Monday, July 27, 2015

የወያኔ ታጣቂዎች በታህታይ አድያቦ ወረዳ እርስ በራሳቸው ተዋጉ

July 27,2015
በታህታይ አድያቦ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ የገዢው የኢህአዴግ ስርዓት ወታደሮች እርሰ በራሳቸው እየተገዳደሉ እንደሚገኙ ተገለፀ። በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞንEthiopian dictatorial regime troopsታህታይ አድያቦ ወረዳ ተሰማርተው የሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት በመካከላቸው አንድነትና ፍቅር እንደሌላቸው የገለፀው መረጃው በተለይ ደግሞ በአባላትና በአዛዦች መሃል በተከሰተው ያለመስማማት ምክንያት ወታደር ታዘዘ ደበበ የተባለ ግለሰብ መቶ አለቃ አስራት ባዩና አምሳ አለቃ ካሳ አለሙ የተባሉን በጥይት ገድሎ ለራሱም ህይወቱን እንዳጠፋ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
በተመሳሳይ- በአዲ ሃገራይ አካባቢ የሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አንድ ወታደር 3ት ኮነሬሎችን ከነ አጃቢዎቻቸው ገድሎ ራሱን ህይወቱን እንዳጠፋ ባላፈው የዜና ዘገባችን መግለፃችን ይታወሳል።
ምንጭ – ትህዴን

No comments: