Tuesday, May 31, 2016

Freed From Prison, Ethiopian Bloggers Still Can’t Leave The Country

May 31,2016

Ethiopia's Zone9 bloggers says "thank you"
(NPR)— Zelalem Kibret remembers the day: July 8, 2015. He was in a prison library reading a biography of Malcolm X, his own copy, when some guards called his name and handed him a piece of paper. The message: All charges against him were withdrawn. He was being released.
“I was asking why,” says Zelalem, a 29-year-old lawyer and blogger. “And nobody was giving us a reason.”
Zelalem, who’d been in jail for more than a year on terrorism charges related to his blog posts, suspected the reason. His release, he believes, was a “personal gift” to President Obama, then three weeks away from an official visit to Ethiopia, the first ever by a U.S. president.
The U.S. had been pushing quietly the release of Zelalem and five other members of Zone 9, his blogging crew. Zone 9 takes its name from the eight zones of the infamous Kality Prison outside Addis Ababa, where political prisoners and journalists are held. Activists joke that the 9th Zone is everything outside the prison walls — the rest of Ethiopia.
“Zone 9 is Ethiopia with relative freedom, but still you felt that you are in detention,” Zelalem explains.
Zelalem and the other Zone 9 bloggers had been critical of corruption and repression by the Ethiopian government, but their blogs and Facebook posts were seen as a relatively safe space for criticism in a country with about 3 percent internet penetration.
But the arrest of six bloggers, including Zelalem, and three other journalists in 2014 sent a signal that as Facebook was becoming more popular in Ethiopia, digital reportage might now become just as censored as print journalism. Journalists are regularly imprisoned under Ethiopia’s wide-ranging anti-terrorism law, which makes it a crime to have contact with any group that the Ethiopian government deems is trying to overthrow it.
At a press conference during Obama’s visit, Prime Minister Hailemariam Desalegn conceded, “We need many young journalists to come up.” But, he said, “We need ethical journalism. There is also capacity limitations in journalism.”
The phrase “capacity limitations” — and its cousin, “capacity building” — came out of development lingo of the 1990s. Ethiopian officials often use “capacity” explanations to assert that journalists are jailed not because they are critical of the government — but because they are less professional, more unethical and more incendiary than Ethiopia’s fledgling democracy can tolerate.
In keeping with this theme, Hailemariam nodded to Obama’s traveling press corps and asked them to “help our journalists to increase their capacity.”
Obama had offered an opportunity for just that, promoting his Young African Leaders Initiative, which gives scholarships for 1,000 African leaders to study in the U.S. each summer.
Zelalem, out of prison but unable to get back his university teaching job, followed Obama’s advice. He applied and was accepted to the Young African Leaders Initiative. This summer, he was supposed to study civic leadership at the University of Virginia.
He won’t be going. Ethiopian immigration officials confiscated his passport at Bole International Airport in November. They also took away the passports of four of his five colleagues who were released in advance of Obama’s visit.
That’s when Zone 9 became more than a metaphor. They were literally imprisoned in their own country.
Zelalem sees this as evidence of a new strategy. In past years, Ethiopia has been willing to let its critical citizens flee the country. (For several years, Ethiopia has ranked on or near the top of the list of countries with the most exiled journalists, according to the Committee to Protect Journalists.) Now, Zelalem says, the government may be deciding that it’s better to keep critics close by.
“Especially for people like us working on social media,” Zelalem says. “Whether we are here or in America or somewhere else, we may write and we can reach our audiences. Therefore, it’s better to keep [us] here and silence [us].”
When I brought up Zelalem’s case with Ethiopia’s Minister of Communication, Getachew Redda, he said he wasn’t familiar with it. But he offered a different explanation for the blogger’s rough treatment at the hands of Ethiopian Immigration: Ethiopia’s young institutions, he said — including its judges and immigration officials — could zealously overstep their bounds. They could even make mistakes that would take months or years to correct.
The minister’s solution? “More capacity building.”

Wednesday, May 18, 2016

የኢየሩሳሌም ተስፋው ደብዳቤ ከቃሊቲ እስር ቤት – ግንቦት 7

May 18,2016
ከእየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)


(እየሩሳሌም ተስፋው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ስትሆን፣ በነብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብ ‹ግንቦት 7›ን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው አሁን የመከላከያ ምስክር ለማስደመጥ በቀጠሮ ላይ ናቸው፡፡ እየሩሳሌም ተስፋው ይህንን ደብዳቤ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግንቦት 7፣ 2008 እንዲታተም ያወጣችው ቢሆንም፤ በተለያዩ እንቅፋቶች በዕለቱ ለሕዝብ ሳይደርስላት ቀርቷል፡፡) (የ እጅ ጽሁፏን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) ይህቺ ቀን ከዛሬ 11 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም. በዕለተ እሁድ ኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ለመረጠው ፓርቲ ሊሰጥ የተሰለፈበት ዕለት ነበረች፡፡ ሕወሓት/ኢሕአዴግ እስቲ እንያቸው ምን ያመጣሉ በማለት ከዛ በፊትም ከዛ በኋላም ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የምርጫ ምኅዳሩን ገርበብ አድርጎ ከፍቶ በሩን አልፈው እንዲገቡ ፈቀደላቸው፡፡ በዛች በር ገብተው ብዙ ነገር ሠሩ፡፡ በውጭ ሚዲያ ላይ እምናውቀውን hard talk በአገራችን ላይ በአገራችን ሚዲያ ለማየት በቃን ተስፋችንም ለመላው ይህ ትውልድ ታሪካዊ (ዕድለኛ) ትውልድ ነው አልን፡፡ ለአገራችን ታሪከ ለመጀመሪያ ጊዜ በመረጥነው መንግሥት ልንተዳደር ነው፡፡ በሠላማዊ መንገድ (በምርጫ) የመንግሥት ለውጥ ልናይ ነው እያልን ስንደሰት ወዲያው በዛች ቀን ምሽት ምርጫው ተጠናቆ ወደቆጠራው ሲገባ ሕወሓት/ኢሕአዴግ አልበዛም?! በሚል መልኩ እስርና ግድያውን ጀመረ፡፡ ብዙ ሺሕ ዜጎቻችንን እንደቀልድ አጣናቸው፡፡ በአልሞ ተኳሽ ግንባር ግንባራቸውን እየተባሉ በየደጃፋችን ተደፍተው ቀሩ፡፡ ኮሎኔል መንግሥ?ቱ ኃ/ማርያም ከዛሬ ጀምሮ ብሎ – መስቀል አደባባይ ላይ ቀይ ሽብርን እንዳወጀ – ታሪክ ራሱን ደገመና ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ዕዝ ስር በማለት የሞቱን ዐዋጅ ዐወጀ፡፡
ትዝ ይለኛል የዛሬ 3 ዓመት አካባቢ 2006 ላይ ሰኔ 3፣ 1997 ዓ.ም. በግፍ የተገደሉትን ንፁኃን ዜጎች ለማሰብ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተሰባስበን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንባቸው በጉንጮቻቸው እየወረደ ‹የማይታመን አምነን ወገኖቻችን አለቁ፡፡ ሰው እንዴት መለስን ያምናል? እንዴት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ይታመናል?› እያሉ በቁጭት የተናገሩት ትዝ አለኝ፡፡ አዎ፣ የማይታመነውን አምባገነን በዚች ዕለት ወገኖቻችን የጥይት ራት ሆኑ!! እነሆ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሠላማዊ ትግል በር ተዘጋ ብለው ያመኑ ድምፃቸው የታፈኑ መብታቸው የተረገጠ ንፁኃን ዜጎች እንዲሁም ከዚህ ቀን በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሠላማዊ ትግል ተዘጋ ሲሉ ግንቦት 7 አሉት፡፡ ይህ ሕዝባዊ ኃይል የተመሠረተበት ዋናው ዓላማ የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በሃገር ወዳድና ለሕዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች ምሁራንና ዜጎች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን መሠረቱ፡፡ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ሰንቆ የተነሳው ራዕይ “የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት የዜጎች መብቶች፣ አገራዊ አንድነት፣ ደኅንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና ማየት” ሲሆን ተልዕኮው ደግሞ “መንግሥትን በኃይል የማስወገድ ሠላማዊና የሥልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነጻ እና ጠንካራ ብቃት ያላቸው ሕገ-መንግሥታዊ የመከላከያ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲኖሩ ማድረግ” ነው፡፡Eyerusalemነገር ግን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለሕዝብ ድምፅ ሥልጣን ላይ የወጣ ፓርቲ አይደለምና በየዕለቱ የሚፈጠረው ኮሽታ ስለሚያስበረግገው እንዲሁም ንፁኃንን ለማሰር እና ለመግደል ምክንያት ይፈልግ ነበርና ይህ ሕዝባዊ ኃይል እንደተመሠረተ “ሽብርተኛ” ስለፈረጀው መስራቾቹን እንዲሁም ወደሃገር እንዲገቡ የማይፈልጋቸውን ተቃዋሚዎች በዚህ አጋጣሚ “አሸባሪዎች” ሲል ፈረጃቸው፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ ጦማሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ለም ብለው ጥያቄ እሚያነሱ ዜጎችን ግንቦት 7 በማለት በየወኅኒው እያሰራቸው ይገኛል፡፡
እንግዲህ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ከላይ እንደገለጽኩላችሁ አሸባሪ ሊያሰኘው የሚችል ዓላማ፣ ራዕይም ሆነ ተልዕኮ የለውም፡፡ ለሠላማዊ መንገድ የተነጠቀውን መብቱን በሁለገብ ትግል ለማስከበር ዓልሞ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ብቻውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ከወንበሩ እንደማያነቃንቀው እስካሁን የታዩት ሙከራዎች በቂ ናቸው ለዚህም ነው በዚህ ሰዐት ብዙ ወጣቶች ይህን ሕዝባዊ ኃይል በቆራጥነት እየተቀላቀሉት የሚገኙት፡፡
ሕወሓት/ኢሕአዴግ ባወጣው የፀረ-ሽብር ዐዋጅ (በነገራችን ላይ ይህን የፀረ-ሽብር ዐዋጅ ልብ ብላችሁ ካያችሁት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለራሱ ያወጣው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ሽብር በሌለበት ሽብር መንዛት አሸባሪነት ነው ይላል፡፡ ታዲያ በአገር ሠላም፣ በጠራራ ፀሐይ ቦንብ አፈነዱ እያለ documentary የሚሠራ ሕወሓት እንጂ ግንቦት 7 ነው እንዴ? በተረፈ ሁሉንም አንቀፆች ተመለከቷቸው ከግንቦት 7 ይልቅ ለሕወሓት ይቀርባሉና ገና ጫካ እያሉ የሕዝብን ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ በገዛ ሕዝባቸው (በሓውዜን) ላይ የጀመሩት እልቂት በደርግ ማሳበብ፣ አሁንም ከ25 ዓመት በኋላ ሳይቀነስ ሳይጨመር እንዳለ ነው፡፡ አሸባሪ ማነው?
እንግዲህ ይህ ሁሉ የተፈፀመው በዚህች ዕለት ነው፡፡ “ግንቦት 7” ይህቺ ቀን የትናንት አሰቃቂ ትዝታችን የዛሬ ክሳችን የነገ ተስፋችን ናት፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተማረ ዜጋ አይገኝም፡፡ ሁሉም ነጻነትን ይናፍቃል፡፡ ነጻ ለመውጣት ግን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈራል፡፡ የሆነ አካል መጥቶ ነጻ እንዲያወጣው ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን አይችልም፡፡ ነጻ ለመውጣት መጀመሪያ ራስን ከታሰሩበት የፍርሓት እስር ነጻ በማውጣት ትግሉን መቀላቀል ነው፡፡ ድርጅታችን ግንቦት 7 ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የተቋቋመ ነጻ አውጪ ድርጅት እንጂ አሸባሪ አይደለም፡፡ ስለዚህ በድፍረት እናገራለሁ፡፡ እኔ ግንቦት 7 ነኝ፤ እናንተስ? ሁሌም እንደምለው የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው፡፡ ይህቺ ቀን ለብዙዎች ሞት፣ አካል መጉደል፣ እስራት አብቅታለች፡፡ መራራውን ሳያልፉ ጣፋጭ፤ ሳይሞቱ ትንሳኤ የለምና ባለፈው ከመፀፀት ባለፈ እልህ አስይዞን ይህንን ዘረኛና አምባገነን የሽፍታ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መንግለን ለመጣል እንዘጋጅ፡፡ ከላይ እንዳልኩት የትላንት ጥቁር ጠባሳ፣ የዛሬ ግርፋትና እስራት፣ የነገ ተስፋ ናትና እንኳን ለዚች ቀን አደረሳችሁ፡፡ ይህች ቀን፣ የነጻነት እንዲሁም የድል ቀናችን እንደምትሆን አልጠራጠርም፡፡ ግንቦት 20 በግንቦት 7 እንደመስሰዋለን!!
የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ አንድ ጊቢ ብንኖርም መገናኘት አልቻልንም፡፡ እንኳን አካልህን ወሬህንም በስንት ስቃይ ነው፡፡ እምሰማው ያንተ መታፈን ወያኔ እንደጠበቀው ትግሉን አላሽመደመደውም፡፡ እንደውም፣ ይበልጥ አጦዘው ለኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ፡፡ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነን፡፡ ዛሬ ታፍነህ ቀንና ሌሊቱን መለየት የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም የነጻነት ቀን ቀርባለችና እስከዛው ዕድሜህን ያርዝምልን፡፡

Tuesday, May 17, 2016

Ethiopia: More soldiers desert the army, join opposition groups

May 17,2016
(ESAT News)— The number of soldiers deserting the Ethiopian army that’s riddled with corruption and joining opposition forces is on the rise.
22 defected Ethiopian soldiers in Eritrea
The Tigray People’s Democratic Movement (TPDM) said in a statement on Monday that several soldiers of the minority regime in Addis Ababa have joined the Movement. TPDM has released a list of the names and other information of those who recently deserted the regime’s army. Some of the deserters had higher ranks in the army.
The soldiers said they had enough of the regime that’s using the army to prolong its stay in power. They said they would rather join democratic forces and fight to save the country from disintegration.
Adem Mohammed and Beshir Yosef said nepotism and corruption were rampant in the army. They said the rank and file were marginalized by the higher officers and generals who hail from one ethnic group. As a result, there is no unity and cohesion in the army, they said, adding that no soldier wish to stay in the army on his will; everyone wants to abandon the army, according to these soldiers.
Unbridled plunder of resources by a handful of generals when the rank and file eke out a living has been one of the causes of the rise in defection; in addition to refusal by some members of the army not to serve as a hit squad for the regime against people who are deemed to be political opponents.

Sunday, May 15, 2016

የመከላከያ ሰራዊት የሚገኝበትን ስፍራና አድራሻ ለተቃዋሚዎች መረጃ አሳልፋችሁ ተብለው ወታደሮች ታሰሩ

May 15,2016

የመከላከያ ሰራዊት የሚገኝበትን ስፍራና አድራሻ ለተቃዋሚዎች መረጃ አሳልፋችሁ ሰጥታችኋል በሚል ወታደሮቹ በጥርጣሬ በወንጀል መታሰራቸው ታወቀ።

መረጃው እንዳስረዳው የተሰጣችሁን አገራዊ አደራ ወደ ጎን ትታችሁ የመከለካያ ሰራዊት ስፍራና አድራሻ ለተቃዋሚ ድርጅቶች ታስተላልፋላችሁ ተብለው የተጠረጠሩ ወታደሮች ያለ ምንም ማስረጃ በግብረ ሽበራ በሚል በወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው መረጃው አስረድቷል።

የፊዴራሉ አቃቢ ህግ የላይኛው ፍርድ ቤት የ1ኛው ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ በርከት ያሉ ወታደሮች ሲሆኑ፣ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፣ አስራ አለቃ አጀናው ታደሰ፤ ምክትል አስራ አለቃ ቻሌ ነጋና ሌሎችም የቀረበላቸው ክስ እንዳስረዳው በኢትዮ_ ኤርትራ ዳር ድምበር ትጥቅ ያነገቡ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት በ6ተኛውና በ25ተኛ ክፍለ ክፈለጦር የሚገኙትን የሬጅመንቶች ብዛትና የት እንደሚገኙ መረጃ በዝርዘር አስልፋችሁ ትሰጣላችሁ በሚል በከባድ ወንጀል ቢከሰሱም ፣ለቀረበላችው ጥያቄ ስላልተቀበሉት በህግ ጠበቃ ለግንቦት 15 /2008 ዓ/ም ቀጠሮ እንደተሳጣቸው አስገነዘበ።

በመጨረሻ በአሁኑ ግዜ በመከላከያ ሰራዊት ያለመተማምንና መጠራጠርን እንደ ተፈጠረና በዚህ ምክንያትም ብዙ ወታደሮች አሃድዋቸውን ትተው እግራቸው ወዳመራቸው እየጠፉ መሆናቸውን ታወቀ።

Tuesday, May 10, 2016

Crestfallen But Resolute! Co-Blogger Zelalem Workagegnehu Sentenced To Five Years And Four Months

May 10,2016
Zelalem Workagegnehu, co-blogger of De Birhan Blog and whose works had appeared on various Diaspora websites, has been sentenced to five years and four months by the Ethiopian regime controlled court in Addis Abeba, Ethiopia today.
zelalem
Zelalem has already been detained for nearly two years – 672 days today.
Zelalem was finishing his Masters Degree in Public Administration at the Addis Abeba University, in July 2014 when he was detained together with nine other opposition politicians, netizens, and activists.
The Court had acquitted  five of the defendants  in August 2015 and two more of Zelalem’s co-defendants on April 15, 2016 when it found Zelalem and two other co-defendants of Zelalem guilty of “supporting terror in any way.”
The movement he is accused of supporting is known as Ginbot 7 (Arebgenoch Ginbot 7 Movement), a pro-democracy movement founded by Professor Berhanu Nega, an Ethiopian economist, who lectured in Bucknell University, U.S.A. The Ethiopian government labelled his movement as well as few other Ethiopian opposition groups as “Terrorist Groups” in 2010.
Like several Ethiopian activists, journalists and politicians, Zelalem was initially accused of being a member and local leader of Ginbot 7 although the charges were later changed to recruiting members to start an Arab Spring styled revolution in Ethiopia and applying for a digital security course.
Zelalem in his defense statements maintained that he has never been a member of Ginbot 7 and does not believe Ginbot 7 is a terror organisation, he does stand for a social change only through a nonviolent means and is against any form of violence.
Zelalem Workagegnehu’s Trial Timeline 
July 8, 2014 – Zelalem Workagegnehu along with seven of his friends and one of his brothers was detained by the Ethiopian Federal Police and Securities. Few months later his older brother and four of his friends were later released after going through long interrogations and torture.
One of his colleagues and distant relative, Eyob, who faced the most torture and ordeal, had agreed with the prosecutors to testify against Zelalem and his colleagues and thus was subsequently released.
October 31, 2014 – After four months of investigation, torture and interrogation, 10 people were officially charged. The 10 were charged under the file of Zelalem Workagenehu :
1. Zelalem Workagenhu – a postgraduate student of Addis Abeba University and a writer
2. Habtamu Ayalew – Public Relations Head of the Unity for Democracy and Justice Party (UDJ) – now acquitted but still battling the Prosecutor’s appeal
3. Daniel Shibeshi – Organisational Affairs Head of UDJ – acquitted
4. Abraha Desta – Central Committee member of Arena Party and lecturer at Mekele University – Acquitted but still in prison
5. Yeshiwas Assfea – Council member of Blue (Semayawi Party) – acquitted
6. Yonatan Wolde – charged with applying for a digital security course – acquitted
7. Abraham Solomon – linked with Zelalem in the Charge – acquitted
8. Solomon Girma – found guilty
9. Bahiru Degu – charged with applying for a digital security course – acquitted
10. Tesfaye Teferi – found guilty
The two main morals of the charges were one “working together with terrorist organisations” and “membership in Ginbot 7 and participation in criminal activities”.  The first defendant Zelalem has been charged with being a leader of Ginbot 7, sending information to Diaspora based websites and recruiting members to start an Arab Spring styled revolution in Ethiopia” and is centrally linked with this writer, Tedla, who is also implicated in the same charge.
The 2nd, 3rd, 4th and 5th defendants have been charged of using legally registered opposition party as a cover to pursue the aims of Ginbot 7 and also using social media to contact Fasil Yenealem, whom the charge referred to as a member of the Movement and others.
Nov. 20, 2014 – They were all denied bail. The Court ordered the prosecutor to complete its evidences on the detainees and submit them on 27 November, 2014.
December 18, 2014 – given another appointment to reappear in Court on December 25, 2014. Reappointed.
Feb. 3, 2015 – Court Declines To Accept The Objections And Defense Of Writer Zelalem Workagegnehu Et Al. Adjourned the hearing to February 19, 2015.
Feb.19, 2015 – They given another appointment to appear again on March 4, 2015 by the Lideta Court.
 March 19, 2015 – Court appointed the defendants to May 21, 22 and 25, 2015 respectively to hear the prosecutors witnesses.
 June 08, 2015 – The Criminal Bench of  the Lideta Federal High Court  in Addis Abeba started hearing the prosecutor’s witnesses.
 June 11, 2015 –  Court tells Zelalem to appear in Court on Monday June 15, 2015 for decisions after witnesses testimony was heard.
June 17, 2015 –  Court adjourns for July 8, 2015 to give verdict on the Public Prosecutor’s evidences.
August 20, 2015 – Five, charged under the file of De Birhan’s Co-blogger Zelalem, acquitted, Zelalem told to Defend. Court adjourned their case to  November 7-9, 2015
August 24, 2015 – Prosecutor lodges an appeal against the acquitted.
November 23, 2015 – Hearing of defense witnesses begins.
November 27, 2015 – hearing postponed to next week Dec.4, 2015 due to incomplete judicial panel.
February 24, 2016 – Andargachew didnot testify, Court postpones co-blogger Zelalem’s trail due to judges absence and Court takes Andargachew’s failure to testify as Zelalem’s own fault.
April 26, 2016 – Prosecutor submits sentencing aggravation statement. Sentencing adjourned to May 10, 2016.
May 10, 2016 – Co-Blogger Zelalem Workagegnehu sentenced to five years and four months.
We are crestfallen but remain resolute! Days will tell! 



Source: De Birhan Blog

Wednesday, May 4, 2016

ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!

May 4,2016
በኮሪያ የተዘጋው የመረጃ ግድግዳ ተወገደ!
obang sk
የመን ትነድዳለች ኢትዮጵያውያን ግን ወደዚያው ያቀናሉ። ሶማሊያ ዋስትና ቢርቃትም ወገኖች ሊረማመዱባት አሁን ድረስ ምርጫቸው ናት። በሲና በረሃ ሰው በቁሙ ይበለታል። ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች ግን አሁንም አማራጭ መንገድ ነው። ሲኦል መሆኑ እየታወቀ እህትና ወንድሞች ወደ አረብ አገር ይተምማሉ። ኬንያን፣ ታንዛኒያን፣ ዛምቢያን፣ … አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ቁጥራቸው ሲቀንስ አይታይም። በደቡብ አፍሪካ ወገኖች በእሳት ሲቃጠሉና በገጀራ ሲጨፈጨፉ ማየት ወደዚያ የሚደረገውን ጉዞ አልቀነሰውም። ለምን?
በቀይ ባህርና በሜዲትራንያን የሰመጡ ወገኖች መርዶ ሳያሰልስ ሌሎች መሰመጥ የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን እያወቁ ይገቡበታል። ሊቢያ የታረዱትን ወገኖች እያዩ ሌሎች ወደ ሊቢያ ለማቅናት አያቀማሙም። ለምን? በኩባ ቪዛ ተነስተው መከራቸውን ለወራት በበረሃ የሚያሳልፉ ወገኖች ቁጥር … ስንቱ ይዘረዘራል? ኢትዮጵያውያኖች እንዲህ ያለውን መከራና አጥንት ዘልቆ የሚገባውን ሃዘን ሳይፈሩ ስደትን የመጨረሻ አማራጭ ያደረጉት ለምን ይሆን? ለገዢውም ሆነ ለተገዢው የሚቀርብ ጥያቄ ነው።
ከሁሉም በላይ ዜጎች በየጊዜው እርዳታ ሲፈልጉና በነፍስ ውጪ ግቢ ውስጥ ሆነው የድረሱልኝ ምልጃ ሲያቀርቡ ሰሚና ተቆርቋሪ የላቸውም። ህወሃት ለእንዲህ ያለው የወገኖች ጥሪ መልሱ “ጥሪ አይቀበልም” መሆኑ ደግሞ ከችግሩ በላይ ቅስም ሰባሪ ነው። ወገኖቻችን ሲታረዱ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ቆይ ላጣራ” የሚል ገዢ ቢኖር ህወሃት ብቻ ነው። ዶላር ባለበትና የስልጣን ጊዜን የሚያራዝም እስከሆነ ብቻ ተጣድፎ ምላሽ የሚሰጠው ህወሃት፣ በቅርቡ በጋምቤላ ለተጨፈጨፉት ወገኖች የሰጠው ምላሽ የዚሁ ተግባሩ መገለጫው ነው።
ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ በበርካታ ጉዳዮች የሚያዝኑ ወገኖች የሚጽናኑበት አንድ ሰው አግኝተዋል። የተግባር ሰው! በሩ ለሁሉም ወገኖች ክፍት የሆነ። ቂምና በቀልን አጥብቆ የሚጠላ፤ ተንኮልን የሚጸየፍ። ወገኖቹን የሚላላክ፤ ለአንድ ግለሰብም ለብዙሃንም በእኩል የሚቆም። ክብሩ አገልጋይነት ብቻ የሆነ። ዝማሬና ሙገሳ የሚጠላ። በውሱን ድጋፍ ወሰን የሚያልፍ፣ አህጉር የሚያቋርጥ ሥራ የሚያከናውን። ብዙ ሊባልለት ሲገባው ግን ያልተባለለት፤ ያልተጨበጨበለት፤ ያልተዘፈነለት፤ … ሥራውን የሚያውቁ ግን “የጥቁር አልማዝ” የሚሉት!!
“ለወገን ደራሽ” ስሙ ነው። በተጠራበትና ችግር አለ በሚባልበት ቦታ ሁሉ ወገኖቹን ተሟግቶ ነጻ ያወጣል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ክብር የሚገባው ግን ክብር ያልተሰጠው” በሚል በማህበራዊ ድረገጾች ስሙ እየተነሳ ነው። የእርሱ ፍላጎት ባይጠየቅም “አንተ ምራን” የሚሉት እየበረከቱ ነው። ጀርባው ሁሉ ከምንም የጸዳ በመሆኑ ብዙዎች “እናምነሃለን፣ እናከብርሃለን፣ እንወድሃለን፣ አምላክ ይጠብቅህ …” እያሉት ነው።
ለሰው ልጆች ክብርና እኩልነት ዋጋ መክፈል እንደሚያስደስተው ደጋግሞ ይናገራል። “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ አይወጣም” በሚለውና ግንባሩ ላይ በታተመው “ከጎሣ በፊት ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል መሪ ቃል ይታወቃል። በሚመራው ድርጅት ውስጥ ባሉት ባልደረቦቹ የሚታመን። ይህ ሰው ኦባንግ ሜቶ ይባላል። በይቅርታ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለማቆም ከመሰሎቹ ጋር ደፋ ቀና ይላል። ርምጃው በተለያዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገሮች መነጽር ውስጥ ከቶታል። ኢትዮጵያን በመወከል በከፍተኛ ቦታዎች የወገኖቹ ድምጽ ከሆነ ሰነባብቷል። ከሚያከናውናቸው በርካታ ተግባሮች ገሃድ ወጥቶ የሚናገረው በጣም ጥቂቱን ነው። ስለ እሱ ጠንቅቀው የሚያውቁ “ኦባንግ አሁን የኢትዮጵያ ምስል ሆኗል” እያሉ ነው። የጎልጉል የኬኒያ ዘጋቢ በቅርቡ ሰፊቃለ ምልልስ ለማካሄድ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቆናል። በዚሁ ሰፊ ቃለምልልስ በማህበራዊ ገጾች ስለሚነሱት ጥሪዎች ምላሽ ይሰጣል።Ethiopian_soldiers_Korea_war
የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች – አባ “ቃኘው
ስደት እንደ ጨው ከረጫቸው ወገኖች መካከል በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ወገኖችን ያስታወሳቸው አልነበረም። ባለፉት ሳምንታት የተሰማውን ዜና አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ጥቁሩ ሰው” በተለይ ለጎልጉል ሲናገር “የተዘጋን በር አስከፍተናል” ነበር ያለው። ወደዚያው ማቅናቱን የሰሙ “የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች አባ – ቃኘው” ሲሉ ጠርተውታል።
“ዘመን የማይሽረው ወዳጅነት ኮሪያና ኢትዮጵያ፤ በኮሪያ ጦርነት የኢትዮጵያ ጦር ተሳትፎ” በሚል ርዕስ ደራሲ ቲኢ-ጂኢ-ውን የጻፉትና በጋሻው ድረሴ ወ/ሰማያት ወደ አማርኛ የመለሱት መጽሃፍ መግቢያ ላይ ከዛሬ 64 ዓመት በፊት ኮሪያን ነጻ ለማውጣት ዘምቶ የነበረው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት መጠሪያ ስሙ “ቃኘው” እንደሚባል አስታውሶ ትርጉሙም “ድብልቅልቁን ሥርዓት አስይዘው” ማለት እንደሆነ ተመልክቷል። ለዚህም ይመስላል ኦባንግ “አባ ቃኘው” የሚል ስም የተበረከተለት።
በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ይህ ተጽፎ ይገኛል “… በጦርነቱ ለማያውቁት ሀገርና አይተውት ለማያውቁት ህዝብ በኮሪያ ጦርነት የህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉት ያለንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡ ዕድሜ ለኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት የኮሪያ ሪፐብሊክ ከጦርነቱ ቁስል ለማገገም ችላለች፡፡ (በአሜሪካዊው) ጄነራል ማክአርተር በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት ለመግለፅ “እነዚህ ሰዎች ይህቺን ሀገር እንደገና ለመስራት 100 ዓመት ያስፈልጋቸዋል” ተብሎ ከተገለፀበት ሙሉ ውድመት ተነስተን ኮሪያን እንደገና ገንብተናታል፡፡ ዛሬ እንደ G20 እና የ2012 ሶውል ኑክሊየር ስብሰባዎች የመሳሰሉት ታላላቅ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማካሄድ የምንመረጥበት ክብር ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ ሁኔታ የሚመሰክረው የኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከንቱ ሆኖ አለመቅረቱን ነው፡፡ ዛሬ ከእርዳታ ተቀባይነት ወደ ሰጭነት በተሸጋገርንበትና ከዓለማች 10 የበለፀጉ ሀገሮች ሰልፍ በተቀላቀልንበት ሁኔታ ለኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ብድር መላሽ ለመሆንና ከድህረ ጦርነት በኋላ ለመጣውም ትውልድ ዕውነታውን በስፋት እንዲታወቅ ጠንክረን እንሠራለን…”።
በመጽሐፉ ላይ ይህ የሰፈረ ቢሆንም በዚያ የሚገኙ 130 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሁሉም ዓይነት በር ጠብቆ የተዘጋባቸው፣ የህግ ከለላ የሌላቸው፣ በቂ የዕለት ማቆያ የማይቆረስላቸው፣ ጠበቃ ማግኘት የማይችሉ፣ በማይታወቅ የስደተኞች ህግና መመሪያ የሚስተናገዱ፣ ሚዲያው የዘነጋቸው፣ ፍትህ ፍለጋ የሚሄዱበት ያጡ፣ ሳይጨልም ለዓመታት የጠቆረባቸው፣ ሲታመሙ ለመታከም የማይችሉ፣ እዛ የተወለዱ ልጆቻቸው የሚንገላቱባቸው፣ ተዘርዝሮ የማያበቃ መከራ የተሸከሙ እንደሆኑ አቶ ኦባንግ ያስረዳል። “ገሃድ አውጥቼ ልናገረው የማልችለው አሳዛኝ ችግሮችን ስሰማ ውስጤ ታመመ” ያለው ኦባንግ ወደ ደቡብ ኮሪያ ያቀናው በዚያው የሚኖሩ የአኢጋን ቤተሰቦች አማካይነት መረጃው ደርሶት ነው። በዚህ አጋጣሚ ጉዞውን የተቃና በማድረግ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ሥራውን በትጋት ለሠራው ሱራፌል አሰፋ እንዲሁም ለአጋሮቹ መቅደስንና ቢኒያምን ታላቅ ምስጋና እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡  obang sk2
ኦባንግ ወገኖቹን ሰብስቦ ማዳመጥ የመጀመሪያ ተግባሩ ነበር። አስቀድሞ ችግሩን እንደሰማ ወደ ስፍራው ለማምራት ቢወስንም በአካል ከተገኘ በኋላ እንባ የተቀላቀለበት ስብሰባ ላይ በሰማው ሁሉ ሃዘን ገባው። “አሁን አናለቅስም” ሲል ኦባንግ ሥራውን ጀመረ። “ዛሬ ተደራጁ፣ እንደራጅ፣ በተናጠል አትሩጡ፣ በወሬ ሳይሆን ራሳቸሁን አክብራችሁ ሌላውን ማክበር በምትችሉበት ጥልቅ ስሜት ተዛዘሉ፣ ተረዳዱ፣ አንድ ሁኑ፣ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች ስለሆናችሁ ባገራችሁ ስም ተሰባሰቡ…” ሲል የተደበላለቀውን ስርዓት ማስያዝ ጀመረ።
“እናንተ አሁን ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ እየተንሳፈፋችሁ አይደለም፣ ሲና በረሃ አይደላችሁም፣ ደቡብ አፍሪካ በጎማ እየተቃጠላችሁ አይደለም፣ በበረሃ ውስጥ አይደላችሁም፣ መብታቸውን እንደጠየቁ የኦሮሞ ልጆች እስር ቤት አልታጎራችሁም፣ በጥይት እየተደበደባችሁ አይደለም። የማንነት ጥያቄ በማቅረባችሁ ህወሃት በጥይት እየፈጃችሁ አይደለም፣ 20 ሚሊዮን ህዝብ በችጋር ሲጠበስ እናንተ ምግብ አላጣችሁም … አዎ በታሪክ ተመዝግቦብን የማያውቅ ውርደት ውስጥ መውደቃችን ባይካድም ዛሬ በህብረት እንቆማለን። እኛ ሁላችን ከተባበርን ከችግሮቻችን ሁሉ በላይ እንሆናለን…” በማለት ጥቁሩ ሰው የዛለውን መንፈሣቸውን አነቃቃው።
ኦባንግ እንደሚለው ወገኖቹ ላይ የደረሰውን በደል መዘርዘሩ ፋይዳ የለውም። በዚህም የተነሳ በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ጉዞ ወደ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሆነ። አቶ ኦባንግ የደቡብ ኮሪያን ምድር ከረገጠበት ሰዓት ጀምሮ በመንግሥት ለደህንነቱ ልዩ ጥበቃ ተመድቦለት ነበር። ይህ የሆነው በሱ ጥያቄ ሳይሆን “የመታፈን ችግር እንዳያጋጥመው” ለጥንቃቄ ነበር። ይህንን ያስረዱትም ራሳቸው ናቸው ። በዚሁ መሠረት በኢሚግሬሽን ቢሮ ተገኝቶ ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኘ። ለኦባንግ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት “the shaker ወይም አባ ነቅንቅ” ያሰኘውን ንግግር አቀረበላቸው። ኢትዮጵያ ላይ የተንሰራፋውን ግፈኛ ኃይልና ተግባሩን አስረግጦ ዘረዘረላቸው።
“የአያቶቻችን ውለታ ይህ ነው? ኢትዮጵያዊያን ህክምና ለማግኘት እንኳን አይመጥኑም? በደቡብ ኮሪያ ሰላማዊ ዋስትና ለማግኘት ብቁ አይደሉም? ጠበቃ ለማግኘትና ጉዳያቸው እስኪታይ የሥራ ፈቃድ አግኝተው እየሰሩ ለመኖር ሚዛን አያነሱም?” ኦባንግ ከማብራሪያው በኋላ ለባለስልጣኖቹ ያቀረበው ጥያቄ ነበር።obang sk3
ኦባንግ ቀጠለ “… ራሳችሁ በከተማችሁ ያቆማችሁትን ለናንተ ነጻነት ደም ያፈሰሱት ኢትዮጵያዊያን መታሰቢያ ለምን ታፈረሳላችሁ? እነዚህ ወጣቶች እኮ የነሱ ልጅ ልጆች ናቸው” ሲል ታሪክን እያጣቀሰ አስረዳ። አሁን ያለው አገዛዝ ጋዜጠኞችን “አሸባሪ” ብሎ የሚያስር፣ ዘረኛና ለትውልዱ የማያስብ አምባገነን አገዛዝ መሆኑን በግብሩ እያስቃኘ የስደተኛ ህጋቸውን ከአለም አቀፍ ህግ ጋር አዛምደው እንዲያሻሽሉ አስገነዘበ። ጉዳዩንም ለዓለም ይፋ እንደሚያደርገው አስጠነቀቀ። ከሰፊ ውይይትና መረዳዳት በኋላ ባለሥልጣናቱ የማስተካከያ ርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገቡ። ከስደተኞች ዓለም አቀፍ ህግ ጋር ብዙም ትውውቅ ስለሌላቸው የተሰራ ስህተት ስለመኖሩ አምነው ተለያዩ። በስተመጨረሻም ኦባንግ ሁሉም ጥገኛ ጠያቂዎች ከለላ እንደሚያሻቸው አሳምኖ ቢሮውን በክብር ለቀቆ ወጣ።
በሲዑል የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የስደተኞች መስሪያ ቤትም ኦባንግ ተገኝቶ ሁኔታውን አሰረድቷል። ባለስልጣናቱ ከዚህ ቀደም ስለ ስደተኞቹ ሰምተው እንደማያውቁ ገልጸው ጉዳዩን የኮሪያ ባለሥልጣናት በዓለምአቀፉ ህግ መሰረት  እንዲያስኬዱት ማሳሰቢያ እንደሚሰጡ ቃል ተገባ። መደራጀታቸው አግባብ በመሆኑ ወኪላቸውን በየጊዜው በማግኘት ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ አብረው እንደሚሰሩ ማረጋገጫ አገኘ “ቃኘው” የተዘጉትን በሮች አስከፍቶ ወጣ። ዝርዝሩን በቃለ ምልልስ እናትመዋለን።
አስገራሚው – የመረጃ ድርቅ በሴዑል
ኦባንግ በሴዑል ቆይታው ሰፊ ጊዜ ወስዶ ካነጋገራቸው መካከል በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ይገኙበታል። እነዚህ ክፍሎች አገራቸው ሚዲያ፣ ከለላ፣ ርዳታ፣ ህክምና፣ ሥራ፣ ወዘተ ተከልክለው ስለሚኖሩት ኢትዮጰያዊያን መረጃ የላቸውም ነበር። የሚያሳዝነው ህወሃት በሚገዛት ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች “አሸባሪ” እየተባሉ ወኅኒ እንደሚወረወሩ አያውቁም ነበር። ኦባንግ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት በያዘው እቅድ መሰረት እነዚህን ክፍሎች በቂ ግንዛቤ አስጨበጠ። የነበረውን የመረጃ ድርቅ ህይወት ዘራበት።
ከ30 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ አካላትና ጠበቆችን ካነጋገረ በኋላ ባገኘው ምላሽ መገረሙን ኦባንግ አልሸሸገም። ደንግጠው “በአገራችሁ ሁሉ ነገር እንደዚህ ከሆነ  የአውሮፓ አገሮች እንዴት አብረዋቸው ይቆማሉ” ሲሉ ጥያቄ ሰነዘሩ። “በአሸባሪ ስም የነሱን ጦርነት ይዋጉላቸዋል” በማለት ስለ ሁኔታው ዝርዝር ምላሽ ሰጠ። በስተመጨረሻም ከጥገኝነት ጠያቂዎቹ ወኪሎች ጋር በመሆን ያገራቸው ህዝብ በቂ መረጃ እንዲያገኝ፣ መንግስታቸውም የከለላ ጥያቄያቸውን እንዲያስተናግድ ሁሉን ዓይነት ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋገጡ።
የመረጃው በር ሲከፈት – ሚዲያ ኦባንግ ዘንድ መጣ
የጥቁሩ ሰው የመጨረሻ እቅድ ያገሪቱን መገናኛዎች በመጠቀም የደቡብ ኮሪያን ህዝብ ማንቃት፣ እንዲያስብ ማድረግና የመከራከሪያ አጀንዳ አቀብሎ ሴዑልን መሰናበት ነበር። በዚሁ እቅድ መሰረት የደቡብ ኮሪያ ታዋቂዎቹ obang sk6ሁለት ሚዲያዎች ኦባንግ አለበት ዘንድ መጡ – በኮሪያ ሲታተም 96ዓመታት ያስቆጠረው Dong-A Ilbo የተሰኘው ጋዜጣ እና በደቡብ ኮሪያ ዋንኛው የእንግሊዝኛ ጋዜጣ የሆነው The Korea Herald። ከጥቂት ዓመታት በፊት አቶ ኦባንግ በህንድ አገር ተገኝቶ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያደረገው ንግግር ድፍን ድጋፍ ያገኘውና ካሩቱሪ ካገሪቱ ባንኮች ብድር እንዳያገኝ የከፈተው ዘመቻ ያስመዘገበውን ውጤት ያስታወሰ ክስተት ተደገመ።
ያገሪቱ ሁለት ታዋቂ ሚዲያዎች በየተራ ሲያነጋግሩት ኦባንግ ከ65 ዓመት በፊት የተከፈለውን የደምና ያጥንት ታሪክ ግንባር አደረገ። የኮሪያ ሚዲያዎች ከዚህ ወርቅ አገር ለመጡ የጀገኖች የልጅ ልጆች በር መቆለፋቸውና ጀርባ መስጠታቸውን ለራሳቸው ህዝብ አሳበቀባቸው። ህግና ደንብ ጠቅሶ ወገኖቹ ከለላ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስረዳ። የኮሪያ አዲሱ ትውልድ ተደብቆት የኖረውንና ባገሩ ምድር እየተፈጸመ ያለውን ችግር አቀረበ። ሚዲያዎቹ ይህንን ከፍተኛ ችግር ዝም ሊሉ እንደማይገባ አሳሰበ። ህወሃት ምን አይነት አገዛዝ እንደሆነም ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውንና የደረሰውን ግፍ በማተት መረጃ አስተላለፈ።
ስንብት – አደራና ክትትልobang sk4
ኦባንግ እና ወገኖቹ ኮሪያ ዘምተው ህይወታቸው ላለፈና አካላቸው ለጎደለ ኢትዮጵያዊያን ማስታወሻ በቆም መታሰቢያ ስር ተሰባሰቡ። ሻማ አብርተው ወገኖቻቸውን አሰቡ። በዚያውም “በኢትዮጵያ ዘረኝነትን፣ የጎሳ ከፋፍልህ ግዛውን አስከፊነት ለመጪው ትውልድ ለማስተማሪያነት የሚውል ምስል በአገራችን እናቆማለን። በዚሁ አስከፊ አገዛዝ ሳቢያ ካገር ሲኮበልሉ ህይወታችው ያለፈ፣ በበረሃ የቀሩ፣ ውሃ የበላቸው፣ የተገደሉ፣ የታሰሩ፣ የታፈኑ፣ የደረሱበት የማይታወቁ፣ የተሰወሩ ወዘተ ስማቸው ከያለበት ተፈልጎ በዝርዝር የሚታይበትና መጪው ትውልድ ያለፉትን መሪዎቹን በተግባር የሚያየበት ይሆናል” ተባብለው ተለያዩ።
obang sk1ኦባንግ ለመጨረሻ ጊዜ ሲለይ “አንድ ሁኑ። አያቶቻችንና አባቶቻችን በኮሪያ ምድር አንድም ምርኮኛ ሳያስመዘግቡ ታሪክ የሰሩት በኢትዮጵያዊነት ኅብረት ነው እንጂ በጎሣ ወይም በወገን ተከፋፍለው አልነበረም፤ ስለዚህ በኅብረታቸው ድል እንደነሱ እናንተም በፍቅር ተዋደዱ፤ አትበታተኑ። አንድ ስትሆኑ ትደመጣላችሁ። አንድ ስትሆኑ ጭብጨባችሁ ይሰማል። አንድነት ነጻ ያወጣችኋል። አንድነታችሁን ጠበቁ … እከታተላችኋለሁ። ሌሎች ወገኖችም ካሁን በኋላ ያስቡዋችኋል!!” በማለት አባ “ቃኘው” የመጀመሪያ ዙር ዘመቻውን አጠናቀቀ። (በዚህ ዘገባ አቶ ኦባንግን “አንተ” ብለን የጠቀስነው በምክንያት ነው)