Monday, June 20, 2016

” የኢህአዴግ” እና “ህግደፍ” የሰሙኑ ዉጥረት



June 20,2016
(የግል እይታ) – ዑስማን ካዋጃ
Ethiopiaየዛሬ 25 አመት የዓረቦች ታላቅ ህልም እና አጀንዳ በኢህአዴግ እና ህዝባዊ ግንባር ንዲሞክራሲን ፍትሕን (ህግደፍ) ኣስፈፃሚነት ተግባራዊ ሆነ ፡፡ የኢ/ያ ህዝቦችን በመሳርያ አፈሙዝ በማስገደድ ፡ ኤርትራውያንን የፈጠራ ታሪክ በመጋት እና Mass hallusination በመፍጠር ሁለት አገሮች ተፈጠሩ፡፡ ኤርትራ የግላችን ኢ/ያ የጋራችን የሚል የዝርፍያ እቅድ በ “ህግደፍ” ተነድፎ ሁለቱም ባለግዜዎች ለተግባራዊነቱ ተረባረቡ፡፡ እነ ቀይባህር ኮርፖሬሽን ተመስርተው ኢ/ያ ያለምንም ከልካይ ተዘረፈች፡ እነ Horn international bank በብድር እና እና እርዳታ የተገኘውን የውጭ ምንዛሪ በሰአታት ፍጥነት ህጋዊነትን አላብሰው አስመራ አደረሱት፡፡ ስለ አገር መቆርቆር እንደወንጀል ተቆጠረ፡ ምስጋና ለወቅቱ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ለነበሩት አቶ ገብሩ አስራት ይህን የዝርፍያ እቅድ በተቻላቸው መጠን ለመከላከል ሞከሩ በውጤቱም በተለምዶ ኢትዮ ኤርትራ የሚባለውን ግጭት ተቀሰቀሰ፡፡
ከ ሁለት ዓመታት ከባድ ጦርነት በኢትዮጵያ ልጆች ከባድ መስዋዕትነት የሻዕብያ ምሽግና ትዕቢት ተናደ፡፡ የኢ/ያ ጦር አሰብን ለመቆጣጠር ጥቂት ኪሎሜትሮች ሲቀሩት ታላቁ ” ባለራአይ” መሪያችን ራዕያችንን እንዳይሆን አድርገው አኮላሹት፡፡
ሰሙኑን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት እንደ አዲስ ተማሙቋል፡ አፍቃሪ ኢህአዴግ ሚድያዎች እና ትናንሽ ካድሬዎት ግቡ ባይታወቅም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ናቸው፡፡ እኔ በግሌ የሰሙኑን የጦርነት አጀንዳ አጥብቄ እቋወማለሁ ለምን ቢባል:
1)ኢህአዴግ ኤርትራ ላይ ባለው ጭንጋፍ አቋም፡
ገዥው ፖርቲ ምን ግዜም ኤርትራ እና ህጋዊ የባህር በር የማግኘት መብታችን በተመለከተ ምን ግዜም ከኢትዮጵያ ህዝቦች በተፃራሪ እነደቆመ ነው፡፡ታድያ ይህን የገዢው ፖርቲ ፀረ ኢ/ያ አቋም ሳይቀየር ምን ለማግኘት ነው ጦርነት ውስጥ የምንገባው? እዚህ ላይ ሻዕብያን አስወግዶ ለኢ/ያ ችግር የማይፈጥር መንግስት ለመመስረት የሚል ውሃ የማይቋጥር ምክንያት በትናንሽ ካድሬዎች ይቀርባል ግን እንበል እና አዲስ የሚመሰረተውስ መንግስት ፀረ ኢ/ያ እንደማይሆን መተማመኛችን ምን ድነው?
2) ቀይ ባህር ላያ የጦር ሰፈሮቻቸው እየገነቡ ባሉ የኢ/ያ ታሪካዊ ባላንጦች ከዚህ አፍራሽ ተግባራቸው በዘላቂነት መከላከል የሚቻለው አስመራ ቤተመንግስት ላይ የሰው ለውጥ በማድረግ ሳይሆን ቀይ ባህርን በቆዋሚነት በመቆጣጠር ነው፡፡ ይህን ማድረግ የሚችል አርቆ አሳቢ መሪ እና ፖርቲ በሌለበት የሚካየድ ጦርነት ኢ/ያን ከባድ ዋጋ ከማስከፈል አልፎ የሚያመጣው ብሄራዊ ጥቅም የለም፡፡
3) የኤርትራውያን ከእንቅልፋቸው አለመንቃት፡
የሆነ ኤርትራዊ የችግራችሁ ምንጭ ምንድነው ብለን ብንጠይቀው መልሳቸው ተመሳሳይ ነው…..ኢሳያስ ኢትዮጵያዊ የደም ሃረግ ስለው ይሉናል ፡፡ታድያ ችግራችሁ እንዴት ይፈታል? የሚል ጥያቄ ብናስከትል አሁንም ገራሚ መልስ ይነግሩናል…..ኤርትራ በንፁህ ኤርትራዊ(ደቂ አባት) ስትመራ ይሉናል፡፡ከኢትዮጵያ ጋር በደም ያልተሳሰረ ንፁህ ኤርትራዊስ ማነው? ማንም ኤርትራዊ ይችን ጥያቄ መመለስ አይችልም፡፡ ታድያ የችግራቸው ምንጭ ትዕቢት፡ክፋት፡ድንቁርና፡ቅዠት፡አዲስ የተፈበረከ የውሸት መንነት: Mass Hallusination መሆኑን መውል ሳይገነዘቡ እና ስህተታቸው ለማረም ከውስጥ እንቅስቃሴ ባልጀመሩበት የኛን በማያገባን ጥልቅ ማለት ምን ለማትረፍ ነው???
እናም የኢህዴግን ባህሪ ባልተቀየረበት ወይም የኢ/ያ ብሄራዊ ጥቅምን ሳይሸራረፍ ሊያስፈፅም የሚችል ፖርቲ ባልተፈጠረበት የሚካየድ ጦርነት ኤርትራውያንን ከኢሳያስ አገዛዝ ነፃ ከማውጣት እና ኢትዮጵያውያን እናቶችን ዳግም ማቅ ከማልበስ ባለፈ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ስለማያመጣ አጥብቄ እቋወማለሁ፡፡

No comments: