Monday, February 24, 2014

ከኃይለመድህን አበራ እናት ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ!! “ከማጥናት በቀር ሌላ ነገር የማያውቁ፤ የተስተካከሉ ልጆች ነው ያሉን።”

February 24/2014
ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ባለፈው ሳምንት፤ ሲያበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጄኔቭ ማሳረፉ የሚታወስ ነው። ከአብራሪው ጋር በተያያዘ እስካሁን እህቱ እና መንድሙ የየራሳቸውን ሃሳብ እና አስተያየት ሰጥተዋል። አሁን ደግሞ ከ እናታቸው ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ይዘን እንቀርባለን። ቃለ ምልልሱን በድምጽ ያደረገው ዳዊት ሰለሞን ነው። ባህርዳር ላይ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር በስፍራው ተገኝቶ ነበር። እናም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። በመግቢያውም ላይ እንዲህ የሚል ማስታወሻ ጽፏል። “በባህርዳር ቆይታዬ ከሰሞኑ ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ከሆነው ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ወላጅ እናት ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች የመገናኘት እድል ተፈጥሮልኝ ነበር፡፡ እናትየው የወንድማቸውን አርባ አውጥተው ከሩቅ ቦታ መመለሳቸው በመሆኑ ድካም ቢነበብባቸውም ለማቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አላመነቱም፡፡ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ልጃቸውን የተመለከተ መልካም ዜና እንዲያደምጡ ጸሎቴ ነው::” ብሏል።
ቃለ ምልልሱን ያደረገው – ዳዊት ሰለሞን
ወደ ጽሁፍ የመለሰው – ዳዊት ከበደ ወየሳ
ጥያቄ – ስምዎትን ማን ልበል?
መልስ – የህዝብአለም ስዩም።
ጥያቄ – እስኪ ስለቤተሰብዎ ያውሩኝ? ከባለቤትዎ ጋር ጋብቻ የፈጸሙት መቼ ነው?
መልስ -ከባለቤቴ ጋር ጋብቻ የፈጸምኩት፤ ሃምሌ 12 ቀን 1955 ዓ.ም. ነው። 12 ልጆች ወልደን አሳድገናል። ከአንዷ በቀር ሁሉም ልጆች በኢንጂነሪንግ የተመረቁ፤ ዶክተር የሆኑ ናቸው። ሁሉም ራሱን የጠበቀ ነው።
ጥያቄ – ሁሉም ልጆች ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚገኙት?
መልስ -ሁለቱ ወንዶች እና ሁለቱ ሴቶች ልጆቼ ውጭ አገር ነው ያሉት።
ጥያቄ – ኃይለመድህን ስንተኛ ልጅዎ ነው?
መልስ -ኃይለመድህን 9ኛ ልጅ ነው።
ጥያቄ – ስለልጆችዎ አስተዳደግ ይንገሩን እስኪ? ባለቤትዎም አራጣ አበዳሪ ናቸው የሚሉ መረጃዎችም ወጥተዋልና ይህንን ጉዳይ ጠቅለል አድርገው ይመልሱልን? (ቀሪውን በPDF ያንብቡ)

No comments: