Friday, April 17, 2015

ወገን ይጠቃል፣ እነርሱ ዳንኪራ ይመታሉ

April 17,2015
ግርማ ካሳ
የአልመነህ ዋሴ ዋዜማ ዘገባ መስረት፣ የናይጄሪያው ተመራጭ ፕሬዘዳንት መሀመድ ቡሃሪ ፓርቲ እና የሃገሪቱ የሲቪል ማህበረሰብ አባላት፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በዉጭ ሃገር ዜጎች ላይ የሚፈጸመዉን ጥቃት ካላስቆመ በናይጄሪያ ያሉ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችን ለማዘጋት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው። የ48 ሰዓት ገደብ የያዘ ማስጠንቀቂያቸዉን ሌጎስ ለሚገነው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ አስገብተዋል።


በተያያዘ ዜና ዋዜማ የናይጄሪያ ፓርላማ አባላት መንግስታቸው አምባሳደሩንስ ከደቡብ አፍሪካ እንዲጠራ መጠየቃቸዉን ጥቅሷል። በዘገባዉ መሰርት የፓርላማ አባላቱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለአፍሪካዊያን ስደተኞች በቂ የደህንነት ጥበቃ ካላደረገ፣ ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ የአጸፋ እርምጃ እንዲሰደም ጠይቀዋል። 
ናይጄሪያዊያኖች ይህን አይነት ዉሳኔ ሲያሳልፉ፣ አንድ ዜጋ ገና አልሞተባቸዉም። ሆኖም በሌሎች አፍሪካዉያን ላይ የደረሰው እነርሱም ላይ እንደደረሰ አድርገው ስለወሰዱት ነው፣ በደቡብ አፍሪካ ያየነዉን ዘግናኝናአ እንሣዊ ተግባር ያወገዙት።
በደቡብ አፍሪካ በተነሳዉ ግጭት በርካታ ኢትዮጵያዉያን ሞተዋል። አንገታቸው ላይ ጎም ተደረጎ እንዲቃጠሉና በማቼቲ (መጥረቢያ ነገር) ሲቆራረጡ፣ በየመንገዱ እንደከብት ሲደበደቡ የሚያሳይ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችንም አይተናል። አለም ሁሉ ወገዛ ሲያቀርብ፣ እነ ቢቢስ፣ አልጃዚራ፣ ቪ.ኦኤ ፣ የናይጄሪያ፣ የማላዊ፣ የሞዛምቢክ የበርካታ አፍሪካ አገሮች ሜዲያዎች በስፋት ሲዘገቡ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ምንም ነገር እንዳይሰማ መደረጉ፣ የሕወሃትን ምመንግስት ምንነት በገሃድ በድጋሚ ያሳየ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ በወገኖቹ ላይ የደረሰውን ምንም ነገር እንዳይሰማ ተደረጎ፣ ሌላው ይቀር ጸሎት እንኳን እንዳያደርግ ሁሉንም ደብቀዉታል።
እንግዲህ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ? መሪያችን ማን ነው ? የፓርላማ ተወካዮቻችንስ ማን ናቸው ? የ”ኢትዮጵያ” መሪ ሙሃመድ ቡሃሪ ነው፣ የፓርላማ ተወካዮቻችን ደግሞ የናይጄሪያ ፓርላማ አባላት ናቸው ብልን እንንሳሳታለን ? እስቲ አስቡት በደብቡ አፍሪክካ ላሉ ወገኖቻችን እየተሟገቱ ያሉት፣ በዝዙማ መንግስት ላይ ጫና እያሳደሩ ያሉት እነ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ፣ እነ አባ ዱላ ሳይሆኑ እነ ፕሬዘዳንት ሞሃመድ ቡሃሪ ናቸው።
በዚህ አጋጣሚ ለናይጄሪያኖች ያለኝ ከበሬታ እገልጻለሁ። THANK YOU OUR NIGERIAN BROTHERS !!! WHEN OUR OUR OWN GOVERNMENT DID NOT CARE YOU STOOD FOR US.

No comments: