Tuesday, July 26, 2016

ሕወሃት በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያደረሰው ግፍና ጭፍጨፋ በዓይን ምስክር እንዲህ ነበር የተገለጸው

July 26,2016
13754669_10155016003415744_8078283661722118718_nወልቃይት በጉልበት ወደ ትግራይ ክልል ሢከለል ለምን ይሆናል ያሉና የተቃወሙ ወጣቶች ላይ የደረሠውን ግፍ አንድ ወታደር እንደሚከተለው ተናግሮ ነበር።በመጀመሪያ ወጣቶቹ ከወልቃይት ተጭነው ወደ ትግራይ ተወሠዱ። ከዚያም እጅና እግራቸው ታጥፎ ተሠበረ። በዚህ ሁኔታ ለሀምሣ ቀናት እራቁታቸውን አንድ ቤት ውሥጥ ተዘግቶባቸው በቀን አንድ ዳቦ ከብዙ ዱላ ጋር እየተሠጣቸው እንዲቆዩ ተደረገ።ሀምሣ ቀን ሙሉ ከዚያ ቤት አልወጡም።

በሀምሣኛው ቀን አንድ የጭነት መኪና መጣና ወጣቶቹ ተዘግተውበት የነበረው ቤት ተከፈተ።በወቅቱ በአካባቢው የነበረውን ሽታ በቃላት ለመግለጽ አዳጋች ነው። ወጣቶቹ በጣም ከመክሣታቸው የተነሣ ወታደሮቹ በአንድ እጃቸው ጸጉራቸውን አንጠልጥለው ወደ መኪናው ይወረውሯቸው ነበር። አንደኛውን ወጣት ጸጉሩን ይዞ ሢወረውረው ጸጉሩ ተነቅሎ ወደቀ። ያንን ሥመለከት ሠው ሆኘ መፈጠሬን ጠላሁት። ወጣቶቹን ጭኖ የሄደው መኪና ማታ አካባቢ ባዶውን ተመለሠ።

ወጣቶቹን እንደገደሏቸው ባውቅም ከዚያ ሁሉ ሥቃይ መሞት እንደሚሻላቸው በመረዳቴ ደሥ አለኝ። ቢሆንም ግን ይህ ድርጊት በአእምሮየ እየተመላለሠ ሥለረበሸኝ ከሥራየ ልለቅ ችያለሁ።በወቅቱ ይህ ሁሉ የሚፈጸመው በትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት በገብሩ አሥራት ቀጥተኛ ትእዛዝ ነበር።

No comments: