘጋት እንዳላስደነቃቸው ተናግረዋል፡፡ ይልቁንም በተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች በተካሄዱ እስላማዊ የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ላይ የሰሙት ነገር በእጅጉ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡ “እስልምናን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ እስልምናን አስፈሪ የማስደረግ ሥራ በፈረንሳይ መንግሥት እንደሚሠራ አንዳንድ ቦታዎች በይፋ ሲነገር ሰምቻለሁ” ብለዋል፡፡
ሆኖም ግን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከጥቃቱ በኋላ ፈረንሳይ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ የመብት ጥሰት እየፈጸመች መሆኗን ይናገራሉ፡፡ የቤት አሰሳ፣ እስራት፣ ሙስሊሞች ባለቤት የሆኑባቸው ድርጅቶችን የመዝጋት፣ ወዘተ የመብት ጥሰት ተከስቶባቸዋል የተባለባቸው ናቸው፡፡
“በአሁኑ ጊዜ በፈረንሳይ ሙስሊም ሆኖ መኖር ቀላል አይደለም” ያሉት ማርቃርት “በተለይ የፊት መሸፈኛ የሚያደርጉ ሴቶች የመድልዖ ሰለባ ሲሆኑ ለወንዶች ደግሞ ሥራ ማግኘት እጅግ ከባድ ነው” በማለት አስረድተዋል፡፡
በፈረንሳይ ውስጥ በድምሩ 2,600 መስጊዶች ይገኛሉ፡፡

የወገኖቻችን ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን፤ ለመፍትሔውም በጋራ እንነሳ!- የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

December 3, 2015
def-thumbበአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ በከተማዋ ዙርያ ያሉ ወገኖቻችንን ማፈናቀል በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የሚፈናቀሉ ገበሬዎች የሁላችን ወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች ናቸው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የምንፈናቀለው ሁላችንም ነን። ይህን መሰሪ ፕላን በመቃወም ላይ ያሉት የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
በዚሁ ወቅት በጎንደር ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ ተከስቷል። ህወሓት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ያጎረበት እስር ቤት በእሳት ሲጋይ ዜጎች ተቆልፎባቸው እንዲነዱ ተደርጓል። ከእሳቱ በእድል ያመለጡት በጥይት ታድነዋል። ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የሚያውቁት በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ነው። ይህን ጥቃት በመቃወም ላይ ያሉ የአማራ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
ግፍ ያልተፈፀመበት የኢትዮጵያ ክፍል ባይኖርም ሰሞኑን በአማራና በኦሮሚያ ላይ በርክቷል። በሁለቱም የአገራችን ክፍሎች የንፁሀን ደም እየፈሰሰ ነው፤ በሁለቱም ቦታዎች የእናቶች ዋይታና እሪታ ጎልቶ እየተሰማ ነው። የህወሓት አገዛዝ የትውልድ ቦታ፣ ቋንቋና ዘር ሳይለይ በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ላይ የተደቀነ አደጋ መሆኑ ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ ግልጽ ሆኗል።
ለዚህ የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው? ዛሬም ኦሮሚያ ውስጥ የሚፈፀመው በደል የኦሮሞ፤ አማራ ውስጥ የሚፈፀመው በደል የአማራ ጉዳይ አድርገን እንወስዳለን? መቸ ነው ኦሮሚያ ላይ ለደረሰው ጥቃት አማራዉ፤ አማራ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኦሮሞው የሚቆረቆረው?
የሁላችን የጋራ ጠላት የሆነው ህወሓት መኖሩ በዘውግ የተከፋፈለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ አንድነት የሚያመጣ ታላቅ ኃይል ሊሆን ይገባል። ይህ የመከራና የመጠቃት ወቅት የምንቀራረብበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ይህ የመከራ ወቅት በህወሓት ላይ በጋራ የምንነሳበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ማኅበረሰቦች በሙሉ በፀረ-ህወሓት ትግል መቀናጀት ይኖርባቸዋል። ይህ ማድረግ ግዴታችን ነው።
ለችግሮቻችን መፍትሄ የምናገኘው ችግሮቹ ከተፈጠሩበት እርከን በላይ ሆነን ስናስብ እንጂ ችግሮቹ በፈጠሩበት ደረጃ ላይ ቆመን መሆን አይችልም። ችግሮቹ ከተፈጠሩበት እርከን በላይ ለመሆን አገር አቀፍ እይታ መኖሩ እጅግ ተፈላጊ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ሁሉ በተለይም የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን ይህንን ጉዳይ አበክረው እንዲያስቡበት አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያሳስባል።
ግፍ ሞልቶ የፈሰሰበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሆኑት ሕፃናት በፌዴራል ፓሊስ ጥይት የሚገደሉበት አሳዛኝ ወቅት ላይ ነን፤ ዜጎች በር ተዘግቶባቸው በእሳት እየጋዩ ነው። ሰፊ እና ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን በስጦታነት ለመስጠት ዝግጁቱ የተጠናቀቀበት ወቅት ላይ ነን። ከአስር ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተርቧል። በፍትህ እጦት እስር ቤቶች በንፁሃን ዜጎች ተሞልተዋል። ውሀ፣ መብራትና የቴሌፎን አገልግሎት ብርቅ ሊሆኑ ነው። ይህ ሁሉ እየሆነ ግን የሥርዓቱ አገልጋዮችና ደጋፊዎች በህንፃ ላይ ህንፃ እየገነቡ በድሀው ላይ ይሳለቃሉ። የህወሓት አገዛዝ ድህነትን፣ ችጋርን፣ ስደትን፣ የእርስበርስ ግጭቶችን እያባባሰ ኢትዮጵያን እየጋጠ የሚኖር አገዛዝ ነው። አገዛዙ በቀደደልን ቦይ ከተጓዝን ችግሮችን ማባባስ እንጂ ማርገብ እንኳን አንችልም። ይህንን ሥርዓት በቃህ ማለት የአማራ ወይም የኦሮሞ አጀንዳ አይደለም፤ ይህ የሁላችንም – የኢትዮጵያዊያን – ጉዳይ ነው።
ለቀምት፣ ሀረር፣ ሱልልታ እና ሌሎች በርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ለደረሱ ጥቃቶች ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ፣ አሶሳ፣ ሁመራ፣ ጋምቤላ ውስጥ ተቃውሞ መሰማት አለበት። በጎንደርና ባህርዳር ለደረሰውም ጥቃት አዳማ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና፣ ጅግጅጋ፣ አክሱም ላይ ተቃውሞ መሰማት አለበት። በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ለሚደርሰው በደል መላዋን ኢትዮጵያ ሊያሳምም ይገባል። መከፋፈላችን መከራችን አብዝቶታል፤ የህወሓት እድሜን አርዝሟል፤ ይብቃ!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የመከራ ጊዜዓችን እንዲያጥር በዘውግ ሀረግ፣ በብሔርና እና በሀይማኖትና ሳንታጠር የወገናችን ህመም ይሰማን፤ ተሰምቶንም ለጋራ ትግል እንነሳ ይላል።


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Thursday, December 3, 2015

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

December 3,2015
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር ሆነው እንዳይቀርቡ ያቀረበውን ይግባኝ ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውድቅ አደርጎታል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ተጠይቆ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክርነት በተጠሩበት ወቅት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ እንደማይችሉ መቃወሚያ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁንና ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት ለዋስት አሊያም ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ሳይሆን ነበሩበት የተባለውን ጉዳይ ለመናገር በመሆኑ ለምስክርነት ሊቀርቡ ይገባል በሚል የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
የልደታ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀርበው ምስክርነት እንዲሰጡ ከወሰነ በኋላ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹ትዕዛዝ አልደረሰኝም፣ የተፃፈው ለቃሊቲ ሳይሆን ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሚል ነው›› እና ሌሎችም ምክንያቶች በማቅረብ በተደጋጋሚ አቶ አንዳርጋቸውን ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ በስተመጨረሻም ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ከተከሰሱት መካከል አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) ውጭ ያሉት የፍትህ ሂደቱ እየተጓተተባባቸው በመሆኑ የአንዳርጋቸው ፅጌ ምስክርነት ቀርቶ በሌሎች መረጃዎች ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ ሁለቱ ተከሳሾች ግን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሊመሰክሩላቸው እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለፀረ ሽብር ግብረ ኃይልና አቶ አንዳርጋቸውን ጠይቀውታል ለተባሉት የብሪታኒያ አምባሳደር ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና ተከሳሾቹ ለሶስቱ አካላት ደብዳቤውን በፃፉበት ማግስት የፌደራል አቃቤ ህግ ከወራት በፊት ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መመስከር አይገባቸውም ብሎ አቅርቦት የነበረውን መከራከሪያ መሰረት በማድረግ አቶ አንዳርጋቸው ምስክር እንዳይሆኑ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡
የአቃቤ ህግን ይግባኝ ያየው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ‹‹አንድ ሰው ለምስክርነት ይቅረብ አይቅረብ በሚል ይግባኝ ሊጠየቅበት አይገባም፡፡ ካስፈለገ ግለሰቡ የሰጡት ምስክረነት መረጃው ተመዝኖ የሚሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ ሊባል ይችላል፡፡ እኛም ጉዳዩን ለማጣራት ምስክርነቱ እንዲቋረጥ አድርገን የነበር ቢሆንም አሁን ግን እንዲቀጥል ወስነናል፡፡ የአቃቤ ህግን ይግባኝም አልተቀበልነውም›› ሲል ይግባኙን ውድቅ አድርጓል፡፡ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር መሆን የለባቸውም ብሎ ያቀረበው ክርክር በፍርድ ቤት ውድቅ ሲሆንበት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡
በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከተከሰሱት በተጨማሪ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት ጠርቷቸዋል፡፡ በሌሎች የክስ መዝገቦች ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ተገናኝታችኋል የተባሉ ተከሳሾችም አቶ አንዳርጋቸውን የመከላከያ ምስክር አድርገው ሊጠሯቸው እንደሚችሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መገኘት ለኢትዮጵያ ዲሞከራሲ ሀይሎች የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው

December 3,2015

ከዚህ ወዲያ አፍ እንዳመጣ “ሽብርተኛ” ማለት የህወሃት መሩ መንግስት እብደት ሆነ!

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋን የአውሮፓ ፓርላማ ንግግር በተመለከተ የኢሳት ዘገባን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ – የቪኦኤ ዘገባ ለማዳመጥ ደግሞ እዚህ ይጫኑ
ቢላል አበጋዝ – ዋሽግተን ዲሲ
ዛሬ ኢትዮጵያ ለህወሃት መሩ መንግስት ተንፈራጦ መግዛት የምትመች አለመሆንዋን ማንም ዜና መከታተል ለሚፈልግ ግልጽ ነው።የህወሃት ባለስልጣናትም ከወትሮው በተለየ መልኩ እርስ በርስ እየተናቆሩ ነው።ተስፋ የቆረጡት ደግሞ ንብረት እያሸሹ ይገኛሉ።በቀይ ባህር አካባቢ አፍሪካ ቀንድን ሊያምስ የሚችል ደመናም ጥሏል ማለት ይቻላል።ሀብታም አረቦችም ልክ እንደ ህወሃት በስጋት ተወጥረዋል።ኢትዮጵያን ማተራመስ ቅር ሳይላቸው ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽሙ ለመሆናቸው የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ይመሰክራል።Professor Berhanu Nega in Eritrea
ከላይ የጠቀስኩት አደጋ ማንጃበቡ ሳያንስ ዛሬ አስራ አምስት ሚሊዮን ወገናችን ለራብ ተዳርጓል።ይህን መከራ በመካድ የጀመረው ህወሃት ህይወት ለማትረፍ የሚጥር አይደለም።በኢትዮጵያ በያለበት እስራትና ግድያው በርትቷል።የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት ስለ ኢትዮጵያ እንዲናገር መጋበዙ ያቀረብኩትን የኢትዮጵያ ሁኔታ ለመንግስታቱ ተወካዮች መግለጽ ብቻ ሳይሆን አጣዳፊ ሁኔታ መፈጠሩንም የማስስጨበጥ ሁኗል። ኢትዮጵያን የፋሺት ኢጣሊያ መንጋጋ ሲያኝካት የተሰደዱ አርበኞች በዓለም መድረክ ጮሆውላት ነበር። ዛሬም በህወሃት መንጋጋ ስትታኘክ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያውያ ወገኖቹ ጋር ሆኖ ድምጹን ከፍ አድርጎ አሰምቶላታል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን የፈጸመው በግንባር ሆነው ህወሃት መሩን መንግስት ብርክ እያስያዙ ያሉትን የኢትዮጵያን ጀግኖች ከበረሃ ተለይቶ ነው።
የኢትዮጵያ ሁኔታ ጊዜ የማይሰጥ ነው።ህወሃት መሩ መንግስት በመለስ ዜናዊና ጀሌዎቹ አማካይነት ያፈላው የጥላቻ ጥንስስ ድንገት ሳይፈነዳ አደጋውን ሊገታ የሚችል ዝግጅት ማድረግን ይጠይቃል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሁሉም የሚወከልበት ጊዜያዊ መንግስት ካልቆመ ወያኔ ፈጽሞ የመግዛት ሀይሉን ሊያጣ የሚችልበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።ህዝቡ በቃኝ ለማለቱ ምልክቶቹ መበራከታቸው ይህን አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ሃይማኖትን ተቋማት ጣልቃ በመግባት አዳክሟል።የእስልምና ሃይማኖት ተቋማትን ደፍሮ መሪዎችን ለእስር ዳርጓል።ነጻነትና ዜግነት በየፈጁ ተደፍሯል።
የዓለም መንግስታት በተለይ ሃያላን የኢትዮጵያን ጉዳይ ወደጎን በመተው ህወሃት መሩን መንግስት መወንጀል ሳይሆን በስመ ሽብርተኝነትን መቋቋም አብረውት እየሰሩ ነው።በታሪካችንም የፋሺት ኢጣሊያውን ሙሶሊኒንም አይዞህ ያሉት ነበሩ።ሁሉም ለየራሱ ጥቅም በዓለም ዲፕሎማሲ ሰልፉን ያስተካክላል።በየጊዜውም ይለውጣል።ኢትዮጵያን የምንል አንድ መሆን የግድ የሚለን ጊዜ አሁን ነው።ህወሃት መሩ መንግስትማ ለሙግት፡ለመልስ እንኳን ያቆመው ቅጥረኛ የውጭ አገር ተላላኪን ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዋለበት መድረክ።የህወሃት ድንቁርና አንድ መገለጫ ምልክት ነው።የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መግለጫ መስጠት ህወሃት መሩን መንግስት ለሚቃወሙና ለተራበው ከተሜ ገጠሬ ወገናችን ትልቅ ግምት የሚሰጠው ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው።ኢትዮጵያ በዚህ የመከራ ዘመን ለታደጓትን አላህ ለነሱም ይመስክርላቸው።
ድል ለዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ሁሉ!
ኢትዮጵያ በአንድነትዋ በነጻነት ለዘለዓለም ትኑር!
አላህ ኢትዮጵያ ይጠብቃት!