Sunday, January 25, 2015

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ባለቤት ስለሺ ሃጎስ በሕወሓት ፖሊሶች ክፉኛ ተደበደበ

January 25,2015
(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ አንድነት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ያስደነገጠው የሕወሓት መንግስት በዜጎች ላይ አሰቃቂ ድብደባ ሲፈጽም መዋሉን ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወሳል:: አሁንም ከሰልፉ በኋላ በአንድነት አመራሮችና አባላት ላይ የመንግስት ተላላኪዎች እጅጅ አሳዛኝ ጭፍጨፋ ማድረጋቸውን የቀጠሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ባለቤት በዚህ በምስሉ ላይ የምታዩት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ እጅግ አሳዛኝና አሰቃቂ ድብደባ ተፈፅሞበታል::
አሁን ባለው ሁኔታ የአንድነት አመራርና አባላት በሰላማዊ ትግሉ እራሳቸውን አሳልፈው እየሰጡ፤ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል እንደማያዋጣ እያሳዩን ያለበት ሁኔታ ነው ያለ ሲሆን በዚህም በደማቸው ደማቅ ታሪክ እየጻፉ ይገኛሉ::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የሚሊዮኖች ድምጽ እንደዘገበው በአንድነት ሰልፍ የተገኙ ዲፕሎማቶች በሆነው ነገር በጣም አዝነዋል። የተጎዱትን ሁኔታ ለመከታተል ወደ ሆስፒታልም ሄደዋል።የተጎዱ ወገኖቻችን ፣ «ከዚህም የበለጠ ዋጋ ለነጻነታች እንከፍላለን። እነርሱ ያላቸውን የመጨረሻ ዱላ ነው የተጠቀሙት፣ እርሱም ኃይል” ያሉ ተጎጂዎች ይህ የትግል ወኔያቸውን የበለጠ የሚያጠናከር እንጂ የሚቀንሰው እንዳልሆነ እያረጋገጡ ነው። ታጣቂዎቹ በተለይም በአቶ ስለሺ ሐጎስ እና በአቶ አሰራት አብርሃ ላይ፣ ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመዉባቸዋል። የሰባት ወር ነፍሰ ጡር ሴት ሆዷ ላይ ተመታለች። የሰባ አመት እናት፣ አባት ሽማግሌ ተደብደበዋል።
ጋዜጠኛ ስለሺ የተደበደበው ሰውነቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ይታያል
ጋዜጠኛ ስለሺ የተደበደበው ሰውነቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ይታያል

No comments: