Thursday, November 26, 2015

“ረሃቡና ኢህአዴጋዊ እውነታዎች!”

November 26,2015
ኤርሚያስ ለገሰ
ህወሃት መራሹ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ በተከሰተ ቁጥር የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ “የአየር ንብረት መዛባት” በሚል ውጫዊ ምክንያት ማላከኩ የተለመደ ሆኗል። ለአብነት ያህል የዛሬ ዘጠኝ አመት በኢትዮጵያ ረሃብ በተነሳ ወቅት “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” በሚል ረዕስ የውስጥ ድርጀት ሰነድ ተዘጋጅቶ ነበር ደራሲው ጓድ መለስ ዜናዊ ነበሩ። በማስከተልም የፓርቲው ከፍተኛ ካድሬዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት እንዲያደርጉበት ተደረገ። በዚህ ሰነድ ገፅ 6 ላይ የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ እንደሚከተለው ይገልጻል።Ermias Legesse of ESAT
“ረሃቡ ከምን እንደሚመነጭ በትክክል ማስቀመጥ መፍትሄውን ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው። የረሃቡ ቀጥተኛ ምንጭ ከአየር ንብረት መዛባት ጋር ተያይዞ የተከሰተው ድርቅ ነው። የአየር ንብረቱ መዛባትና ድርቁ እኛ ያልፈጠርነው ልናስተካክለው የማንችለው ነባራዊ ሃቅ ነው። በዚህ ነባራዊ ሁኔታ ማዕቀፍ ድርቁን ተቋቁመን ረሃቡን ለማስወገድ ያስቀመጥነው ስትራቴጂ ተዓምር ሰሪነቱ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባር ተረጋግጧል። የረሃቡ ዋነና ምንጭም የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ ነባራዊ ሁኔታን መቋቋም ረሃብን ለማጥፋት የቀየስነው ስትራቴጂ በሚፈለገው ፍጥነት በሁሉም አካባቢዎችን ስላልተፈጸመ ነው” ይላል።
እስኪ ይታያችሁ! ከዛሬ ዘጠኝ አመት በፊት (በ 1999 ዓም) የድርቁ መንስዔ የአየር ንብረት መዛባት እንደሆነ ተነገረን። ከዚያ በፊትም ምንጩ ተመሳሳይ ነበር። አሁንማ ልማድ ሆኖብን በኢትዮጵያ ምድር በየሁለት አመቱ ረሃብ የሚከሰት ሲሆን ምንጩ የአየር ንብረት ለውጥ ሆኗል። በነገራችን ላይ በሃገራችን ላይ በተጠቀሰው አመት ድርቁ ወደረሃብ በመቀየሩ ምክንያት በርካታ ህጻናት እና እናቶች ሞተዋል። በአራቱም ማዕዘናት ዜጎች ቀዬአቸውን ለቀው ተሰደዋል። የተፈጠረው አስደንጋጭ ሁኔታ ከህሊና የሚጠፋ አልነበረም።
በዛን ወቅት “በምጥቁ መሪ!” አብዮታዊ አመራር ሰጪነት የተሰራው ወንጀል ዘመን ተሻጋሪና ነገ ከነገ ወዲያ ተጠያቂነትን የሚያመጣ ነው።
እንዲህ ነበር የሆነው፥
በኢትዮጵያ አዲስ ሚሊኒየም ዋዜማ የተከሰተው ድርቅ ወደረሃብ መሸገገሩን የሚያሳይ ረፖርቶች ከመላው ሃገሪቱ መሰማት ጀመሩ። የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ ማሽን ከዛ አመት በፊት በነበሩት አራት አመታት ኢኮኖሚያችን በሁለት አህዝ አድጓል፥ ሚሊየነር አርሶ አደሮች መፍጠር ችለናል በሚል ቅኝት የሚመራ ስለነበረ ይህን መርዶ ለመቀበል አስቸጋሪ ሆነ። ረሃብን አስወግደናል ብለን ባወጅን ማግስት በረሃብ ተጠቅተን መገኘት በእርግጥም አሳፋሪ ነበር። የአመራርና የማስፈፀም አቅማችን፣ ምርጥ ልምዶች የማስፋት ስትራቴጂያችን ለአለም ተምሳሌት ሆኗል ባልን ጥቂት ቀናት ህዝቡ ረሃቡን መቋቋም አቅቶት እየተሰደደ መሆኑ መመልከት ፕሮፓጋንዳችን “ቢወቅጡት እምቦጭ” እንደሆነ የሚያመላክት ሆነ።
እንደ ተፈራው በዕልፍ አመቱ ዋዜማ የሰው ህይወት በየቦታው መውደቅ ጀመረ፥ ረሃቡን መቋቋም የማንችልበት ሁኔታ ግልፅ ሆኖ ወጣ። የመጀመሪያ ሰሞን እውነታውን አውገርግሮ ከማቅረብ ይልቅ ትክክለኛው መረጃ ተሰብስቦ ወደኢህእዴግ ቢሮ እንዲመጣ ልዩ ውሳኔ ተላለፈ። ለማመን በሚቸግር ሁኔታ የረሃቡ ዋነኛ ሰለባ ከሆኑት አካባቢዎች የሚመጣው መረጃ እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ሆነ። ከሶማሊያ ጫፍ እስከ አብርሃ አጽብሃ የሚባል የትግራይ ቀበሌ ድረስ ህዝቡ የሚላስ የሚቀመስ ማጣቱ ታወቀ። የከፋ ረሃብ ያጋጠማቸው አካባቢዎች ልጆቻቸውን እየቀበሩ ቀዬአቸውን እየለቀቁ መሰደድ መጀመራቸው እሙን ሆነ።
በሚሊኒየሙ ዋዜማ የችጋሩ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት አካባቢዎች የመጀመሪያው የሱማሌ ክልል ነበር። የሱማሌ ክልል ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ለስርዓቱ ተገዢ እንዳልሆነ በገሃድ የሚታወቅ እውነታ ነው። በዛ ላይ አካባቢው በጦርነት የሚታመስ መሆኑ የረሃብ አደጋው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አደረገው። በወቅቱ የተፈጠረው ረሃብ በ10ሺዎች የሚጠጉ የቀንድ እና የጋማ ከብቶች መሞታቸው ታወቀ። ከ80 -100 የሚሆኑ ህጻናት በረሃቡ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ የሚያሳይ መረጃ የስም ዝርዝር ረፖርት ቀረበ።
ይህንን የሱማሊያ የረሃብ ሁኔታ የተቀበለው ጓድ በረከት ከ “ባለራዕዩ መሪ!” ጋር በመነጋገር አንድ ጠንካራ ትዕዛዝ ሰጠ። ጥብቁ ትዕዛዝ “ማንኛውም የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ጋዜጠኛ፣ በመንግስት ክትትል የማይደረግበት በጎ አድርጎት ድርጀት (NGO) ወደሶማሊያ ዝር እንዳይል!” የሚል ነበር። እነሆ ላለፉት 10 አመታት የትኛውም የነጻ ፕሬስ ሆነ የውጭ ጋዜጠኛ ወደሶማሊያ ክልል ልሂድ ብሎ ጥያቄ ቢያቀርብ ኣይፈቀድለትም። ከጓድ በረከት ጋር የቅርብ ወዳጅነት የመሰረቱትም ቢሆን ፍቃድ አያገኙም። የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰጣቸው ጥያቄዎች እንዲጥሉ ይደረጋል። በዚህ ምክንያት በሱማሊያ በረሃቡ የሞቱት ህጻናት ከሪፖርቱ ውጪ እንዲሆኑ ተደረገ። እስከ 100 የሚደርሱት ህውየታቸው ያለፉት ህጻናት ማህደር በኢህአዴግ ቢሮ ተቆለፈበት።
በሚሊኒየሙ ዋዜማ ሌላኛው የረሃቡ ተጠቂ አካባቢ ደቡብ ኢትዮጵያ ነበር። ረሃብ ታሪክ ተደርጎበታል የተባለው የደቡብ ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች እየረገፉ መሆኑን አስቀድመው መረጃ የመጡት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የውጭ ጋዜጠኞች በመሆናቸው መደበቅ የሚቻል አልነበረም። ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ጋዜጠኞች የተፈናቀሉ እና የሞቱ ሰዎች የሚያሳዩት ዘገባዎችን ለዓለም ህዝብ በማስተላለፋቸው ምክንያት መነጋገሪያነቱ ከጫፍ ጫፍ ናኘ። በመሆኑም ነባራዊ ሁኔታውን እንደቅቡል መውሰድ፣ ግን ደግሞ እውነታውን አውረግርጎ ማቅረብ የአቶ መለስ መራሹ የመንግስት የፕሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ሆኖ እንዲቀረፅ ተደረገ።
በዚህም ምክንያት የተራበው ህዝብ ከ 14 ሚሊዮን በላይ ቢሆንም ጓድ! መለስ ባዘጋጀው “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” የውስጠ-ድርጅት ሰነድ ጨምሮ የመንግስት ሚዲያ ተቋማት 6.4 ሚሊዮን ብቻ ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸው አሳወቁ። በሱማሊያ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ከ500 ያላነሱ ህጻናት በረሃብ ቢሞቱም የፕሮፓጋንዳ ማሽን ከ30 እንደማይበልጡ ይፋ አደረገ። ይህንን አውነታ በማስረጃ ለማስደገፍ ያህል “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” በሚለው የፓርቲ ሰነድ ከገፅ 7-8 የሚከተለውን ይላል፥
“በአንዳንድ የደቡብ አካባቢዎች አደጋውን በወቅቱ ካለማየት ጋር ተያይዞ ባለፈው አመት 26 ያህል ህጻናት ለሞት የተዳረጉበት ሁኔታ ተከስቷል። ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ በረሃብ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች የሉም። አልፎ አልፎ በአፈጻጸም ጉድለት ምክንያት እንደተጠቀሰው የሟች ዜጎች ቢኖሩም በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች ቀርቶ በመቶዎች የማይሞቱበት ተፈጥሯል። በተወሰኑ አካባቢዎች የሚታየው የአፈጻጸም ጉድለት ካስተካከልን ምንም ዜጋ የማይሞትበት ሁኔታ መፍጠር እንደምንችልም ጥርጥር የለውም” ይላል።
እንዲህ እውነቱ ተቀናንሶ እና በብዕር ቆንጨራ ተከታትፎ ቢቀርብም በአደባባይ ያለው ሚስጥር ሃቁን መሸፋፈን አልቻለም። ዛሬም ዜጎች በረሃብ ሰቆቃ ውስጥ እየኖሩ ነው። ህይወታቸው እየተቀጠፈ እየተመለከትን “የምጥቁ መሪ!” ተከታዮች ረሃብ የለም ይሉናል። ችግር የተከሰተው “ምናምንቴ” የሚል ስያሜ በተሰጠው አየር መዛባት ምክንያት ድርቅ ስለተከሰተ እንደሆነ ይሰብኩናል። ፍቱን መድሃኒቱም በተግባር የተረጋገጠው “ኪራይ የሚሰበስበው” ስትራቴጂያቸው እንደሆነ ይነግሩናል። ርግጥ ሃቁን በትክክል ቢያስቀምጡ ከትናንትናው ምላሳቸው ጋር ስለሚጣሉ አጣሞ ማቅረብ ግዴታቸው ይሆናል። ምንም እንኳን ያሳምንልናል ብለው የሚያቀርቡት መከራከሪያ ከተጨባጭ ሃቁና መሬት ላይ ካላው እውነታ የትየለሌ በመሆኑ በህዝቡ ትዝብት ላይ ቢወድቁም!….
እዚህ ላይ ማንም አእምሮ ያለውና የአለምን ፖለቲካል ኢኮኖሚ የሚከታተል ሰው የአየር መዛባት፣ የዝናብ እጥረት አልተከሰተም አይልም። ከአገዛዙ ከበለጠ የድርቅ ባህሪያና ትርጉም መረዳት የሚያቅተውም አይደለም። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የምግብ ምርት ወይም የውሃ አቅርቦት በመቀነሱ ከፍተኛ ጫና የሚያስከትሉ የእርጥበት እጥረት መከሰቱን የሚክድ የለም። የድርቅ መነሻ ምክንያቱ ከመደበኛ እና ከሚጠበቀው በታች በአየር ጠባይ መለያየት የተነሳ የዝናብ እጥረት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። በአለም አቀፍ ደረጃም በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት በተለያዩ ዘመናት ሃገሮች በድርቅ ሲጠቁ ተመልክተናል።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ባለፈው ክረምት ጓድ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከውጭ የመጡ የሃገሬ ሰዎች በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስቦ ያሰማው “ኢህአዴጋዊ አውነታ” የኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በተለይ በካሊፎርኒያ የአሜሪካ ዜጋ በድርቅ እየተሰቃየ መሆኑ አስረግጦ ሲናገር የተሰማው ጭብጨባ እስከዛሬም ጆሮዬን ይሰቀጥጠናል። የሆነው ሆኖ “ካሊፎርኒያ በድርቅ ተሰቃየች” የሚለው አባባል የትኛውን ግብ ለማሳካት በጭብጨባ እንደታጀበ የሚያውቁት አጨብጫቢዎች ብቻ ቢሆንም የገባንበትን የሰብዕና መላሸቅ አጉልቶ የሚያሳይ ነበር። የአውስትራሊያ አሊያም የካሊፎርኒያ ህዝብ በድርቅ ቢጠቃ ደስ ይለናል ማለት ነው?
የአገጣሚ ነገር ሆኖ የዛሬ ሳምንት እኔና ተወልደ በየነ (ተቦርነ) ለኢሳት የገቢ ማስገኛ ዝግጅት የካሊፎርኒያ እምብርት ወደሆነችው ሎስ አንጀለስ (LA) (ተቦርነ “ላይ አርማጭሆ” ይላታል) ሄደን ነበር። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ የእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ “እንኳን በድርቅ ምክንያት እየተሰቃየች ያለችውን ካሊፎርኒያ በሰላም መጣችሁ!” በሚል ነበር የጀመሩት።
ይህንን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በአርምሞ ሲያዳምጡ የነበሩት ተሰብሳቢዎች በጭበ አስከትሎም የማያባራ ሳቅ አጀቡት። መቼስ! ተንኮል ካልሆነ በስተቀር ጭብጨባና ሳቅ ምን አመጣው? እንኳንም ጓድ! ሃይለማርያም በስብሰባው አልኖረ! እንኳንም በሚሊኒየም አዳራሽ የተገኙ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች አልሆኑ።
እናማ የስብሰባው አዘጋጆች ፕሮግራም ከተጠናቀቀ በኋላ በያዙልን ዕለታዊ መርሃግብር መሰረት ካሊፎርኒያን ያስጎበኙ ነበር። የድሮ ካድሬ ነገር ሆኖብኝ የምንሄድበት መኪና በቆመ ቁጥር ነጩን፣ ጥቁሩን፣ ስፓኒሹን፣ አፍሪካዊውን ካሊፎርኒያ “ ድርቁ እንዴት ነው? ምን ጉዳት አስከተለ?” የሚል ጥያቄ አነሳ ነበር። ያለማጋነን ጥያቄ ከመለሱልኝ ሰዎች ውስጥ ዘጠና በመቶው ድርቅ መኖሩን አያውቁም። የተቀሩት ውሃ ለመቆጠብ የሻወር ቤታቸውን የውሃ ወንፊት እንዳጠበቡ ነግረውናል። ከፊሎቹ ለውሃ ቁጠባ ሲባል መኪናቸውን በሁለት ሳምንት አንዴ እያጠቡ መሆኑን እያዘኑ አጫውተውናል። ሃዘናቸውንም ተጋርተነዋል። የሻወር ቤት ወንፊት ከማጥበብ፣ መኪናን በሳምንት ሁለት ጊዜ ከማጠብ በላይ ምን ስቃይ አለ? አትክልትን ከሳምንት አምስት ቀን ሁለት ቀን ውሃ እንዲጠጡ ከማድረግ በላይ ምን የሚያበሳጭ ነገር አለ?
የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በግዛቱ የመንግስት ተቋም ውስጥ የሚሰራ ሙያተኛ ከአስጎብኚዎች አንዱ ነበር። ግለሰቡ ካሊፎርኒያ ያጋጠማት ችግር ጓድ ሃይለማሪያም ከጠቀሱት በተቃራኒ፣ ከልክ በላይ መብላት የሚመጣ ውፍረት (Obesity) መሆኑን ነገረን። ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ እንዲሉ ወዳጃችን የካሊፎርኒያ ችግር ከመጠን በላይ ምግብ በመብላት እና የአካል እንቅስቃሴ ባለማድረግ የሚመጣ የሰውነት ውፍረት እንደሆነ አጫወተን። በመፍትሄ ደረጃም በግዛቱ በሚገኙ ት/ቤቶች “Child obesity school program” ቀርጸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ነገረን። በየመቶ ሜትሩ የምናያቸው የተዘረጠጡ ህጻናት ለፕሮግራሙ ተገቢነት የሚያረጋግጡ ነበር። እርግጥም ካሊፎርኒያን ጨምሮ በመላው አሜሪካ ጭንቀትና ስቃዩ የዜጎች የስብ ክምችት መሆኑን ለማወቅ ብዙ መልፋት አይጠበቅም። ለጥቂት ደቂቃዎች ወደኢንተርኔት ጎራ ያለ ሰው ከአሜሪካ አጠቃላይ ህዝብ 78 ሚሊዮኑ (ከዚሁም 12 ሚሊዮን ህጻናት) በውፍረት ግዝፈት መጠቃቱን ይመለከታል። ዘለግ አድርጎ ለተመለከተ ደግሞ የሰውነት ግዝፈት መጠን (obesity rate) በውፍረት በሽታ የግዛቶቹ ተደርድሮ ያያል። ለምሳሌ ካሊፎርኒያ 24.1%፣ ሚሲሲፒ 35%፣ ቨርጂኒያ 35.1% ወዘተ እያለ ይቀጥላል።
እነዚህን የመሳሰሉ ሀገሮች በአየር መዛባት ምክንያት ድርቅ ሲከሰትባቸው ትክክለኛ ፖሊሲ በመቅረፅ ዜጎቻቸውን ታድገዋል። የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂካል እቅዶችን ከማውጣት ባሻገር ተስማሚ ቴክኖሎጂ በመምረጥ፣ የውሃ እና አፈር አጠባበቅ ተግባርን በማሻሻል፣ የግብርና ምርት ውጤቶችን ወደውጭ እንዳይወጡ በማገድ፣ የገጠር እና የከተማው ልማት በማቀናጀት… ወዘተ ዘላቂ መፍትሄ አስቀምጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሰፋፊ ዘመናዊ እርሻዎች በማስፋፋት፣ የግብርና ምርታቸውን በከፍተኛ እጥፍ በማሳደግና፣ የህዝቡን የመግዛት አቃም በማጎልበት በድርቅ ምክንያት የሚከሰተውን አደጋ ከቁጥጥራቸው ውጪ እንዳይሆን አድርገዋል። ድርቅ ተፈጥሯዊ ነውና በማንኛውም ሰዓት ይመጣል፥ ግን ደግሞ እዚህ ግባ የማይባል ጉዳት አያደርስም። በፖለቲካው መስክም ቢሆን የገነቡት ዲሞክራሲያው ስርዓት ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገት የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል። ያለነጻነት ሁሉን አቀፍ ልማት ማምጣት እንደማይቻል ተገንዝበው ለዜጎቻቸው ነጻነት አጎናጽፈዋል።
እንግዲህ በአለም ያለው እውነታ ይህ ነው። ይሁን እንጂ፣ “ የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ ገዢዎቻችን በስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ በየሁለት አመቱ የሚከሰተውን ከድርቅ የተሻገረ ረሃብ በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት እንደሆነ ሊያስረዱን ይሞክራሉ። አገዛዙ ስልጣን በያዘ ሁለት አመታት ጀምሮ መጀመሪያ 6 ሚሊዮን፣ ቀጥሎ 10 ሚሊዮን፣ በማስከተል 14 ሚሊዮን ህዝብ በረሃብ ተጋልጦ ነበር። አሁን ደግሞ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ የረሃብ አደጋ አንዣቦበታል። እነዚህ ጥሬ ሃቆች የሚካዱ አይደሉም። በኢትዮጵያ ቀይ፣ ጥቁር፣ መረሬ አፈር ላይ የተነጠፉ እውነታዎች ናቸው። ዛሬም አገዛዙ በሚከተለው ፖሊሲ ምክንያት ራሳችንን መመገብ አቅቶን አቅማዳችንን ለመጽዋት ክፍት አድርገናል። አገዛዙ ዲሞክራሲያዊ፣ ሰብዓዊና ሌሎች የህዝብ መብቶችን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን እስካልቀየረ አሊያም ስርዓቱ እስካልተቀየረ ድረስ የወደፊት እድላችን የከፋ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሆኗል። የፊተኛው መፍትሄ ኣያለፈበት ይመስላል። የስርዓት ለውጥ የሚለው ደግሞ ይበልጥ ተቀባይነት ማግኘቱ የሚታይበት ሁኔታ ፈጥሯል። ፍጥነቱ በደረሰው መከራ እና አበሳ፣ በደረብን ቁጭት ልክ ባይሆንም። ዞሮ ዞሮ ሃገራችን የገባችበትን የረሃብ አዙሪት ትግሉን ከሚያዘውሩት ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ መሆኑ አልቀረም!

Tuesday, November 24, 2015

በወላይታ ሶዶ ህዝቡን ለትግል የሚያነሳሱ መፈክሮችና ምስሎች በብዛት ተለጠፉ

November 24,2015
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
በወላይታ ሶዶ በሦስቱም ክፍለ ከተሞች አርበኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን የነፃነት አርበኝነት የሚደግፉና ህዝቡን ለትግል የሚያነሳሱ መፈክሮችና ምስሎች በብዛት ተለጠፉ፡፡
ህዝቡ በአርበኞች ግንቦት 7 ሁለገብ የትግል ማዕቀፍ ውስጥ ተሰባስቦ ሁሉም በአንድት ተነስቶ ለተጀመረው ፀረ-ወያኔ፣ ፀረ-አምባገነናዊ የህወሓት አገዛዝ ፍልሚያ የየበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ የሚያስተላልፉት ፅሁፎችና ምስሎች ወላይታ ሶዶን ዳር እስከ ዳር ያጥለቀለቋት እሁድ ዕለት ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ሲሆን ትናንት ከፍተኛ ውጥረትና ግርግር በከተማዋ ሰፍኖ ውሏል፡፡
"የክልሉን አስተዳደር" ጨምሮ የአካባቢው የህወሓት-ደህዴግ ሹሞችን የተቃውሞ ፅሁፎችና ምስሎችን የያዙ ወረቀቶች በሁሉም ቦታዎች ተለጥፈው መታየት በእጅጉ አስደንግጧቸዋል፡፡ 
በአሁኑ ሰዓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ያገኙትን ወጣት ሁሉ እያፈሱ ወደ ወህኒ በማጋዝ ላይ ናቸው፡፡
በወላይታ ሶዶ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ከተለጠፉት ምስሎች የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፎቶ ይገኝበታል፡፡

Saturday, November 21, 2015

በሞት ጥላ መካከል ብሄድ እንኳን ክፉን አልፈራም !!! የሀብታሙ አያሌው መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት

Millions of voices for freedom - UDJ's photo.November 21,2015
የልቤን ምጥ ልፃፈው ብዬ ደጋግሜ ብዕሬን ይዤ ወረቀቱ ላይ ብፅፍም እንደተራበው ወገኔ ሆድ ብዕሬ ባዶ ሆኖ ቀለም አልነጥበው አለ፡፡ በቅሊንጦ ማጎሪያ ቤት ሰማይ ስር ነፍሴ ሀዘን አቆርዝዛ በማይገፉ ቀንና ሌሊቶች ውስጥ ባዘነች፡፡ ለወትሮው ወገኔ እንደከፋው ስሰማ እንደወፍ በርሬ ችግሩን ልጋራው ከመሃሉ እደርስ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የህዝቤ ስቃይ ወደ ሰማይ ጉኖ በጠኔ ሲንበረከክ እንደ ጅብራ ተገትረው በማያንቀሳቅሱኝ ወታደሮች ተከብቤ በጭንቀት እየባዘንኩ ከመጠውለግ በቀር አደርገው ነገር አጣሁ ፡፡ ወይ ሀገሬ!!! ወይ ወገኔ!!! 
….. እመነኝ እንዳልኩህ አሁንም እመነኝ … አሁንም እመነኝ !!! እመነኝ ደርግ ወድቋል ኢህአዴግ ይወድቃል፡፡ ዛሬ በአሳሪዎቼ ጡጫ ተደቁሼ፤ ድምፄ በኢትዮዮጵያ ሰማይ ስር ባይሰማም የታገልኩለት እውነት ወደ አደባባይ ወጥቶ ህዝቤ የነፃነት ሻማ እሚጎናፀፍበት ቀን እንደሚመጣ ግን ጥርጥር የለኝም፡፡ 

የልጄ ናፍቆት የሚስቴ ስቃይና እንግልት የእህቶቼ መባከን እና መሳቀቅ አቅሜን ሲፈታተኑት በማዕከላዊ የስቃይ ማማ ስር ጉዳት ያተረፉት ሁለቱ ኩላሊቶቼ የቀን ከሌት ስቃዬን ሲያረዝሙት የነከስኩት ጥርሴ ጉልበቴ አበርትቶ የነፍሴን መዛል ብሸሽግም… ዛሬ ግን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖ የታገልኩለት ህዝብ በረሃብ ጠኔ እየተመታ በሞት ጥላ መንበርከኩን ስሰማ ነፍሴ በውስጤ አለቀች እናም የልቤን ሀዘን እፅፍ ዘንድ ሞከርኩ… ሞከርኩ ግን አቃተኝ….

ጃርት እንደ በላው ዱባ በየቦታው የተፈረካከሰው ፓለቲካችን ዛሬም እርስ በእርስ እየተሸነቋቆጠ ይቀጥላል ወይስ ወገኑን ለመታደግ እንኳ አንድ ይሆናል? ነፍሴ በየእለቱ የምትሟግተኝ ጥያቄ ነው ፡፡ ሳንተባበር ጉልበት አንድ ሳንሆን ኃይል ከወዴት እናገኝ ይሆን ? የአምባገነኖች ጡጫ እየደቆሰን ረሃብ በየዘመኑ የሚቆላንስ እስከመቼ ነው? በእውነቱ በሀሳብ ብዙ ባከንኩ አገኝለት ዘንድ ግን መልስ አጣሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እና የኢትዮጵያ ህዝብ መልስ አጥተው አያውቁም እና ተስፋዬ ፈፅሞ አይመክንም፡፡ 

እናም ያገባናል ለሚሉ ሁሉ እላለሁ የኢትዮጵያ ገፅታ የሚገነባው በየሰርጡ በጠኔ የሚሞቱ የወገኖችን እሬሳ በመደበቅ እንዳልሆነ ካሳለፍናቸው ክፉ ጊዜያት ተምረን ባለን አቅም ተረባርበን ወገኖቻችንን ለመታደግ እንበርታ እላለሁ…!!! በአዲስ አበባ፤ በባህር ዳር፤በአርባ ምንጭ፤ በጎንደር፤ በደሴ፤ በአዳማ፤ በአዋሳ፤ በወላይታ ህዝብ በሚንቀለቀል የለውጥ ፍላጎት ድምፁን ባሰማባቸው ሰላማዊ ሰልፎች… ‹‹ኢህአዴግ ከታሪክ ይማር፤›› ‹‹አምባገነኖች ባሉበት ሀገር የጀግና ሞቱ እስር ቤት ነው ፤›› ‹‹ታጋይ ይታሰራል ትግሉ ይቀጥላል፤ ›› ‹‹ እጃችን ባዶ ነው እነዚህ አምባገነኖች ነገ አሸባሪ ይሉናል›› ፤ ‹‹እመነኝ ደርግ ይወድቃል ኢህአዴግም ይወድቃል›› ማለታችንን ….. በእርግጥም ልክ ነበርን፡፡ ዛሬ አሸባሪ ተብለን ከትግል አጋሮቼ ከዳንኤል ሺበሺ ፤አብርሃ ደስታ ፤ የሺዋስ አሰፋ ፤አንዷለም አራጌ፤ ተመስገን ደሳለኝ ፤እስክንድር ነጋ ፤ ወዘተ…. ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ጋር የነፃነት ቀንን እየናፈቅን በእስር ቤት አለን ፡፡ የፍርድ ቤት ድራማውም ተጠናክሮ ቀጥሏል ፍርድ ቤቶችን ከጀርባ ቆመው የሚዘውሩ በቀጭን ትዕዛዝ ማረሚያ ቤቶችን የሚያሽቆጠቁጡ፤ በፍትህ ስም የሚቀልዱ ፓርቲዬን ያፈረሱ፤ የህዝቤን ተስፋ ለማምከን ቀን ከሌት የሚደክሙ የካዛንቺሱ መንግስቶች እጃቸው የሚያጥርበትን ቀን አብዝተን እንናፍቃለን ፡፡

በእውነት እላለሁ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ክፉን አልፈራም !!!

Thursday, November 19, 2015

አሁንም እስረኞች ነን - ከዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ

November 19,2015
ከሚያዝያ 17 2006 ጀምሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስርውለን የነበርነው 3 ጋዜጠኞችና እና 6 የዞን9 ጦማርያን ከአንድአመት ከሁለት ወር እና ከአንድ አመት ከ5 ወር የእስር ቆይታ በኋላ ሁላችንም ከእስር አንደተፈታን ይታወሳል፡፡ በሃምሌ ወር መጀመሪያሶስት ጋዜጠኞች እና ሁለት ጦማርያን አቃቤ ህግ ክስ አቋርጦ፣ በማስከተል አራት ጦማርያን ደግሞ ነጻ ተብለው ከእስር መለቀቃችንየሚታወስ ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስትና ላይ ሆኖ የቀረበበትን “አመጽ የማነሳሳት ክስ” እንዲከላከል መባሉም ይታወቃል፡፡

ይሁን አንጂ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከተፈታን ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ነጻ አለመውጣታችንን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች በመኖራቸውእና ሊቀየሩም ባለመቻላቸው ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡

1.     የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ32 በሚደነግገው መሰረት “ ማንኛውም ኢትዮጲያዊ … በፈለገው ጊዜ ከአገር መውጣት ነጻነትን” በሚጻረር መልኩ “የመንቀሳቀስ መብታችን”አሁንም ተገድቧል፡፡ ለምሳሌ ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህዳር 7/2008 በፈረንሳይ አገር በሪፓርተርስ ሳንስ ፍሮንቲየርስ (ድንበርየለሽ ጋዜጠኞች ድርጅት) ለዞን 9 ጦማር የተበረከተውን 2015 የሲቲዝንጆርናሊዝም ሽልማት የዞን9 ጦማርን ወክሎ ለመገኘት ህዳር 6/2008 ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኝም ባልታወቀ ምክንያት ከአገር መውጣት ተከልክሎ ፓስፓርቱንምተቀምቷል፡፡ በዚህም የተነሳ የሚቀጥለው ሳምንት በሚከናወነው በአለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ የሆነ የሲፒጄ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ላይ መገኘቱን እድልም በጣም አጥብቦታል ፡፡

2.    ጦማሪ አቤል ዋበላ (የኢትዮጵያአየር መንገድ ኢንጂነር) ፣ ጦማሪ ዘላለም ክብረት (የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር) ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን( የጤና ጥበቃሚኒስትር የዳታ ኦፌሰር) እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ (በፕላን ኢንተርናሽናል የኮምኒኬሽን እና ኖውሌጅ ማኔጅመንት ሰራተኛ) ወደስራገበታችን መመለስ አልቻልንም ፡፡ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆነው መንገድ ተገደን ከአንድ አመት በላይ እስር ቤት መቆየታችን የእኛ ጥፋትአንደሆነ ተቆጥሮ ከስራ ተባረናል ፡፡ሌሎቻችንም በግል እንሰራቸው የነበሩ ስራዎችንም መቀጠል አልቻልንም ፡፡

3.    ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከክሳችሁሙሉ ለሙሉ ነጻ ወጥታችኋል ብሎ የበየነልን ሶስት ጦማርያን ስንያዝ “ማአከላዊ” ምርመራ የተወሰደብን ፓስፓርታችን እና ሌሎች እቃዎቻችንእንዲመለሱልን ብንጠይቅም “ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባችኋል” በሚል ሰበብ እስካሁን አልተመለሱልንም፡፡

4.    ቢቢሲ አንደዘገበው የኢፌዴሪጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አሁንም “ ታስረው የነበሩት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን የእውነት ጋዜጠኞች አይደሉም ከሽብርጋር ግንኙነት አላቸው” በማለታቸው እንዲሁም የተለያዬ የመንግስት ባለስልጣናት የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ የሚሰጡት አስተያየት ፍርድቤቱ ያወጀልንን ነጻነታችንን ኢ- ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ እየናደው ነው ፡፡

በእነዚህእና በሌሎች ጫናዎች ምክንያት ራሳችንን ሳንሱር አንድናደርግ እና ሁሉም ጉዳያችን በእንጥልጥል ላይ ያለ የቁም እስረኞች የሆንንእንዲመስለን እየተደረገ ነው ፡፡ ስለሆነም

-      ህግ መንግስታዊ መብታችን የሆነውእና ምንም ህጋዊ ገደብ ያልተቀመጠበት በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት መብታችን እንዲመለስልን
-      በኢግዚቢት ስም በማእከላዊምርምራ የሚገኙት እና ካለምንም ህጋዊ ምክንያት የተያዙት ፓስፓርት እና ሌሎች የግል እቃዎቻችን እንዲመለሱልን

-      መንግሰት የራሱን ፍርድ ቤትውሳኔ አክብሮ አሁንም ወንጀለኛ ስያሜ የሚሰጠንን ስም ማጥፋት እና የእጅ አዙር ጫና አንዲያቆምልን
-      የፓለቲካ ታማኝነትን ለማሳየትያለህግ አግባብ ወደስራ ገበታችን አንዳንመለስ ያደረጉን አካላት ውሳኔያቸውን መለስ ብለው እንዲያዩልን እንጠይቃለን፡፡

ሕገ መንግስቱ ይከበር
ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

Wednesday, November 18, 2015

“ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” ረሃቡን በሚመለከት የስራ እቅዶችን አውጥቷል

November 18,2015

ረሃቡን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ፣ ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (Global Alliance for the Rights of Ethiopians – GARE)

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ከተቋቋመበት ወቅት ጀምሮ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ በያሉበት ለሚደርስባቸው ግፍና ችግር ያልተቆጠበ ጥረት በማካሄድ ላይ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በሳውዲ አረቢያ፤ በየመን፤ በሊቢያ፤ በኬንያ፤ በሰሜን ሱዳንና በማላዊ ችግር ለገጠማቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የገንዘብ፤ የዲፕሎማሲ፤ የምክርና ሌሎች ድጋፎች አድርጓል። ይኼ ግዙፍ ድጋፍ ስኬታማ ሊሆን የቻለበት ዋና ምክንያት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በያሉበት የገንዘብ ድጋፍ ስላደረጉ ነው። ድርጅታችን እነዚህን ደጋፊዎች ያመሰግናል።Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)
አሁን የተከሰተውን የድርቅ ረሃብ፤ ቢቢሲ የተባለው ድርጅትና ሌሎች ተቋሞች ከዛሬ ሰላሳ ዓመታት በፊት “ከተከሰተው የድርቅ ረሃብ የማያንስና አሳሳቢ ነው” ያሉትን ረሃብ በሚመለከት ድርጅታችን መረጃዎችን ሰብስⶅ የችግሩን ጥልቀትና ስፋት ተገንዝቧል። የስራ እቅዶችን አውጥቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት “እኔ ራሴ እወጣዋለሁ” ያለውን ብናውቅም፤ በሌላ በኩል የችግሩን መጠን በመረዳት መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት፤ ወዘተ እና በያሉበት ለኢትዮጵያዊያን ያቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በጽሞና ተመልክተነዋል። የተጎዱት ወገኖቻችን ቁጥር ወደ አስራ አምስት ሚሊየን እንደሚደርስ መታወቁ ብቻ ሳይሆን፤ በእኛ ግምትና ግንዛቤ በድርቅ ረሃብ ምክንያት አንድ ህጻን፤ አንድ እናት ወይንም አንድ አባት መሞት የለበትም።
ድርጅታችን ማንኛውም ከሕዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ፤ ተጠያቂነት፤ ግልፅነትና ሃላፊነት ባለው መልክ፤ መንገድና ድርጅት አማካይነት ለተጠቃሚዎች መድረስ አለበት የሚል መርህ ሲከተል ቆይቷል። ከInternational Organization for Migration (IOM) ያደረግነውና አሁንም የምናደርገው ስራ ምሳሌ ነው። በዚህም መሰረት ትብብሩ አግባብ ያላቸውን፤ በረሃቡ ዙሪያ በኢትዮጵያ ሰብአዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሞችን ሲያነጋግር ቆይቶ በቅርቡ አጥጋቢ መልስ እንደሚደርሰውና ከስምምነት ላይ እንደሚደርስ ይተማመናል።
ይኼን በሚመለከት ትብብሩን በመወከል በNovember 17, 2015 በኢሳት ሬዲዮ ለታዳሚዎች አንደገለጽነው በሚከተሉት ቀናቶችና ሳምንታት ትኩረት የምንሰጠው በረሃብ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ድርሻችን ለመወጣት የተቀነባበር የገንዘብ ስብሰባ ዘመቻ ማካሄድና የተሰበሰበው ገንዘብ ለተጠቃሚዎቹ እንዲደርስ ማድረግ ነው። በዚህ አጋጣሚ ከዚህ በፊት በየአካባቢው ያልተቆጠበ ጥረት ላደረጉት፤ ለወገኖቻችን እንደርስላቸው ለሚሉትና ለሌሎች ጥሪ የምናደርገው በያላችሁበት የገንዘብ መሰብሰብ ጥረቱን እንድትቀጥሉ፤ ያልጀመራችሁ እንድትጀምሩና ላልሰሙት እንድታሰሙ ነው።
የትብብሩን ድጋፍ የምትፈልጉ በቴሌፎንና በኢሜይል ለመገናኘትና የተዋጣውን ገንዘብ በትብብሩ ባንክ ለመላክ እንደምትችሉ እናሳስባለን።
4ruleoflaw@gmail.com
Tele: 877-746-4384
www.DefendEthiopians.org

Monday, November 16, 2015

The 2015-16 Ethiopian Famine: Yet Another Avoidable Tragedy is Underway!

November 16,2015
Ethiopiawinnet: Council for the Defense of Citizen Rights
Just as the world’s leading development agencies are vowing to finally make poverty history in the four corners of the globe and they are heaping praises on the Ethiopian Government for its “double-digit” economic growth rates and self-serving rhetoric about “transformation,” Ethiopia is once again under the grips of what appears to be yet another famine of “biblical proportion.” The World Food Program of the United Nations and the Government itself have announced that over 8 million Ethiopians are at the risk of death by starvation. Chronically food-deficit areas have been hit by El Nino-related failures of both the small and the big rainy seasons this year.
We must underscore two things at the outset. First, predictable weather-related or pest-related shocks to the food system should not result in mass starvation or high mortality in the presence of an accountable government with a capacity to feed its people. Drought may be an act of God but famine is surely a political act of man. Second, The Citizens Charter for a Democratic Ethiopia embraces the greatest of all human rights—the right to life. Basic food security for all is, therefore, the most fundamental right to which all Ethiopians are entitled. This is why eliminating famine is the litmus test for all who profess commitment to human rights and democratic accountability.
The world has made a remarkable progress over the past 25 years. Millions of Ethiopians are among the one billion people lifted out of debilitating poverty. National and regional famines that claimed the lives of millions in South Asia and Sub-Saharan Africa are thankfully a thing of the past, save the most an unpredictable natural catastrophe. To understand why Ethiopia remains so vulnerable to chronic hunger even in normal years, one needs to keep the following facts in mind:
  • One out ten rural Ethiopian (or 8 million out of 80 million) suffer chronic hunger (under-nutrition and malnutrition), especially during the hunger season between May and September. This is because the lack of adequate land, water, and income diversification has hopelessly eroded the livelihoods of so many. Entire districts have thereby been rendered highly vulnerable to even moderate shocks let alone a total failure of the rains or significant food-price inflation (which also hits the urban poor hard). In this respect, it is quite telling that about half of the $1 billion U.S. annual aid to Ethiopia is food aid—mostly going to the food-for-work program that alleviates food insecurity rather than eradicating it for good.
  • Many more millions live just above this precarious subsistence line even in years of normal rainfall. Drought, pest invasion or civil strife swell the ranks of the starving in short order, with the negative effects persisting for at least a decade. It is no surprise then that Ethiopia faced regional famines in 1965/66, 2000/01, and 2011/12; and regime-destabilizing national famines in 1972-73 and 1974-85.
  • The 2015-16 famine underway bears the telltale signs a national tragedy and must be averted with decisive action. The current is already being compared in its potential devastation, by the survivors, to the infamous 1984 famine of Live Aid (which claimed over 1 million lives). A good indicator of this impending disaster is its national scope: the chronically food-deficit areas of southeastern Tigray, northeastern Wollo, all of Afar and parts of Somali, the southern lowlands of Sidamo and Bale, and the Enset-dependent areas southwestern Ethiopia.
  • In the fine tradition of unaccountable governments torn between publicly revealing the extent of the famine (terrified by the political fallouts) and their strong incentive to tap into international assistance (the donor practice of feeding the greedy to reach the needy), the Ethiopian Government is currently denying the patently obvious mounting loss of livestock and the rising mortality of the most enfeebled (as attested by BBC TV) while claiming to have allocated half of the relief supplies required from its own resources. While we are encouraged by the improved early warning system and the allocation of domestic funds, we are unimpressed by their inadequacy relative to the needs and to what is being spent on white elephant projects. We are also offended by the shameful insinuation of high government officials that it is ultimately the responsibility of the international community to save the most vulnerable in Ethiopia.
Ethiopiawinnet is compelled to implore:
1. The Ethiopian Government to own up to its sole responsibility to spare all its citizens from starvation and death by devoting all the resources necessary to tide them over to the next harvest. In the medium run, it should reform its land policy by granting ownership rights to farmers and pastoralists, invest in food production for domestic use instead of only exports, fostering off-farm employment opportunities, scrapping the current ethnic homeland system of regional administration that has hamstrung the traditional coping mechanism of seasonal inter-regional migration to work, and accelerating industrial development.
2. The international community to once again provide generous and timely relief aid to avert large losses of lives instead of waiting for large-scale deaths as “proof of need.” We also implore donors to insist on sensible food security policies that would make such recurrent dependency on food aid unnecessary for a country that has a great potential to feed itself.
3. All Ethiopians and friends of Ethiopia in the Diaspora to put politics aside for now and extend a generous helping hand through famine relief organizations with a proven record. Thank you.
Ethiopiawinnet, a rights-based CSO, believes that:
  • Famine is a political act of transgression on the mother of all human rights—the right to live.
  • Drought may be unavoidable, but famine certainly is. In the twenty-first century, this abomination belongs nowhere else but in the dustbin of history!

Sunday, November 15, 2015

የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ውጤቱ ጦርነት ነዉ! (የጎንደር ሕብረት)

November 15,2015
ልዩ መግለጫ
በጎንደር ክፍለሃገር ፤ በላይ አርማጭሆ ወረዳ፤ ልዩ ቦታው ማዉራ፤ ሮቢት፤ ጫጭቁና፤ ጋባ ጋላገር እንዲሁም ሌላም ብዙ አካባቢወች እና ከዚህ ቀደም ሲል ደግሞ፤ በጭልጋ አካባቢ ወገኖቻችን ላይ የወያኔ ሰራዊት የፈጸመዉን ኢሰባዊ ጭፍጨፋ በጥብቅ እናወግዛለን። ኢትዮጵያዊ ቆዳ ለብሶ፤ በሞሶሎኒ ጭንቅላት የሚያስበው ወያኔ፤ ገና ሲፈጠር ጀምሮ፤ ለዘመናት ሃይማኖት ፤ ቋንቋ ፤ ዘር ሳይገድበዉ አብሮ የኖረ ህዝባችንን፤ ከፋፍሎ እድሜ ልኩን ለመግዛት ሲል፤ በጎሳ ነፃነት ስም አንቀጽ 39ኝን በማር የተለወሰ መርዙን ለመላ ሕዝባችን እየጋተ አገራችንን እያተራመሰ ይገኛል። ይህ የጎሳ ፖለቲካው፤ በየተኛውም አካባቢ፤ ሰላም እና መረጋጋትን እንዳላመጣ በተግባር እያየ እንኳ ከሥህተቱ የማይማረው ግትር መንግሥት፤ በመሽ ሰዓት ወደ ሰሜኗ ክፍለ ሀገራችን ጎንደር ላይ ለመተግበር እየሞከረ ባለው የክልል ጣጣ ምክንያት፤ በጋባ፤ ትክል ድንጋይና እና በጭልጋ አካባቢ በከፈተዉ ጦርነት የንጹህ ወገኖቻችንን ህይወት ማጥፋቱ እጅግ አሳዝኖናል። በጣም የሚያስቆጨውና የሚያሳዝነው ደግሞ የወያኔ መንግሥት ሆን ብሎ አስቦና ተዘጋጅቶ አርሶ አደሩ በሳለም አርሶ ከሚኖርበት ቀየው ድረስ በመሄድ የፈጸመው የግፍ ጭፍጨፋ በመሆኑ ነው።gonder-unity
ይህ መንግሥት ተብዬ የአሸባሪ ቡድን፤ እንዲህ አይነቱን ግፍ ሲፈጸም የመጀመሪያው ባይሆንም የመጨረሻው እንደማይሆን እርግጠኞች ነን። በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ህጻናት፤ ከቤት የዋሉ አረጋዊያን፤ እሴቱች ሳይቀሩ መገደላቸውን በአካባቢው የሚኖሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል። አሁንም የፌደራል ወታደር ከቤት፤ ቤት እየተዘዋወረ ሰላማዊ ዜጎችን እያፈነ ነው። ሕዝቡም ቤቱን እና ንብረቱን ለማስከበር ሳይወድ በግድ ከመጣው ወራሪ ጦር ጋር እየተጋፈጠ ይገኛል። የወያኔ መንግሥት እንዲህ አይነቱን አረመኒያዊ ጭፍጨፋ በጎንደር ህዝብ ላይ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ሥልጣን ከመያዙ በፊት ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ እና በጠለምት ህዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እርምጃን በመውሰድ ነው። አሁንም ይህንን እኩይ ተግባሩን እንደቀጠለ ነው። ወያኔ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ፤ የህዝብን ጥያቄ በሰላም እና በዴሞክራሲዊ መንገድ የሚያሰተናግድ መንግሥት አለመሆኑን በተላያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እያደረግ ያለውን ጭፍጨፋ መመልከቱ በቂ ነው። ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደማይገኝ ሁሉ፤ ከወያኔ መንግሥትም ሰላም እና ዴሞክራሲ ይገኛል ብሎ መጠበቅ እራስን ማታለል ነው።
በመሆኑም፤ ይህ አርመኔያዊ፤ ጨፍጫፊ እና ከፋፋይ ሥራዓት በየተራ በየአካባቢያችን እየዘለቀ በልቶን ከመጨረሱ በፊት፤ የጎንደር ህዝብ ትጥቁን ሳይፈታ በአንድነት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመተባበር ከማስወገድ ውጪ፤ ፈጽሞ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለዉም። ይህ ካልሆነ መሬት መንጠቁን፤ በዘር እየከፋፈለ ርስ በርስ ማዋጋቱን እና መከፋፈሉን ያለማቋረጥ ይቀጥላል።
ጎንድር የአማራዉ፤ የቅማንቱ፤ የሽናሻዉ፤ የቤተ እስራኤሉ፤ የአገዉ የጋራ ርስት አገሩ ናት። ጎንደርን በጎሳ ለመከፋፈል እየተሞከር ያለው እቅድ፤ ከጥፋት ላይ ጥፋት ከመሆኑም በላይ ለቅድስት አገራችን ኢትዮጳያም የተቀነባበረ የብተና ሞሶሎኒያዊ የወያኔ አደጋ ነዉ።
ወያኔ በአሁኑ ሰዓት በጎንደር ዙሪያ እየሰራ ያለው መሰሪ ተንኮል፤ በአንድ በኩል ለቅማንት ብሄረሰብ የሰጠውን አነስተኛ ቀበሌ ለመከለል፤ ጥቂቶችን ሲያስገድድ፤ በሌላ በኩል የጠየቁትን ሙሉውን ቀበሌ ማግኘት ይገባናል? የሚሉ ካድሬወችን በብዙ ገንዘብ ቀጥሮ ወደ ህዝቡ አሰርጎ በማሥገባት ህብረተሰቡ ዕርስ በርሱ ቅራኔ ውሥጥ እንዲገባ በመገፋፋት፤ ጎንደርን የመገነጣጠል አላማውን ለማሳካት ሌተ ከቀን የጥፋት ስራዉን እየሰራ ይገኛል። የተከበርከዉ ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ሆይ! ከምንጊዜዉም በበለጠ አንድነትህን አጠናክረህ ትጥቅህን አጥብቀህ ታሪካዊ ጎንደርን አድን። ለሃያ ዓምስት ዓመታት የወልቃይት ጠገዴ፤ የጠለምት ሁመራ መሬትህ በትግራይ ነጻ አዉጭ ነኝ በሚሉ ባንዳወች ተወሮ ተዘርፏል፤ የዘር ማጥፋትና አፈናቅሎ የማጽዳት ጭፍጨፋ ተፈጽሞበት ጩሆቱን እያሰማ ይገኛል።
ነጻነት በልመና አይገኝምና ተባብረህ የሰባቱም አዉራጃ ህዝብ በአንድነት ዘረኛ ወራሪዉን ወያኔ ከታሪካዊ መሬትህ ጠራርገህ አስወጣ። በጎንደር የሚኖር የትግራይ ተወላጆች ሁሉ በጎንደር መሬት የመኖር ገደብ የሌለዉ የኢትዮጵያዊነት መብታቸው ነዉ። ካድሬወች፤ ሰላዮች፤ ጦረኛ ወራሪ ታጣቂወች ግን የጎንደር ህዝብ ፍጹም አይፈልጋቸዉም፤ በግፈ ትዉልድ ጨርሰዋልና፤ በአስቸኳይ መዉጣት አለባቸዉ። ዛሬ በአንድ አካባቢ ያለው ወገንህ በግፈኛው ቡድን በወያኔ ሲጨፈጨፍ፤ አሻግረህ እያየህ ተራህን ከመጠበቅ ይልቅ፤ “ሳይቃጠል፤ በቅጠል” እንዲሉ፤ እዚያው ችግሩን ከጫረበት ቦታ ድረስ በመሄድ እና ተባብረህ በመዋጋት ለአንዴና ለመጨረሻ ነፃነትክን ተጎናጸፍ። የጎንደር ሕዝብ ወራሪና ከፋፋይ ሃይልን መሸከም ይብቃው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! የጎንደር አርሶ አደር ከበደል ላይ በደል ተደራርቦበታል። ሱዳን አዝመራውን እያቃጠለ ፊት ለፊት ሲወጋዉ፤ ወያኔ ከኋላዉ ሃብቱን ይዘርፋል፤ ሚሊሻዉን ወደ ጎንደር ለም መሬቶች ያሰማራል። ይህንን አገራዊ ስሜት የሌለውን የዘረኛ መንግሥት የኢትዮጵያ ህዝብ ተከፋፍሎ ወይም ወኔ በሌለው ስሜት ከዳር ቆሞ ከንፈር መምጠጥ እና በባዶ ቁጭት እራስን ማቃጠል ሳይሆን፤ በቆራጥነት በጋራ ሆ! ብሎ በመነሳት ተባብሮ ማሥወገድ ይገባዋል።
የጎንደር ህብረት በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖቻችን መራራ ሃዘናችን እየገለጽን፤ ከርሃቡ በላይ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባችዉን ለመርዳት ከጎንደር ህዝብ ጎን እንደምንቆም እያረጋገጥን፤ እንዲሁም ለዚህ ጉዳት ዋነኛ ተጠያቂ ወያኔ የሚመራዉ መንግስት ስለሆነ፤ እጁን በአስቸኳይ ከህዝባችን ጫንቃ ላይ እንዲያነሳ እንጠይቃለን። በመጨረሻም፤ በማንኛውም በክፍለ ሀገሩ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን አሥመልክቶ መላዉ የጎንደር ህዝብ ተባብሮ እና ተመካክሮ እንደጥንቱ እንዲፈታ ጥሪያችን እናቀርባለን።
ጎንደርን በአንድነት እናድን። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ከጎንደር ህብረት

Saturday, November 14, 2015

በረሀብ ለተጠቁ ወገኖቻችን እንድረስላቸው !!!

November 14, 2015
def-thumbበወቅታዊ ሁኔታ ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 የአቋም መግለጫ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳግም ለአስከፊ ረሀብና ችጋር ተጋልጧል፤ ስፋት ጥልቀቱ በ70ዎቹና 80ዎቹ ከነበሩት ጋር ይስተካከላል ተብሎ ተፈርቷል። ከአሁኑ ሰው በረሀብ መሞት መጀመሩ ከአራትና አምስት ወራት በኋላ የሚመጣውን አደጋ ከባድነት መገመት ያስችላል።
ለአስር ተከታታይ ዓመታት ከአስር በመቶ በላይ ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት በማምጣት ዓለምን እየመራን ነው የሚለው ዓይን ያወጣ ውሸት፤ “ድህነትን ተረት እናደርጋለን” የሚለው ጉረኛ መፈክር፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራድዮ “የህዳሴ ብስራቶች”፣ የአባይ ግድብና የከተማ ባቡር ግንባታ ዜናዎች ለኢትዮጵያዊው አርሶ አደር ቁርስ፣ ምሳና እራት አልሆኑም።
“አድገናል”፣ “ተመንድገናል”፣ “በምግብ ራሳችንን ችለናል” ሲል የከረመው የህወሓት አገዛዝ የረሀቡ ዜና አፈትልኮ ሲወጣ እና የዓለም መገናኛ ብዙሀን መነጋገሪያ ሲሆን የተራበውን ወገናችንን ለማብላት ከመሯሯጥ ይልቅ ተፈጥሮ ላይ ማላከኩን ተያይዞታል። ከዚህ አልፎ ዓመታዊ ድግሶቹ እና ለባለሥልጣናቱ የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ ከረሀብ በላይ አሳሳቢ በመሆኑ 15 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በሞት አፋፍ ላይ እያለ የአገሪቱ ሀብት ለድግስና ፈንጠዚያ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ባለሥልጣን ቤተመንግሥት አከል መኖሪያ ቤት ማሠሪያ እየዋለ ነው። መቀሌ ላይ ህወሃት 40ኛ ልደቱን ለማክበር ወደ ግማሽ ቢልዮን ብር ባወጣ ማግስት በአማራ ስም ለወያኔ ባርነት የገባው ብአዴን 300 ሚሊዮን ወጪ በማድረግ በረሃብተኛው ሕዝብ አናት ላይ እየጨፈረ ነው:: ይህ የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅ ብቻ ሳይሆን ደግሞ ደጋግሞ ከመግደል የሚቆጠር ወንጀል ነው።
ለመሆኑ የአየር ንብረት መዛባት እየተደጋገመ ለሚመጣ ችጋርና ቸነፈር በቂ ምክንያት ሆኖ ያውቃልን? ለምንድነው ፍትህና ነፃነት በሰፈነባቸው አገሮች ውስጥ ዝናብ ጠፍቶ የእርሻ ምርት ቢቀንስ እንኳን ሰው በረሀብ የማይሞተው? አስከፊ የረሀብ ዜናዎች የሚሰማባቸው አገሮች በሙሉ ነፃነት የታፈነባቸው አገሮች መሆናቸውስ የአጋጣሚ ጉዳይ ነው? ለምንድነው ተደጋግሞ ከሚመጣ የረሀብ አዙሪት መውጣት ያቃተን?
የእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ አጭርና ቀጥተኛ ነው። ለችግሮች መፍትሄ መሻት የሚቻለው በነፃነት ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ሲኖር ነው። በባርነት ጨለማ ውስጥ ያለ ጭንቅላት ለችግሮች መፍትሄ የማፍለቅ አቅም የለውም። እንዲያውም እንዲህ ዓይነቱ ድኩም ጭንቅላት ችግሮችን ማሸነፍ ሳይሆን ተሸናፊነትን ተቀብሎ ከችግሮች ጋር ተስማምቶና ተወዳጅቶ መኖርን ይመርጣል። ለዚህም ነው የአስተዳደር በደልና ረሀብ ምክንያትና ውጤት ብቻ ሳይሆን እጅና ጓንትም ጭምር የሆኑት።
ነፃነት ያለው ሕዝብ ረሀብን እንደሚያሸነፍ ተደጋግሞ የታየ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ረሀብን የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት ውጤት ብቻ አድርጎ ማቅረብ እውነትን መሸፈጥ የሚሆነው። ረሀብ የብልሹ አስተዳደር ውጤት መሆኑ ያፈጠጠ፣ ያገጠጠ ሀቅ ነው። ከረሀብ መገላገያ መንገድም የተበላሸ አስተዳደር ተወግዶ ኃላፊነት የሚሰማው፣ የዜጎች የማሰብ ነፃነት የሚያረጋግጥ ሕዝባዊ አስተዳደር ሲኖር ነው።
አገራችን ኢትዮጵያን የረሀብ ቀጠና ካደረጉ የ24 ዓመታት የወያኔ “የዘርፈህ ብላ” የኢኮኖሚ ፓሊሲ ውጤቶች መካከል አንዳንዱን ለአብነት ያህል መዘርዘር ይቻላል።
1.ገበሬና መሬት ተለያይተዋል። ኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች መሬት አልባ ሆነዋል። ለም መሬቶች በኢንቨስትመንት ስም ለህወሓት ጉልተኞችና ምስለኔዎቻቸው ታድሏል፤ እነሱ ደግሞ በተራቸው ለባዕዳን ሽጠውታል። ኢትዮጵያዊው አርሶ አደር በሀገሩ ጭሰኝነት እንኳን አጥቶ ለቀን ሠራተኝነትና ልመና ተዳርጓል። በዚህም ምክንያት ገበሬው እንኳንስ ትልቁን የአየር መዛባት ትንሿንም የዋጋ ንረት መቋቋም እስከማይችልበት ደረጃ ተዳክሟል።
2.ዘርን መሠረተ ባደረገ ክልላዊ ድንበር ሳቢያ ኢትዮጵያዊው ጎበዝ አርሶ አደር አንዱ ቦታ ቢከፋ ወደ ተሻለ ቦታ ተዛውሮ ማረስ አልቻለም። ከሰሜን ወደ ደቡብ ከሄደ የአገራችን አርሶ አደር ይልቅ ባህር ተሻግሮ የመጣ ኤንቨርስተር ነኝ ባይ መሬት ማግኘት ይቀለዋል። እንዲያውም ኢትዮጵያዊው ገበሬ በዱላና በጥይት ሲባረር፤ ከባዕድ አገር የመጣው ብድርና ማበረታቻዎች ይሰጠዋል።
3.የህወሓት ባላሥልጣኖችና በየቦታው ያስቀመጧቸው ምስለኔዎቻቸው ራሳቸውን ባለሚሊዮኖች፣ ከፍ ሲልም ባለ ቢሊዮኖች አድርገዋል። እነዚህ በአንድ ጀምበር ከትቢያ የተነሱ ቱጃሮች ከገንዘብ በተጨማሪም የጄኔራልነት፣ የሚኒስቴርነት፣ የክልል ገዢነት፣ እጅግ ቢያንስ የቢሮ ኃላፊነት ሥልጣንን ኪሳቸው ውሰጥ ከተዋል። የመንግሥት ሥልጣንና ሃብት ይኸን ያህል የተቆራኙበት ሥርዓት በኢትዮጵያ ኖሮ አያውቅም። የጥቂቶች ያለአገባብና ያለቅጥ መክበር በአንፃሩ ደግሞ የብሃኑን ሕዝብ መደህየት ረሀብ እጣ ፈንታችን እንዲሆን አድርጓል።
4.በአቋራጭና በፍጥነት ለመክበር አስተማማኙ መንገድ የገዛ ራስ ጥረትና ታታሪነት ሳይሆን ቅጥፈት፣ አጭበርባሪነትና ሎሌነት ማደር መሆኑን የህወሓት አበጋዞች በተግባር እያሳዩ ሠርቶ፣ ለፍቶ ማደግ ሞኝነት እንዲሆን አድርገውታል። በዚህም ምክንያት በባህላችን ውስጥ ኮትኩተው ያሳደጓቸው አድርባይነት፣ ስንፍናና እና ልመና ችግርን የመጋፈጥ አቅማችንን ሰልበውታል።
5.ደኖቻችን ተጨፍጭፈው፣ ለም መሬታችን ተሸርሽሮ በማለቁ የግብርናችን ምርታማነት በእጅጉ ቀንሷል። በህወሓት የአገዛዝ ዘመን የደን ጭፍጨፋና የመሬት መሸርሸር በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ በፍጥነት ወደ ምድረበዳነት እየተቀየረች ነው።
6.ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች ድርቅን መቋቋም ስለሚችሉ ሰብሎች ወይም የአስተራረስ ዘዴዎች ማሰብ፣ መመራመርና መፈተሽ አይችሉም። አዲስ ነገር መሞከር “የኢህአዴግ የግብርና ፓሊሲን“ በመቃወም ወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር ሆኗል። በዚህም ምክንያት ገበሬው ድርቅን መቋቋሚያ አዳዲስ ዘዴዎች መፈለግ ቀርቶ በተለምዶ የሚያውቃቸውንም መጠቀም አልቻለም።
7.የህወሓት አገዛዝ፣ እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዛት ሊቆጣጠር የሚሞክረው ቢሮ ውስጥ ቁጭ ተብሎ በሚደረግ የቁጥር ጨዋታ ነው። አገዛዙ ውጤታማ የስነ ሕዝብ ፓሊሲ የለውም፤ እንኳንስ የቀጣይ ዓመታት የሕዝብ እድገት ምጣኔን ሊቆጣጠር አሁን ያለነው ቁጥራችን ስንት እንደሆነ እንኳን በትክክል ሊነግረን አልቻለም፤ ረሀብ ነው መብዛታችንን እየነገረን ያለው።
አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህና የመሳሰሉት ጭብጦችን በማንሳት የረሀቡ መሠረታዊ ምክንያት የህወሓት አገዛዝ ያሰፈነው ብልሹ አስተዳደር መሆኑን በአንጽዖት ይናገራል። ሕዝባችን በነፃነት ማሰብ፣ መመራመር፣ መፈተሽ ቢችል ኖሮ ረሀብን መከላከያ ብልሃት ማግኘት ባላቃተውም ነበር ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። ረሀብን ለማጥፋት ህወሓትን ከሥልጣን ማስወገድ ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ የሆነ ጊዜ ላይ ተደርሶአል ብሎ አርበኖች ግንቦት 7 ያምናል።
ነገር ግን ረሀብ ጊዜ አይሰጥም። የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ በሞት አፋፍ ላይ ላለ ወገናችን መፍትሄ አይሆንም። ስለሆነም ለረሀቡ መሠረታዊ መፍትሄ የሆነውን ትግላችንን ሳንዘነጋ የወገኖቻችንን ሕይወት ለመታገድ የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል። ሲቪክ ማኅበራት የተራበው ወገናችን የወያኔ መጠቀሚያ ሳይሆን የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚያገኝበት መንገድ እንዲያፈላልጉ እና ወገን ለወገን የሚቆምበትን ዘመቻ እንዲያስተባብሩ ጥሪ ያደርጋል። ለወገኖቻችን የሚላከው እርዳታ ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ ወደአገዛዙ ባለሥልጣኖች የግል ኪስ እንዳይፈስ ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባል። ለወገኖቻችን ለመድረስ እያንዳንዳችን በግል፤ እንዲሁም በቡድን የተቻለንን ሁሉ እናድርግ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኅዳር 3 ቀን 2008 ዓ.ም.

Friday, November 13, 2015

ለድርቁ አስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል ይቋቋም!

November 13,11 2015
“ህይወት ለማትረፍ በቅድሚያ መተማመን”
drought and hope

* ከአገዛዝ ለውጥ በፊት ችጋር ይቀድማል?
* “በአሁኑ ጊዜ ችጋሩ እንደ 1977 ሆኗል!”
በኢትዮጵያ ላለፉት ፴ ዓመታት ያለታየ ችጋር ተከስቷል። ድርቁና ረሃቡ ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ኢህአዴግን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይፋ እያደረጉ ነው። “የምግብ ዋስትናን አረጋግጫለሁ” በማለት ሲወተውት የኖረው ህወሃት ተገዶ ያመነው ችጋር ከ፩፱፯፯ ድርቅ በላይ የከፋ እንደሚሆን ስጋት አይሏል። ከዚህ በፊት እንደተከሰቱት ለውጦች ይህኛውም የአገዛዝ ለውጥ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ። በአስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል መቋቋም እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ህወሃት ከድርቅ እና ድርቅን ተከትሎ ከሚገኝ ዕርዳታ ጋር በተያያዘ ካለው አስጸያፊ ተሞክሮ በመነሳት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት ከድርቁ ጋር በተያያዘ ፍትሐዊነት ያሳስባቸዋል፡፡ ሲያብራሩም በከፍተኛ የሙስና እና የአድልዖ ወጥመድ ውስጥ መዘፈቁን ራሱ ያመነው ህወሃት የሚመራው አገዛዝ ችጋር በመታቸው ወገኖች ስም የሚመጣውን የውጭ ምንዛሪ በአግባቡ ሥራ ላይ የማዋል አቅምም ሆነ ተዓማኒነትም በጭራሽ የለውም ይላሉ፡፡ መለስ “እስከ እንጥላችን ገምተናል” ያሉትንና በቅርቡ ደግሞ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ሕዝብ ያውቀናል፤ አያምነንም፤ ቀበሌ እንኳን ስብሰባ መጥራት አንችልም” በማለት የተናገሩትን ለአብነት ይጠቅሳሉ፡፡ ራሱ “አልታመንም፤ ሌባ ነኝ” እያለ የሚለፍፍ አገዛዝ እንዴት በረሃብ ለተጠቁ በፍትሐዊነት ዕርዳታ ያደርሳል በማለት ይጠይቃሉ?
እነዚሁ ክፍሎች የሚሉትን በመደገፍ ስማቸውን ያልገለጹ የኢህአዴግ ዲፕሎማት እንዳሉት ከሆነ አንድ ከፍተኛ ብሔራዊ መነቃቃት ካልተፈጠረ ኢህአዴግና ካድሬዎቹ ሕዝብን በማነቃነቅ ችግሩን በፍትሐዊ መንገድ ሊፈቱት እንደማይቻላቸው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ዲፕሎማቱ የኢህአዴግ ሎሌ ቢሆኑም የህወሃት የበረሃ ውጤት ስላልሆኑ ህወሃት በበረሃው ተሞክሮ በዕርዳታ እህል ስም እያጭበረበረ ስለዘረፈው ገንዘብ ሲያስቡ አሁንም ይዘገንናቸዋል፡፡
ኢህአዴግ “ብሔራዊ” በሚል የሚጀምሩ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን የመውደድ ባህርይ ባይኖረውም፤ የተፈጠረውን ድርቅና ችጋር አስመልክቶ በጋራ ለመሥራት የግድ ይህንን ማድረግ እንደሚገባው የሚጠቁሙ ክፍሎች ህወሃትና ድርቅ ያላቸውን የጠነከረ መሳሳብና ግንኙነት መረጃ በማጣቀስ ያስታውሳሉ፡፡eTHIOPIA-worst-drought-of-africa-in-60-years
በተገንጣይ ስም ራሱን የሚጠራውና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የሚገዛት ኢትዮጵያ “በልማት ተጥለቅልቃለች፣ ልማት ላይ ነን” እየተባለ ቢዘመረላትም በውል የታየው ግን ሌላ ነው። ለዝርፊያው ሽፋን የሚለፈፈው የልማት ቀረርቶ ችጋር የሚያቃጥላቸውን ህጻናትና አረጋዊያን አንድ ወር እንኳን መታደግ የሚችል አቅም አልፈጠረም። ለምርጫ ዘመቻ ሲባል ተደብቆ የነበረው ችጋር ይፋ ሲሆን የታየው እውነት የመሰከረው ሃቅ ቢኖር አገሪቱ በባዶ ቀረርቶ እየደነቆረች መሆኑን ነው።
ህወሃት ሥልጣን ላይ በቆየበት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ ችጋር ከመከሰቱ አንጻር ጉዳዩን የሚመለከቱ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እንደታየው አስከፊው ችጋር የአገዛዝ ለውጥ ለማምጣት የራሱን የሆነ ከፍተኛ ሚና ተጫውቶ አልፏል፡፡ ይኸኛውንም ከዚሁ ጋር በመዳመር የለውጥ ማዕበል ሊያመጣ ይችል ይሆን የሚለው የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ችጋሩን በግምባር የተጋፈጡ ነዋሪዎች አሁን ያለው የጠኔ ደረጃ እንደ 1977ቱ ዓይነት ነው ይላሉ፡፡ ከዚያም የሚያስበልጡት አሉ።
ህወሃት/ኢህአዴግ ለማድበስበስና ለመሸፋፈን የሚጥረው ችጋር ዓይኑን አፍጥጦ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እየተሰማ ነው፡፡ በመሆኑም በመጪው የአውሮጳውያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ በችጋር የተመታው ሕዝብ ቁጥር 15 ሚሊዮን እንደሚደርስ የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቋል፡፡ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ግማሽ የሚያህሉት ህጻናት እንደሆኑም ይገመታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ 8.2 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እንደሚስፈልገው ይኸው የተባበሩት መንግሥታት ዘገባ ያስረዳል፡፡ ይህ አኻዝ ከስድስት ወር በፊት በችጋር ከተጠቃው በዕጥፍ እንዳደገ መረጃው ይጠቁማል፡፡ ይህም ህወሃት/ኢህአዴግ “ልማት፣ ውዳሴ፣ ህዳሴ፣ …” በማለት እንደ ጎበዝ ተማሪ መቶ በመቶ ያመጣበት “ምርጫ” ከመደረጉበፊት ነበር፡፡ በወቅቱ የችጋርና የድርቅ ጉዳይ አልተነሳም፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎችም እንደሌላው ጉዳይ በቂ ሽፋን ሲሰጡበት አልታየም፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ “የጎበዝ ተማሪ” ሰርቲፊኬቱን ከተቀበለ፣ ከበሮውን ከደለቀ፣ ድግሱን ከደገሰ፣ መሸከም እስኪያቅተው ከበላና ከጠጣ በኋላ ከሰከረበት በቅርሻትና በግሳት ሲነቃ የመልካም አስተዳደር መጓደል፣ የድርቅና ረሃብ፣ የሙስና፣ … ጉዳዮችን ከዚህ በፊት እንዳልነበሩ አድርጎ ሕዝብ ሊያሳምን መሞከሩ ተቀባይነት እንደሌለው ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን የላኩ በአጽዕኖት የሚያስረዱት ነው፡፡
ሰሞኑን ከቪኦኤ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ ቴድሮስ አድሃኖም “የህዝብ ቁጥር እጥፍ በመጨመሩ ፰ ሚሊዮን ህዝብ ቢራብ ፹ ሚሊዮኑ በአስተማማኝ ደረጃ በምግብ ራሱን ችሏል” በማለት መሳለቃቸው ይታወሳል። ከእንደ ቴድሮስ ዓይነቱ ችጋርን በቴሌቪዥን መስኮት ከመመልከት ያለፈ ዕውቀትና ርኅራኄ የሌለው ይህ መሰሉ የድንቁርና አነጋገር መሰማቱ የሚያስደንቅ እንዳልሆነ የሚናገሩ ወገኖች ቴድሮስ ለቪኦኤ የተናገሩትን ሃሳብ ሞት ካስፈነጠራቸው መለስ እንደኮረጁት ይናገራሉ፡፡ ሕዝብ በተራበ ቁጥር መለስ ዜናዊ ምክንያቱን ሲጠየቁ የሕዝብ ቁጥር በመጨመሩ እንደሆነ የመሃይም መልስ በመስጠት ተደናቁረው ሲያደናቁሩና ሎሌዎቻቸውን ሲያስጨበጭቡ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ መለስ የሥልጣኑን ኮርቻ መጋለብ እንደጀመሩም አምላካዊነት ተሰምቷቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እንመግባለን ብለው የተነበዩት ወደ ዜሮ ወርዶ በሞት መቀደማቸው የአስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን የምኞትም ደሃ መሆናቸውን ያረጋገጡበት እንደሆነ በርካታዎች የሚመሰክሩት ነው፡፡
ህወሃት ቃላት በማሳመርና ቁጥሩን በመቀነስ “የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው፣ የምግብ ዕጥረት የደረሰባቸው፣ …” በማለት ንብረቱ ባደረገው ሚዲያ ጉዳዩን አቃልሎ ቢያስወራም እውነታው ግን ሕዝብና እንስሳት በችጋር እየሞቱ መሆናቸው ነው በማለት በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ የግብርና ባለሙያ ተናግረዋል፡፡ ምናልባትም በጠኔ እየተቃጠለ ያለው ሕዝብ ብዛት ከተገመተው በላይ ሊሆን እንደሚችልና ጉዳቱም እጅግ አስከፊ እንደሚሆን እኚሁ ባለሙያ አስረድተዋል፡፡ በመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ መሠረት በቀን ቢያንስ ሁለት ህጻናት ይሞታሉ፡፡
አበራ ወልዱ የተባሉ የ60 ዓመት አዛውንት የግብርናው ባለሙያ የተናገሩትን ሃሳብ የሚያጠናክር አስተያየት መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ “ችጋሩ ገና ጅማሮ ቢሆንም እየከፋ ነው የሄደው፤ ገና ካሁኑ በጣም አስከፊ ሆኗል፤ ሰዎች እየሞቱ ነው፤ ሌሎች ሰዎችም (በችጋር ምክንያት) ታምመው አልጋ ላይ ወድቀዋል” በማለት አዛውንቱ ተናግረዋል፡፡ አክለውም “እንዲያውም አሁን ልክ እንደ 1977ቱ ችጋር ሆኗል” በማለት የሰጡትን ምስክርነት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ዘመን የተከሰተውን የወሎ ችጋር (የወሎ ድርቅ የሚባለውን) ለመደበቅ የተደረገው ሁኔታ ለንጉሣዊው አገዛዝ መውደቅ ክብሪት ከጫሩ ምክንያቶች እንደ ዋንኛው ይጠቀሳል፡፡ በወቅቱ ንጉሣውያን ቤተሰቦች ለንጉሡ ልደት በርካታ ገንዘብ በከንቱ እንዳባከኑ ደርግ የአጼ ኃይሥላሴን አገዛዝ ሲያማበትና ሲኮንንበት የነበረ ፕሮፓጋንዳ ነበር፡፡
Gebremedhin Araya (L) says he posed as a merchant, but was in fact a rebel
ከውጭ ዜጋው በስተቀኝ አቶ ገብረመድኅን አርአያ “ለሸጡት እህል” ገንዘብ ቆጥረው ሲቀበሉ::
ከላይ አቶ አበራ ወልዱ ያወሱት የ1977ቱ ረሃብ በተከሰተበት ወቅት ደርግ ለ10ኛው ዓመት የአገዛዝ ዘመኑን አገር ምድሩን በሰሜን ኮሪያ ብልጭልጭ ማድመቂያዎች “አስውቦ” ነበር፡፡ ይኸው ችጋር ለደርግ መውደቂያ ምክንያት ሲሆን በሌላ በኩል ለህወሃት ደግሞ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የፋይናንስ “ዕድል” ከፍቶለት ነበር፡፡ በወቅቱ ለበዓሉ ድግስ የወጣው ወጪ ለተረጂ ወገኖች መዋል ነበረበት በማለት ህወሃት ከበረሃ ሲጮህ በተመሳሳይ መልኩ ለትግራይ ሕዝብ እህል መግዣነት የመጣውን ገንዘብ ህወሃት ለራሱ ማድረጉን የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ማረጋገጡን ቢቢሲ ሲዘግብ የቀድሞ አባላቱም የድርጊቱን ትክክለኛነት አረጋግጠው ነበር፡፡
የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ በቢቢሲ ይፋ የተደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው በ1977 በተከሰተው አስከፊ ችጋር ምዕራባውያን ድርጅቶች እና ለጋሾች ወደ ኢትዮጵያ ለእህል መግዣነት እንዲውል የላኩት ገንዘብ የህወሃት ሹሞች ራሳቸውን በመደበቅ እህል ሻጭ መስለው በመቅረብ ከላዩ እህል ከሥሩ በአሸዋ የተሞላ ጆኒያዎችን እንዳረካከቡ በወቅቱ በሽያጩ ላይ የነበሩት የቀድሞው ከፍተኛ አመራር አባል አሁን በአውስትራሊያ የሚገኙት አቶ ገብረመድህን አርአያ አረጋግጠዋል፡፡ ቢቢሲ ባሰራጨው ፎቶግራፍ ላይ እንደሚታየው ሻጭ ሆነው የቀረቡት ገብረመድኅን ለሸጡበጥ ገንዘብ ቆጥረው ሲረከቡ የሚታዩት ራሳቸው መሆናችን ከመመስከር በተጨማሪ ሙስሊም መስለው በመቅረብ ጉዳዩን እንደፈጸሙም ተናግረዋል፡፡ የሸጡበትንም ገንዘብ ለመለስ ዜናዊና ለሌሎቹ የህወሃት አመራሮች ማስረከባቸውን ጨምረው አስረድተዋል፡፡ ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ መለስን ቢጠይቅም እርሳቸው ግን ምንም ዓይነት አስተያየት ሳይሰጡ ጥቂት ቆይተው በዚያው አልፈዋል፡፡
በወቅቱ Christian Aid ከተባለው የዕርዳታ ድርጅት 500ሺህ ዶላር በብር ይዞ እህል ለመግዛት የመጣው ማክስ ፐበርዲ እንደሚለው ገንዘቡን ለእህል መግዣ እንዳዋለውና አንዳችም የዕርዳታ ገንዘብ ለሌላ ነገር እንዳልዋለ ቢናገርም ግብይይቱን የፈጸመው ግን ከከፍተኛ የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) አመራር ጋር እንደሆነ መናገሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይህንን ተግባር አሁን በኔዘርላንድስ በስደት የሚገኙት የቀድሞ የህወሃት አመራር አረጋዊ በርሄም ያረጋገጡ መሆናቸው በወቅቱ የተዘገበ ጉዳይ ነበር፡፡ “የዕርዳታ ሠራተኞቹ ተሞኝተው ነበር” ያሉት አረጋዊ በርሄ እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ መገኘቱንና ከዚህ ውስጥ 95በመቶ የሚያክለው የጦር መሣሪያ ለመግዛትና ማርክሲስት ሌኒንስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊትን) ለመገንባት ወጪ እንደተደረገ መስክረዋል፡፡
“ነጻ አወጣዋለሁ” ያለውን ሕዝብ የዕርዳታ እህል እንዳይደርሰው በማድረግ አሰቃቂ ግፍን የፈጸመው ህወሃት አሁንም ተመሳሳይ ተግባር ከማድረግ የሚቆጥበው ምንድነው በማለት የሚጠይቁ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በተለይ ችጋሩ ከበረታባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ በሆነው ትግራይ የሚገኙ ነዋሪዎች በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ እንዳሉና ይህንኑ ችግራቸውን ከህወሃት ይልቅ ለአረና ሰዎች እና ለሌሎች ሊሰሟቸው ለሚችሉ እየተናገሩ እንደሆነ ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
eprdf homesየችጋር ሰቆቃ በአገሪቱ መከሰቱ እየታወቀ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት አገር ለማፍረስ የተመሠረተበትን 40ኛ የልደት ዓመት በዓል ሲያከብር 2 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን እንዲሁም በትግራይ የዳያስፖራ ቀን ሲያከብር 200 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን፤ “እጅግ ቅንጡ የሆኑ ዘመናዊ ቪላዎች ለስድስት የቀድሞ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት በ154 ሚሊዮን ብር ተሰርተው” እየተጠናቀቁ መሆናቸውን፣ እንዲሁም “የህወሃት የአማርኛ ክፍል” የሆነው ብአዴን በህወሃት እንደ ጭቃ ተጠፍጥፎ የተሰራበትን 35ኛ ዓመት ለማክበር 300 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚሆን (ትክክለኛው ከዚህ ሊበልጥም ይችላል) በተሰማበት ሰሞን 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለአስከፊ ችጋር መጋለጡን የዓለም ሚዲያ መዘገቡ “ችጋር ውድቀትን ይቀድማል” የሚለውን አባባል እያጠናከረው መጥቷል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ከሆነ የኢትዮጵያን ችጋር ለጊዜው ለመታደግ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ብሏል፡፡ ችጋሩ በአገሪቱ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን ከምስራቅ እስከ ሰሜን ዘልቋል፡፡ ሰሞኑን ከሚከሰተው ዝናብ ጋር በተያያዘ በጥቂቱም ቢሆን እየበቀለ ያለው ሰብል እንደሚወድም ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ አሁን የሚታየው ሁኔታ “የምጥ ጣዕር መጀመሪያ” የሚባለው ሆኖ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ችጋሩ እየዘለቀና እየከረረ እንደሚሄድ በግልጽ የሚታየው ሁኔታና ሌሎች በርካታ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የመጨረሻውን የጠኔ ሳል ስለው ህይወታቸው የሚጠፋው ህጻናት ቁጥር በቀን ሁለት ብቻ ተወስኖ የሚቀር እንዳልሆነ በስፋት ይገመታል፡፡
ለተረጂው ወገን በዕርዳታ ስም የሚገባ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ለሚንፏቀቀው ኢህአዴግ ታላቅ ገጸበረከት እንደሚሆን የብዙዎች ግምት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ የማይታመን ድርጅት የሆነው በሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን ከከፍተኛ አመራሮቹ አንስቶ እስከ ቀበሌ ያለው እርስበርሱ አንዳች አመኔታ የለውም፡፡ በሙስና “መበስበሳቸውን” ደጋግመው በአደባባይ ይናገራሉ፤ ይደሰኩራሉ፤ ይመሰክራሉ፡፡ ስለዚህ “በመንግሥት ሌቦች” የተሞላው ኢህአዴግ የተረጂዎችን ገንዘብ የግሉ ከማድረጉ በፊት የዕርዳታውን አሰባሰብና ፍትሐዊ አሰረጫጨት የሚቆጣጠር፣ የሚመራና የሚያስተዳድር ብሔራዊ ግብረኃይል መቋቋም እንዳለበት በአጽዕኖት የሚያምኑ ወገኖች ሃሳባቸውን ለዝግጅት ክፍላችን ለግሰዋል፡፡ ይህ ግብረኃይል ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ፤ ህወሃት ባዋረደው “ሽምግልና” ያልቀለሉ፤ በዕድሜ ብቻ ሳይሆን በተግባራቸው “አንቱ” የተባሉ አገር ውስጥና ውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መሆን እንደሚገባው አበክረው ይማጸናሉ፡፡ የአምስት ለአንድና መሰል የህወሃት አደረጃጀቶችን ለጊዜው ወደ ጎን ተደርገው ለሕዝብ ሲባል አስቸኳይ ውሳኔ ላይ ካልተደረሰ የችጋሩ ጉዳይ በትንሹም ቢሆን የቀረውን ክብራችንን አሟጥጦ በየሄድንበት ዕድሜ ልካችንን አንገታችንን የምንደፋበት እንደሚሆን በየዕለቱ በችጋር በሚሞቱት ህጻናት ስም ተማጽነዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ስለ “ውዳሴ፣ ህዳሴ፣ ባቡር፣ መንገድ፣ ፎቅ፣ ትልቅነትና ትልቅ መሆን፣ …” ሲደሰኮር ቢዋል መቀመጫን ገልቦ ፊት ከመከናነብ የማያልፍ ግብዝነት እንደሚሆንና ይህም ጊዜውን ጠብቆ ዋጋ እንደሚያስከፍል በእርግጠኝነት ይናገራሉ፡፡

Monday, November 9, 2015

ከትናንት በፊት የተቀሰቀሰው ጦርነት ሮቢት፣ ጎንደሮች ማሪያምና ጋባ በተባሉ አካባቢዎችም ጭምር ዛሬም ለሦስተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፡፡

November 9,2015
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
ከጎንደር 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው ማውራ መንደር በገበሬው ህዝብና በህወሓት ልዩ ኃይል መካከል ከትናንት በፊት የተቀሰቀሰው ጦርነት አድማሱን አስፍቶ ሮቢት፣ ጎንደሮች ማሪያምና ጋባ በተባሉ አካባቢዎችም ጭምር ዛሬም ለሦስተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፡፡
ቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 27 2008 ዓ.ም ከ200 በላይ የህወሓት ልዩ ኃይል አባላት በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውንና እንደ መሪ የሚታዩትን የአገር ሽማግሌዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ወደ ማውራ ለመግባት ሞክረው የአካባቢው ገበሬ በጠቅላላ በአንድነት ሆ ብሎ ታጥቆ በመውጣት ወደ ቀዬው አላስደርስም በማለቱ ሲሆን ግጭቱ የተቀሰቀሰው ወደ ማውራ ከሄዱት 200 የህወሓት ልዩ ኃይል አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከገበሬዎቹ በተተኮሰባቸው ጥይት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ 
ማውራ ላይ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ ሌሎች አጎራባች መንደሮችም በመቀጣጠል ተስፋፍቶ በጎንደሮች ማርያም፣ ሮቢትና ጋባ በጎንደር ገበሬዎችና በህወሓት ልዩ ኃይሎች መካከል ደም ባፋሰሰ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በተለይም ደግሞ የጎንደሮች ማርያም ገበሬ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር በመክበብ መውጫ ቀዳዳ አሳጥቶ ጭፍጭፎ አስቀርቶታል፡፡
በማውራ የተከፈተው ጦርነት ትናንት ቀኑን ሙሉ ውሎ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት ያለምንም ፋታ መቀጠሉን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ረፋዱ አራት ሰዓት ድረስ በማውራ ገበሬዎችና በህወሓት ልዩ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ ተካሂዷል፡፡ 
በአሁኑ ሰዓት የማውራና ሌሎች መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ወንዶች በጠቅላላ ታጥቀው ባቅራቢያቸው ወደሚገኝ ጫካ የገቡ ሲሆን መንደሮቹ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የህወሓት ፌደራል ፖሊስ ጦር ተወረዋል፡፡ በመንደሮቹ ውስጥ የቀሩት ህፃናትና ሴቶች ብቻ ናቸው፡፡ አስገድዶ መድፈር፣ ግድያ፣ ግርፋትና እስር በፖሊሶቹ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ፡፡ መፈናቀልም ተፈጥሮ ብዙ ጎጆዎች ውስጣቸው ኦና ሆኖ በሮቻቸው ተዘግተዋል፡፡
በውጊያ ከገበሬዎች በኩል 1 ተዋጊ ብቻ እስካሁን ተሰውቷል ሌሎችም የቆሰሉ አሉ እየተባለ ነው፡፡ በተጨማሪም ቁጥራቸው ያልታወቁ ህፃናትና ሴቶች ተገድለዋል፡፡ 
የህወሓት አገልጋይ የሆነው ብአዴን አባል የሆኑት የጎንደር ሹሞች ነፍጥ አንስተው እየተፋለሙ ከሚገኙት ገበሬዎች ጋር በስልክ ለመደራደር ሞክረው "እንኳን ለእናንተ ልንሸነፍ እነ ገዛኸኝ ወርቄንም አርበድብደናቸዋል፡፡" የሚል ምላሽ እንዳገኙ ታውቋል፡

ኢህዴን/ብአዴን የአማራን ሕዝብ አይወክልም ሞራሉም ብቃቱም የለውም!!

November 9,2011
አንተነህ ገብርየ
መብርሓቱ ገብረእግዚአብሔር ወይም በረከት ስምኦን በበርሃ ስሙ (አንበርብር) እየተባለ የሚታወቀው ጎንደር የተወለደው ኤርትራዊ የአማራ ሕዝብ ጠላት ከኢህአፓ እስከ ብአዴን የፈፀማቸው ፀረ-ሕዝብ ተግባሮቹ ።Bereket Simon/Mebratu
ይህን ሰው በሚመለከት ከዚህ ቀደም ትውልዱና የዘር ሀረጉን የቤተሰቡን ሁኔታ መጻፌና ጹሁፉ ለአንባቢያን መቅረቡን አስታውሳለሁ። ሌሎች ለሕዝብ ይፋ ያልተደረጉ ኅልቆ መስፈርያ የሌላቸውን ጉዳዮች ጊዜ ወስዶ ለማጋለጥ ይህ ባካናም ዘመን እድል ሊሰጠኝ አልቻለም እንጅ በውስጥ ከመቃጠል አላረፍኩም። ያም ሆነ ይህ በዚህ በያዝነው ወር 35ኛውን ዓመት የአማራውን ሕዝብ የገደሉበትን፤እስር ቤት ያጎሩበትን፤አካሉን ያጎደሉበትን፤ንብረቱን የዘረፉበትን፤አገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረጉበትን፤የዘር ፍሬውን ያመከኑበትን፤ጦርነት ውስጥ ማግደው ያስፈጁበትን፤እንደከብት ቆዳውን ገፈው በሕይወቱ ገደል የጨመሩበትን፤እቤት ውስጥ አስገብተው በሳት ያቃጠሉበትን፤ደሙን የመጠጡበትን፤የሰውነት ክፍሉን አውጥተው የሸጡበትን፤ተወልዶ ካደገበት ቀየው አፈናቅለው መሬቱን የሸጡበትን ልደት ለማክበር የቀረህን አራግፈህ ወዲህ በል እያሉ አማራውን እያመሱ ያሉበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ እንደ አንድ የአማራ ነገድ ተወላጅ በአለሁበት ሆኜም አንደበቱ የታፈነውን አማራ ሕዝብ ድምጽ ማሰማት ኃላፊነትና ግዴታየ በመሆኑ ለዛሬ ይህን መጣጥፌን አቀርባለሁ።
በረከት ከላይ እንደተገለጸው ትውልዱ በእናት በአባቱ ኤርትራዊ መሆኑ ግልጽ ነው ተወልዶ ያደገው ጎንደር ሲሆን በረከት ያችን የጎንደሬነት ካርድ እየመዘዘ የጎንደርን ተወላጆች ከሌላው ነጥሎ ለማስመታት የሄደባቸው መንገዶች በጣም አደገኛ እንደነበሩና አሁንም ስልታቸውን እየቀያየረ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ በግልጽ ሊታወቅበት ይገባል።ይህን ጉዳይ ነባር የኢህዴን ታጋዮችም ሆነ የአሁኖቹ የብአዴን ታጋዮች ያውቁታል።አዲሱ ለገሰ የአማራ ክልል ገዥ በነበረበት ወቅት በረከት በቀጥታ ወደ ጎንደር እየሄደ ጎንደርን አትንኩ አይነት ቃላትን እየተጠቀመ ጎንደሬ የሆኑ ካድሬዎችን ይቀጣ ነበር።ካድሬዎችን ለምን ቀጣ ሳይሆን ወደ ጎንደር መመላለስ ሲያበዛ አንድ የፈለገው ነገር እንዳለ አውቅ ነበር። 1ኛው ጉዳይ አንዳንድ አስተሳሰበ ደካማ የሆኑ ቅማንቶችን አስተባብሮ በአማራው ላይ አመጽ እንዲያነሱ ለማድረግ መሆኑ ግልጽ ነበር ይህም አሁን እየተደረገ ያለ ጉዳይ ነው። 2ኛው ጉዳይ የህወሃትን ወደ ጎንደር መስፋፋት ለማጠናከር እንደሆነም ይታወቃል። ጎንደሬ ነኝ እያለ ግን የጎንደር ሕዝብ ሥራ የማይወድና ሰነፍ ሕዝብ ስለሆነ መሬቱ ጦሙን ከሚያድር ቢለማ ምን አለበት? የምትለዋን ቃላት በስፋት ይጠቀማል።ስለጎንደር ሲነሳ ትግሬዎችም ሆኑ ትግርኛ ተናጋሪዎች አስቀድመው የሚወረውሯት ቃል ይህችው ናት።በረከት እንደ የብአዴን አመራር ከብአዴን ማ/ኮ ጋር ሳይሆን የሚማከረውና ትእዛዝ የሚቀበለው መለስ በነበረበት ወቅት ከመለስ ሲሆን አሁን ደግሞ የመለስ ራእይ አራማጅ ከሆኑ የህወሃት መሪዎች ጋር ነው። ይህን የብአዴን ማ/ኮ ሳያውቀው በስሎ የሚቀርብን ሃሳብ በተግባር ለማዋል በተናጠል እያሳመኑ እጅ እንዲሰጡ በማድረግ መሄድ የተለመደ ነበር።ዋናው ግብ በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ጎሳዎችን ውስጥ ለውስጥ በማደራጀት በአማራው ላይ አምጸው እንዲቆሙ ማድረግና በተለመደው የአማራ ጥላቻ ከአናሳዎቹ ጎን በመሆን አማራውን ለመምታት የሚጠቀሙበት መሣርያ ነበር አሁንም በዚሁ መንገድ እንደሚሄዱ ሥራዎቹ ወይም የሚፈጽሟቸው ተግባሮች በግልጽ ያሳያሉ።
የዚህን መሰሪ ሰው ተንኮል ለመመልከት ወደ ኋላ ሄጀ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፦በደርግ አገዛዝ ወቅት ህወሃት ጎንደርን በተለይም የሰሜኑን ክፍል ይዞ ነበር በ1977 ዓ/ም የተወሰነውን ቦታ ለኢህዴን አስረክቦ ሲንቀሳቀስ በመጀመርያዎቹ አካባቢ ህዝቡ ከደርግ ጋር በነበረው ጥላቻ ብቻ ተቀብሎ ማስተናገዱ አልቀረም ይህ በዚህ እንዳለ በ1978 እና በ1979 ዓ/ም ኢህዴን በሁለት ተከፍሎ የመበተን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር።ምክንያቱ ያሬድ ጥበቡ ወይም ጌታቸው ጀቤሳ እየተባለ የሚጠራው የኢህዴን ሊቀመንበር የነበረ በኋላ ታምራትና መለስ በፈጠሩት ሴራ ጌታቸው በውጭ ሄዶ የማደራጀትና ኢህዴንን የማጠናከር ሥራ እንዲሰራ ተብሎ ወደ ውጭ ወጣ የሱን ቦታ ታምራት ተካ።በዚህ ወቅት አብዛኛው ታጋይ በታምራት ላይ ቅሬታ ያሳደረና በጌታቸው መነሳት ቅሬታ የተሰማው ነበር። ጌታቸው ሳያኮርፍና ተስፋ ሳይቆርጥ ኢህዴንን የማጠናከር ተግባሩን ቀጥሎ ተጓዘ በየጊዜው የሚፈጽመውን ተግባርም አገር ቤት ላለው የኢህዴን ማ/ኮ ሪፖርት ያደርግ ነበር።መልእክቱ ከአሜሪካ ወደ ሱዳን በህወሃት መስመር ይላካል የራዲዮ መልእክት የጹሑፍ ይላካሉ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የህወሃትን በጎ ፈቃድ ማግኘት ነበረበት።ከእለታት አንድ ቀን ህወሃት የኢህዴንን የጹሑፍ መልእክት ይጠልፍና ፖስታው ተከፍቶ ይነበባል የሰው ስም ዝርዝር ያለበት ነበር ጌታቸው የላከው ለኢህዴን አባልነት፤ደጋፊና ተባባሪ ይሆናሉ የተባሉትን ስም የያዘ ደብዳቤ።
ኋላስ ምን ሆነ? አጅሬ ህወሃት ይህን ደብዳቤ አፍኖ ከቆየ በኋላ በውጭ ያለውና በአገር ቤት ያለውን የኢህዴን አመራር በጥርጣሬ ላይ አክርመው ደብዳቤው እጃቸው መግባቱንና ጌታቸው የመለመላቸው ሰዎች ለኢህዴን አደገኛ ስለሚሆኑ ኢህዴንን ከአደጋ ለመከላከል ስንል ያደረግነው ነው ተብሎ በበጎነት እንዲታይና የኢህዴን አመራር እምነት እንዲጥሉበት ተደረገ።አደጋው ግን ለኢህዴን ሳይሆን ለህወሃት እንደነበር ግልጽ ነበር ይህ ይፋ ሲሆን የኢህዴን አባላትና አመራር በጌታቸውና ታምራት ቲፎዞነት ሲጦዝ ከረመ ህወሃትና ኢህዴን በጹሑፍ መባጠስ የጀመሩበት ወቅትም ነበር ዋናው ነጥብ አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርዓ ጽዮንን በገዳሪፍና ካርቱም የኢህዴን ጽ/ቤት በማስተናገዱ ህወሃትን ደፍሯል የሚል ሲሆን ኢህዴን ደግሞ ምሥጢሬን አይታችኋል በሚለው ዙርያ ነበር።በዚህ ወቅት አያ በረከት ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሲሸመገል የነበረው ከጌታቸው ወገን በመሆን ሲሆን እስከ መቼ የህወሃት ሸሚዝ ሆነን ልንኖር ነው በማለት አኩራፊ ነበር ይህች ግን በነመለስ ቅንብር ከጌታቸው ጎን ገፍተው የሚወጡትን የአማራ ተወላጆች ለማጥመድና ጊዜ ገዝቶ(ጠብቆ)ፀጥ ለማድረግ ያለመ ነበር ተሳካ። የበረከት ወንድም ካሣሁን የተገደለው በህወሃትና በኢህአፓ በተደረገ ጦርነት ከህወሃት በተተኮሰ ጥይት ነው ይህ ግን ለበረከት ምኑም አልነበረም በሬ ካራጁ ብንልም የበረከት ዓላማ ሌላ ነበርና ዛሬ ላይ ሆነን በረከት የመጣበትን መንገድ ስንመለከት ዘለቀ፤ሙሉዓለም፤ጌጡ(ኡስማን)፤አውጃኖ፤አገኘሁ፤ንጉሤ…ወዘተ የተገደሉበትን ሁኔታ በገሃድ ያስያል።
ሌላው በረከት በአማራ ህዝብ ደም ምን ያህል እንደቀለደ የሚያሳየው በ1984 ዓ/ም ደቡብ አካባቢ ምክንያቱ ኦነግን ያደረገ ነገር ግን ኢህአዴግ በዋናነት የመራው በሐረር፤በአርባ ጉጉ፤ወተርና እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የአማራ ነገድ ባላቸው ምስኪን ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው እልቂትን አስመልክቶ እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ በማለት ማስረጃዎች ተቀብረው የሚቀሩ ይመስል ነገርን ከራስ አውርዶ ለመጣል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አማራዎችን ሆድ ለማባበል ሲባል የጎንደር 21 ቀበሌዎች ያዘጋጁት እንዲባልና ኢህዴን ወደ ብአዴንነት ሽግግርን በሚያደርግበት ወቅት ለደቡብ አማራዎች ትርንስፖርት ተዘጋጅቶ ጎንደር ከተማ ድረስ እንዲሄዱ ተደርጎ ሰፊ ድግስ ተደርጎ የደቡብ አማራ ወገኖቼ አይዟችሁን ተችረው እንዲመለሱ የተደረገው ትራጀዲ ወደ ኋላ ተመልሸ ሳስበው ያመኛል።በድርጅት ገንዘብ ወጭ ተመድቦ ነገር ግን ገንዘቡ ደብዛው ጠፍቶ ዝግጅቱ በ21ዱ ቀበሌዎች በጀት ተሸፈነ። ያ ዝግጅት በጎንደር አማራዎችና ከደቡብ ወገኖቹ በመጡ አማራዎች መካከል ልብ ለልብ ያገናኘ ከበረት የጠነከረ አንድነትን ፈጥሮ ነበር የሚያሳዝነው ነገር ያኔ የተወረወረች የውሸት አይዟችሁ ለምን ከክልሌ መጣችሁብኝ በማለት በሽፈራው ሽጉጤ ፊታውራሪነት በጉራ ፈርዳና በቬንሻንጉል በጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች አማራን አያሳየኝ በማለት ምስኪን ወገኖቻችን ሲያልቁ የደረሰላቸው አልተገኘም በራሳቸው የአማራ ክልል በሚባለው እንኳን የሚተባበራቸው ጠፍቶ የአማራው ገዥዎች ጀርባቸውን ሲሰጡ ተመልክተናል።
ዛሬ የ35ኛ ዓመታችን ልደት ልናከብር ስለሆነ ገንዘብህን አምጣ የሚሉት ደሙን መጥምጠው የጠቡትን አጥንቱን የጋጡትን አማራ ምን አለውና ነው ገንዘብ የሚጠየቀው? ለነ ህላዊ ታደሰና ዓለምነው መኮንን ፈንጠዝያ ወይስ የአማራው ህዝብ እንባ አባሽና ድምጽ ለሆነ ድርጅት? መንደር ለመንደር የእያንዳንዱን አርሶ አደርና አባወራ ቤት በማሰስ አስገድዶ ገንዘብ መሰብሰብ ሊቆም ይገባዋል። ማን አለብኝነት ለደርግ አልበጀም ይህ ሕዝብ ሆ!! ብሎ ሲነሳ የሚከፈለው ዋጋ እጥፍ ድርብ እንደሚሆን መዘንጋት አይገባም ዛሬ ሆድህን ወደህ አንድነትን ከሚንዱ የውጭ ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ታሪክ ከሚያጠፉ፤አገር ከሚሸጡ የሀገር ሀብት ከሚዘርፉና ትውልድን እየበሉ ከሚገኙ ፀረ-ሕዝቦች ወግነህ ዜጐችህን እያጫረስክ ያለህ ካድሬ፤የደህንነትና የፖሊስ ኃይል፤የመከላከያ ሰራዊት የአማራውን ሕዝብ ክንድ ጠምዝዘህ እያሳረድክ ያለህን እያንዳንድህን ታሪክ ስለሚፋረድህ ነገ ይህ የአማራ ነገድ ሕዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ መሄድ ሲጀምር መሬት ከምትጠብህ አሁን ታሪክ ለመስራትና ከወገንህ ጐን ቆመህ አይዞሽ እማየ!! አይዞህ አባየ!! አይዞህ ወንድም ዓለም!! ይዞሽ እህት ዓለም!!ማለት ብትሞክር ትናንት ለግል ጥቅም ስትል የፈጸምክበትን በደል ሁሉ ይቅር ሊልህ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።
የአማራ ህዝብ አማራ ባልሆኑ መሪዎች አይገዛም!

Saturday, November 7, 2015

እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው፡፡

November 7,2015
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የህወሓት አገዛዝ የሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው፡፡

ራሱን በመንግስትነት ስም የሚጠራው የማፍያው ቡድን ህወሓት የምዕራባዊያንን ቁሳዊና ፖለቲካዊ ድጋፍ በማግኘት ስልጣኑን ለማደላደል ሲል ብቻ ከ10 ዓመታት በፊት ማለትም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ የሆኑ ዕልፍ አዕላፍ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያለማቋረጥ ወደ ሶማሊያ በረሃማ ምድር እያስገባ እጅግ በጣም አሰቃቂ ለሆነ እልቂት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ ...

የህወሓት አመራሮች የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትን ከሁለት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በመደምሰስ አፈራርሰውት ለቀው እንደሚወጡ ለህዝቡ ገልፀው ወደ ምድራዊ ሲኦል ወደሆነችው ሶማሊያ ጦር ጭነው ያስገቡ ሲሆን ነገር ግን አልሸባብ የተባለ ሌላ ፅንፈኛ ቡድን ፈጥረው ምስኪን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ከማይወጡበት የጦርነት አዙሪት ውስጥ ከተዋቸው ለድፍን 10 ዓመታት ሰቅጣጭ የሞት ገፈትን ሲግቷቸው ቆይተዋል፡፡ ቀጠናውንም የባሰ አለመረጋጋት እንዲሰፍንበት አድርገውታል፡፡


በዶላር ፍቅር ዓይኑ የታወረው የህወሓት አገዛዝ ከ10 ዓመታት በፊት ጦሩን ወደ ሶማሊያ ሲያስገባ እሱ እንደሚነግረን መጀመሪያ ላይ ጦርነት የገጠመው ከእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት ከሶማሊያ ጎሳዎች መካከል በጠንካራነቱና በታላቅነቱ ከሚታወቀው የሃውዬ ጎሳ ጋር ነበር፡፡ በመሆኑም በገብረ ዲላ እና በሌሎች ህወሓታዊ ድኩማን የጦር አዛዦች የሚመሩት 43ኛ እና 44ኛ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፤ መሪዎቹ ጭነዋቸው የሄዱትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች ለሶማሊያ በረሃ ገብረው አምስትና ስድስት ወታደሮችን ብቻ አስከትለው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ሞቃዲሹ ውስጥ አንድ የሃውዬ ጎሳ አባል በአንድ ህንፃ ውስጥ መትረየስ ጠምዶ ቢያንስ አንድ ሻምበል ጦር ብቻውን ጨርሷል፡፡ የድሃ ልጆች ለኢትዮጵያ ምንም አይነት ጠቀሜታ በሌለው ጦርነት በክንቱ ደማቸው ፈሶ ረግፈው ያለቀባሪ ቀርተዋል፡፡ አሁንም በዘግናኝ ሁኔታ መገደላቸው ቀጥሏል፡፡ ሬሳቸውም እንዳያርፍ ተፈርዶበት በየጎዳናው በገመድ ታስሮ ሲጎተት ታይቷል፡፡ 


ምንም እንኳን አሮጌዎቹ የአየር ኃይል አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች የወታደር ሬሳና ቁስለኛ ወደ ድሬ ደዋ ያለማቋረጥ ማመላለስ የጀመሩት ካለፈው 2007 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም አሁን አሁን ደግሞ የባሰውኑ ስራ በዝቶባቸዋል፡፡ ዳሽ-6 አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር በቁስለኛ ወታደሮች ጥቅጥቅ ብለው ተሞልተው ከወደ ሶማሊያ እየመጡ ድሬ ደዋ ላይ በማራገፍ ላይ ናቸው፡፡
ከሶማሊያ በአውሮፕላንና በሄሊኮፕተር ተጭነው ድሬ ደዋ ላይ የተራገፉት ቁስለኛ የሰራዊቱ አባላት ወደ ሐረር ወታደራዊ ሆስፒታል እየተወሰዱ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም የሐረሩ የመከላከያ ሆስፒታል ከአቅሙ በላይ በቆስለኞች መሞላቱን የሆስፒታሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
ሆኖም ለቁስለኞች የሚደረገው ህክምና እና እንክብካቤ በራሱ ከአድሏዊነት የፀዳ እንዳልሆነ ተጎጅዎች ቅሬታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ የህወሓት ታጋዮች የነበሩ የሰራዊቱ አባላት ሆዳቸውን በቆረጣቸው ቁጥር ደቡብ አፍሪካና ሳዑዲ አረቢያ ድረስ እየሄዱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየታከሙ ተገደው የሶማሊያው ጦርነት ውስጥ ተማግደው ስጋቸው በእሳት ተጠብሶ የተመለሱት ወታደሮች ግን ጦር ኃይሎች ሆስፒታልን እንኳን በዓይኖቻቸው የማየት እድላቸው የጠበበ እንደሆነ እና አካላቸውን ላጡትም ምንም አይነት የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው ብሶታቸውን ዘርዝረዋል፡፡
በተጨማሪም ሶማሊያ ውስጥ የሚገኙ የአየር ኃይል አባላት በአውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ብልሽትና እንዲሁም የመለዋወጫ እጥረት ምክንያት ስራ ፈትተው ለረጂም ጊዜ በመቀመጣቸው በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ያዘለ ጥያቄ በአንድነት አንስተዋል፡፡ የአየር ኃይሉ ምክትል አዛዥ ጀነራል ማዕሾ ሐጎስ ወደ ቦታው አምርቶ ጥያቄ ያነሱ አባላትን የማረጋጋት ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ለተነሳው ጥያቄ ተገቢ መፍትሄ ባለመሰጠቱ አሁንም ቅሬታው ባለበት ቀጠለ እንጂ ሊቀረፍ አልቻለም፡፡
የእነዚህን ሶማሊያ ዘማቾች የአየር ኃይል አባላት ሚስቶች የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ የሆነው ኮሎኔል አበበ ተካ በየተራ እያማገጠ እንደሚገኝም ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡
በአጠቃላይ ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር ላይ በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል ከባድ ጦርነት እንደተካሄደ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡


Thursday, November 5, 2015

የኢትዮጵያ ወጣቶች ክልል፣ ቋንቋም ሆነ ሀይማኖት ሳይገድባቸው በጋራ ይቁሙ!

November 5, 2015
def-thumbከ1950ዎቹ ጀምሮ የተደረጉ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች በሙሉ የተጠነሰሱትና የተመሩት እድሜያቸው ከሠላሳ አምስት ዓመት በታች በሆኑ ወጣቶች ነው። የ1997 ምርጫ ታሪካዊ እንዲሆን ያደረጉ፤ የሚያዝያ 30 ቀን 1997ን ታላቅ ሰልፍ ያደራጁ፤ ሕዝብን አደፈፍረው ለምርጫ በማሰለፍ ግንቦት 7 ቀን 1997 ታሪካዊ ዕለት እንድትሆን ያደረጉ፤ በኋላም “ድምፃችንን አናስነጥቅም” በማለት የአግዓዚ ፋሽስቶችን በድንጋይና ዱላ የገጠሙ የኢትዮጵያ ወጣቶች ናቸው። በዚህ ትግል ሽብሬ ደሳለኝን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ሕይወታቸውን ሰውተዋል፤ በቁጥር የበዙት ደግሞ አካሎቻቸውን አጥተዋል፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አሁንም በአገዛዙ እስር ቤቶች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። ጥቃቱ ቢበዛም ትግሉ ደግሞ የዚያኑ ያህል ተጠናክሮ ቀጥሏል። የኢትዮጵያ ወጣት ጥቃትን አሜን ብሎ አይቀበልም።
ህወሓትና ህወሓት የፈጠራቸው አድርባይ ድርጅቶች የዛሬው ወጣት ወኔው የላሸቀ፤ ኑሮው የተጎሳቆለ፤ የነገ ተስፋውም የጨለመ እንዲሆን ፓሊሲ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ነው። ህወሓት “መብት ተነፈግን” ብለው ብረት ባነሱ ወጣቶች መቋቋሙን ረስቶ የዛሬ ወጣቶች መብቶቻቸውን ተጠቅመው ሕይወታቸውን መምራት ቀርቶ መብቶቻቸው ምን እንደሆኑ እንዲጠይቁ እንኳን አይፈቅድላቸውም። በህወሓት አገዛዝ የትምህርት ተቋማት የሚሰጡት ትምህርት ጥራት እጅግ የወረደ በመሆኑ ወጣቶች የሕይወትን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል ክህሎት ሳይዙ እንዲመረቁ እየተደረገ የተመራቂ ሥራ አጦች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ተደርጓል። ለወጣቱ የሥራ እድሎችን የመክፈት ጉዳይ አገዛዙን የሚያስጨንቀው አይደለም። ለም መሬታችን ለባዕዳን በመሸጡ የገጠሩ ወጣት የሚያርሰው ቁራሽ መሬት እያጣ መሰደድ ከጀመረ ውሎ አድሯል። በሀገር ውስጥ ተስፋ በመታጣቱ በገጠርም በከተማም የሚገኙ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ወደ ደቡብ አፍሪቃና አረብ አገራት ለመሄድ በረሃ ማቋረጥ፤ ባህርን በታንኳ መሻገር የጀመሩት በዚሁ የግፍ አገዛዝ ዘመን ነው። ዘመናዊ ትምህርት ያገኘው ወጣትም በተማረው ትምህርት አገሩንና ወገኑን የማገልገል ህልሙ ተጨናግፎ ስደት እጣ ፈንታው የሆነው በዚሁ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ነው። በጫትና ሌሎች ሱሶች አዕምሮው የደነዘዘው ወጣት ቁጥርም አስደንጋጭ ነው።
ከዚህ ሁሉ የከፋው ደግሞ ወጣቱን በዘር በማደራጀት እርስ በርሱ እንዲጣላ መደረጉ ነው። በየጊዜው በሚፈለፈሉ “የወጣቶች ፎረሞች” አማካይነት የወጣቱ ወኔ ተሰልቦ አድርባይነትን እንዲለማመድ ተደርጓል። የጎንደሩ ወጣት ለአሰላው፣ የመቀሌው ለባህርዳሩ፣ የጅማው ለአዋሳው ባዕድ እንዲሆን፤ በጥርጣሬም እንዲጠባበቅ፤ በሰበብ አስባቡም እንዲቆራቆስ ተደርጓል። ህወሓት ወጣቶችን በወጣቶች ላይ የሚያዘምት እርኩስ ኃይል ነው።
አገዛዙ ይኸ ሁሉ ቢያደርግም ዛሬም የኢትዮጵያ ወጣት፣ የነብር ጣት መሆኑን እያስመሰከረ ነው። አገሩን ከህወሓት ፋሽስቶች ለማዳን ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በመቀላቀል ላይ ያለው የወጣት ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው፤ በያለበት ከተማና መንደር ሆኖ በመደራጀት ላይ ያለው ወጣት ቁጥር ደግሞ በጣም አበረታች ነው። ከዚህም በላይ የቴፒ፣ አርባምንጭ፣ ባህርዳርና ጎንደር ወጣቶች እያደረጉት እንዳለው በተደራጀ መንገድ አምባገነኑን ሥርዓት መጋፈጥ ጀምሯል። ጊዜው የአርበኖች ግንቦት 7ቱ አርበኛ አምሳሉ ተሾመን የመሰሉ ለጠላት እጅ ከመስጠት በራስ ላይ እርምጃ መውሰድን የሚመርጡ ቆራጦችን ፈጥሯል።
በእንዲህ ዓይነት ወቅት ክልልን፣ ቋንቋን፣ ዘርንና ሀይማኖትን የተሻገረ የወጣቶች ኅብረት መኖሩ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በቴፒ ወጣቶች ላይ በሚደርሰው ጥቃት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወጣት ሊቆጭና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል። የአርባምንጭ ወጣቶች ሲሳደዱ፣ ሲደበደቡና ሲገደሉ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ ወጣቶች ሊንቀሳቀሱ ይገባል። በለቀምት ወጣቶች በደል ሲደርስ በመላው የኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ የደረሰ ጥቃት ነውና ሁሉም ሊያመውና ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። በባህርዳርና ጎንደር ወጣቶች ላይ በደል ሲደርስ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶች ከጎናቸው ሊቆሙ ይገባል።
የህወወሓት “ወጣቱን ከፋፍለህ፣ አዳክመህ ግዛ” ፓሊሲ በራሱ በወጣቱ ቁርጠኝነትና የጋራ ስሜት ሊከሽፍ ይገባል። ህወሓትን ወደ መቃብሩ የሚገፋው በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ተወልዶ ያደገ ወጣት መሆኑ የአገዛዙ ኋላቀርነትና የመጪው ጊዜ ብሩህነት ማረጋገጫ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የወደፊቷ ኢትዮጵያ ለወጣቱ ምቹ አገር መሆን አለባት፤ መገንባት የሚኖርባትም በወጣቱ ትውልድ ነው ብሎ ያምናል። በዚህም የኢትዮጵያ ወጣቶች ክልል፣ ዘር፣ ቋንቋም ሆነ ሀይማኖት ሳይገድባቸው ለጋራ መብቶቻቸው በጋራ እንዲቆሙ፤ በአንድ አካባቢ ወጣቶች ለሚደርስ ጥቃት የሌላ አካባቢ ወጣቶች አፀፋዊ ምላሽ እንዲሰጡ ያበረታታል። ኢትዮጵያ በወጣቶቿ ያላሰለሰ ትግል ከወያኔ አምባገናዊ አገዛዝ ነፃ ትወጣለች።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ

November
• በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው
• ‹‹ሰው በርሃብ እያለቀ ነው››
• ‹‹የሚላስ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል››
• ‹‹እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡››
መንግስት በርሃብ ለተጎዱት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ቀያቸውን ለቀው አዲስ አበባ የገቡት የርሃቡ ሰለባዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች በርሃብ የተጠቁ ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወሎ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች አልፈው ወደ ጎጃም፣ ጎንደርን እንዲሁም አዲስ አበባ እየተሰደዱ ሲሆን አዲስ አበባ በርካታ ተጎጅዎች ህፃናትን አዝለው እየለመኑ ይገኛሉ፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ካነጋገራቸው መካከል ሁሉም መንግስት ለርሃቡ ተጎጅዎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውና ጎረቤቶቻቸውም እንደነሱ ቀያቸውን ጥለው ወደ መተማ፣ ሁመራ፣ ባህርዳር፣ ደሴ፣ እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ መሰደዳቸውን በሀዘን ገልፀዋል፡፡
ወሎ ውስጥ ጮሬ ሶዶማ ከተባለ ቦታ ተነስታ እንደመጣች፣ አዲስ አበባ ከገባች ሶስት ሳምንት እንደሆናት የገለፀችውና ሁለት ህፃናትን ይዛ ስትለምን ያገኘናት፤ በግምት በ30ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ የምትገኝ እናት ‹‹የመጣነው የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡ እኛ ሴቶቹ ወደ ከተማው ስንመጣ ወንዶቹ ደግሞ ወደ ሁመራና መተማ ሄደዋል፡፡ እኛም ከዚህ የመጣነው ጉልበት ስላለን ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደካሞች በዛው አካባቢ ቀርተዋል፡፡›› ስትል በሀዘን ገልፃልናለች፡፡ መንግስት እርዳታ አይሰጥም ወይ ብለን ላነሳንላት ጥያቄም ‹‹ምንም እርዳታ አልተሰጠንም፡፡ እርዳታ ቢሰጥ ኖሮ ቤታችን ጥለን አንመጣም ነበር፡፡ ባያበቅልም መሬት አለን፡፡ የከተማው ሰው ይሻላል ብለን ነው ወደዚህ የመጣነው›› ስትል ስለ ርሃቡ አስከፊነትና መንግስትም እርዳታ እየተሰጠ እንዳልሆነ ገልፃልናለች፡፡
ባለቤቷ ወደ መታማ ሲሄድ እሷም ቤቷን ጥላ ወደማታውቀው አዲስ አበባ እየጠየቀች እንደመጣች የገለፀችልን ወጣት በበኩሏ ‹‹ቤቴ ተፈትቷል፡፡ ባለፈው አመት ከብቶችም እህልም ነበረን፡፡ ዘንድሮ ግን ምንም ነገር የለም፡፡ ጊዜው ከፍቷል፡፡ ባሌ ወደ መተማ ሄዷል፡፡ እኔም ልጄን አዝዬ እስከ ደሴ በእግሬ መጣሁ፡፡ ከዛ በኋላ እየለምንኩ ከዚህ ደርሻለሁ፡፡ ማንም እርዳታ አልሰጠንም፡፡›› ስትል ስለሁኔታው ገለፃልናለች፡፡
ከመርሳ ወረዳ እንደመጡ የገለፁልንና ከልጃቸው ልጅ ጋር እየለመኑ ያገኘናቸው የ65 አመት አዛውንት በበኩላቸው ‹‹ዝናቡ ሲቀር ከብቶቻችንም ሞቱ፡፡ አዝመራ የሚባልም ነገር የለም፡፡ ከመርሳ ደሴ እየለመንኩ መጣሁ፡፡ ደሴም እንደኛ ብዙ ሰው አለ፡፡ አገኝ ብሎ በየከተማው ተሰራጭቷል፡፡ ወደዚህ ይሻላል ብዬ በለመንኳት ተሳፍሬ መጣሁ፡፡ ርሃቡ ሲብስብን ወደማናውቀው አገር መጣን፡፡›› ሲሉ የርሃቡን አስከፉነት ገልፀውልናል፡፡
‹‹እርዱኝ!›› እያሉ እየለመኑ ያገኘናቸው ከኬሚሴ አካባቢ እንደመጡና ከ8 ቀን በፊት አዲስ አበባ እንደደረሱ የገለፁልን ሌላኛዋ እናትም ቤታቸውን ጥለው እንደመጡና፣ ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ወደ የት እንደሄዱ እንኳን እንደማያውቁ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ መንግስት እርዳታ እየሰጠሁ ነው እንደሚል ስንገልፅላቸው ‹‹ለእኔ አልደረሰኝም፡፡ እርዳታ ተሰጠኝ ያለም አልሰማሁም፡፡ እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አልመጣም ነበር፡፡ አሁን ነው ከከተማው ሰው ትንሽ ትንሽ እያገኘን ያለነው፡፡ በየ ከተማው ስንደርስ ሰው አይነፍገንም›› ሲሉ ከህዝብ እንጅ ከመንግስት እርዳታ እንዳላገኙ ገልፀዋል፡፡
ካሳንቺስ አካባቢ ልጅ አዝለው ታክሲ ተሳፋሪዎችን ምንም አይነት ቃል ሳያሰሙ ልጃቸውን በመዘርጋት ብቻ እንዲረዷቸው እየጠየቁ ያገኘናቸው እናትም የራሳቸውንና የታዘለውን ልጅ ነፍስ ለማዳን ቀያቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
የርሃቡ ተጎጅዎች አዲስ አበባ ውስጥም ነፍሳቸውን ለማቆየት በጠራራ ፀሀይ ሲለምኑ እንደሚውሉና ምቹ ያልሆነ ቦታ አንድ ላይ የሚያድሩ በመሆኑ ልጆቻቸው ለበሽታ እየተጋለጡ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ተማሪ የነበሩና በርሃቡ ምክንያት ለማቋረጥ የተገደዱት ልጆቻቸው ከእነሱ ጋር ወይንም ወደ ሌላ አካባቢ ነፍሳቸውን ለመዳን መሰደዳቸውን፣ በያለፉበት ከተማም በርካታ ስደተኛ እንዳለም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡