Friday, February 21, 2014

ሰበር ዜና፤ ወያኔ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገው የስለላ ወንጀል ስለተጋለጠ አሜሪካ ውስጥ ክስ ተመሠረተበት

February 21/2014























ዜናውን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።   ወያኔ በስለላ ወንጀል አሜሪካ ውስጥ ተከሰሰ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለ22 ዓመታት የግድያ፣ የማሰቃየት፣ የማፈንና ሌሎችም ዘግናኝ ወንጀሎችን ሲፈጽም የኖረው ወያኔ “ተሸሽጎ የሚኖር ነገር የለም” እንደሚባለው አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው የኢሳት ጋዜጠኞች ላይ ያካሂድ የነበረው የስለላ መረብ በመበጣጠሱና እጅ ከፍንጅ በመያዙ በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ ክስ እንደተመሠረተበት ታላቁ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስታውቋል።

ክሱን የመሠረተው አሜሪካ ውስጥ ላለፉት 22 ዓመታት የኖረው ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ግለሰብ ሲሆን የወያኔ አገዛዝ የአሜሪካን ህግ በመጣስ የስለላ መረቦችን በግልኮምፒውሩ ላይ በማስጠመድ ግለሰቡ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሲከታተል እንደነበር ተመልክቷል። ይህ የተመሠረተው ክስ የቅርብ የአሜሪካን መንግስት ወዳጅና ተመጽዋች የሆነው የወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚዎችን፣ጋዜጠኞችንና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችን፣ የማፈን ታሪክ ያለው ከመሆኑም በላይ የተራቀቁ የድረገጽ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጠላቶቼ የሚላቸውን ሲሰልል መገኘቱን ምልክት የሚሰጥ መሆኑ በጋዜጣው ውስጥ ተጠቁሟል።

ክሱን ያቀረበው “Electronic Frontier Foundation” በመባል የሚጠራው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ጠበቃ የሆኑት ሚ/ር ኔት ካርዶዞ እንደገለጹት “የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተለይም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚላቸውን እንደሚሰልል መረጋገጡን አስታውቀዋል። የወያኔ ወኪሎች ስለቀረበባቸው ክስ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው የሰጡት መልስ የተለመደ ክህደታቸውንና ቅጥፈታቸውን ነው። የኮምፒውተር ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት የወያኔ አገዛዝ የአፈናና የስለላ ወንጀሎችን ከሚፈጽሙ አገሮች ተርታ ውስጥ ይገኛል።

ከአራት ወራት በፊት ነጻ የሆነው የጥናትና ምርምር ተቋም የወያኔ አገዛዝ “ፊን እስፓይ” በመባል የሚጠራ የጆሮጠቢ መረብ እንደሚጠቀም መረጃዎች መገኘታቸውን የሚያሳይ ዝርዝር ዘገባ አቅርበው ነበር። ቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኝው ዓለም-አቀፍ ጉዳዮች ትምህርት ቤት የወያኔ አገዛዝ የስለላውን መረብ ብቸኛ ተጠቃሚ መሆኑን አርጋግጠዋል። ይህ ሪፖርት ከወጣና ዜናው ከፍተኛ ሽፋን ከተሰጠው ከ5 ቀናቶች በኋላ የወያኔ አገዛዝ መጋለጡን በማወቅ ያካሂድ የነበረውን የስለላ መረብ ማቋረጡ ታውቋል። ሆኖም የወያኔ የስለላ  መረብ ባላሟሎች እንዳይያዙ መረጃዎችን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርቦሽ ቢያደርጉም ሙሉ በሙሉ አሻራቸውን ለማጥፋት ሳይችሉ በመቅረታቸው እጅ ከፍንጅ ሊያሲዝቸው የሚችል መረጃ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ እንግሊዝ አገር ውስጥም በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች ላይ የሚያደርገው ስለላ ስለተደረሰበት ተጨማሪም ክስ ተመስርቶበታል። ከዚህ ለማጠቃለል የሚቻለው ወያኔ የአሜሪካን ህግ በመጣስ አማሪካ መሬት ላይ የፈጸመው ወንጀል ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት በእጅጉ እንደሚያበላሽበት አይጠረጠርም። የዚህ ወንጀል መፈጸም መጋለጥና ክስ መመስረት ለወያኔ አገዛዝ ድጋፍ የሚሰጡ የአሜሪካን ባለሥልጣኖችንም ጭምር በወያኔ ድፍረትና ጥጋብ በአገራቸው ምድር ላይ ወንጀል መፈጸሙ በእጅጉ እንደሚያበሳጫቸውና እንደሚያስቆጫቸው እንዲሁም “ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ” እንደሚያስብላቸው ይገመታል። በአጠቃላይ ወያኔ ይህንን የስለላ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ መያዙ እንደ መንግስት ሳይሆን ወንበዴነቱን፣ሌብነቱን፣ማጅራት መቺነቱንና ኪስ አውላቂነቱን በዓለም-አቀፍ ደረጃ ያሳየና እርቃኑን ያስቀረው መሆኑን ለመገመት አያዳግትም። ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ ከደደቢት ዋሻ ውንብድናውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በርካታ ደረቅ ወንጀሎችን ለምሳሌም ባንኮችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ ቤተክርስቲያኖችን፣ የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶችን፣ ሱቆችንና ሌሎች የኢትዮጵያውያንን ንብረቶችን መዝረፍ፣ ሀኪም ቤት የተኙ በሽተኞችን ከአልጋቸው አውርዶ መሬት ላይ በመጣል አልጋቸውን መዝረፍ፤ ሌሎችንም ወንጀሎች ሲፈጽም መኖሩና ብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን ወርቅ በምትሃት ወደ ቦንዳነት የለወጠ መሆኑና በርካታ ኩንታል ቡና ወደ አቧራነት የቀየረ መሆኑ አይዘነጋም።



No comments: