Wednesday, September 23, 2015

በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል የሕወሃት/ብአዴን ታጣቂዎች 2 ነዋሪዎችን ገደሉ፣ ከ50 በላይ አቆሰሉ

September 23,2015

picture

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ሕወሃት) የፈጠረው የብአዴን ታጣቂዎች በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል ሁለት ነዋሪዎችን መግደላቸው፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው እንዲሁም ከሃምሳ በላይ ማቁሰላቸው ተሰማ።
የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም።
pictureለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን።
እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። (ምንጭ፦ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት Dr.Getachew Reda ጠቅሶ መስከረም ፱ ቀን ፪ሺህ፰ ዓም የላከው መረጃ)

No comments: