Wednesday, March 4, 2015

በግፍ ላይ ግፍ በህወሓት..! ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ዘግናኝ ድብደባ ደርሰባቸው

March 4,2015
ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ ይባላሉ። በምዕራባዊ ዞን ቓፍታ ሑመራ ወረዳ በረኸት ከተማ(ቀበሌ) ኑዋሪ የሆኑት የዓረና-መድረክ ኣባል ናቸው።በፎተው እንደሚታዩት የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ይህ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሂወታቸው ልታልፍ ምንም ኣልቀረላቸውም ነበር።ይህ ድብደባ በ17/ 2007ዓ/ም ማታ 1 ሰዓት ኣከባቢ በ1ፖሊስ ድምብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የፈጥኖ ደራሻ ደንብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የመከላከያ ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ከለላነት ተደብቆ የነበረ ሰው በድንጋይ ደጋግሞ በመደብደብ ለዚህ ኣደጋ እንዲዳረጉ ኣድርገዋል።
3ቱ የታጠቁ ሰዎች ሰው እርዳታ እንዳያደርግ የተከላከሉ ሲሆን ደብዳቢውም በቁጥጥር ስር እንዳይውል ከፍተኛ ከለላ ሰጥተዋል።ቐሺ ሕሉፍ ኻሕሳይ በክረምት 2006 ዓ/ም በቀበሌው ህዝብ ፊት ቀርበው "..ይህ ሰውየ ዓረና ነው፣ በቤታቹ ቃጠሎ እንዳያደርስባቹ፣ እንዳይሰርቃቹ.." ወዘተ የመሳሰሉ የስም ማጥፋት ዘመቻና ማስፈራርያ ከሌሎች3 የዓረና ኣባላት ጋር ደርሶባቸው ነበር።ኣቶ መዓሾ ኣስመላሽ የተባለ የቀበሌ ኣመራርም ሰበካ ጉባኤ(የቤተክርስትያን ሃላፊዎች) በመሰብሰብ "...ቐሺ ሕሉፍ በዓረናነት ስለተጠረጠረ እንዳይቀድስ .." የሚል ትእዛዝ ባስተላለፈው መሰረት ከቅዳሴ ታገዱ።
ቐሺ ሕሉፍ የካድሬው እገዳ ተከትለው ወደ ቀበሌው ፖሊስ ኣቤቱታ በማሰማታቸው የቅስና ምስክር ወረቀታቸው እንድያመጡ በታዘዙት መሰረት ምስር ወረቀታቸው ለፖሊስ በማስረከብ ፍትህ እንዲያገኙ ጥረት ኣደረጉ።

ፖሊስም በተረዋ ምስክር ወረቀታቸው ለሁለት ሳምንት ይዞ ያለ ምንም መፍትሄ ኣቆየባቸው።
የምስክር ወረቀቱ ለማስመለስም ተጨማሪ ክስ ኣስፈለጋቸው። ፖሊስ በስንት ውጣ ውረድ ወረቀታቸው የመለሰላቸው ሲሆን ከዚህ በሗላም ስንት ዛቻ ደረሳቸው።
ዘግናኝ ድብደባ የተፈፀመባቸውም ከዚህ ሁሉ ውጣ ወረድና ማንገላታት በሗላ ነበር። ህግ ባለበት ሃገር የሰው ልጅ እንዲህ ተቀጥቅጦ ይጣላል እንዴ...?
እነዚህ ለለውጥ ብለው የተሰዉ 60 ሺ ሰማእታት፣ 100 ሺ ኣካል ጉዳተኞች ውጤታቸው መሆን የነበረበት ይህ ነው...? በጣም ሗላቀርና ህወሓት ታግየ ጣልኩት ካለቸው ደርግ በእኩልነት የሚያስመድባት ኣፀያፊ ተግባር ነው። በትግራይ የዓረና መድረክ ኣባል መሆን ይሄ የመሰለ መስዋእትነት ያስከፍላል።
በሉ ያገራችን ሰዎች ..! ታፍሩበት ትኮሩበት ዘንድ ይሄውላቹ የኛ ዲሞክራሲ፣ የኛ ፍትህ፣ የኛ ነፃነት።
ይህ ኣስቃቂ ተግባር ሁሉም ዜጋ ሊቃወመው ይገባል።
ነፃናታችን በእጃችን ነው..!
IT IS SO..!

No comments: